TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.2K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Breaking

ንብረትነቱ የሳውዝ ዌስት አየር መንገድ የሆነ ሌላ ቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን ባጋጠመው የሞተር ብልሽት ምክንያት በረራውን #አቋረጠ

በኢትዮጵያ አየር መንገድ ላይ በደረሰው #አደጋ ምክንያት ከበረራ #የታገደው ይህ ቦይንግ 737 አውሮፕላን በወቅቱ ተሳፋሪ ያልጫነ ሲሆን አብራሪዎቹ ካሊፎርኒያ ወደሚገኘው የሳውዝ ዌስት አየር መንገድ ወስዶ ለማቆም ጉዞ በጀመሩ በአስር ደቂቃ ውስጥ በአውሮፕላኑ አንደኛ ሞተር ላይ በተፈጠረ ብልሽት ሞተሩ ከልክ በላይ #በመሞቁ ምክንያት ወደ ካሊፎርኒያ ያደርጉት የነበረው በረራ ተቋርጦ ኦርላንዶ ውስጥ በድንገት ለማረፍ ተገደዋል ሲል cnbc ከደቂቃዎች በፊት ዘግቧል።

'የቦይንግ ካምፓኒ በአለም አቀፍ ደረጃ የደረሰበትን ኪሳራ ለማካካስ በማሰብ በሚመስል መልኩ ሰሞኑን በኢትዮጵያ አየር መንገድ ላይ የደረሰውን አደጋ ከማሰልጠኛ ሲሙሌተርና አውሮፕላኑን ያበር ከነበረው ፓይለት ጋር በተያያዘ ያጋጠመ አደጋ ለማስመሰል በኒውዮርክ ታይምስና በአንዳንድ የውጭ ሚዲያዎች አማካኝነት የተሳሳተ ዘገባ መሰራቱ ይታወሳል።

Via waltainfo.com
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Free_Nazrawit_Abera‼️

በቻይና ዕፅ ይዛ ተገኝታለች በሚል ወንጀል ተጠርጥራ በእስር የምትገኘው የናዝራዊት አበራን ጉዳይ የሚከታተል ቡድን ተዋቅሮ ስራ መጀመሩን ጠቅላይ አቃቤ ህግ ገለፀ፡፡

የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ኢትዮጵያ ከቻይና ጋር ያላትን የሁለትዮሽ የህግ ማዕቀፍ፣ አለም አቀፍ የህግ ስምምነቶችና ከሀገሪቱ ጋር ያለውን መልካም ግንኙነት በመጠቀም ጉዳዩን የሚከታተል ቡድን ማዋቀሩን ገልጿል፡፡

በፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ የህግ ኦዲትና ኢንስፔክሽን ዳይሬክተር አቶ አለምአንተ አግደው ጠቅላይ አቃቤ ህግ ያደራጀው የባለሞያዎች ቡድን በቻይና በናዝራዊት ላይ አየተካሄደ የሚገኘውን ምርመራና እዚህ አገር ቤት ከድርጊቱ አፈፃፀም ጋር ያለውን ሂደት የሚከታተል ይሆናል ነው ያሉት፡፡

በቻይና ዕፅ ይዛ ተገኝታለች በሚል ወንጀል ተጠርጥራ በቁጥጥር ስር የዋለችው ናዝራዊት በሲቪል ምህንድስና ተመርቃ በኮንዶሚኒየም ቤቶች ግንባታ ዘርፍ ተሠማርታ ኢትዮጵያ ውስጥ ትሰራ እንደነበር ከቤተሰቦቿ የተገኘው መረጃ ያስረዳል፡፡

የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ኢትዮጵያ ከቻይና ጋር ያላትን የሁለትዮሽ የህግ ማዕቀፍ፣ አለም አቀፍ የህግ ስምምነቶችና ከሀገሪቱ ጋር ያለውን መልካም ግንኙነት በመጠቀም ጉዳዩን የሚከታተል ቡድን አዋቅሮ ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተለው መሆኑን አመልክቷል፡፡

ቡድኑም በቻይና በናዝራዊት ላይ አየተካሄደ የሚገኘውን ምርመራና ኢትዮጵያ ላይ ከድርጊቱ አፈፃፀም ጋር ያለውን ሂደት አቆራኝቶ የቅርብ ክትትል ያደርጋልም ተብሏል።

Via EBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 737 በደረሰው አደጋ ህይወታቸውን ላጡ ቤተሰቦች በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወሳኝ ኩነት ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ የሞት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ሰጥቶ ማጠናቀቁን አስታወቀ፡፡ በአደጋው ህይወታቸውን ላጡ 141 የ33 ሀገራት ዜግነት ላላቸው ቤተሰቦች የሞት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት መሰጠቱን የወሳኝ ኩነት ማስረጃ አገልገሎት ቡድን መሪ አቶ መልካሙ ክብረት ተናግረዋል፡፡ የሞት ማረጋገጫ ሰርተፍኬቱ የተሰጠው የኢትዮጵያ አየር መንገድን ወክለው በመጡት በአቶ ኤርሚያስ አበባ አማካኝነት መሆኑንም አቶ መልካሙ ክብረት ጨምረው ገልፀዋል፡፡

Via በአ/አ ከተማ አስተዳደር የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ኤጀንሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ልዩ ተሰጥኦ ያላቸው ተማሪዎች እንዲማሩበት ታስቦ በግንባታ ላይ የሚገኘው የኢኖቬሽን ማዕከል ከ50 በመቶ በላይ መጠናቀቁን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አስታውቋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ዋና ኦዲተር ለመለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ መምህራን በነጻ የታደሉ የጋራ መኖሪያ ቤቶችን እየመረመረ መሆኑን ካፒታል አስነብቧል፡፡ ለመምህራኑ የተሰጡት በቦሌ ቡልቡላ የሚገኙ 30 ኮንዶሚኒየም ቤቶች ናቸው፡፡ መምህኑ በወር 5 ሺህ ብር የቤት አበል እያላቸው ነው በ500 ብር ኪራይ እንዲኖሩባቸው የታደላቸው፡፡ አካዳሚው በጠቅላይ ሚንስትር ጽፈት ቤት ስር ያለ የፌደራል ተቋም ነው፡፡ የአካዳሚክ ፕሬዝዳንቱ ጸሃፊ ዳዊት ለገሠ ግን ብቃት ያላቸውን አስተማሪዎች በተቋማችን ለማቆየት ስንል የሰጠናቸው ጥቅማጥቅም ነው ብለዋል፡፡

Via ካፒታል(በዋዜማ)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መልዕክት ለአዲስ አበባ ልጆች፦
(ከዶክተር ኤልያስ ገብሩ)

...ኢትዮጵያን እወዳታለሁኝ። አዲስ አበባም ያደግኩባት አድባሬ ነች። እናም ኢትዮጵያንም አዲስ አበባንም ስለምወዳቸው የውስጤን የስሜት ግፊያ(Urge) ትቼ እውነትን እናገራለሁኝ። >>>ጀዋርም እስክንድርም ቁጥራቸው ይለያይ እንጂ የሚሊዮኖች ድጋፍ ያላቸው። በእነርሱ የማይደራደር ተከታዮች ያላቸው አክቲቪስቶች ናቸው።

እናም የዚህን ወቅታዊ ትኩሳት መዳረሻ የሚሆኑትን ሁለት መራር እውነታዎች ተቀበል...

1ኛ>> አንዱን ደግፈህ አንዱን ስለጠላህ የኢትዮጵያን ሰላምና አንድነት የምታስጠብቅ ከመሰለህ ተሳስተሃል።

2ኛ>> በዚህ አላስፈላጊ ፍትጊያ አንዱ ወገን አሸናፊ ይሆናል ብለህ የምታስብ ካለህ ተሳስተሃል። አንዱ ወገን አሸናፊ ቢሆን እንኳን ኢትዮጵያን እንደ ሐገር ሊያስቀጥል የማይችል የእርስ በርስ ደም መፋሰስ አይቀሬ ነው።

***ስለዚህ ወገኔ ሆይ ኢትዮጵያን እወዳታለሁኝ የምትል፣ ከሆነ ጎራ ለይተህ መገፋፋቱን ተውና ቆም ብለህ አስብ። እውነት ነው የምልህ አርቀህ ተመልከት። አዲስ አበባንም እወዳታለሁኝ የምትል የሸገር ልጅ ንቃ። እንደ ሰበታ፣ ሱሉልታ፣ ቡራዩ፣ ለገጣፎ፣ ወለቴ፣ ካራቆሬ... ያሉ ቦታዎች ላይ ሊከሰት የሚችለውን ነገር አሻግሮ ማየት ያስፈልጋል። መቻቻል...የኦሮሞ ወንድምህን አክብረህ መወያየትና አብረህ መኖር እንጂ እልህና የቃላት ልውውጥ ለማንም አይጠቅምም። ዋናው ነገር ፍቅሩ ነው የሚሉ የአራዳ ልጆች አሁን ብዙ ስራ ይጠበቅባችኋል።

#ወደ_ልቦናችን_እንመለስ
#ኢትዮጵያ_የሁላችንም_መሰብሰቢያ_ዋርካ_ናት

(ዶ/ር ኤልያስ ገብሩ አዕምሮ)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ትግራይ ክልል ሀገር ዐቀፉ ሕዝብና ቤቶች ቆጠራ መራዘሙን ተቃውሟል፡፡ ለቆጠራው ዝግጅቶች ተደርገው ሳለ በአስቸኳይ ስብሰባ መራዘሙ ሕገ መንግሥቱን ይሸረሽራል፤ ሀገሪቱንም ለኪሳራ ይዳርጋል ብለዋል የክልሉ ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ሃላፊ ዶክተር አብርሃም ተከስተ ለኢቢሲ፡፡ ውሳኔው የመንግሥትን የአመራር ግልጽነት አለመኖሩን ያሳያል፤ ሀገሪቱ በዐለም ላይ ያላትን አመኔታ ያሳጣል፡፡

Via #ebc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአማራ ክልል መንግስት ለ4 ሺህ 280 የህግ ታራሚዎች ይቅርታ ማድረጉን አስታውቋል። እነዚህ የህግ ታራሚዎች #ከነገ ጀምሮ በይቅርታ እደሚለቀቁ የተገለፀ ሲሆን ይቅርታ ከተደረገላቸው ታራሚዎች ውስጥ 67 ሴቶች ናቸው ተብሏል፡፡

Via AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በየካ ክፍለ ከተማ #በቅርስነት የተመዘገበውን የደጃዝማች አምኃ አበራ መኖሪያ ቤት በከፊል #እንዳፈረሰው ሸገር ዘግቧል፡፡ የከተማዋ ባሕል፣ ኪነ ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ግን ቅርሱን እንዳያፈርስ ኮርፔሬሽኑ ጋር ደብዳቤ ተለዋውጠን ተስማምተን ነበር ብሏል፡፡ በየካ ክፍለ ከተማ የቢሮው ሃላፊ ታርጋ የሌለው እስካቫተር ነው ያፈረሰው፤ አፍራሾቹን ከድርጊታቸው አስቁመን በፖሊስ አስይዘናቸዋል ብለዋል፡፡ ካሁን በፊትም ኮርፖሬሽኑ የቅርሱን እልፍኞች አፍርሶ ጉዳዩ ክስ ላይ ነበር፡፡ ቅርሱ የ90 ዐመታት ዕድሜ አለው፡፡ ደጃዝማች አምኃ የእውቁ አርበኛ ልዑል ራስ ካሳ ኃይሉ የልጅ ልጅ ናቸው፡፡ አባታቸው አበራ ካሳ ከወንድማቸው ወንድወሰን ካሳ ጋር ከፋሽስት ጣሊያን ጋር ሲዋጉ ተይዘው በስቅላት የተገደሉ አርበኛ ናቸው።

Via ሸገር 102.1
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የፈረሰውን በቅርስነት የተመዘገበ መኖሪያ ቤት ጉዳይ በህግ አግባብ ለመፍታት ጥረት ይደረጋል-የአዲስ አበባ ከተማ ባህልና ቱሪዝም
.
.
በአዲስ አበባ ትላንት የፈረሰው የደጃዝማች ዐምዴ አበራ ካሳ መኖሪያ ቤት ጉዳይ በህግ አግባብ ለመፍታት እንሚንቀሳቀስ የአዲስ አበባ ከተማ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ አስታወቀ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ አንድ የሚገኘውና በቅርስነት የተመዘገበው መኖሪያ ቤቱ በትላንትናው ዕለት መፍረሱ ይታወቃል፡፡

የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ጉዳዩን በተመለከተ በዛሬው ዕለት ወደ ስፍራው በመሄድ #እንደረጋገጠው ከሆነ ከ90 ዓመታት በላይ ያስቆጠረዉ መኖሪያ ቤቱ የፈረሰው በፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን አማካኝነት ነው፡፡

በአዲስ አበበ ከተማ በቅርስነት ከተያዙ ታሪካዊ ግንባታዎች አንዱ እንደሆነ የሚነገርለት የደጃዝማች ዐምዴ አበራ ቤት ለምን እንዳፈረሰ የተጠየቀው የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በበኩሉ ቤቱ በቅርስነት ስለመመዝገቡ ምንም ዓይነት መረጃ እንደሌለው በተለይ ለኢቲቪ ገልጿል፡፡

ኢቲቪ የፈረሰው ታሪካዊ መኖሪያ ቤት በከተማዋ በቅርስነት ከተመዘገቡ ከ400 በላይ ቅርሶች መካከል አንዱ መሆኑን ከአዲስ አበበ ከተማ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ በዛሬው ዕለት ማረጋገጥ ችሏል፡፡

በቅርስነት ተመዝግቧል የተባለዉን መኖሪያ ቤት ጉዳይ ወደ ፊት በህግ አግባብ ለመፍታት እንሚንቀሳቀስ ነው የአዲስ አበበ ከተማ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ የገለፀው፡፡

Via etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በባህርዳር ከተማ የሚገኘውን የአባይ ድልድይ ለማስገንባት በዛሬው ዕለት ስምምነት ተፈርሟል። ለበርካታ አመታት በባህር ዳር ከተማ ነዋሪዎች ጥያቄ ሲነሳበት የቆየው ይህ ድልድይ በ 1 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር ነው የሚገነባው፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia