TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ደሴ🔝

በኦሮሞ ልዩ ዞን በተከሰተው #ግጭት የተገደለን የአማራ ልዩ ሀይል አባል የቀብር ስነስርዐት ተከትሎ በደሴ ከተማ መለስተኛ የተቃውሞ ሰልፍ የተደረገ ሲሆን፣ #መንገዶችም ተዘግተው ውለዋል።

Via ELU
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የጀርመኑ #ሲመንስ ኩባንያ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ #የቴክኒክ_ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልጿል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአፋር ውሎ...🔝

በአፋር ክልል አንድ ታዳጊ በመከላከያ ሰራዊት አባላት #መገደሉን ተከትሎ #ፍትህ የጠየቁ ወጣቶች በገዋኔ፣ በረሃሌና አዋሽ አካባቢዎች መንገዶችን ዘግተው ውለዋል። በዚህም አዲስ አበባን ከጅቡቲና የትግራይ ክልልን ከአዲስ አበባ የሚያገናኘው መንገድ ለሰዐታት ተዘግቶ ነበር።

Via #ELU
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ የተከሰተውን እሳት ሙሉ በሙሉ ማጥፋት መቻሉ ተገለጸ፡፡ እሳቱን ለመቆጣጠር 5 ሺህ ሰዎች ተሳትፈዋል፤ 500 ሺህ ብር የሚጠጋ ገንዘብም ወጭ መሆኑንም ነው የተነገረው፡፡ ሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ለ21 ዓመታት በአደጋ መዝገብ ዝርዝር ውስጥ ከቆዬ በኋላ ነበር ከአደጋ መዝገብ የወጣው፡፡ ፓርኩ በዩኔስኮ ከተመዘገቡ የኢትዮጵያ ቅርሶች ውስጥ ከቀዳሚዎች መካከል ነው፡፡

Via አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Alert‼️

"ፀግሽ ባሁኑ ሰአት የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ምክንያቱ #ባልተረጋገጠ ጉዳይ ፀጥታው አስጊ ሁኔታላይ ይገኛል። የሚመለከተውም አካል ጉዳዩን አጥንቶ መፍትሔ እንዲያበጅልን።"

ውድ ተማሪዎች እባካችሁ #ከግጭት እና #አለመግባባት ርቃችሁ ለሀገራችሁ ሰላም እና እድገት እንድትሰሩ በTIKVAH-ETH ስም እንጠይቃለን!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጥረት ኮርፖሬት...

ጥረት ኮርፖሬት በአማራ ክልል ለሚገኙ የዳስ መማሪያ ክፍሎችን ወደ መደበኛ ክፍሎች ለመቀየር የሚውል 17.2 ሚልዮን ብር ድጋፍ አደረገ፡፡

የጥረት ኮርፖሬት ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር በአምላክ አስረስ እና የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ሃላፊ ዶ/ር ይልቃል ከፍያለ የድጋፍ ስምምነቱን ተፈራርመዋል።

ድጋፉ በክልሉ 7 ዞኖች የሚገኙ 514 የዳስ ክፍሎችን በማደራጀት ሙሉ ለሙሉ ወደ መደበኛ ክፍሎች ለመቀየር እንደሚውል ገልጸዋል።

የጥረት ኮርፖሬት ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር በአምላኩ አስረስ በበኩላቸው በክልሉ በመማሪያ ክፍሎች ዙሪያ የሚታየውን ችግር ለመቅረፍ ኮርፖሬቱ የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ እንደሆነም ገልጸዋል። አክለውም ኮርፖሬቱ በዋግ ህምራ ዞንም ሁለት የመጀመሪያ ደረጃ እና ሁለት የሁለተኛ ደረጃ ትምህት ቤቶችን እያስገነባ መሆኑንም ገልጸዋል።

Via #etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የTIKVAH ETHIOPIA #የሰላም እና #የፍቅር አምባሳደሮች በነገው ዕለት #አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ይገባሉ፦

(StopHateSpeech)

1. አቅለሲያ ሲሳይ
2. የምስራች ጋሻው
3. በረከት ጉዲሳ
4. ቢንያም ይርጋ
5. ዱሬሳ በዳሶ
6. እዩኤል በቀለ
7. እዮብ ተስፋዬ
8. ቤቴል አባይነህ
9. ፍላጎት ጥላሁን
10. ሀያት እንድሪስ
11. አዚዛ እንድሪስ
12. ቤተልሄም ሴታ
13. አዲስወርቅ ተክሊ
14. ጉተማ ብርሃኑ
15. ፉአድ ኑሪ
16. አበበ ከበደ
17. ሲሳይ ታደሰ
18. ይድነቃቸው አዳነ
19. ዳንኤል ጥበቡ
20. ንብረት አበበ
21. ዮርዳኖስ ግርማ
22. ቤተልሄም እንዳልክ
23. ፍሬህይወት ማቴዎስ
24. ቃልኪዳን አክሊሉ
25. ሳሮን ገ/መድን
26. ገመቺስ ፍቃዱ
27. ሙልጌታ አደሩ
28. ምሩፅ ደማሶ
29. ቤተልሄም ቱሉ

ትሩ ላይፍ የኪነጥበብ ክበብ፦

•4 የውዝዋዜ አቅራቢዎች
•2 ገጣሚያን

ከወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ፦

•የተማሪዎች ህብረት ፕሬዘዳት(ወጣት ዘገየ)

#አርባምንጭ ተዘጋጁ...

እኛ ኢትዮጵያ ልጆች ነን!
እኛ የአንድነት ልጆች ነን!
ከጥላቻ ንግግሮች እንቆጠብ!

#StopHateSpeech

በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች እንመጣለን!
#TIKVAH_ETHIOPIA - እኛ ከጥላቻ የነፃን፤ ሰውነትን ያስቀደምን #የፍቅር እና #የሰላም አምባሳደሮች ነን!!

አርባምንጭ...🔄
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አርባምንጭ...

ለሀገራችን ለእናታችን ኢትዮጵያ ሰላም፣ እኩልነት፣ እድገት፣ ብልፅግና የሚከፈለውን ዋጋ ለመክፈል ተዘጋጅተናል። #TIKVAH_ETH

ይህን አስከፊ #የድህነት_ታሪካችንን የምንፍቀው እርስ በእርሳችን ተዋደን ተከባበርን እንጂ እርስ በእርሳችን እየተጠላላን፤ አንዱ ሌላውን እየሰደበና እያቋሸሸ አይደለም!!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
IDP_Steering Comittee_WeeklyUpdate (1).pdf
840.7 KB
የሰላም ሚኒስቴር🔝

ተፈናቃይ ዜጎችን መልሶ #በማቋቋም የሥራ ክንውን ላይ ብሔራዊ አስተባባሪ ኮሚቴው ሳምንታዊ ውይይት አካሂዷል።

Via የሰላም ሚኒስቴር(ለTIKVAH-ETH)
@tsegabwolde @tikvahethiopia