TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ቃጠሎው ቀጥሏል🔝

ትናንት ምሽት የጀመረው የስሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ቃጠሎ አሁንም ከቁጥጥር ውጭ ሐሆኑ ታውቋል። በፓርኩ በእሳት ማጥፋት ሲሳተፉ የዋሉ ወጣቶች እንደተናገሩት በእሜትጎጎ
አካባቢ ያለው እሳት ወደ ገደላማ አካባቢዎች በመግባቱ ከቁጥጥር ውጭ ሆኗል።

ወጣቶቹ ለአብመድ በሰጡት አስተያዬት "ከትናንት ሌሊት ጀምሮ በአራት አይሱዙ ሄደን ለማጥፋት ጥረት አዶርገናል፤ ግን ወደ ረፋድ ተቆጣጥረነው የነበረ ቢሆንም ቀትር ላይ እንደገና ተነስቷል፤ ከድካም ጋር ተዳምሮም አይሎን ወደ ገደሉ ወርዷል"ብለዋል።

በአውሮፕላን የታገዘ የመቆጣጠር ሥራ ካልተሠራ እሳቱ የፓርኩን ኅልውና አደጋ ውስጥ እንደሚጥለውም ወጣቶቹ ተናግረዋል።የሰሜን ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ወርቁ ለምለሙ ደግሞ እሳቱ በፓርኩ ላይ የከፋ አደጋ እያደረሰ በመሆኑ የመንግሥትን ከፍተኛ ድጋፍ እንደሚሻ አስታውቀዋል።

እሳቱን ሳንቃ በር አካባቢ በሰው ኃይል ለመቆጣጠር እንደሚቻል የገለፁት ዋና አስተዳዳሪው እሜትጎጎ አካባቢ ግን ከአቅም በላይ መሆኑን አስረድተዋል። የፌዴራል የዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ኩመራ ዋቅጅራ ግን አሁንም በሰው ኃይል ለመቆጣጠር መጣር የተሻለ አማራጭ መሆኑን ነው ያስረዱት።

"በአውሮፕላን ለመቆጣጠር መሞከር የተሻለ አማራጭ ነው፤ ግን እንደ ሀገር የእሳት መቆጣጠሪያ አውሮፕላን የለንም። ያላቸው ደቡብ አፍሪካ እና ኬንያ ናቸው። የሚጠይቀውን ከፍተኛ ወጭ እንኳ ችለን ብንከራዬው ሂደቱ ቀናትን ይወስዳል። ስለዚህ በሰው ኃይል ለመቆጣጠር መሞከሩ ይሻላል" ነው ያሉት።

Via AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አውሮፕላን ውስጥ መንትያ ልጆች የተገላገለችው ኢትዮጵያዊት አዲስ አበባ ገብታለች‼️
.
.
ከጅዳ ወደ አዲስ አበባ ይጓዝ በነበረ የሳውዲ ዓረቢያ አውሮፕላን ተሳፍራ እዛው አውሮፕላኑ ውስጥ መንታ ሴት ህፃናት በመውለዷ አስመራ ዓለምቀፍ አውሮፕላን ጣቢያ እንድታርፍ የተደረገችው ኢትዮጵያዊት እናት ዛሬ አዲስ አበባ ገባች።

በሥራ ምክንያት ሳዑዲ አረቢያ መዲና ከተማ የምትኖረው የ35 ዓመቷ ወይዘሮ ጀነት ሁሴን የስምንት ወር ነፍሰ ጡር በመሆኗ አገር ቤት ለመዉለድ ነበር ባለፈው መጋቢት 13 ቀን 2011 ዓም በሳዑዲ አየር መንገድ የተሳፈረቸው።

ሆኖም እርሷ ያሰበችው ሳይሆን ቀረና ከጊዜዋ ቀድማ መንትያ ሴት ልጆቿን መንገድ ላይ ተገላግላለች።

ነገሩ የሆነው እንዲህ ነው፦

አውሮፕላኑ በኤርትራ አየር ክልል ውስጥ እንደገባ ነበር ወይዘሮ ጀነት በድንገት ምጥ የያዛት።

እናም ፖይለቱ ከኤርትራ አየር ተቆጣጣሪዎች ጋር በመነጋገር አውሮፕላኑ አስመራ አየር ማረፊያ እንዲያርፍ ተደረገ።

አንዷ ህፃን ወደዚህ ምድር የተቀላቀለችው አውሮፕላኑ አየር ላይ እያለ ሲሆን ሁለተኛዋ ግን አውሮፕላኑ እንዳረፈ ነበር የተወለደቸው።

መንታ ልጆቿን ይዛ ዛሬ አዲስ አበባ የገባችው ወይዘሮ ጀነት ለጋዜጠኞች በሰጠችው ቃል አውሮፕላን ውስጥ ከተሳፈረች በኋላ ባልጠበቀችው ሁኔታ ምጥ እንደጀመራት ነው የገለጸችው።

ምንጭ፦ etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ኢትዮጵያዊያን መርማሪዎች ቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን ከመከስከሱ በፊት MCAS የተሰኘው የበረራ ተቆጣጣሪ ሶፍትዌር ጥቅም ላይ ውሎ እንደነበር ጊዜያዊ ድምዳሜ ላይ እንደደረሱ ዎል ስትሪት ጆርናል ዘግቧል፡፡ መረጃው ትክክል ከሆነ አውሮፕላኑ አፍንጫን ዘቅዝቆ እንዲከሰከስ ያደረገው ይሄው ሶፍትዌር ይሆናል፡፡ በሌላ ዜና አውሮፕላኑ የተከሰከሰው በብልሹ ሶፍትዌር ሳቢያ ነው በማለት ቦይንግ ኩባንያ በአሜሪካ ክስ ተመስርቶበታል፡፡ ከሳሾቹ በአደጋው የሞተው የሩዋንዳዊው ጃክሰን ሙሶኒ ቤተሰቦች መሆናቸውን ጋርዲያን አስነብቧል፡፡ የአደጋው ተጎጅ ቤተሰቦች በአሜሪካ ፍርድ ቤቶች በኩባንያው ላይ ክስ መመስረት እንደሚችሉ ባለሙያዎች ይገልጻሉ፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
Ethiopia_ጀዋር_እና_እስክንድር_በDW_የአዲስ.mp3
14.9 MB
ጀዋር መሀመድ እና እክንድር ነጋ በDW የአዲስ አበባ የባለቤትነት ዉዝግብ፦

«እኛ የምንለዉ ሕጉ የሚለዉን ነዉ። የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ሕግ አዲስ አበባ የኦሮሚያ ዋና ከተማ ነች ይላል። የፌደራሉ ሕገ መንግሥትም ኦሮሚያ (ከአዲስ አበባ) ልዩ ጥቅም እንዳለዉ ያስቀምጣል------»የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ ሥራ አስኪያጅና የመብት አቀንቃኝ #ጀዋር_መሐመድ

«የአዲስ አበባ ጉዳይ የዜግነት ጥያቄ ነዉ-----ሕገ መንግስቱ ከየት መጣ? ማን አወጣዉ? ምንስ አላማ ነበረዉ?------» ጋዜጠኛና የመብት አቀንቃኝ #እስክንድር_ነጋ

«እንዴ!! ምነዉ እባክሕ? እስክንድር ነጋ እኮ የመብት ታጋይ ነዉ----ልንቃወመዉ፣ ልንተቸዉ እንችላለን፣ ከዚያ ባለፈ ግን ዛሬ እስክንድርን ያስፈራሩ ነገ ጀዋርን #ያስፈራራሉ-----እስክንድር ብቻዉን ሳይሆን ሁላችንም አብረነዉ ተሰልፈን እንታገላለን----»ጀዋር መሐመድ

ጀዋር ያለዉን «የምጠራጠርበት ምንም ምንም ምክንያት የለኝም። #አመሰግነዋለሁ።-------»እስክንድር ነጋ።

«በግሌ ከጠይቀከኝ ከእስክንዳር ጋር አይደለም ከማንም ጋር በማንኛዉም ሰዓት በዚሕ በአዲስ አበባ ጉዳይ ላይ ብቻ ሳይሆን በሌላም ጉዳይ ላይ ለመወያየት ዝግጁ ነን----»ጀዋር መሐመድ

«ለመወያየት መቶ በመቶ ዝግጁ ነኝ። እምንፈታዉም በድርድርና ዉይይት ነዉ።----ብስለቱም አለን» እስክንድር ነጋ።

Via የጀርመን ድምፅ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት...

(ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ)
#STOP_HATE_SPEECH

በሀገር አቀፍ ደረጃ TIKVAH-ETH "የፀረ ጥላቻ ንግግር" ዘመቻ በማካሄድ ላይ ይገኛል። በተለይም በማህበራዊ ሚዲያዎች እየተሰራጩ ያሉ የጥላቻ ንግግሮች ሀገራችንን #ወደማትወጣው መከራ ውስጥ የሚከታት በመሆኑ ጊዜው ሳይረፍድ ይህን እኩይ ተግባር በጋራ መዋጋት ያስፈልጋል።

በቅድሚያ በሺዎች የሚቆጠሩ የሀገራችን ወጣቶች በሚገኙባቸው ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ ትኩረት በማድረግ የጥላቻ ንግግር ሊያመጣ የሚችለውን ችግር የማስገንዘብ ስራ እየሰራን እንገኛልን።

ሀሳቡን ካቀረብንላቸው የሀገራችን ዩኒቨርሲቲዎች መካከል የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ፈጣን ምላሽ በመስጠት ሀሳቡን በመደገፍ እንዲሁም ዘመቻውን ለማገዝ ፍቃደኝነቱን ያሳየን #የመጀመሪያውን ተቋም ነው። በዚህ አጋጣሚ በዶክተር #ታከለ ለሚመራው የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር እንዲሁም #ለተማሪዎች_ህብረቱ ያለንን ላቅ ያለ ምስጋናና ክብር እንገልፃለን!!
.
.
.
ውድ የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ኑ ...3 ተከታታይ ምሽቶችን ከTIKVAH-ETH ጋር አሳልፉ! ስለጥላቻ ንግግሮች እና ከጊዜ ወደጊዜ እየከፋ ስለመጣው አግባብነት የሌለው የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም እንነጋገር! የሀገራችሁ ጉዳይ ካሳሰባችሁ ሀሳባችሁን ስጡ...የመፍትሄ አቅጣጫዎችን ጠቁሙ!

ቅዳሜ፣ እሁድ እና ሰኞ በተከታታይ!

🔹ቦታ - ዋናው ግቢ(በተማሪዎች መግቢያና መውጫ በር አካባቢ)

⌚️ሰዓት - ከምሽቱ 12:30 ጀምሮ

እንግዶች ይኖራሉ!!

#በፍቅር ኢትዮጵያን እንገንባ!!
ከጥላቻ ንግግሮች #እንቆጠብ!!

(የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ህብረት)

በቀጣይ፦

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ
አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
ጅማ ዩኒቨርሲቲ
ዲላ ዩኒቨርሲቲ
አምቦ ዩኒቨርሲቲ
ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ
ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ
መቀለ ዩኒቨርሲቲ
ጎንደር ዩኒቨርሲቲ

#ለቀጣዩ_ትውልድ ከጥላቻ የራቀችን ሀገር እናወርሳለን! ሀሳቡን ለመደገፍ የምትፈልጉ፦
0919 74 36 30 @tsegabwolde

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update እነ እስክንድር ነጋ #በራስ_ሆቴል ሊያረጉት የነበረው ስብሰባ በአዲስ አበባ እና ፈደራል ፖሊሶች ጥምረት እንዳይካሄድ መከልከሉ ተሰምቷል።

ዝርዝር መረጃዎችን ይጠብቁ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰቆጣ🔝

በርዕሰ መስተዳድር ዶክተር አምባቸው መኮንን የተመራው የክልሉ ከፍተኛ አመራር ልዑክ ሰቆጣ ገብቷል፡፡ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶር. አምባቸው መኮንን፣ የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ክብርት ወርቅ ሰሙ ማሞ፣ የአዴፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዮሃንስ ቧያለው እና የክልሉ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አሰማኸኝ አስረስ ሰቆጣ ሲገቡ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡ ከሕዝብ ጋር የሚያደርጉት ውይይትም ከደቂቃዎች በፊት ተጀምሯል።

Via AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
እንዳያመልጣችሁ!

የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች፦

ዛሬ ምሽት ከ12:30 ጀምሮ የ #STOP_HATE_SPEECH የመጀመሪያው የፊት ለፊት ውይይት ዛሬ ይካሂዳል። ልዩ የኪነ ጥበብ ዝግጅትም ይኖራል። #በማህበራዊ_ሚዲያ አጠቃቀም እና #በጥላቻ_ንግግሮች ዙሪያ ንግግር ይደረጋል።

አዘጋጅ፦ TIKVAH-ETH ከወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር!

#ሼር #Share
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አለም አቀፍ የኦቲዝም ግንዛቤ ቀን!
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)