TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በዛሬው የከሰዓት በፊት የችሎት ውሎው በእነ አቶ በረከት ስምዖን እና አቶ ታደሰ ካሳ የክስ መዝገብ ላይ የዐቃቤ ህግን ምስክሮች ቃል ሰምቷል፡፡

ዛሬ ግንቦት 22/2011 ከሰዓት በኋላ ሌሎች የዐቃቤ ህግ ምስክሮችን ቃል ለመስማት ቀጠሮ ሰጥቶም ችሎቱ ተጠናቋል፡፡

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፊቼ ጫምባላላ!! ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ለፊቼ ጫምባላላ በዓል ያስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት👇

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ኢትዮጵያዊቷ ኢንተርናሽናል ዳኛ ሊዲያ ታፈሰ በዓለም ዋንጫ ለመዳኘት ወደ ፈረንሳይ አቀናች፡፡

በፈረንሳይ አስተናጋጅነት ለስምንተኛ ጊዜ የሚከናወነው የፊፋ የዓለም ሴቶች ዋንጫ ከጁን 7 እስከ ጁላይ 7 ድረስ በ24 ሀገሮች መካከል ይካሄዳል።

በዚህ ውድድር ላይ ለመዳኘት ከተመረጡት ዳኞች አንዷ የሆነችው ኢትዮጵያዊቷ ሊዲያ ታፈሰም ወደ ፈረንሳይ አቅንታለች።

ምንጭ፡ ሶከር ኢትዮጵያ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በሀገሪቱ ከተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው ከነበሩ ዜጎች መካከል 1 ነጥብ 2 ሚሊዮኑ ወደ ቀያቸው መመለሳቸውን የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል ገለፁ።

ሚኒስትሯ ከምእራብ ጉጂ ዞን ተፈናቅለው የነበሩና በጌዲኦ ዞን ገደብ ወረዳ ተጠልለው የቆዮ ወገኖች ወደ ቄያቸው ተመልሰው የተቋቋሙበትን ሁኔታ ከኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር በመሆን ቅኝት ካደረጉ በኋላ እንደገለጹት፥ በመላው ሀገሪቱ ተፈናቅለው የሚገኙ ወገኖችን መልሶ የማቋቋሙ ስራ እስከ ሰኔ መጨረሻ ለማጠናቀቅ በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ከሰላም ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል፣ ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና ከደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሚሊዮን ማቴዎስ ጋር በመሆን በቅርቡ ወደቀያቸው የተመለሱ የጉጂና የጌዴኦ ማኅበረሰብ አባላትን አነጋግረዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአሜሪካው ቦይንግ ኩባንያ የበላይ ዴኒስ ሙለንበርግ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት በሆነው ቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን መከስከስ በግሌ ይቅርታ እጠይቃለሁ አሉ፡፡

ከ2 ወራት በፊት በተከሰከሰው የበረራ ቁጥር 302 አውሮፕላን አደጋ የ157 ሰዎች ሕይወት መቀጠፉ ይታወቃል፡፡

ከዚህ አደጋ 5 ወራት ቀደም ብሎ የኢንዶኔዥያው ላየን ኤር ንብረት የሆነ መሰል አውሮፕላን ወድቆ 189 ሰዎች እንደሞቱ ቢቢሲ አስታውሷል፡፡

ቀደም ሲል ለነዚህ አደጋዎች በኩባንያ ደረጃ እናዝናለን ያሉት የቦይንግ የበላይ ዴኒስ ሙለምበርግ በግሌ የሟች ቤተሰቦችን ይቅርታ እጠይቃለሁ ማለታቸው ተሰምቷል፡፡

አደጋ የገጠመው የኢትዮጵያው አውሮፕላን ዋና አብራሪ አባት ዶ/ር ጌታቸው ተሰማ የቦይንግ ዋና ስራ አስፈፃሚውን ይቅርታ የዘገየ እና የረፈደበት ነው ማለታቸው በመረጃው ተጠቅሷል፡፡

በአሁኑ ወቅት ማክስ 8 ስሪት አውሮፕላኖች የበረራ አስተማማኝነታቸው እስኪረጋገጥ ከአገልግሎት ውጭ እንደተደረጉ ነው፡፡

Via #BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አሜሪካ ሽብርተኝነትን ለመዋጋት በማደርገው ዘመቻ ተባባሪ አይደሉም በሚል ከፈረጀቻቸው ሃገራት ዝርዝር ውስጥ (Counterterror Non-Cooperation List) ተካታ የነበረቸው ጎረቤት ኤርትራ ነፃ ነሽ ተብላለች።

አሜሪካ አሁንም የዘመቻዬ አጋር አይደሉም ያለቻቸውን ኢራን፣ ሰሜን ኮሪያ፣ ሶሪያንና ቬኔዙዌላን በጠላትነት እንደመዘገበቻቸው ነው። ለኤርትራ ከዚህ ዝርዝር ውስጥ መውጣት የመንግሥታቱ ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት በሃገሪቱ ላይ ጥሎት የነበረውን ማዕቀብ ማንሳቱ፣ የአሜሪካ ኮንግረስ ልዑካን ከ14 አመታት በኋላ የኤርትራን መሬት መርገጥ መቻሉ እንዲሁም ኤርትራ ከኢትዮጵያና ሌሎች የአፍሪካ ቀንድ ሃገራት ጋር የጀመረችው መልካም ጉርብትና ከፍተኛ አስተዋፅዖ እንዳደረጉ የፖለቲካ ተንታኞች ይናገራሉ።

Via Petros Ashenafi
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቃቤ ህግ በአቶ በረከት ስምዖንና አቶ ታደሰ ካሳ ላይ ያቀረባቸውን ተጨማሪ የቃል ምስክሮች አዳመጠ።

ፍርድ ቤቱ ከትናንት ግንቦት 21ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ዛሬ ከሰዓት ባስቻለው ችሎት አቶ በረከት ስምዖን እና አቶ ታደሰ ካሳ በተከሰሱበት የዳሸን ቢራ አክሲዮን ማኅበር ሽያጭ ጉዳይ አቃቤ ህግ ያቀረባቸውን ምስክሮች ቃል አድምጧል።

ከዳሸን ቢራ አክሲዮን ማኅበር ሽያጭ ጋር በተያያዘ አቃቤ ህግ ካቀረባቸው ስምንት የቃል ምስክሮች አምስቱን በማዳመጥ የዛሬ ከሰዓት ችሎት ተጠናቋል።

አቃቤ ህግ ሦስቱን ምስክሮች ከሌሎች የተለየ መረጃ አይሰጡም በሚል እንዲቋረጥ በጠየቀው መሠረት ፍርድ ቤቱ ጥያቄውን ተቀብሎ እንዲቋረጥ ማድረጉን አብመድ ዘግቧል።

ተጠርጣሪዎቹ በተከሰሱባቸው ሌሎች የክስ መዝገቦች ላይ የአቃቤ ህግን ምስክሮች ለመስማት ፍርድ ቤቱ ለግንቦት 28 ቀን 2011 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል።

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አፕል የምታክል ጨቅላ ተወለደች ቢባል ማን ያምናል?

በአሜሪካ 245 ግራም ብቻ የምትመዝን የአለም ትንሿ ጨቅላ ተወልዳለች። ህፃኗ ያለጊዜ የተወለደች ሲሆን፤ በሆስፒታል በማሞቂያ ውስጥ ቆይታ ከሰሞኑ ከሆስፒታል ወጥታለች።

ሳይቤ የሚል ስያሜ የተሰጣት ይህች ጨቅላ በ23ኛ ሳምንቷ በታህሳስ ወር የተወለደች ሲሆን፤ ሚዛኗ ከአንድ አፕል የማይበልጥ መሆኑ በአለም ዘንድ አግራሞትን ፈጥሯል።

ዶክተሮች ለሰአታት ብቻ በህይወት እንደምትቆይ ሞያዊ አስተያየታቸውን ቢሰጡም ይኼው አምስት ወራት ቆይታዋ 2.5 ከ.ግራም ሆና ከሆስፒታል ወጥታለች። ሲያቤን ስትንከባከባት የነበረችው ነርስ በህይወት መትረፏ "ተአምር" ነው ብላለች።

Via #BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ባምላክ ጥቃት ተፈፅሞባቸው ነበር...

የግብጹ ዛማሌክ ከሞሮኮው ሬይኔሳንስ ቤርካን (RS Berkane) ያደረጉትን የአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የእግር ኳስ ጨዋታ የዳኙት ባምላክ ተሰማ ሜዳ ውስጥ ጥቃት ተፈጽሞባቸዋል። ባምላክ ጥቃቱ የተፈጸመባቸው ባለፈው እሁድ የተደረገውን ጨዋታ በዳኙበት ወቅት ነው። የግብፅ ሰዎች እንደሚሉት ጥቃቱን የፈጸሙት የሞሮኮ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን እና የሬይኔሳንስ ቤርካን ፕሬዝዳንት ፎክዚ ሌክጃ ናቸው። ክለቡ በደርሶ መልሱ ጨዋታ ዳኛ ባምላክ ተሰማ ፍጹም ቅጣት ምት መስጠታቸውን በመቃወም ክስ እንደሚመሰርትባቸው አስታውቋል። የግብፁ ዛማሌክ በመለያ ምት አርኤስ ቤርካን የተባለውን የሞሮኮ ክለብ አሸንፎ የካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ባለቤት የሆነው ባለፈው እሁድ ነበር።

Via #Eshete_Bekele
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ከውጭ ከሚገቡ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ላይ የተነሳው የ30 በመቶ የዕርጅና ግብር ቅነሳ መመሪያው ከመውጣቱ በፊት የታዘዙ ተሽከርካሪዎችን አይመለከትም- ብሏል የገቢዎች ሚኒስቴር፡፡ መመሪያው ከመውጣቱ በፊት ተገዝተው ወደ ሀገር ውስጥ እየተጓጓዙ ያሉትንና ለመጓጓዝ ዝግጁ የሆኑትን እንደማይመለከትም አስታውቋል፡፡ የባንክ ፈቃድ ማረጋገጫ ያገኙ ያገለገሉ እቃዎችን እንዲሁም ያለውጭ ምንዛሬ ክፍያ ተገዝተው ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት የተጫኑ ያገለገሉ እቃዎችም መመሪያው እንደማይመለከታቸው ተሰምቷል። አንዳንድ አስመጭዎች እንደሚሉት መመሪያው ተግባራዊ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ወደ ሀገር ውስጥ በሚገቡ ያገለገሉ መኪናዎች ላይ በትንሹ የጨመረው ቀረጥ ከ80 ሺህ ብር በላይ ደርሷል።

Via የገቢዎች ሚኒስቴር/#wazema/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የሲዳማ ብሄረሰብ ዘመን መለወጫ ፊቼ ጨምበላላ ዐመታዊ በዓል በሀወሳ ከተማ በመከበር ላይ ነው፡፡ በበዓሉ ላይ የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሸመልስ አብዲሳ የተመራ ልዑክ ተገኝቷል፡፡ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድም ለሲዳማ ሕዝብ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ ፊቼ ጨምበላላን የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) በልዩ ባህላዊ ቅርስነት መዝግቦታል፡፡ በተያያዘ ዜና የብሄረሰቡ መብት ተሟጋቾች “የሲዳማ ሜዲያ ኔትወርክ” የተሰኘ የሳተላይት ቴሌቪዥን ሥርጭት ዛሬ መጀመራቸውን አስታውቀዋል፡፡

Via #ዋዜማ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የቻይናው ሁጂያን ግሩፕ በጅማ ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ በተለያዩ ዘርፎች የማምረቻ ፋብሪካዎቹን እንዲተክል የሚያስችል ስምምነት ዛሬ ተፈርሟል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ለገጠመው የገንዘብ ችግር ህዝበ ሙስሊሙና ባለሃብቶች ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቀረበ።

ጠቅላይ ምክር ቤቱ ለገጠመው የገንዘብ ችግር ህዝበ ሙስሊሙና ባለሃብቶች ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ ያቀረቡት የኡላማዎች ምክር ቤት ሰብሳቢ ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጅ ኡመር እድሪስ ናቸዉ፡፡

የኡላማዎች ምክር ቤት ሰብሳቢ ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጅ ኡመር እድሪስ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ፤ምክርቤቱ ለሰራተኞች ደሞዝ መክፈል የማይችልበት ደረጃ ላይ ደርሷል ብለዋል።

ጊዜያዊ ምክር ቤቱ ተቋሙን ሲረከብ በባንክ አካውንቱ የተገኘው አንድ ሚሊየን ብር ብቻ መሆኑን ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጅ ኡመር ገልፀዋል። አሁን ላይም በወር ለሰራተኛ የሚከፈለውን 3 ሚሊየን ብር መክፈል እንደማይችልና ለሰራተኞች የግንቦት ወር ደመወዝም እንዳልተከፈላቸውም ገልጸዋል።

የጊዜያዊ ምክር ቤቱን ለመደገፍ የተቋቋመው የቴክኒክ ቦርድ ሰብሳቢ ሀጅ ከማል ሀሩን የፋይናንስ መመሪያን ባልተከተለ አሰራር ችግሮች መፈጠራቸውን ገልፀዋል።

የተፈጠረው የገንዘብ ችግር እጅግ አሳሳቢ እንደሆነ ያነሱት ሀጅ ኡመር፥ተቋሙ የተረከበውን ዝቅተኛ ገንዘብ ከግምት ውስጥ በማስገባት የራሱን ቋሚ የገንዘብ ምንጭ እስኪፈጥር ድረስ ባለሀብቶች እና ህዝበ ሙስሊሙ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።

ድጋፍ ማድረግ ለሚፈልጉ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጦር ሀይሎች ቅርንጫፍ የሂሳብ ቁጥር 1000024736408 እንዲሁም በኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ ሂሳብ ቁጥር 137526 ማስገባት እንደሚችሉ ገልፀዋል።

Via #ArtsTV
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አንድ ተሳቢ መኪና 26 የቀንድ ከብቶች ላይ ጉዳት አደረሰ። ግንቦት 19/2011 ዓ·ም ከምሽቱ 2:00 አካባቢ ከፓዊ ጃዊ እየሄደ የነበረ ኮድ ኢት 41829, የተሳቢ ኮድ 08068 የሆነ ተሳቢ መኪና ከ26 የቀንድ ከብቶች ላይ ጉዳት አድርሷል። ከ26ቱ ከብቶች ውስጥ 17ቱ የሞቱ እና 9ኙ ደግሞ የቆሰሉ ናቸው።

ምንጭ፦አዊ ኮሙዩኒኬሽን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በአዲስ አበባ የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 በህገወጥ መንገድ መሬት በመውረር ግንባታ ያከናወኑ የተገኙ የፖሊስ አባላት በቁጥጥር ስር ዋሉ።

fbc አረጋግጫለሁ እንዳለው በቁጥጥር ስር ከዋሉት የፖሊስ አባላት መካከል ዋና ሳጅን #ዘሪሁን_ወልዴ፣ ረዳት ሳጅን #አሸናፊ_ካንኮ፣ ረዳት ሳጅን #አግማስ_አንዱዓለም እና ረዳት ሳጅን #ሀብተማርያም_ጓንጉል ይገኙበታል።

በቀጣይነትም በህገወጥ የመሬት ወረራ ላይ ተሳትፈው የተገኙ የመንግስት አካላት፣ ባለሃብቶች እና ግለሰቦች ላይ የከተማ አስተዳደሩ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድም ተገልጿል።

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ፅ/ቤት👇

የመሬት ወረራ በተካሄደባቸው አምስቱ ክ/ከተሞች ውስጥ በህገወጥ መንገድ መሬት በመውረር ግንባታ ያካሄዱ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች እና የፖሊስ አባላት በቁጥጥር ስር እየዋሉ ነው፡፡

የተደረገውን የመሬት ወረራ እና የተሳታፊዎቹን ሙሉ መረጃ በተመለከተ ተጨማሪ መረጃዎች በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በኩል ይፋ ይደረጋል።

በቀጣይነትም በህገወጥ የመሬት ወረራ ላይ ተሳትፈው የተገኙ የመንግስት አካላት ፣ ባለሃብቶች እና ግለሰቦች ላይ የከተማ አስተዳደሩ ህጋዊ እርምጃ መውሰዱን ይቀጥላል፡፡

ህብረተሰቡም ህገ-ወጥ የመሬት ወረራ የሚያደርጉ እና የሚያስተባብሩ አካላትን ለከተማ አስተዳደሩ በመጠቆም ህወጥነትን በጋራ እንድንከላከል የከንቲባ ፅ/ቤት ጥሪውን ያቀርባል፡፡

Via @mayorofficeAA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update እስራኤል ምክር ቤት በመጪዉ መስከረም አዲስ ምርጫ ለማድረግ ዛሬ እራሱን አፈረሰ። ምክር ቤቱ የተሰየመዉ ባለፈዉ ሚያዚያ በተደረገዉ ምርጫ ማግስት ነበር። በእስራኤል ታሪክ ለአጭር ጊዜ የቆየዉ ምክር ቤት አዲስ ምርጫ እንዲደረግ ጠርቶ እራሱን የበተነዉ 74 ለ 45 በሆነ ድምፅ ነዉ። አዲስ ምርጫ እንዲደረግ መጠራቱ በምርጫዉ ያሸነፈዉን የሊኩድ ፓርቲን ለሚመሩት ለጠቅላይ ሚንስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ታላቅ ዉድቀት ነዉ። ምርጫዉ የተጠራዉም ሆነ ፓርላማዉ የተበተነዉ ጠቅላይ ሚንስትሩ የስራኤል ቤይታኑ የተሰኘዉን ፓርቲ ከሚመሩት ከቀድሞዉ መከላከያ ሚንስትር አቪግዶር ሊበርማን ጋር መስርተዉት የነበረዉን ጥምረት መቀጠል ባለመቻላቸዉ ነዉ። እስራኤልን ለበርካታ አዓመታት የመሩት አክራሪዉ ፖለቲከኛ ኔታንያሁ በተጠረጠሩበት የሙስና ወንጀል ይከሰሳሉ የሚለዉ ዘገባም እየተደጋጋመ ነዉ። የሕግ ሰዎች እንደሚሉት ኔታንያሁ በሙስናዉ ከተወነጀሉ ሥልጣናቸዉም፣ ፖለቲካዊ ሕልዉናቸዉም ያበቃል።

Via #DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia