TIKVAH-ETHIOPIA
#Peace የተደራዳሪ ቡድኑ ! የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት #በሰላም_ድርድር እንዲፈታ ገዢው የብልፅግና ፓርቲ ውሳኔ ማሳለፉ ይታወቃል። በዚህም መሰረት በፌዴራል መንግሥት በኩል የሰላም ተደራዳሪ ቡድን መሰየሙ ተረጋግጧል። የቡድኑ አባላት ፦ 1ኛ. አቶ ደመቀ መኮንን ➡️ ሰብሳቢ 2ኛ. ዶ/ር ጌድዮን ጢሞቲዎስ ➡️ አባል 3ኛ. አቶ ተመስገን ጥሩነህ ➡️ አባል 4ኛ. አምባሳደር ሀሰን አብዱልቃድር ➡️…
#Update
ከጥቂት ሳምንታት በፊት የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት በሰላም መቋጫ እንዲያገኝ የፌዴራል መንግስት የሰላም ተደራዳሪ ቡድን መቋቋሙ ይታወሳል።
የተደራዳሪ ቡድን አባላቱም ይፋ መደረጋቸው አይዘነጋም።
አሁን ደግሞ ትግራይ ክልልን እያስተዳደረ የሚገኘው ህወሓት ተደራዳሪ ቡድን ማቋቋሙን ገልጿል።
የህወሓት ቃል አቀባይ ለአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ የዜና ወኪል በሰጡት ቃል ፤ ለድርድር የሚሆን ልዑክ ወደ #ናይሮቢ ለመላክ ዝግጁ እንሆናለን ብለዋል።
በከፍተኛ ሥልጣን ደረጃ የሚገኙ አባላት ያሉት ኮሚቴም ተቋቁሟል ሲሉ አሳውቀዋል።
ተደራዳሪ ሊሆኑ የሚችሉ ግለሰቦች እነማን እንደሆኑ እንዲሁም ቁጥራቸውን በተመለከተ የተባለ ነገር የለም።
ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ መንግስት ከህወሓት ጋር የሚደረገው ምንም አይነት ድርድር ሊመራ የሚችለው በአፍሪካ ኅብረት ብቻ መሆኑን ያስታወቀ ሲሆን፣ የህወሓት አመራሮች ድርድሩ በኅብረቱ ጥላ ስር ብቻ እንዲሆን እንደማይፈልጉ ገልጸዋል።
" ሁሉንም የድርድር ሂደቶች ለአፍሪካ ኅብረት መስጠቱ ለእኛ በጣም ኃላፊነት የጎደለው ተግባር ነው” ያሉት አቶ ጌታቸው፣ ማንኛውም ድርድር በሰላም ጥረት ውስጥ ንቁ ሚና የተጫወቱትን ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታን ማካተት አለበት " ብለዋል።
መረጃው የአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ /ቢቢሲ ነው።
@tikvahethiopia