#ኢትዮጵያ
የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል የ4 አብያተ ክርስቲያናትና ሚኒስትሪዎች ሠርተፍኬት #እንዲሰረዝ መወሰኑን አሳውቋል።
ሠርተፍኬታቸው የተሰረዘው ፦
1ኛ. ጋድስ ላይት ግሎሪ ኢንተርናሽናል ሚኒስትሪ ➡ ነብይ ኢዮብ ጭሮ
2ኛ. ገዥዋ ዓለም አቀፍ የክርስቶስ ቤተክርስቲያን ➡ መጋቢ ካሳ ኪራጋ
3ኛ. የሰማይቱ ጽዮን ማኅበርተኞች የክርስቶስ ቤተክርስቲያን ➡ መጋቢ ሚስጥሩ መዝገቡ
4ኛ. የእግዚአብሔር መንግስት እውነት ዓለም አቀፍ ሚኒስትሪ ➡ መጋቢ ቢንያም ሽታዬ ... ናቸው።
ውሳኔው የተለለፈባቸው በስህተት ትምህርትና ልምምዶች ምክንያት ነው።
ካውንስሉ እነዚህ አካላት የተሰጣቸውን የሕግ ከለላ በመጠቀም ከመጽሐፍ ቅዱስ አስተምሮና ጤናማ ሥነ ምግባር ውጭ የሆነ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ እንደነበሩ ገልጿል።
ከዚህ ተግባራቸው ይመለሱ ዘንድም አስፈላጊውን ትምህርትና ምክር ሲሰጥ ቆይቷል።
ይሁን እንጂ ምክሩ ተቀበለው ሕዝብን ከሚያሳስት ተግባራቸው #ለመመለስ ፈቃደኛ ሆነው ባለመገኘታቸው ሠርተፍኬታቸው እንዲሰረዝ ወስኗል።
(ካንውስሉ ለሁሉም መገናኛ ብዙሃን የላከው መግለጫ ከላይ ተያይዟል)
@tikvahethiopia