TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ስፖርት

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን U23 በማሊ አቻው 4 ለ 0 በሆነ ውጤት #ተሸንፏል#MALI 4 - 0 #ETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ማሊ 4-0 ኢትዮጵያ🔝

#አጠቃላይ_ውጤት ማሊ ከ23 ዓመት በታች 5-1 ኢትዮጵያ ከ23ዓመት በታች! #ETHIOPIA #MALI

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዲስ አበባ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #አብይ_አህመድ ከአዲስ አበባ ጋር ተያይዞ ለሚነሱ ሀሳቦች አዲስ አበባ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ባህር ዳር፣ መቐለ፣ ሀዋሳ፣ ጅማ፣ ነቀምት ሂዶ እንደሚሰራውና የኔ ናቸው እንደሚለው ሁሉ አዲስ አበባም ተመሳሳይ ነች፤ #የሁሉም ኢትዮጵያውያን መኖሪያ ነች ብለዋል። #ODP

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Breaking

ንብረትነቱ የሳውዝ ዌስት አየር መንገድ የሆነ ሌላ ቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን ባጋጠመው የሞተር ብልሽት ምክንያት በረራውን #አቋረጠ

በኢትዮጵያ አየር መንገድ ላይ በደረሰው #አደጋ ምክንያት ከበረራ #የታገደው ይህ ቦይንግ 737 አውሮፕላን በወቅቱ ተሳፋሪ ያልጫነ ሲሆን አብራሪዎቹ ካሊፎርኒያ ወደሚገኘው የሳውዝ ዌስት አየር መንገድ ወስዶ ለማቆም ጉዞ በጀመሩ በአስር ደቂቃ ውስጥ በአውሮፕላኑ አንደኛ ሞተር ላይ በተፈጠረ ብልሽት ሞተሩ ከልክ በላይ #በመሞቁ ምክንያት ወደ ካሊፎርኒያ ያደርጉት የነበረው በረራ ተቋርጦ ኦርላንዶ ውስጥ በድንገት ለማረፍ ተገደዋል ሲል cnbc ከደቂቃዎች በፊት ዘግቧል።

'የቦይንግ ካምፓኒ በአለም አቀፍ ደረጃ የደረሰበትን ኪሳራ ለማካካስ በማሰብ በሚመስል መልኩ ሰሞኑን በኢትዮጵያ አየር መንገድ ላይ የደረሰውን አደጋ ከማሰልጠኛ ሲሙሌተርና አውሮፕላኑን ያበር ከነበረው ፓይለት ጋር በተያያዘ ያጋጠመ አደጋ ለማስመሰል በኒውዮርክ ታይምስና በአንዳንድ የውጭ ሚዲያዎች አማካኝነት የተሳሳተ ዘገባ መሰራቱ ይታወሳል።

Via waltainfo.com
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Free_Nazrawit_Abera‼️

በቻይና ዕፅ ይዛ ተገኝታለች በሚል ወንጀል ተጠርጥራ በእስር የምትገኘው የናዝራዊት አበራን ጉዳይ የሚከታተል ቡድን ተዋቅሮ ስራ መጀመሩን ጠቅላይ አቃቤ ህግ ገለፀ፡፡

የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ኢትዮጵያ ከቻይና ጋር ያላትን የሁለትዮሽ የህግ ማዕቀፍ፣ አለም አቀፍ የህግ ስምምነቶችና ከሀገሪቱ ጋር ያለውን መልካም ግንኙነት በመጠቀም ጉዳዩን የሚከታተል ቡድን ማዋቀሩን ገልጿል፡፡

በፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ የህግ ኦዲትና ኢንስፔክሽን ዳይሬክተር አቶ አለምአንተ አግደው ጠቅላይ አቃቤ ህግ ያደራጀው የባለሞያዎች ቡድን በቻይና በናዝራዊት ላይ አየተካሄደ የሚገኘውን ምርመራና እዚህ አገር ቤት ከድርጊቱ አፈፃፀም ጋር ያለውን ሂደት የሚከታተል ይሆናል ነው ያሉት፡፡

በቻይና ዕፅ ይዛ ተገኝታለች በሚል ወንጀል ተጠርጥራ በቁጥጥር ስር የዋለችው ናዝራዊት በሲቪል ምህንድስና ተመርቃ በኮንዶሚኒየም ቤቶች ግንባታ ዘርፍ ተሠማርታ ኢትዮጵያ ውስጥ ትሰራ እንደነበር ከቤተሰቦቿ የተገኘው መረጃ ያስረዳል፡፡

የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ኢትዮጵያ ከቻይና ጋር ያላትን የሁለትዮሽ የህግ ማዕቀፍ፣ አለም አቀፍ የህግ ስምምነቶችና ከሀገሪቱ ጋር ያለውን መልካም ግንኙነት በመጠቀም ጉዳዩን የሚከታተል ቡድን አዋቅሮ ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተለው መሆኑን አመልክቷል፡፡

ቡድኑም በቻይና በናዝራዊት ላይ አየተካሄደ የሚገኘውን ምርመራና ኢትዮጵያ ላይ ከድርጊቱ አፈፃፀም ጋር ያለውን ሂደት አቆራኝቶ የቅርብ ክትትል ያደርጋልም ተብሏል።

Via EBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 737 በደረሰው አደጋ ህይወታቸውን ላጡ ቤተሰቦች በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወሳኝ ኩነት ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ የሞት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ሰጥቶ ማጠናቀቁን አስታወቀ፡፡ በአደጋው ህይወታቸውን ላጡ 141 የ33 ሀገራት ዜግነት ላላቸው ቤተሰቦች የሞት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት መሰጠቱን የወሳኝ ኩነት ማስረጃ አገልገሎት ቡድን መሪ አቶ መልካሙ ክብረት ተናግረዋል፡፡ የሞት ማረጋገጫ ሰርተፍኬቱ የተሰጠው የኢትዮጵያ አየር መንገድን ወክለው በመጡት በአቶ ኤርሚያስ አበባ አማካኝነት መሆኑንም አቶ መልካሙ ክብረት ጨምረው ገልፀዋል፡፡

Via በአ/አ ከተማ አስተዳደር የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ኤጀንሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ልዩ ተሰጥኦ ያላቸው ተማሪዎች እንዲማሩበት ታስቦ በግንባታ ላይ የሚገኘው የኢኖቬሽን ማዕከል ከ50 በመቶ በላይ መጠናቀቁን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አስታውቋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ዋና ኦዲተር ለመለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ መምህራን በነጻ የታደሉ የጋራ መኖሪያ ቤቶችን እየመረመረ መሆኑን ካፒታል አስነብቧል፡፡ ለመምህራኑ የተሰጡት በቦሌ ቡልቡላ የሚገኙ 30 ኮንዶሚኒየም ቤቶች ናቸው፡፡ መምህኑ በወር 5 ሺህ ብር የቤት አበል እያላቸው ነው በ500 ብር ኪራይ እንዲኖሩባቸው የታደላቸው፡፡ አካዳሚው በጠቅላይ ሚንስትር ጽፈት ቤት ስር ያለ የፌደራል ተቋም ነው፡፡ የአካዳሚክ ፕሬዝዳንቱ ጸሃፊ ዳዊት ለገሠ ግን ብቃት ያላቸውን አስተማሪዎች በተቋማችን ለማቆየት ስንል የሰጠናቸው ጥቅማጥቅም ነው ብለዋል፡፡

Via ካፒታል(በዋዜማ)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መልዕክት ለአዲስ አበባ ልጆች፦
(ከዶክተር ኤልያስ ገብሩ)

...ኢትዮጵያን እወዳታለሁኝ። አዲስ አበባም ያደግኩባት አድባሬ ነች። እናም ኢትዮጵያንም አዲስ አበባንም ስለምወዳቸው የውስጤን የስሜት ግፊያ(Urge) ትቼ እውነትን እናገራለሁኝ። >>>ጀዋርም እስክንድርም ቁጥራቸው ይለያይ እንጂ የሚሊዮኖች ድጋፍ ያላቸው። በእነርሱ የማይደራደር ተከታዮች ያላቸው አክቲቪስቶች ናቸው።

እናም የዚህን ወቅታዊ ትኩሳት መዳረሻ የሚሆኑትን ሁለት መራር እውነታዎች ተቀበል...

1ኛ>> አንዱን ደግፈህ አንዱን ስለጠላህ የኢትዮጵያን ሰላምና አንድነት የምታስጠብቅ ከመሰለህ ተሳስተሃል።

2ኛ>> በዚህ አላስፈላጊ ፍትጊያ አንዱ ወገን አሸናፊ ይሆናል ብለህ የምታስብ ካለህ ተሳስተሃል። አንዱ ወገን አሸናፊ ቢሆን እንኳን ኢትዮጵያን እንደ ሐገር ሊያስቀጥል የማይችል የእርስ በርስ ደም መፋሰስ አይቀሬ ነው።

***ስለዚህ ወገኔ ሆይ ኢትዮጵያን እወዳታለሁኝ የምትል፣ ከሆነ ጎራ ለይተህ መገፋፋቱን ተውና ቆም ብለህ አስብ። እውነት ነው የምልህ አርቀህ ተመልከት። አዲስ አበባንም እወዳታለሁኝ የምትል የሸገር ልጅ ንቃ። እንደ ሰበታ፣ ሱሉልታ፣ ቡራዩ፣ ለገጣፎ፣ ወለቴ፣ ካራቆሬ... ያሉ ቦታዎች ላይ ሊከሰት የሚችለውን ነገር አሻግሮ ማየት ያስፈልጋል። መቻቻል...የኦሮሞ ወንድምህን አክብረህ መወያየትና አብረህ መኖር እንጂ እልህና የቃላት ልውውጥ ለማንም አይጠቅምም። ዋናው ነገር ፍቅሩ ነው የሚሉ የአራዳ ልጆች አሁን ብዙ ስራ ይጠበቅባችኋል።

#ወደ_ልቦናችን_እንመለስ
#ኢትዮጵያ_የሁላችንም_መሰብሰቢያ_ዋርካ_ናት

(ዶ/ር ኤልያስ ገብሩ አዕምሮ)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ትግራይ ክልል ሀገር ዐቀፉ ሕዝብና ቤቶች ቆጠራ መራዘሙን ተቃውሟል፡፡ ለቆጠራው ዝግጅቶች ተደርገው ሳለ በአስቸኳይ ስብሰባ መራዘሙ ሕገ መንግሥቱን ይሸረሽራል፤ ሀገሪቱንም ለኪሳራ ይዳርጋል ብለዋል የክልሉ ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ሃላፊ ዶክተር አብርሃም ተከስተ ለኢቢሲ፡፡ ውሳኔው የመንግሥትን የአመራር ግልጽነት አለመኖሩን ያሳያል፤ ሀገሪቱ በዐለም ላይ ያላትን አመኔታ ያሳጣል፡፡

Via #ebc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአማራ ክልል መንግስት ለ4 ሺህ 280 የህግ ታራሚዎች ይቅርታ ማድረጉን አስታውቋል። እነዚህ የህግ ታራሚዎች #ከነገ ጀምሮ በይቅርታ እደሚለቀቁ የተገለፀ ሲሆን ይቅርታ ከተደረገላቸው ታራሚዎች ውስጥ 67 ሴቶች ናቸው ተብሏል፡፡

Via AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia