TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ከጎንደር👆

"ዛሬ በጎንደር ከተማ #የረመዳን መግቢያን በማስመልከት በረመዳን ወር ተወዳጁ ስራ #ሰደቃ እንደመሆኑ የበረካ 'የበጎ አድራጎት እና የልማት ማህበር' ትልቁን ሰደቃ #የደም_መለገስ ፕሮግራም ያካሄደ ሲሆን በ45 ወንዶች እና በ1ሴት በጥቅሉ የ46 ሰዎች የደም ልገሳ አካሂደዋል #አላህ ኸይር ጀዛችሁን ይክፈላቹህ!" Nurhusien Shimelash

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ትኩረት በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል #መተከል አካባቢ ለሚገኙ የሀገራችን ዜጎች‼️ #ኢትዮጵያ #ETHIOPIA #ቤንሻንጉል

#መከላከያ_ሰራዊት
#ፌደራል_ፖሊስ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Audio
#በጎ_ኢትዮጵያዊያን!

በአማራ ክልል “በጎ ኢትዮጵያዊያን” በሚል ስያሜ የተደራጁ #ወጣቶች ትላንት #ባሕር_ዳር ላይ ወርኃዊ ስብሰባቸውን ሲያካሂዱ #ይቅር መባባል እስከዛሬ ለተጠራቀሙ ችግሮች መፍትኄ ያስገኛሉ ብለው እንደሚያምኑ ተናግረዋል።

Via VOA 24
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቡሌ ሆራ👆

#አለን_ኢትዮጵያ_የሰው_ልጆች_የለውጥ_ማዕከል ቡሌ ሆራ ቅርንጫፍ የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ በማዕከሉ ለሚያሰለጥናቸው ሰልጣኞች የምሣ ግብዣ በማድረግ በአሉን በጋር አክብሯል።

Via www.alenethiopia.org

@tsegabwolde @tikvahethiopia
Audio
ሊደመጥ የሚገባው⬆️

"አብረን ከፍ እንበል"

ከዝቅታው እንነጠል
ከሀኬቱ ከቶማታው እንገለል
ከክፋቱ ካሉባልታው እንከለል
አብረን ሆነን አብረን ከፍ እንበል
ከመቀናናት
ከመቆራቆስ
ከመተናናቅ
እንጠንቀቅ!
ከመጠላላት
ከመኮናነን
ከመጠቋቆም
እንቁም!
ከመዛዛት
ከመካሰስ
ከመጠበቅ
እንራቅ!
ከስሜታዊነት
ከጭፍንነት
ጥራዝ ከመንጠቅ
እንወቅ!
ከመበታተን
ከመለያየት
ከመገንጠል
እንነጠል!
አንድ ሆነን
አንድ እንሁን
ሁላችን የኢትዮጵያ ልጆች
የታላቅ አካል ብልቶች
ልዩ የሆንን ህብሮች
አንዳችን ለአንዱ ህይወቶች
የማንዘረዝ እውነቶች
የማንደበዝዝ ውበቶች
.
.
.
#አበባው_መላኩ

#ሼር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከመቀለ👆

"ትናንት በመቀለ #አረህማን_መስጊድ የአካባቢው ነዋሪዎች ከመቀለ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ጋር በመተባበር ታላቁን የረመዷን ወር በማስመልከት #የደም_ልገሳ ኘሮግራም አድርገዋል፡፡ ከሀያ በላይ ሴቶችና ከአርባ በላይ ወንዶች የተሳተፉበት ሲሆን በአጠቃላይ 75 ሠወች ደም ለግሰዋል፡፡ ነዋሪዎችና የመቀለ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ተመሳሳይ ወገንን ደም በመለገስ የመርዳት ተግባር ከዚህም በፊት በተደጋጋሚ ያደርጉት ነበር፡፡ስራቸውም ይበል የሚያሰኝና ለወደፊቱም ሊቀጥሉበት የሚገባ ሠናይ ምግባር ነው፡፡ ተምኪን ነኝ ከአይደር ግቢ"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ~~እናመሰግናለን!!

በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ ለጠየቅነው የትራንስፖርት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት #እየተረባረባችሁ ለምትገኙ የተቋሙ አመራሮች እና የተማሪ ተወካዮች በመላው የTIKVAH-ETH ቤተሰብ ስም ምስጋናችንን ለማቅረብ እንወዳለን። ሀሳባችን ከግብ እንዲደረስ ለማድረግ ሁሌም ከጎናችን እንደምትሆኑ እናምናለን። #የStopHateSpeech የግንዛቤ ማስጨበጫ ቀጣይ መድረክ ወሎ ዩኒቨርሲቲ፣ ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ እና መቐለ ዩኒቨርሲቲ ነው በዚህም ዝግጅት ላይ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ከ20 በላይ ተማሪዎቹን ለዚህ ሀገር አድን ዘመቻ ይልካል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሼህ ሙሐመድአሚን ጀማል ከኃላፊነታው ለመነሳት መልቀቂያ አቀረቡ። ፕሬዝዳንቱ መልቀቂያውን ያቀረቡት ምክር ቤቱ በዛሬው ዕለት እያካሄደ ባለው ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ነው፡፡ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ህዝብ ግንኙነት ክፍል እንዳስታወቀው ፕሬዝዳንቱ በጤና እክል ምክንያት ከኃላፊነት ለመልቀቅ መወሰናቸውን አመልክተዋል፡፡ የምክር ቤቱ ፕሬዝዳንት ሐጂ ሙሐመድአሚን መልቀቂያ ያቅርቡ እንጂ የምክር ቤቱ ጉባኤተኛ እስካሁን በመልቀቂያው ላይ ውሳኔ እንዳላሳለፈም ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

Via EBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አየር መንገዱ ተሸለመ...

የኢትዮጵያ አየር መንገድ እኤአ የ2019 የአፍሪካ #ምርጥ_የጭነት አየር መንገድ አገልግሎት ሽልማትን ተቀዳጀ። ሽልማቱን ያዘጋጀው የኤር ካርጎ ኒውስ ተቋም በዓለም አቀፍ ደረጃ የካርጎ ዜናዎችን በመዘገብ፣ የኢንዱስትሪውን መሪዎች ቃለ መጠይቅ በማድረግና ኢንዱስትሪውን የተመለከቱ ትንታኔዎችን በመስራትና ለአለም አቀፍ የአየር ጭነት አገልግሎት ሰጪዎች ሪፖርቶችን በማዘጋጀት የታወቀ ነው። በአፍሪካ ግዙፍ የሆነው የአየር ጭነት አገልግሎት አቅራቢው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሽልማቱን ሚያዚያ 18 በእንግሊዝ ለንዴን ተቀብሏል።

“ቤስት ካርጎ ኤር ላይን 2019 “ተሸላሚ የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከዚህ በፊት ተደጋጋሚ ሽልማቶችን መቀዳጀቱንም ዘገባው አስታውሷል።
በኤር ካርጎ ኒውስ የሚዘጋጀው “የአመቱ ምርጥ የጭነት አየር መንገድ “ የሚሰኘው ሽልማት በዘርፉ የተከበረና ከፍተኛ እውቅና ያለው ሽልማት ነው። ሽልማቱን አስመልክቶ መልዕክታቸውን ያስተላለፉት የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈጻሚ ተወልደ ገብረ ማርያም”ይህነን የተከበረ ሽልማት በመቀዳጀታችን ከፍ ያለ ኩራት ተሰምቶናል ብለዋል።

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቤንሻንጉል ጉምዝ
/ከጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት/

የአማራ ክልል ቃል አቀባይ አቶ #አሰማኸኝ _አስረስ በቤንሻንጉል ጉሙዝ በነበረው ግጭት ዙርያ ለአለም አቀፉ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት የተናገሩት፦

"በቤንሻንጉል ሰሞኑን በነበረው ሁከት በአማራ ተወላጆች (በአካባቢው 'ቀይ' ይባላሉ) ላይ የግድያ፣ የዘረፋ እንዲሁም የማሳደድ ተግባር ተፈፅሟል። እስካሁን ባለኝ መረጃም ወደ 17 ሰዎች ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ 11ዶቹ የአማራ ክልል ተወላጆች ሲሆኑ ቀሪዎቹ የአካባቢው ሰዎች ናቸው። እስካሁን መረጃ ባልተሰበሰበባቸው አካቢዎች ሌሎች ሰዎች ተገድለውም ሊሆን ስለሚችል ማጣራት እያረግን ነው። ግጭቱ የጀመረው ሚያዝያ 17 በዳንድር ወረዳ ሲሆን መነሻው በእቃ ጫኝ እና አውራጆች መሀል ነበር። በዚህ መሀል የአንድ የአካባቢው ሰው ህይወት ያልፋል። ከዚያ በሁዋላ ባሉት ሶስት ቀናት ያንን ለመበቀል ጥቃቶች በቀስት፣ ወንጭፍ እና በጥይት ተፈፀመዋል። #በሁለቱም ወገን የበቀል እንቅስቃሴዌች ሲደረጉ ነበር። ትናንት ብቻ በፓዌ ወረዳ አባወሬኛ ቀበሌ 25 ቤቶች ተቃጥለዋል፣ እነዚህ የጉሙዞች ቤቶች ናቸው። ዛሬ አንድ ግብረ- ሀይል ሁኔታውን ለማርገብ ወደቦታው እያመራ ነው።" @eliasmeseret

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሁኔታው አሁንም አሳሳቢ ነው...

በቤኔሻንጉል ጉሙዝ ብሔራዊ ክልል ያለው #የፀጥታ ሁኔታ አሁንም #አሳሳቢ መሆኑን አብመድ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች እየገለጹ ነው፡፡ ከፓዊ ወረዳ ሕዳሴ ቀበሌ አባወረኛ አካባቢ ነዋሪዎች ለአብመድ እንደተናሩት ከትናንት ከሰዓት በኋላ ጀምሮ የተኩስ ልውውጥ #ቆሟል፤ ቀስት #የሚያስወነጭፍም የለም፡፡ ጥቃት አድራሾቹ በከፊል ወደ #ጫካ ውስጥ #ሸሽተዋል፤ በከፊልም በቁጥጥር ሥር ውለዋል፡፡ ‹‹በዚህም ግልጽ የሚታይ ግጭት የለም፤ የሰላም ድባብ ግን #አይታይም›› ብለዋል፡፡

ሌላኛው ነዋሪ ደግሞ ከትናንት ምሽት 12፡00 አካባቢ ጀምሮ እስካሁን ግጨት አለመኖሩን ገልጸው ያንዣበበ #ስጋት መኖሩን አመልክተዋል፡፡ ትናንት ቤቶች መቃጠላቸውንና የተናገሩት እኚሁ አስተያየት ሰጪ ዛሬ ከሰዓት በኋላ #የአፀፋ እርምጃ ለመውሰድ ቅድመ ዝግጅት እንዳለ በመጠቆም መንግሥት #ጥፋት እንዳይደርስ እንዲቆጣጠር #አሳስበዋል፡፡ ‹‹ወንዶች ሚስቶቻቸውንና ልጆቻቸውን እያሸሹ ቅድመ ዝግጅት እያደረጉ ነው፡፡ ትናንት ሙሉ በሙሉ ቤተሰባቸውን ከአካባቢው ያሸሹ ሰዎችም አሉ፤ የትናንቱ ጥቃት አድራሽ ቡድንም ዛሬም ለሌላ ጥፋት እየተንቀሳቀሰ በከፊል በቁጥጥር ሥር ሲውል ተመልክቻለሁ፡፡ ቀስትና የጦር መሣሪያ የያዙ ቡድኖች ወደ መንደር 49 እየተንቀሳቀሱ አባት በለስ ወንዝ ድልድይ ላይ መከላከያና የፌዴራል ፖሊስ ይዘዋቸዋል›› ብለዋል አስተያየት ሰጪው።

በበለስ ከተማ መንደር ሁለት ነዋሪ የሆኑ አስተያየት ሰጪም የጦር መሣሪያና ቀስት የያዙ ከ30 በላይ ሰዎች በለስ ወንዝ አካባቢ መከላከያ ሠራዊትና የፌዴራል ፖሊስ አባላት ዛሬ ረፋድ 3፡30 አካባቢ #ተይዘው መመለሳቸውን ተናግረዋል፡፡ ‹‹አባወረኛ ላይ ብዙ ነገር ወድሟል፤ የክልሉ መንግሥት ምን እንደሚያደርግ #አናውቅም፤ እንዲያውም የመንግሥት ባለስልጣናት ሴራ እንዳለበት እናምናለን፡፡ የምናደርገው ግራ ገብቶናል›› ብለዋል ነዋሪው፡፡

መንግሥት ግጭቶችን ከማብረድ በውጥን ላይ ማስቀረትን ትኩረት እንዲሰጥ ያሳሰቡት ነዋሪዎቹ የመከላከያና የፌዴራል ፖሊስ ኃይል በብዛት ወደ አካባቢው እንዲገቡና ለረዥም ጊዜ ቁጥጥር እንዲያደርጉ በተለይም ዛሬ ከሰዓት በኋላ እንደሚኖር የሚሰጋውን ጥቃት እንዲያከሽፉም ጠይቀዋል፡፡ ‹‹አሁን ግጭቱ ያለው ቀይና ጥቁር በሚል ነው፤ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ የፌዴራል መንግሥት ዘላቂ መፍትሔ ካልፈለገ ሁኔታው አሳሳቢ ነው›› ብለዋል አስተያዬት ሰጭዎቹ፡፡

Via AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ተጨማሪ የፀጥታ ሀይል ይግባ...

በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል የፀጥታ ችግር በተፈጠረባቸው አካባቢዎች የሚኖሩ ነዋሪዎች ተጨማሪ የመከላከያ ሰራዊት እና የፌደራል ፖሊስ እንዲገባ ጠይቀዋል። ነዋሪዎቹ ዛሬ ሊፈፀም የታሰበ ጥቃት ይኖራል በሚል ስጋት ውስጥ መውደቃቸውን ገልፀው መንግስት የህዝቡን ደህንነት እንዲያስጠብቅ እና ተጨማሪ የፀጥታ ሀይል በስፍራው እንዲያሰማራ ጠይቀዋል። የመከላከያ ሰራዊቱ እና የፌደራል ፖሊስ ግጭት ያለባቸው አካባቢዎች አስተማማኝ ሰላም እስኪሰፍን አካባቢውን ለቀው መውጣት እንደሌለባቸው አስገንዝበዋል።
.
.
በሁለት ግለሰቦች መካከል የተፈጠረ ግጭት ነው አድጎ ለበርካቶች ህይወት መጥፋት አካል መጉደል፣ ንብረት መውደም እና ለሰላም መደፍረስ ምክንያት የሆነው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia