JiT👆
"ጅማ ዩንቨርሲቲ(JIT) ሙስሊም ተማሪዎች ረመዳን ጾም ስለሆነ ሌሊት ምግብ ልዘጋጅልን ይገባል በምል ሰልፍ ላይ ናቸው።"
@tsegabwolde @tikvahethiopia

#Breaking
አቶ ጌታቸው አሰፋን ጨምሮ በ26 የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት የሥራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች ላይ ክስ መመስረቱን ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ አስታወቀ።
ከባድ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ፈጽመዋል በሚል በፌደራል ፖሊስ ወንጀል መርማሪዎች ላይ፤ በማረሚያ ቤት የሥራ ኃላፊዎች ላይ እንዲሁም በብሔራው መረጃና ደህንነት አገልግሎት የሥራ ኃላፊዎች ላይ ሲካሔድ የነበረው የወንጀል ምርመራ ሲካሔድ መቆየቱ ያስታወሰው ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ፤ በዚሁ መሰረት ዓቃቤ ሕግ በወንጀል መርማሪዎች ላይ፤ በማረሚያ ቤቱ የሥራ ኃላፊዎች ላይ እንዲሁም በብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት የስራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች ላይ በሶስት የተለያዩ መዝገቦች ክስ ተመስርቷ ብሏል፡፡
በመርማሪዎች ላይ በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የተከፈተው እና በማረሚያ ቤት ኃላፊዎች በነበሩት ላይ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የተከፈቱት መዛግብት የከስ ሂደቱ ቀጥሎ ምስክር ለመስማት ተቀጥረዋል፡፡
በሶስተኛውና በዚህኛው የመጨረሻ መዝገብ ላይ 26 የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት የሥራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች በጠቅላላው 46 ክሶች ተመስርቶባቸዋል፡፡
በክሶቹ ውስጥ 22ቱ ተከሳሾች በአሁኑ ወቅት በእስር ላይ የሚገኙ ሲሆን፤ በሌላ በኩል የቀድሞ የአገልግሎቱን ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው አሰፋን ጨምሮ አቶ አጽብሃ ግደይ፣ አቶ አሠፋ በላይ እና አቶ ሽሻይ ልዑል በተባሉ የቀድሞ የአገልግሎቱ የሥራ ኃላፊዎች ላይ በሌሉበት ክስ ዛሬ ሚያዚያ 29 ቀን 2011 ዓ.ም በከፍተኛ ፍርድ ቤት ልዴታ ምድብ ችሎት ይመሰረትባችዋል፡፡
በአቶ ጌታቸው ላይ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ህግ አንቀጽ 32/1/ (ሀ) (ለ) እና 407/1/ (ለ) (ሐ) እና 407/3/ ላይ የተደነገገውን በመተላለፍ ስልጣንን ያለአግባብ መገልገል ከባድ የሙስና ወንጀል መፈጸም እንዲሁም በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ህግ አንቀጽ 32 (1) ሀ እና ለ እንዲሁም የሙስና ወንጀሎችን ለመደንገግ የወጣውን አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 9 /1/ (ለ) እና (ሐ) እና 9/3/ ላይ የተደነገገውን በመተላለፍ ስልጣንን ያለአግባብ መገልገል ከባድ የሙስና ወንጀል ፈጽመዋል በሚል ክስ ቀርቦባቸዋል፡፡
በሌሎቹ ሁሉም ተከሳሾች ላይ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ህግ አንቀጽ 32/1/ (ሀ) (ለ) እና 407/1/ (ለ) (ሐ) እና 407/2/ ላይ የተደነገገውን በመተላለፍ ስልጣንን ያለአግባብ መገልገል ከባድ የሙስና ወንጀል መፈጸም እንዲሁም በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ህግ አንቀጽ 32 (1) ሀ እና ለ እንዲሁም የሙስና ወንጀሎችን ለመደንገግ የወጣውን አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 9 /1/ (ለ) እና (ሐ) እና 9/2/ ላይ የተደነገገውን በመተላለፍ ስልጣንን ያለአግባብ መገልገል ከባድ የሙስና ወንጀል ፈጽመዋል በሚል ክስ ተመስርቶባቸዋል፡፡
ሥልጣንን ያለአግባብ መገልገል ክስ ሊቀርብባቸው የቻለው ተከሳሾች በግልጽ ከተሰጣቸው ሥልጣን ወይም ኃላፊነት አሳልፈው በመስራት እንዲሁም ሥልጣናቸው ወይም ኃላፊነታቸው የማይፈቅድላቸውን በተለይም ሥልጣን ወይም ኃላፊነት ሳይኖራቸው በሌላ ሰው መብት ላይ ጉዳት እንዲደርስ በማሰብ በተበዳዮች ላይ ከባድ የሰብዓዊ መብት ጥሰት በመፈጸማቸው ነው፡፡
በአቶ ጌታቸው ላይ በንዑስ አንቀጽ 3 መሰረት ክስ ሊቀርብባቸው የቻለው፦
1ኛ) በሚኒስትር ማዕረግ የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ጀነራል የነበሩ በመሆናቸው የኃላፊነት ወይም የሥልጣን ደረጃቸው ከፍተኛ በመሆኑ፤
2ኛ) ኃላፊነታቸውን የጣሱበት ዓላማ ከባድ በመሆኑ እንዲሁም
3ኛ) በሕዝቦች ወይም በተጎጂዎች ላይ የደረሰው ጉዳት ከባድ በመሆኑ የተፈጸመውን ወንጀል ከባድ ሊያደርገው በመቻሉ ነው፡፡
ቀሪዎቹ ተከሳሾች በሙሉ በንዑስ አንቀጽ 2 መሰረት ክስ ሊቀርብባቸው የቻለው ከላይ ለአቶ ጌታቸው ወንጀል ከባድነት ከተጠቀሱት ምክንያቶች ውስጥ ቢያንስ አንዱ ተሟልቶ በመገኘቱ ነው፡፡
አቶ ጌታቸውን ጨምሮ በአራቱ ተከሳሾች ላይ በሌሉበት ክስ ሊመሰረት የቻለው ደግሞ በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 42/1/ለ እና 161/2/ሀ መሰረት ተከሳሾች የቀረቡባቸው ክሶች ከባድ በመሆናቸው በህጉ መሰረት በሌሉበት ክስ ሊቀርብባቸው የሚገባ በመሆኑ ነው ተብሏል።
Via #EPA

#update የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በ67ኛው የኢጋድ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ልዩ ስብሰባ ለመሳተፍ ዛሬ (ሚያዝያ 29 ቀን 2011 ዓም)ጧት ወደ ደቡብ ሱዳን ጁባ ተጉዘዋል። ዛሬ እና ነገ የሚካሄደው 67ኛው የኢጋድ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ልዩ ሰብሰባ በደቡብ ሱዳን ተደራዳሪ ወገኖች የተደረሰው ስምምነት አፈጻጸም የደረሰበትን ደረጃ በመገምገም የመፍትሄ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል።
Via ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከዲላ...
"ጤና ይስጥለኝ ፀግሽ ሁሉ ሰላም ነዋ ኤርምያስ እባላለው ከዲላ ነው ማወራህ ዲላ ላይ የመብራት ችግር ከቀን ወደ ቀን እየባሰበት መቷል የፋሲካን በዓል እንኳን ያለ መብራት ነው ያሳለፍነው ለተከታታይ 6 ቀናት መብራት አይኖርም ምክኒያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ይደጋገማል በተለያየ የስራ ዘርፍ የተሰማሩ የቀን ገቢ ያላቸው ሰዎች ስራቸውን መስራት አልቻሉም ዲላ ላይ የውሃ ችግርን አውርተን ሳንጨርስ መብራትንም ጨመሩብን ግራ ተጋብተናል ለስኳር መሰለፍ የለመደ እግር ጄነሬተር ያለበት ስልክ እኳን ቻርጅ ለማድረግ እየተሰለፈ ነው። መላ በሉን መብራት ሀይሎች!"

#update የዜግነት ፖለቲካና ማህበራዊ ፍትህን መሰረት አድርጎ በቅርብ የሚመሰረተው አዲስ ፓርቲ በባለፉት ስምንት ወራት ሲያደርገው የነበረውን ዝግጅት አጠናቀቀ፡፡ የሚመሰረተው አዲስ ፓርቲም ቀደም ሲል የነበሩ ሰባት ፓርቲዎችን በማዋሀድ የሚፈጠር እንደሆነ ተነግሯል፡፡ የአዲስ ፓርቲ ዝግጅቱም ከዚህ በፊት የነበረውን የፓርቲዎችን መዋቅር ለማክሰም እንዲሁም በተለያዮ ጉዳዮች መግባባት እንዲደረስበት ለማድረግ የተካሄደ መሆኑ ተመልክቷል፡፡ ፓርቲው በባለፉት ስምንት ወራት ሲያደርግ የነበረውን የውህደት ስራ አጠናቆ በመጪው ሐሙስና አርብ የፓርቲ መስራች ጠቅላላ ጉባዔ እንደሚያካሄድ አስታውቋል፡፡ በጉባዔውም 1 ሺህ 700 ከየወረዳው የተወጣጡ ተወካዮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እንደሚሳተፉ ይጠበቃል፡፡ ፓርቲው የዜግነት ፖለቲካ በአሁኑ ሰዓት አስፈላጊ እንደሆነ ገልጿል ሲል ኢቢሲ ዘግቧል፡፡
Via #EBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via #EBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለሥራ ወደ መካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ለመጓዝ የሚፈልጉ ዜጎች ሊያውቋቸው የሚገቡ መሠረታዊ ጉዳዮች፦
https://telegra.ph/ለሥራ-ወደ-መካከለኛው-ምስራቅ-ሀገራት-ለመጓዝ-የሚፈልጉ-ዜጎች-ሊያውቋቸው-የሚገቡ-መሠረታዊ-ጉዳዮች-05-07

Telegraph
ለሥራ ወደ መካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ለመጓዝ የሚፈልጉ ዜጎች ሊያውቋቸው የሚገቡ መሠረታዊ ጉዳዮች፦
መንግስት በሀገር ውስጥ የተለያዩ የስራ እድሎችን በማስፋፋት ስራ ፈላጊ ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡ መስራት ለሚችሉ ዜጎች ሁሉ በሀገር ውስጥ ላሉ የስራ እድሎች ቅድሚያ በመስጠት ሰርተው የሚለወጡበትን ሁኔታዎች በማመቻቸት ዜጎችን ተጠቃሚ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ሠርቶ ለመኖር በርካታ መልካም አጋጣሚዎች አሉ፡፡ ለዚህም ምሳሌ የሚሆኑ በሀገራቸው ሠርተው የተለወጡ በርካታ…
ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ህይወት (የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዘዳንት) በትዊተር ገፃቸው፦
"የTIKVAH-ETH አባላት ግቢያችን አፅድተዋል። #በማህበር_ሕውነት_ደቂስብ_ማእከል ለወላጅ አልባ ህፃናት የኢንፎርመሽን ሳይንስ ተመራቂ ተማሪዎቻን ባዘጋጁት የዳግማይ ትንሳኤ የምሳ ፕሮግራምም ተገኝተዋል። እናመሰግናለን። መልካም ጉዞ!!"
Pic Cr: #ግደይ_ልኡል
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"የTIKVAH-ETH አባላት ግቢያችን አፅድተዋል። #በማህበር_ሕውነት_ደቂስብ_ማእከል ለወላጅ አልባ ህፃናት የኢንፎርመሽን ሳይንስ ተመራቂ ተማሪዎቻን ባዘጋጁት የዳግማይ ትንሳኤ የምሳ ፕሮግራምም ተገኝተዋል። እናመሰግናለን። መልካም ጉዞ!!"
Pic Cr: #ግደይ_ልኡል
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በጫማው ውስጥ 130 የክላሽንኮቭ #ጥይቶች ሊያሳልፍ የሞከረ ግለሰብ በመቱ ከተማ በቁጥጥር ሥር መዋሉን ፖሊስ አስታወቀ። ከጋምቤላ ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ በነበረው የሕዝብ ማመላለሻ ተሸከርካሪ ውስጥ ግለሰቡ ጥይቶቹን በጫማ ውስጥ አድርጎ ለማሳለፍ ሲሞክር ነው በሶር ፍተሻ ኬላ የተያዘው። የከተማው ፖሊስ የወንጀል ምርመራና ፍትህ ማሰጠት ስራ ሂደት መሪ ኮማንደር አበበ እንዳሉት ግለሰቡ የተያዘው በኮድ 3 - 00769 ጋም በሆነ ተሽከርካሪ ላይ በተደረገው ፍተሻ መገኘቱንና ግለሰቡ በሕግ ቁጥጥር ሥር ውሎ ምርመራ እየተደረገበት እንደሆነም ገልጸዋል።
Via #Ahadu
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via #Ahadu
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሼህ ሞሐመድ አሚን ጀማል ዛሬ ሃላፊነታቸውን ለተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጅ ኡመር አስረክበዋል፡፡ ሰላማዊው ርክክብ የተከናወነው ባለፈው ሳምንት ቃል በተገባው መሠረት ነው፡፡ አዲሱ የኡለማና የባላደራ ቦርድ ኮሚቴዎች እና የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የተቋማዊ ለውጥ የጋራ ኮሚቴ አመራሮች በርክክብ ስነ ሥርዓቱ መገኘታቸውን ጠቅላይ ምክር ቤቱ በፌስቡክ ገጹ አስታውቋል፡፡
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከጦር መሳሪያዎች ጋር በቁጥጥር ስር የዋሉት መነኩሴ፦
በምስራቅ ጎጃም ዞን የምትገኘው የእነጋትራ ሐና ገዳም አስተዳዳሪ መነኩሴ ከስድስት ክላሽንኮቭና ከአንድ ሽጉጥ ጋር #በቁጥጥር ስር ዋሉ።
መነኩሴው ከስድስት ክላሽንኮቭና ከአንድ ሽጉጥ ጋር በቁጥጥር ስር የዋሉት ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር ግጭት መፍጠራቸውን ተከትሎ መሆኑን የወረዳው አስተዳደርና ጸጥታ ጽህፈት ቤት አስታውቋል።
የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ይሄነው አበባው ለኢዜአ እንደገለጹት በቁጥጥር ስር የዋሉት አባ ገብረ ስላሴ ሳሙኤል የተባሉ ተጠርጣሪ በምስራቅ ጎጃም ዞን አዋበል ወረዳ በምትገኘው ጥንታዊቷ የእነጋትራ ሐና ገዳምን ከ28 ዓመታት በላይ አስተዳድረዋል።
ተጠርጣሪው መነኩሴ ከሃይማኖታዊ አገልግሎትና የገዳም መሬት ጋር በተያያዘ ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር ለረጂም ጊዜ የቆየ አለመግባባት ነበራቸው። ህብረተሰቡም በአስተዳዳሪው ላይ ተደጋጋሚ ቅሬታ ለሚመለከተው አካል ሲያቀርብ መቆየቱን አቶ ይሄነው አስታውሰዋል።
በትናትናው ዕለት ሚያዝያ 28 ቀን 2011 ዓ.ም ግን አባ ገብረ ስላሴ ጭቅጭቅ በሚነሳበት መሬት ላይ እርሻ ማረስ ሲጀምሩ፣ የአካባቢው ማህበረሰብ በነቂስ ወጥቶ ግጭት መቀስቀሱን ነው የተናገሩት።
በግጭቱም አስር ክፍሎች ያሉት ቤት መቃጠሉን፣ በገዳሙ አስተዳዳሪ ግብረ አበሮቻቸው በተተኮሰ ጥይት በአንድ ሰው ላይ የመቁሰል አደጋ መድረሱን ተናግረዋል።
ምንጭ፦ ኢዜአ

#update በኢትዮጵያና ኬንያ ድንበር ትናንት 11 ሰዎች መገደላቸውን ተከትሎ ውጥረት መንገሱን የኬንያው ዘ ኢስት አፍሪካን ጋዜጣ አስነብቧል፡፡ በውሃ ሳቢያ በተቀሰቀሰ ውዝግብ ከኬንያዋ መርሳቢት ከተማ 250 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ባለች መንደር ጥቃቱ የተፈጸመው ነው፡፡ በጥቃቱ ሌሎች 2 ሰዎች ቆስለው 4ቱ ደሞ እስካሁን የደረሱበት አለመታወቁን ከኢትዮጵያ ወገን በተጠራ የሰላም ውይይት ላይ ሳሉ በተገኙ ኬንዊያን ላይ ግድያውን የፈጸሙት ከኢትዮጵያ በኩል የገቡ ታጣቂዎች መሆናቸውንም ዘገባው ጠቅሷል፡፡
Via #WazemRadio
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via #WazemRadio
@tsegabwolde @tikvahethiopia