TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የሲዳማ ዞን ከተሞች እንዴት ዋሉ? የዛሬ ዉሎ ምን ይመስል ነበር?

ከ20 ደቂቃ በኃላ እመለሳለሁ!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሀዋሳ

የሀዋሳ ከተማ ሰላም ቀድሞ ወደነበረበት እየተመለሰ ይገኛል። በከተማይቱ የንግድ እና የትራንስፖርት እንቅስቃሴም እየተጀመረ ነው። ካለፉት ቀናት በእጅጉ የተሻለ መረጋጋት እና ሰላም በከተማዋ መስፈኑን በስልክ ያነጋገርናቸው የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ገልፀዋል።

#ወንዶገነት

በወንዶ ገነት ከተማ አርብ ዕለት ተከስቶ በነበረው ግጭት ቢያንስ ሦስት ሰዎች መገደላቸውን የሚታወስ ሲሆን ትናንት ቅዳሜም በወንዶ ገነት ውጥረት ነግሶ ነው የዋለው። ይሁን እንጂ ዛሬ እሑድ በከተማው መረጋጋት እንደሚታይ አንድ የአይን እማኝ ለቢቢሲ ገልፀዋል “የትራንስፖርት አገልግሎት ጀምሯል። ሱቆችም ከሞላ ጎደል ተከፍተዋል። የጸጥታ ኃይል አስከባሪዎች በስፋት በከተማዋ ሲንቀሳቀሱ ነው የዋሉት።
/BBC/

#ይጋለም

ከተማዋ ወደ ቀድሞ እንቀስቃሴ አልተመለሰችም፤ ሆኖም ግን ካለፉት ሁለት ቀናት የተሻለ #መረጋጋት አለ። ዛሬ ላይም ቢሆን በይርጋለም ከተማ የደህንነት ስጋት መኖሩን ለBBC የተናገሩ የከተማዋ ነዋሪ፤ በዚሁ ምክንያት በርካታ የንግድ ተቋሟት በራቸውን ዝግ አድርገው እንደዋሉ ገልፀዋል።

#ሀገረሰላም

በስልክ ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች ዛሬ ካለፉት ሁለት ቀናት የተሻለ ሰላም እና መረጋጋት እንደታየ ገልፀዋል፤ ስጋቶች ግን አሁንም አሉ ብለዋል። የመከላከያ ሰራዊት በከተማው ይገኛል በየቦታውም ቅኝት ሲያሰርግ ውሏል ሲሉ የዛሬውን ሁኔታ አስረድተዋል።

#አለታወንዶ

የዛሬው ዉሎ ከትላንትና እና ከትላንት በስቲያ ከነበረው እጅጉ የተሻለ እና መረጋጋት የታየበት እንደነበር ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች ገልፀዋል።

በሲዳማ ዞን የኢንተርኔት አገልግሎት አልተጀመረም!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር ቴዎድሮስ ወ/ሚካኤል ለetv የተናገሩት፦

“በሲዳማ ዞን ተከስቶ የነበረውን የጸጥታ መደፍረስ የጸጥታ ኃይሉ ከሕዝቡ ጋር በመሆን ሙሉ በሙሉ በቁጥጥሩ ሥር አውሎታል። ይርጋለም፣ አለታ ወንዶ፣ ሃገረ ሰላም እና ወንዶ ገነት ችግሮች ተከስተው ነበር፤ በተጠቀሱት አከባቢዎች ንብረት የመዝረፍ እና የማውደም ተግባራት ተስተውሏል፤ በተፈጠረው ሁከት በሰው እና በንብረት ላይ የደረሰውን ጉዳት አጣርተን ስንጨር ለሕዝብ ይፋ እናደርጋለን!"

#ቢቢሲ_አማርኛ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሲዳማ_ዞን

በሲዳማ ዞን ስለጠፋው ክቡር የሰው ህይወት የተቃዋሚ ፓርቲዎች እና ዓለም ዓቀፍ ሚዲያዎች ነዋሪዎችን ዋቢ አድርገው ከሚገልፁት ቁጥር ውጪ በመንግስት በኩል ይፋ የተደረገ መረጃ የለም። እኛም በተለያየ መልኩ ስለጠፋው የሰው ህይወት የተረጋገጠ መረጃ ለማግኘት እየጣርን ነው። የወደመ የተቋማት እና የግለሰቦች ንብረትን በተመለከተም አስተማማኝ መረጃ ወድናተ ለማድረስ ጥረት እያደረግን ነው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ዱከም_መልካ

በኦሮሚያ ክልል በመጪው ኃምሌ 22 ቀን 2011 ዓም ለሚካሄደው የ“አረንጓዴ አሻራ ቀን” ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በቂ ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ተናግረዋል። ምክትል ፕሬዝዳንቱ የቪዥን ብራይት በጎ አድራጎት ማህበር  በመተባበር በዱከም ከተማ አካባቢ ያለውን አነስተኛ የደን ሽፋን ለመመለስ ‘ዱከም መልካ’ በሚባል ስፍራ ዛሬ ተገኝተው  ከማህበሩ አባላት ጋር ችግኝ ተክለዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የምርጫ “ይራዘም አይራዘም” አስገራሚ ውዝግብ!

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/AD-07-21
ኑ ምርቃትዎን ከእኛ ጋር! ሀምሌ 21 በአበበች ጎበና ሕፃናት እንክብካቤና ልማት ድርጅት አብረን እናክብር። #ቲክቫህ_ኢትዮጵያ

በጎ ማድረግን ከበጎዋ እናት በተግባር ይማራሉ!
#እንገናኝ

#TIKVAH_ETHIOPIA🎂2⃣
#NewsAlert አቶ ተመስገን ጥሩነህ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ተሹመዋል። የአማራ ብሔራዊ ክልል ምክር ቤት 5ኛ ዙር፣ 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 13ኛ መደበኛ ጉባኤ በዛሬው ዕለት ማካሄድ ጀምሯል።

ምክር ቤቱ በጉባኤው ለአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድርነት በእጩነት የቀረቡትን የአቶ ተመስገን ጥሩነህ ሹመት አፅድቋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ ሹመታቸው ከፀደቀ በኋላም ንግግር የሚያደርጉ መሆኑን ከወጣው መርሃ ግብር ለማወቅ ተችሏል። በመቀጠልም የስራ አስፈፃሚ አካላት የክልሉን የ2011 በጀት ዓመት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት የሚያቀርቡ ይሆናል።

ከዚህ ባለፈም ምክር ቤቱ የ2012 ረቂቅ በጀትን መርምሮ እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል፡፡ የምክር ቤቱ ስብሰባ ከዛሬው ዕለት ጀምሮ እስከ ሐምሌ 18 ቀን 2011 ዓመተ ምህረት በባሕር ዳር ከተማ ይካሄዳል።

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NewsAlert አቶ ተመስገን ጥሩነህ ድንቁ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ተሾሙ፡፡ ከምክር ቤት አባላት ከዚህ በፊት ካላቸው ልምድ አንጻር ክልሉን ሊያሻግሩ እንደሚችሉ አስተያዬት ከተሰጠ በኋላ ነው ዕጩ ርዕሰ መስተዳድሩ ሹመታቸው የጸደቀው፡፡ በጋራ አመራር ሰጭነት የሚያምኑና ያመኑበትን ዳር ለማድረስ የሚተጉ መሆናቸውም ተገልጿል፡፡ የተለዬ አስያዬት ባለመኖሩም ድምጽ መስጠት ሳያስፈልግ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 60 መሠረት ሹመታቸው ጸድቋል፡፡

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አቶ_ተመስገን_ጥሩነህ

የወሰንና የማንነት ጥያቄዎች ለግጭት ምክንያት ሳይሆኑ በሕግ እንዲመለሱ እንደሚሠሩ ርዕሰ መስተዳድር ተመስገን ጥሩነህ ተናገሩ፡፡ ዛሬ ሹመታቸው የጸደቀላቸው የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ለምክር ቤት አባላትና ለሕዝቡ መልዕክት እያስተላለፉ ነው፡፡

በመልዕክታቸውም የወሰንና የማንነት ጥያቄዎች ለግጭት ምክንያት ሳይሆኑ በሕግ እንዲመለሱ እንደሚሠሩ ነው ርዕሰ መስተዳድሩ የተናገሩት፡፡

የኢኮኖሚ ዕድገቱም ትኩረት ይሰጠዋል ነው ያሉት፡፡ ለሥራ ዕድል ፈጠራ፣ ለመኖሪያ ቤቶች ግንባታ እና ለኢንቨስትመንት ዕድገትም ትኩረት ይሰጣል ብለዋል አቶ ተመስገን፡፡ ‹‹የሕግ የበላይነትን ማስፈንም ለነገ የምንለው ጉዳይ አይሆንም›› ብለዋል ርዕሰ መስተዳድሩ ለአማራ ክልል ሕዝብ ባስተላለፉት መልዕክት፡፡

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
20,000 ሰው

"በቃና ቴሌቪዥን 20 ሺ ሰው የሚፈልግ የስራ ማስታወቂያ ወጥቶ ነበር፤ ስራውን #ለመመዝገብ 2480 ብር አካባቢ ያስከፍላሉ እናም ዛሬ ለመመዝገብ "ልደታ መርካቶ" ህንፃ ሄደን ቢሮው #ታሽጓል፤ እነሱም #ታስረዋል ብለው መለሱን። እነዚህ አካላት እውነተኛ ናቸው? አይደሉም? ደግሞስ በሚዲያ እንዴት ይለቀቃል ታማኝ ካልሆነ?? እባክህ አጣራልን። አመሰግናለሁ!"

B ከተባለች የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባል የደረሰኝን ይህን ጥቆማ ይዤ "አብዛን ንግድ" ወደተባለው ድርጅት ጋር በተደጋጋሚ ስልክ ብደውልም ስልኮቹ በመዘጋታቸው ምክንያት ስለጉዳዩ መጠየቅ አልቻልኩም። ከድርጅቱ ምላሽ ሊሰጥ የሚችል አካል ካለ @tsegabwolde መልዕክት ያኑርልኝ።

/0930787232/
/0902087777/

ጉዳዩን አጣርቼ የምደርስበትን አሳውቃችኃለሁ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አብዛን_ንግድ20 ሺ ሰው

"እኔም በአካል ቦታው ድረስ ሄጄ ነበር በፖሊስ ተይዞ ሄደ ብለውናል። በሩ ላይ #ፖሊስ ነበር።" #David

ይህን መልዕክት የላከልኝ የቤተሰባችን አባል የሆነ ወጣት የዩኒቨርሲቲ ምርቁ ነው። ከ30 ደቂቃ በፊት ቦታው ላይ ነበር። ወጣቱ ከክፍለ ሀገር ድረስ ይህን የስራ እድል አገኛለሁ ብሎ ነው የመጣው። አሁን ግን ወደመጣበት ሊመለስ ነው።

ብዙ ሰዎች ማስታወቂያውን #የሰሙት "ቃና ቴሌቪዥን" ከተባለው የሚዲያ ተቋም እንደሆነ ነግረውናል። የቴሌቪዥን ጣቢያው ስለሁኔታው አጣርቶ ለህዝብ ማሳወቅ ያለበትን ሊያሳውቅ ይገባል።

20 ሺ ሰው ፈልጋለሁ ያለው ድርጅት ህጋዊ ነው? ስለድርጅቱ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት እሞክራለሁ። የድርጅቱ ተወካዮችም ስልካቸው ከሰራልኝ ስለጉዳዩ ጠይቄ የሚሉኝን ነግራችኃለሁ።

ምላሽ ለሚሰጥ አካል በራችን ሁሌም ክፍት ነው @tsegabwolde

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከአውሮፓ ህብረት ዓለም አቀፍ የልማት ትብብር ኮሚሽነር ኔቨን ሚሚካ ጋር ተወያዩ። ኮሚሽነሩ የአውሮፓ ህብረት መንግስት እያካሄደ ላለው ማሻሻያ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል መናገራቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል። ከዚህ ባለፈም በኢትዮጵያ ዴሞክራሲን ለማስፈን ለሚደረገው ጥረት ህብረቱ ድጋፉን አጠናክሮ ይቀጥላልም ብለዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
«የሀገረ ሰላም ተፈናቃዮች #በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ጉጂ ዞን ተጠልለዋል፤ ቤተርስትያናቸዉ የተቃጠለባቸዉ ዲያቆናትም ይገኙበታል»

በደቡብ ክልል ሲዳማ ዞን የተከሰተዉን ግጭት ተከትሎ ከ 470 በላይ ተፈናቃዮች በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ጉጂ ዞን ቦሬ ከተማ ተጠልለዉ እንደሚገኙ ተፈናቃዮች እና የአካባቢዉ ባለስልጣናት ለጀርመን ራድዮ ተናግረዋል።

ተጨማሪ የንብቡ👇
https://telegra.ph/HG-07-22-2

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ክፍት የስራ ቦታ ማስታወቂያ፦ #ሁሉንአቀፍ_ፕሮሞሽን

ይደውሉ፡ 0984 95 80 40/0955 45 81 75
የጎርፍ እና የእሳት አደጋዎች #በአዲስ_አበባ

በአዲስ አበባ ከተማ #ቅዳሜና #እሁድ ሁለት የእሳት እንዲሁም ሶስት የጎርፍ አደጋዎች እንደተከሰቱ የእሳትና የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል፡፡ በአደጋዎቹ ሳብያም የሰው ሂወት አለመጥፋቱን የኮሚሽኑ የህዝብ ግኑኝነት ባለሙያው አቶ ሲለሺ ተስፋዬ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ራድዮ ገልጸዋል፡፡

የእሳት አደጋዎቹ የደረሱት በአዲስ ከታማ ክፍለ ከተማ መርካቶ በርበሬ በረንዳ ላይ በሚገኙ የንግድ ሱቆች ላይ ሲሆን በአደጋው ሳቢያም አንድ ሚሊየን ብር የሚገመት ንብረት ወድቧል ተብሏል። ኮሚሽኑ ሀያ ሚሊየን የሚጠጋ ንብረት ከውድመት ታዲጌያለሁ ብሏል።

ሁለተኛው የእሳት አደጋ የደረሰው በኮሊፌ ክፍለ ከተማ ወረዳ አራት ልዩ ስሙ አለም ባንክ አካባቢ በሚገኙ የንግድ ሱቆች ላይ ሲሆን በአደጋው 850 ሺ ብር የሚጠጋ ንብረት እንደጠፋና ስምንት ሚሊየን የሚገመት ንብረት ደግሞ ማዳን ተችላል፡፡

የጎርፍ አደጋዎቹ የደረሱት ደግሞ ሁለቱ በአራዳ ክፍለ ከተማ ሲሆን አንደኛው በወረዳ አምስት ሶር አምባ ሆቴል አካባቢ ሲሆን ሌላኛው የጎርፍ አደጋ ደግሞ በወረዳ ሁለት ጣሊያን ሰፈር አካባቢ በመኖርያ ቤት የደረሰ የጎርፍ አደጋ ነው። በሁለቱም የጎርፍ አደጋዎች በግምት ሁለት መቶ ሺ ብር የሚገመት ንብረት መጥፋቱ ተገልጿል፡፡

Via #ኢትዮ_ኤፍኤም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#መቐለ

የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ባደረገው ጥሪ መሰረት የመቐለ ንግድ ዘርፍ ማህበራት ባደረገው የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት 519 ሚሊየን ብር ቃል እንደተገባ ነው የተገለፀው።

የክልሉ መንግስት የክልሉን ልማት ለማጠናከር እና ስራ አጥነትን ለመቀነስ በማቀድ የህብረተሰቡን የገንዘብ ድጋፍ በጠየቀው መሰረት ነው ቴሌቶኑ የተካሄደው።

ጥሪውን መሰረት በማድረግም የመቐለ ከተማ ባለሃብቶች ባዘጋጁት ቴሌቶን በክልሉ በሃገሪቱና በተለያዩ የአለም ክፍሎች የሚገኙ የትግራይ ወላጆችና ወዳጆች የበኩላቸውን ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገብተዋል።

በገቢ ማሰባሰቢያው 400 ሚሊዮን ብር ለማስገባት ታቅዶ የነበረ ቢሆንም ከዕቅዱ በላይ ማሳካት ተችሏል። የትግራይ ክልል ም/ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል በዝግጅቱ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት በገጠርም ሆነ በከተማ ያለውን ችግር ለመፍታት መንግስት ባደረገው የገንዘብ ድጋፍ ጥሪ ሁሉም የራሱን ድርሻ እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።

Via #etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደሩ ከባንኮች ጋር በመሆን የከተማዋን ወጣቶች ተጠቃሚ የሚያደርግ የተቀናጀ ማዕከል ሊገነባ ነው፡፡ ኢ/ር ታከለ ኡማ ከሁሉም ባንክ ስራ አስፈፃሚዎች ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡ የከተማዋን ወጣቶች ተጠቃሚ ለማድረግ ባንኮቹ ከከተማ አስተዳደሩ ጋር ለመስራት ፍላጎት እንዳላቸው ለኢ/ር ታከለ ኡማ ተናግረዋል፡፡

በዚህም ከከተማ አስተዳደሩ ጋር በመተባበር ዘመናዊ የመኪና ማቆሚያ (ፓርኪንግ ) እና የንግድ ማዕከልን አንድ ላይ ያጣመረ የተቀናጀ ማዕከል (Complex Center ) ለመገንባት እና ለወጣቶች ተጨማሪ የስራ ዕድል ለመፍጠር ከስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡

ኢ/ር ታከለ ኡማ በበኩላቸው የገቢ ግብርን ጨምሮ በንግድ ባንክ ብቻ ይሰጥ የነበረው እና በከተማ አስተዳደሩ ስር የሚሰበሰብ ማንኛውም የክፍያ አሰራር አገልግሎቱ በሁሉም የፋይናንስ ተቋማት(ባንኮች) ማድረግ በሚቻልበት ሁኔታ ዙሪያ ጥናት እየተደረገ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

በመጨረሻም የባንክ ስራ አስፈፃሚዎቹ የከተማ አስተዳደሩ ለመንግስት ት/ቤት ተማሪዎች ዩኒፎርምን ጨምሮ ሌሎች የትምህርት ቁሳቁሶችን ለማቅረብ እያደረገ ያለውን ተግባር ለመደገፍ ቃል መግባታቸውን ከከንቲባው ፅ/ቤት የተገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

Via @mayorofficeAA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የህግ ፍትህና ዴሞክራሲያዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የኢትዮጵያ ምርጫና የፖለቲካ ፓርቲዎች ረቂቅ አዋጅ ላይ ከፖለቲካ ፓርቲዎችና ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ሊያደርገው የነበረውን ውይይት ለቀጣዩ ሳምንት አራዘመ፡፡ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሰኔ 27 ቀን 2011 ዓ.ም ባካሄደው 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 47ኛ መደበኛና ልዩ ስብሰባው የኢትዮጵያ ምርጫና የፖለቲካ ፓርቲዎች ረቂቅ አዋጅን ለዝርዝር ዕይታ ለህግ፣ ፍትህና ዴሞክራሲያዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የመራ መሆኑ ይታወሳል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ኢትዮጵያ እና የአዉሮጳ ኅብረት የአየር ንብረት ክብካቤን በተመለከተ ለሚዉሉ መርሃ-ግብሮች ማስፈፀምያ የሚዉል የ36 ሚሊዮን ዩሮ በጀት ተፈራርመዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia