#update በ10ኛ ክፍል ማጠቃላያ ፈተና የሁለት ቀናት ቆይታ 9 እናቶች በሰላም መውለዳቸውን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ ሚኒስቴሩ በሀሉት ቀናት የፈተና ጊዜ 8 የመደበኛ ተማሪና 1 የግል ተፈታኝ ተማሪዎች በሰላም እንደወለዱ አስታውቋል፡፡
Via #fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via #fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የአዴፓ ሊቀ መንበር አቶ #ደመቀ_መኮንንን የሚመሩት ሕዝባዊ ውይይት #በባሕር_ዳር እየተካሄደ ነው።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Alert‼️
የሚመለከታችሁ አካላት #በአምቦ_ዩኒቨርሲቲ አዋሮ ካምፓስ የተፈጠረውን ችግር በትኩረት እንድትከታተሉት ከTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ጥሪ ቀርቧል።

#update በጀርመን የኢትዮጵያ አምባሳደር ወይዘሮ ሙሉ ሰሎሞን ትናንት ለጀርመን ፕሬዝዳንት ፍራንክ ቫልተር ሽታይንማየር የሹመት ደብዳቤያቸውን አቀረቡ።በሥነ-ስርዓቱ ላይ አምባሳደር ሙሉ እጅግ በጣም ጥሩውን የኢትዮጵያ እና የጀርመን ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር እንደሚሰሩ ማስታወቃቸውን በጀርመን የኢትዮጵያ ኤምባሲ በድረገጹ ባሰራጨው መረጃ ገልጿል። አምባሳዷሯ በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ በመካሄድ ላይ ስላለው ለውጥ እና በአፍሪቃ ቀንድ ሰላም እና መረጋጋት ለማስፈን ስለሚጫወተው ሚናም ለፕሬዝዳንት ሽታይንማየር ገለጻ አድርገዋል። ፕሬዝዳንት ሽታይንማየር በበኩላቸው ወይዘሮ ሙሉ የአምባሳደርነት ሃላፊነታቸው እንዲወጡ የፌደራል ጀርመን ሪፐብሊክ ድጋፍ እንደሚያደርግላቸው አስታውቀዋል። በጎርጎሮሳዊው ጥር 2019 ዓ.ም ኢትዮጵያን በጎበኙበት ወቅት የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ላደረጉላቸው የሞቀ አቀባበልም አድናቆታቸውን ገልጸዋል።
Via #DW
ፎቶ፦ (ኢትዮጵያ ኤምባሲ በርሊን)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via #DW
ፎቶ፦ (ኢትዮጵያ ኤምባሲ በርሊን)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዜጎች ወደቀያቸው እየተመለሱ ነው...
ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል #ከማሺ_ዞን በፀጥታ ችግር ምክንያት ተፈናቅለው በአማራ ክልል ተጠልለው የቆዩ ዜጎች ወደ ነበሩበት ስፍራ መመለስ መጀመራቸውን የቤኒሻንጉል ክልል መንግስት አስታወቀ።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል #ከማሺ_ዞን በፀጥታ ችግር ምክንያት ተፈናቅለው በአማራ ክልል ተጠልለው የቆዩ ዜጎች ወደ ነበሩበት ስፍራ መመለስ መጀመራቸውን የቤኒሻንጉል ክልል መንግስት አስታወቀ።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"አቶ ጌታቸው አሰፋን በሚመለከት እስከ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ድረስ ሊያስጠይቅ የሚችል ጉዳይ አለ።" ዶክተር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የተቋረጠው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ከአርብ ጀምሮ ይቀጥላል። ኢትዮጵያ ቡና ከመቐለ 70 እንድርታ በ9 ሰዓት የፊታችን ዓርብ በአዲስ አበባ በዝግ ይካሄዳል።
ምንጭ፦ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምንጭ፦ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አበበ ተካ~ሆስፒታል ገባ!
ተወዳጁ ድምፃዊ አበበ ተካ በድንገት በገጠመው የጤና ችግር ሆስፒታል ገብቷል። ትላንት ጠዋት በተፈጠረበት ድንገተኛ የጤና ችግር ዋሽንግተን ሆስፒታል የገባው አቤ ከፍተኛ የህክምና ክትትል እየተደረገለት #አርአያ ተስፋማሪያም አሰታውቋል።
አያይዞም እንደተናገረው \\"ድምፃዊ #አበበ_ተካ የህክምና ክትትል እያደረጉለት የሚገኙትን የህክምና ባለሙያዎች የሚሰጡንን አጠቃላይ ውጤት በመጠበቅ ላይ ስንሆን፣ ሁሉም ወገን አበበ ተካን በጸሎት ያስበው\\" ሲል ተማጽኗል
ምንጭ፦ ጌጡ ተመስገን

በመላው ሀገሪቱ ላለፉት ቀናት ተቋርጦ የቆየው የኢንተርኔት አገልግሎት መስራት ጀምሯል! #ETHIOPIA
#update ነቀምቴ ከተማ ውስጥ ከትላንት በስቲያ ምሽት በአንድ ሆቴል ላይ በተጣለ የእጅ ቦምብ አደጋ አንድ ሰው ተገድሏል፤ ዘጠኝ ሰው መቁሰሉ ተነግሯል።
ባለፈው ሣምንትም የዚሁ ትናንት ጥቃቱ የተፈፀመበት “ሶከር” የሚባል ሆቴል ባለቤት አቶ ፈለቀ ዓለሙ ንብረት በሆነ ሌላ ሆቴል ላይ ተመሣሣይ አደጋ ተጥሎ ሰባት ሰው መቁሰሉ ተዘግቧል።
ቦምቡ ትናንት ሆቴሉ ላይ መወርወሩን ለቪኦኤ ያረጋገጥት የነቀምቴ ምክትል ከንቲባ አቶ ጫላ ገመዳ የቆሰለው ሰው ሰባት መሆኑን ተናግረዋል። እስከአሁን የተያዘ ተጠርጣሪ ወይም ለጥቃቱ ኃላፊነት የወሰደ የለም።
Via #VOA

ጨዋታው ለማክሰኞ ተላልፏል...
በዛሬው ዕለት ኢትዮጵያ ቡና ከመቐለ ሰባ እንደርታ ሊያደርጉት የነበረው ጨዋታ በመጪው ማክሰኞ እንዲካሄድ ተወሰነ። በፀጥታ ስጋት ምክንያት በተደጋጋሚ ሳይካሄድ የቆየው ይህ ጨዋታ በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ስታድየም ይካሄዳል ተብሎ ሲጠበቅ ነበር።
ሆኖም በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተሰጠ በሚገኘው ፈተና ምክንያት በፀጥታ አካላት ላይ ጫና በመኖሩ ፈተናው ከተጠናቀቀ በኋላ ጨዋታው እንዲካሄድ ፓሊስ በመጠየቁ ለማክሰኞ መዘዋወሩን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳን አቶ ኢሳያስ ጂራ አስታውቀዋል።
ፓሊስም ሆነ የእግር ኳስ ክለቦቹ ሀላፊነት የሚወስዱ መሆናቸውን በመግለፃቸው ጨዋታው ደጋፊዎች በተገኙበት ማክሰኞ በ10 ሰዓት በአዲስ አበባ ስታድየም ይካሄዳል።
Via #FBC

👍1
አሳዛኝ ዜና‼️
በአዲስ አበባ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን #ቡራዩ_ከተማ አስተዳደር መልካ ገፈርሳ ቀበሌ ዛሬ በአንድ መዋዕለ ሕጻናት ትምህርት ቤት ውስጥ የሚገኝ መጸዳጃ ቤት ተደርምሶ የ4 ሕጻናት ሕይወት አልፏል።
በአደጋው ስምንት ሕጻናት ወደ መጸዳጃ ቤቱ #ጉድጓድ ገብተው እንደነበር የዘገበው ኤፍ ቢ ሲ ከእነዚህ ውስጥም የአራቱ ሕይወት #ወዲያውኑ ማለፉን አመልክቷል።
ቀሪዎቹ አራት ሕጻናት ደግሞ በአደጋው ጉዳት ደርሶባቸው በቤተልና አለርት ሆስፒታሎች የሕክምና #ዕርዳታ እየተደረገላቸው መሆኑን የከተማዋ መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ወይዘሮ በየኑ ረዳ ተናግረዋል።
በአደጋው ሕይወታቸው ላለፉት ሕጻናት ጥልቅ ሐዘን የተሰማቸው መሆኑን በከተማ አስተዳድሩ ስም የገለጹት ወይዘሮ #በየኑ ለሟች ቤተሰቦችና ወዳጅ ዘመዶቻቸው መፅናናትን ተመኝተዋል። ትምህርት ቤቶች በግቢያቸው ውስጥ የሚገኙ መጸዳጃ ቤቶች ለተማሪዎች ደኅንነት ምቹ መሆናቸውን ማረጋገጥ ተገቢ መሆኑንም ጠቁመዋል።
የቡራዩ ከተማ ፖሊስ ምክትል ሳጅን #ሲሳይ_ዓለሙ በበኩላቸው መጸዳጃ ቤቱ የተደረመሰው በነበረበት የጥራት ችግር መሆኑን ተናግረዋል። ጉዳዩን አስመልክቶ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘትም ፖሊስ ምርመራ መጀመሩን ጠቁመዋል።
Via #AMMA

መንግሥት ለቀናት አቋርጦት የነበረውን የሞባይል ዳታ፣ ዋይፋና ብሮድባንድ ኢንተርኔት ፣ የፅሁፍ መልዕክት አገልግሎቶች ወደ መደበኛ አገልግሎቱ መልሷል፡፡
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኢትዮ ቴሌኮም ኢንተርኔት በማቋረጡ ሊከሰስ ነው!
ኢትዮጵያውያን ጠበቆች ኢትዮ ቴሌኮም ለቀናት ኢንተርኔት በማቋረጡ ፍርድ ቤት ሊገትሩት ነው። ጠበቆቹ ኢንተርኔት ማቋረጡ የዜጎችን መረጃ የማግኘት መብት የሚጥስ ነው ብለዋል።
ኔት ብሎክስ የተባለ ድርጅት እንዳስታወቀው ኢትዮ ቴሌኮም ኢንተርኔት በተቋረጠበት ወቅት በቀን ቢያንስ 4.5 ሚልዮን ዶላር እንዳጣ ዘግቧል።
Via @eliasmeseret/bbc/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኢትዮጵያውያን ጠበቆች ኢትዮ ቴሌኮም ለቀናት ኢንተርኔት በማቋረጡ ፍርድ ቤት ሊገትሩት ነው። ጠበቆቹ ኢንተርኔት ማቋረጡ የዜጎችን መረጃ የማግኘት መብት የሚጥስ ነው ብለዋል።
ኔት ብሎክስ የተባለ ድርጅት እንዳስታወቀው ኢትዮ ቴሌኮም ኢንተርኔት በተቋረጠበት ወቅት በቀን ቢያንስ 4.5 ሚልዮን ዶላር እንዳጣ ዘግቧል።
Via @eliasmeseret/bbc/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኢንትርኔት መቋረጥ፡ የሕግ ባለሙያዎች ኢትዮ-ቴሌኮምን ለመክሰስ አቅደዋል‼️
.
.
ሃገር አቀፍ ፈተና በመጣ ቁጥር ከተፈታኞች ቀጥሎ ጭንቀት ውስጥ የሚገባው የበይነ-መረብ [ኢንተርኔት] ተጠቃሚው ነው።
ባለፈው ሳምንት፤ ማክሰኞ የሆነው ይህ ነው። ሃገር አማን ብለው ዓለም እንዴት እንዳደረች ለመቃኘት የጎገሉ አንጀት የሚያርስ መረጃ ማግኘት አልቻሉም። ኧረ እንደውም ምንም ዓይነት መረጃ ማግኘት ይቅርና የሞባይልም ሆነ ኮምፒውተር ስክሪናቸው ላይ ብቅ ሊል አልቻለም።
ተጠቃሚው የሞባይልና ብሮድባንድ ኢንተርኔት አገልግሎት እንደተቋረጠ የገባው ዘግየት ብሎ ነው። ኢንተርኔት ብትጠበቅ የውሃ ሽታ ሆና ቀረች። ከሰዓት በኋላ አካባቢ ግን ብቅ አለች።
ደግሞ በነገታው አንዲሁ. . .ኢትዮ-ቴሌኮም ምን ገጠመህ? ተብሎ ቢጠየቅ እኔ 'ማውቀው ነገር የለም ሆነ ምላሹ። እንደው ክቡር ሚኒስትሩ ያውቁ ይሆን ቢባል 'ኢትዮ-ቴሌኮም እንጂ እኛ ምን አገባን' ነበር ለመገናኛ ብዙሃን የተሰጠው መልስ።
እርግጥ ሰዎች የኢንተርኔት መቋረጡ ከሃገር አቀፍ ፈተናዎች ጋር የተያያዘ ሊሆን እንደሚችል ገምተዋል [አምና፣ አቻምና የተከሰተውን ልብ ይሏል]፤ ይህ ግን መላ ምት እንጂ የተጨበጠ መረጃ አይደለም።
ሐሙስ ዕለት ከኢንተርኔቱ አልፎ አጭር የፅሑፍ መልዕክት አገልግሎት እንደተቋረጠ ተሰማ። 'ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ወደ ሥልጣን ከመጡ በኋላማ እንዲህ ዓይነት ነገር አይታሰብም?' ያሉ ሁኔታው ግራ አጋባቸው።
በጉጉት ስትጠበቅ የነበረችው ኢንተርኔት አርብ ጀምበር ልትጠልቅ ስታኮበኩብ ገደማ ብቅ አለች። አጭር የፅሑፍ መልዕክቱ ግን እንደቀለጠ ቀረ። አሁንም ቢሆንም የኢንተርኔት አገልግሎት ተመልሶ ያልመጣባቸው ሥፍራዎች እንዳሉ ይነገራል።
«ኢትዮ-ቴሌኮምን እከሳለሁ»
የሕግ ባለሙያው አቶ ዮሐንስ እንየው በሰመራ ዩኒቨርሲቲ የሕግ መምህር እና የዲጂታል መብት አማካሪ ናቸው። ከሰሞኑ በተፈጠረው ጉዳይ ኢትዮ-ቴሌኮም በሕግ ሊጠየቅ ይገባል ከሚሉ ሰዎች መካከል ናቸው።
«ኢንተርኔት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ከመጡ ወዲህ እንኳ አራት ጊዜ ያክል ተቋርጧል። እርግጥ ጉዳዩ እንደ ቅንጦት ነው የሚታየው። በሕግ ባለሙያዎች አንድም አንገብጋቢ ከሚባሉ ጉዳዮች ተርታ አይመደብም። ወደሌሎች የአፍሪካ ሃገራት ስትመጣ ግን መንግሥት መሰል ድርጊቶችን ሲፈጽም ይከሰሳል። ብሩንዲ ብትል፣ ታንዛኒያ ሆነ ኡጋንዳ ብትሄድ ኢንተርኔት ሲቋረጥ ይከሳሉ። እንዲህ ዓይነት ጉዳዮችን በቀላል አይልፏቸውም ሌሎች ሃገራት። እኛ ጋር ግን እንደ ቀልድ ነው የሚታየው፤ ማንም ተጠያቂ አይሆንም።»
እርግጥ አቶ ዮሐንስ እና ሌሎች የሕግ ባለሙያዎች ጉዳዩ ውልብ ያለላቸው ከሰሞኑ ነው፤ ሂደቱም ገና ጅማሬ ላይ ነው። ቢሆንም እንደውም ሃሳቡን ማጫር በራሱ አንድ እርምጃ ነው ይላሉ ባለሙያው።
«እንደው ውይይቱን ብናስጀምረው ብለን ነው። በቀጣይ መንግሥትም ይሁን ኢትዮ-ቴሌኮም፤ አሁን ደግሞ ሌሎች 'ኔትዎርክ ፕሮቫይደሮች' እየመጡ ስለሆነ [ፕራይቬታይዝ እየተደረገ ስለሆነ] ወደፊት ለሚያጋጥሙ የተለያዩ ክስተቶች አላግባብ በሆነ መልኩ ከሕግ ውጭ መሰል ድርጊት እንዳይጸሙም ነው።»
ምን ተብሎ ይከሰሳል?
ባለፈው ሳምንት እንደ ፌስቡክና ትዊትር ያሉ ማህበራዊ ድር አምባዎች ጭር ብለው ነው የከረሙት [ዕድሜ ለኢንተርኔት መቋረጡ]። ከሃገር ውጭ ያሉ ኢትዮጵያዊያን ግን ተቃውሟቸውን 'በነፃነት' ሲገልጹ ከርመዋል።
ኢትዮ-ቴሌኮም ተከሰሰ እንበል. . .በዋናነት ክሱ የሚሆነው ምንድን ነው? የመረጃ ነፃነት መግፈፍ? ተጠቃሚዎች ለገዙት 'ዳታ' ሳይጠቀሙበት መክሰሩ ነው? ግራ ያጋባል።
«እርግጥ ነው ኢንተርኔት መዘጋት ብዙ ችግር ፈጥሯል። ግን እኛ በዋናነት ከምንም በላይ የመናገር ነፃነት፤ ሁለተኛ ደግሞ መረጃ የማግኘት መብት ላይ ነው የምናተኩረው። ምናልባት ሌሎችም ክሱን ፋይል ስናደርግ የሚቀላቀሉን ካሉ ያስከተለውን ኪሳራን ልናካታት እንችላለን። ለምሳሌ አንድ ሪፖርት ኢንተርኔት መቋረጥ ሃገሪቱን 4.5 ሚሊዮን ዶላር በቀን ያሳጣታል ይላል። ይህ ማለት የማህበራዊ እና ምጣኔ ሃብታዊ መብቶችንም ይነካል ማለት ነው።»
«የተደራጁ ማህበራት ቢኖሩን. . .» ይላሉ አቶ ዮሐንስ፤ «የተደራጁ ማህበራት ቢኖሩን ክሱ በተነፃፃሪ ቀላል ይሆን ነበር። ለምሳሌ የብሎገሮች [ጦማሪያን] ማህበር ቢኖር በኢንትርኔት መቋረጡ የደረሰባቸውን ተፅዕኖ አስረድቶ ክስ ማቅረብ ይቻላል። ሌሎችም አሁን ስማቸውን መጥቀስ የማያስፈልግ ማህበራት እና የግል ተቋማትም ይመለከታቸዋል።»
እርግጥ ነው ቴሌ ቢከሰስ የክሱ ፋይል በርካታ ወረቀቶች እንደሚፈጅ ይታሰባል። ከምጣኔ ሃብት፣ ከማህበራዊ ትስስር፣ እና ከሰብአዊ መብት ጥሰት አንፃር ጉዳዩን ማየት ይቻላልና።
ምናባዊ ክስ
ኢትዮ-ቴሌኮምን የመክሰስ ሂደቱ ገና እንጭጭ ቢሆንም፤ ሃሳቡ ግን መንሸራሸር ጀምሯል። ድርጅቱ ከሰሞኑ ለፈፀመው ድርጊት በፍርድ አደባባይ ሊቆም እንደሚገባ በርካታ የሕግ ሰዎች ይስማማሉ።
'ኢትየ-ቴሌኮም ሊከሰስ እንደሆነ ሰምተው ይሆን?' ብለን የጠይቅናቸው ታዋቂው የሕግ ሰው አቶ አምሃ መኮንን «እርግጥ ጉዳዩ ለእኔ አዲስ ነው ግን ኢትዮ-ቴሌኮም መከሰስ እንዳለበት አምናለሁ» የሚል ምላሽ ነበር የሰጡን።
እስቲ ክሱ ፋይል ተደረገ እንበል። የፍርድ ቤት ምላሽ ምን ይሆናል ብላችሁ ታስባላችሁ? ለሕግ ባለሙያው አቶ ዮሐንስ ያቀረብነው ጥያቄ።
«ፍርድ ቤቱ ሥልጣን የለኝም ሊለን ይችላል። ጥቅም የላችሁም ሊል ይችላል። በፍትሀ-ብሔር ጉዳይ ወይንም በሕዝብ ጥቅም ጉዳይ አንድ ክስ ሲቀርብ ጥቅም ሊኖር ይገባል። ጥቅም የሚባለው የንብረት ወይንም መብት ማስከበር ሊሆን ይችላል። ሆኖም ግን አሁን እኛ የምናቀርበው 'ስትራቴጂክ ሊቲጌሽን' [ሰብዓዊ መብትን ለማስከበር የሚቀርብ ክስ] ስለሆነ የሕዝብ ጥቅም ጉዳይ ነው። ሕገ-መንግሥቱ አንቀፅ 37 ላይ ፍትህ የማግኘት መብት የሚለውን መሠረት አድርገን ነው ክሱን ለማቅረብ የምንሞክረው።»
ክሱ ተሳካም አልተሳካ፤ ፍርዱ የሕግ ባለሙያዎቹ የሚሹት ሆነም አልሆነ፤ አንድ ጉዳይ ግን ግልፅ ይመስላል። ሰማይ አይታረስም ንጉሥ አይከሰስ ተደርምሶ፤ ሰማይ ባይታረስ ንጉሥ ግን ይከሰስ ሆናል። ንጉሡ ኢትዮ-ቴሌኮም መሆኑ ነው እንግዲህ።
ምንጭ፦ BBC

ኢትዮ ቴሌኮም❓
ኢትዮ-ቴሌኮም በመላ ሀገሪቱ ኢንተርኔት መቆራረጡን ተከትሎ ደንበኞች ያልተጠቀሙበትን የክፍያ ማስተካከያ እንደሚያደርግ አስታውቋል።

ትናንት በድንገት ሕይወታቸው ያለፈው የቀድሞው የግብፅ ፕሬዝዳንት መሐመድ ሙርሲ ሥርዓተ-ቀብር ተፈጸመ!
በካይሮ ፍርድ ቤት ጉዳያቸውን በመከታተል ላይ ሳሉ ድንገት ተዝለፍልፈው ከወደቁ በኋላ ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት የሙርሲ ሥርዓተ-ቀብር ሲፈጸም ከፍተኛ የጸጥታ ጥበቃ ነበር። የቀድሞው ፕሬዝዳንት ቤተሰቦች በካሮ ከተማ የቶራ እስር ቤት ውስጥ በሚገኝ መስጊድ የተደረገውን የጸሎት ሥነ-ሥርዓት እና ሥርዓተ ቀብራቸውን መታደማቸውን ከሙርሲ ጠበቆች አንዱ የሆኑት አብዱል ሙነይም አብደል ማቅሱድ ተናግረዋል።
የመሐመድ ሙርሲ ልጅ አሕመድ እንደተናገሩት የአገሪቱ የጸጥታ ኃይሎች የቀድሞው ፕሬዝዳንት በሻርቂያ ግዛት በሚገኘው የትውልድ መንደራቸው በሚገኝ የቤተሰቦቻቸው የመቃብር ሥፍራ እንዳያርፉ ክልከላ አድርገዋል።
አሶሼትድ ፕሬስ እንደዘገበው ጋዜጠኞች የቀብር ሥነ-ሥርዓቱን እንዳይከታተሉ ፎቶ ግራፍም እንዳያነሱ የጸጥታ አስከባሪዎች ክልከላ አድርገዋል። ጋዜጠኞች ወደ ሙርሲ የትውልድ ከተማ መጓዝም ተከልክለዋል።
የ67 አመቱ መሐመድ ሙርሲ አሁን በሕግ የታገደውን የሙስሊም ወንድማማቾች የፖለቲካ ንቅናቄ በመወከል በጎርጎሮሳዊው 2012 ዓ.ም. በተደረገው ምርጫ አሸንፈው የግብፅ ፕሬዝዳንት ሆነው ነበር። ከአንድ አመት መሪነት በኋላ በአገሪቱ ጦር ከሥልጣናቸው የወረዱት ሙርሲ በእስር ላይ በነበሩባቸው አመታት የስኳር ሕመም ነበረባቸው። በተደጋጋሚ በጠባብ ክፍል ታስረው እንዲቆዩ የተደረጉት ሙርሲ ከጎብኚዎቻቸው እንዳይገናኙ ክልከላ ተደርጎባቸው ቆይቷል።
ሙስሊም ወንድማማቾች ንቅናቄ ሥልጣን ላይ ያለው መንግሥት ሙርሲን ለአመታት በአስከፊ ሁኔታ በእስር ላይ በማቆየት "ገድሏቸዋል" ሲል ከሷል።
Via DW Amharic

ነብስ ይማር!!
የጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ አባት አህመድ ዓሊ በትላንትናው ዕለት አረፉ። አቶ አህመድ ዓሊ ትላንት 8 ሰዓት አካባቢ ነው ህይወታቸው ያለፈው።

#update በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 አካባቢ እንጀራን ከባዕድ ነገር ጋር ቀላቅለው ለገበያ ሲያቀርቡ የተገኙ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ።
በቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ወረዳ 7 ጉርድ ሾላ አካባቢ እንጀራን ከባዕድ ነገር ጋር ቀላቅለው ለገበያ ሲያቀርቡ የተገኙ ግለሰቦች በቁጥጥር መዋላቸውን የወረዳው የምግብ የመድሃኒትና ጤና እንክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ፅህፈት ቤት አስታውቋል።
በዚህ መሰረትም ባዕድ ነገር የተቀላቀለበት 3 በርሜል ተኩል የተቦካ ሊጥ፣ ከ80 በላይ የተጋገረ እንጀራና 3 ማዳበሪያ የተበላሸ እንጀራ መያዙን የጽህፈት ቤቱ ሃላፊ አቶ ደረጀ መንግስቱ ተናግረዋል።
በድርጊቱ የተሳተፉት ግለሰቦችም በቀን 1ሺህ የሚደርስ እንጀራ ለተለያዩ ደንበኞቻቸው ያከፋፍሉ የነበረ መሆኑን ከቦሌ ክፍለ ከተማ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
የአካባቢው ነዋሪዎች በበኩላቸው መንግስት አስተማሪ እርምጃ ባለመውሰዱ ችግሩ እየተባባሰ መምጣቱን በመግለጽ መንግስት አስተማሪ እርምጃ እንዲወስድ ጠይቀዋል።
ወቅቱ የኮሌራ ወረርሽኝ የሚስፋፋበት በመሆኑ ህብረተሰቡ ራሱን ከመሰል ህገወጥ ድርጊቶች እንዲጠበብቅም አቶ ደረጀ አሳስበዋል።
Via FBC