TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.5K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
Forwarded from TIKVAH-SPORT
ሞሮኳዊው የዳኛ ባምላክ ደብዳቢ ተቀጡ!

ኢትዮጵያዊውን ኢንተርናሽናል አርቢትር ባምላክ ተሰማን የደበደቡት የሞሮኮ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት፣ የካፍ ምክትል ፕሬዚዳንትና የሞሮኮው ቤርካን ክለብ የክብር ፕሬዚዳንት ፉዚ ሌክጃ በአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን የዲስፕሊን ኮሚቴ ለአንድ አመት ከማንኛውም ስፖርታዊ አመራር ታግደዋል።

Via #PetrosAshenafi
@tikvahethsport
#ባምላክ_ተሰማ

ማራቶን በአንድ ርምጃ ይጀመራል እንዲሉ የዛሬው የአፍሪካ ቁንጮ ኢንተርናሽናል አርቢትር የቀድሞዎቹን የኢትዮጵያ ምርጥ ተጫዋቾች የሆኑትን እነ ሙሉጌታ ከበደን (ወለዬው) ለመዳኘት ወደ ሜዳ ሲያመራ ልዩ ስሜት ተሰምቶት ነበር። እነሆ ዛሬ ከአመታት በኋላ የአህጉራችን አፍሪካ ኮኮቦችን እየመራ የአህጉሪቱን ታላቅ ውድድር ፍፃሜ ለመዳኘት ፊት አውራሪ ዳኛ ሆኖ ተመርጧል።

ባምላክ የፊታችን አርብ በካይሮ ስታዲዬም ታላቁ ሊቨርፑልን ለአውሮፓ ሻምፒዮንነት ያበቃውን ሳዲዮ ማኔን እና የፔፕ ጋርዲዮላን ማንቼስተር ሲቲ እንዲሁም የክላውዲዮ ራኒዬሪን ሌስተር ሲቲን ለእንግሊዝ ሻምፒዮንነት ያበቃው ሪያድ ማህሬዝን እየመራ ወደ ሜዳ ይገባል።

በአላማና መንፈሰ ጠንካራነት የተገነባው የባምላክ ጉዞ በአለም ዋንጫ ትውልድ አህጉሩን አፍሪካን ወክሎ የወርቅ ኳስ አሸናፊዎቹን ከመዳኘት የሚያግደው እንደማይኖር መናገር ይቻላል። በአለም አቀፍ የእግር ኳስ መድረክ ጥሩ ተጫዋች አይውጣብሽ የተባለች የሚመስለው ሃገራችን አሁን ስሟን የሚያስጠራ ጥሩ አጫዋች አግኝታለች።

Via #PetrosAshenafi

@tsegabwolde @tikvahethiopia