TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
አቶ ግርማ የሺጥላ ተገደሉ። የአማራ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ግርማ የሺጥላ ዛሬ በሰሜን ሸዋ " መሀል ሜዳ " ላይ በተፈፀመባቸው ጥቃት ተገድለዋል። የአቶ ግርማን ግድያ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አረጋግጠዋል። ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፤ " ሐሳብን በሐሳብ ማሸነፍ ያቃታቸው አካላት የወንድማችንን የግርማ የሺጥላን ነፍስ ነጥቀዋል። " ብለዋል። ዶ/ር ዐቢይ የግድያውን ሁኔታ በተመለከተ #ዝርዝር_መረጃ…
" አቶ ግርማ የሺጥላን ጨምሮ አምስት ሰዎች ተገድለዋል " - የአማራ ክልል መንግስት

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ባወጣው የሀዘን መግለጫ በአቶ ግርማ የሺጥላ ላይ የተፈፀመው ግድያ ዛሬ ከሰዓት በኋላ፤ የመንግሥትና የድርጅት ሥራዎችን ሠርተው ከመሃል ሜዳ ወደ ደብረ ብርሃን ሲመለሱ በመንዝ ጓሳ ላይ መሆኑንና ግድያው የተፈፀመው በታጠቁ ኢ-መደበኛ ኃይሎች እንደሆነ ገልጿል።

ከእሳቸው በተጨማሪ በግል ጥበቃዎቻቸው እና ቤተሰቦቻቸው ላይ ጥቃት መፈጸሙ የተገለጸ ሲሆን እስካሁን #የአምስት_ሰዎች ሕይወት ስለማለፉ መረጃው እንደደረሰው ክልሉ ባወጣው መግለጫ ጠቅሷል።

ክልሉ በመግለጫው፥ "ይህንን የሽብር ሥራ እየሠሩ ያሉ እንዲህ አይነት ኃይሎች ላይ የክልሉ መንግሥት የማያዳግም እርምጃ ይወስዳል፡፡ የጥቃቱን አድራሾችም ለሕግ ያቀርባል " ብሏል።

አክሎም፥ "የጥፋት ኃይሎች ከዚህ በላይ ዓላማ ያላቸው እና ክልሉን የማፍረስ ተልዕኮ ይዘው የሚንቀሳቀሱ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን ከዚህ በኋላ የክልሉ መንግሥት እንደማይታገስ እና ጥብቅ እርምጃ እንደሚወስድ እናረጋግጣለን " ሲል ገልጿል።

@tikvahethiopia