TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
214 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
"መንገድ ለሰው" - ከተሽከርካሪ ነፃ ቀን አዲስ አበባ-#CarFreeDayEthiopia

ፎቶ፦ samy(TIKVAH-ETH)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ🔝

ትላንት የካቲት 23 #የወልቂጤ_ዩኒቨርሲቲ ለ5 ዓመት ከ5 ወር በArchitecture ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች #አስመርቋል

Via አንተነህ (From Staff of Architecture)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ እና የኬንያው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ዛሬ ጠዋት ወደ ኤርትራ አቅንተዋል። መሪዎቹ አስመራ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም በኢሳያስ አፈወርቂ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል። መሪዎቹ በኤርትራ አስመራ በሚኖራቸው ቆይታ ሶስቱም መሪዎች በአፍሪካ ቀንድ ስላለው ቀጠናዊ ትብብር ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል። ህብረትን በማጠናከር አገራቱ በጋራ መልማት የሚቻልባቸው ሁኔታዎችን ማመቻቸት እና የሰላም ጉዳይ ዋናኛ አጀንዳ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

Via etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በዛሬው እለት ለ4ኛ ጊዜ ከተሽከርካሪ ፍሰት የጸዱ መንገዶች ቀን በአዲስ አበባ በደመቀ መልኩ ተከብሮ ውሏል፡፡ መንገድ ለሰው በሚል መሪ ቃል በየወሩ መጨረሻ የሚካሄደው ከተሽከርካሪ ፍሰት የጸዱ መንገዶች ቀን የጤና ሚኒስትር ዶ/ር #አሚር_አማንን ጨምሮ የተለያዩ ባለሥልጣናትና የህብረተሰብ ክፍሎችን ባሳተፈ መልኩ የተለያየ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች የተካሄዱ ሲሆን የተለያዩ የጤና ምርመራዎቸም ተደርገዋል፡፡

Via AfriHealth
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የካቲት 11...

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር #ታከለ_ኡማ የተገኙበት የህወሃት 44ኛ ዐመት የምስረታ በዓል በአዲስ አበባ #ኢንተር_ኮንትኔንታል ሆቴል እየተከበረ ይገኛል። #በድምፂ_ወያነ እና #በትግራይ_ቲቪ በቀጥታ እየተላለፈ ስለመሚገኘ መከታተል ትችላላችሁ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia