TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ከቢሾፍቱ🔝

"ሰላም ፀግሽ....የቢሾፍቱ ከተማ ወጣቶች ማህበር ዛሬ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት በሆነው boing 737 max8 አውሮፕላን አደጋ ህይወታቸውን ያጡ ወገኖች 40ኛ ቀን መታሰቢያ በሚያስደንቅ መልኩ በተለያዩ ስነስርዓቶች አክብረው ውለዋል። ወጣቶቹ ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር በመተባበር የሚያስመሰግን ስራ ሰርተዋልና #ሊመሰገኑ ይገባል።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከአርባ ምንጭ...🔝

"ፀግሽ በአሁኑ ሰዓት በጎፋ ዛን ከመኖርያ ስፍራዎች ለተፈናቀሉ ወገኖቻችን ድጋፍ ለማድረግ የአርባምንጭ ከተማ ወጣቶች እና አባቶች በጋራ በመሆን ወደጰስፍራው እያቀናን እንገኛለን። በዚህ አጋጣሚ የአርባምንጭ ከተማን ነዋሪ አመስግንልን!!" #ፋሪስ ነኝ!

#ኢትዮጵያዊነትን ከመናገር በዘለለ #በተግባር ያገረጋገቹ የአርባምንጭ ከተማ እና አካባቢዋ ማህበረሰብ ላደረጋቹት መልካም ተግባር በፈጣሪ ስም እናመሰግናለን!!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሰላም አምባሳደር -- ሀዋሳ ዩንቨርስቲ!
(TIKVAH-ETH)

ከ3 ዩኒቨርሲቲዎች የተውጣጡ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ቅዳሜ #ሀዋሳ_ዩኒቨርሲቲ ይገባሉ። ወጣቶቹ ሀገር የማዳን እና መላውን የሀገሪቱ ህዝብ በተስፋ የመሙላት እቅድ ይዘው እየተንቀሳቀሱ የሚገኙት #StopHateSpeech በማለት ሲሆን ይህ እንቅስቃሴ በተለይ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ራሳቸውን እንዲፈትሹ እና እንዲገመግሙ፤ ራሳቸውን በፍቅር እንዲሞሉ፤ ሰውን ሁሉ ልክ እንደ ራሳቸው እንዲወዱ እና እንዲያከብሩ የማስገንዘብ ስራ ይሰራል።

#ሀዋሳ_ዝግጁ
ፍቅር፤ ሰላም፤ አንድነት

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የፕሬዚዳንት ምርጫ ተካሂዷል። በምርጫ ስነ-ስርዓቱም የማዕድንና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ሳሙኤል ኡርቃቶ፣ የዩኒቨርሲቲው የቦርድ አባላት፣ም/ፕሬዚዳንቶች፣ ዲኖች፣ ዳይሬክተሮች እና ሌሎች የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ አባላት ተገኝተዋል፡፡ በዚህ የፕሬዚዳንት ምርጫ ስነ-ስርአት ዘጠኝ ተወዳዳሪዎች ለመወዳደሪያ የሚያበቃቸውን ስትራቴጅካዊ እቅድ በጽሁፍ አቅርበው በተሳታፊዎች አስተያየት ተሰጥቷል፤ ጥያቄዎችም ቀርበው በተወዳዳሪዎች ምላሽ ተሰጥቷል፡፡ ከዚህም በመቀጠል በዩኒቨርሲቲው ሰኔት እና በተለያዩ የውድድር መስፈርቶች ለተወዳዳሪዎች ውጤት የተሰጠ ሲሆን፣ ውጤቱ ከላይ ባለው መልኩ ቀርቧል፡፡

Via #ጎንደር_ዩኒቨርሲቲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"የህክምና ባለሙያዎች ጥያቄዎቻቸውን በሰላማዊና ህጋዊ መንገድ የማቅረብ መብት አላቸው። በአርሲ ዩኒቨርስቲ ኢንተርን ሀኪሞች ላይ በደረሰው ጉዳትና ባነሷቸው ጥያቄዎች ዙሪያ ከሚመለከታቸው አካላት የተውጣጣ ቡድን በስፍራው በመገኘት ውይይት አካሂዷል።" ዶ/ር አሚር አማን

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የስራ ማቆም አድማ መቱ...

#የኮይሻ_ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ ሠራተኞች የስራ ማቆም አዱማ ከአምስት ሺህ በላይ የኮይሻ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ ሠራተኞች የስራ ማቆም አዱማ ከመቱ ሁለተኛ ሳምንት መያዙን ተናገሩ፡፡
 
ሰራተኞቹ ሥራ አቆምን ያሉት በሚደረስባቸው የአስተዳደር በደል ፣ ከደመወዝና ጥቅማጥቅም ጋር በተያያዙ ችግሮች ሲሆን በደል አድርሰውብናል ያሏቸው ስድስት የፕሮጀክቱ ኃላፊዎች እንዲባረሩ ይጠይቃሉ፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ጥያቄቸው ተገቢ ባይሆንም ከምግባቸው ላይ የሚቀነሰውን ገቢ ግብር ሳሊኒ ኩባኒያ እንዲሸፍን፤ በደመወዛቸው ላይ ደግሞ 450 ብር እንዲጨመር ተማምነናል ብሏል፡፡

የፕሮጀክቱ ሥራ መቀጠል ስላለበት ይህንን የማይቀበሉ ሠራተኞች እንደሚሰናበቱ ተወስኗልም ተብሏል፡፡

በህግና በማስረጃ እንጂ የደቦ ፍትህ በመፈለግ ስድስት የፕሮጀክቱ ኃላፊዎች ይባረሩ ማለታቸው ስህተት ነው ብሏል፡፡

Via #VOA24
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ከግማሽ በላዩ ምዘናውን አላለፉም...

በአገር አቀፍ ደረጃ ለሙያ ብቃት ምዘና ከተቀመጡ የ2ኛ ደረጃ #መምህራን ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ምዘናውን አላለፉም ተባለ፡፡

Via #ShegerFM
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል በአቶ ለማ መገርሳ የሽኝት ፕሮግራም ላይ ያደረጉት ንግግር...

@tsegabwolde @tikvahethiopia