TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
‹‹የክህደት ዘመን ላይ ደርሰናል›› ሕወሓት

‹‹ትዕግሥት ሁሌ ስለማይሠራ ዕርምጃ መውሰድ ያስፈልጋል›› ዶ/ር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል
.
.
የትግራይ ክልል ምክትል ፕሬዚዳንት ዶ/ር #ደብረ ጽዮን_ገብረሚካኤል ‹‹ሕገ መንግሥቱ እየተጣሰ ትዕግሥት የሚባል ነገር ሁሌ አይሠራም፣ ዕርምጃ መውሰድ ያስፈልጋል፤›› ሲሉ ለክልሉ ቴሌቪዥን ተናገሩ፡፡

በአገሪቱ ያለው ፖለቲካዊ ሁኔታ ሕገ መንግስቱ የሚጣስበት እና በትግራይ ሕዝብ ላይ ያነጣጠሩ #ጥቃቶች የሚሰነዘሩበት ነው ብለዋል ምክትል ፕሬዝዳንቱ፡፡

ሕወሓት 44ኛ አመት የምሥረታ በዓሉን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ድርጅቱ እና ደጋፊዎቹ የምሥረታ በዓሉን የሚያከብሩት በኢትዮጵያ የተጀመረው ዕድገት ወደ ኋላ እየተቀለበሰ ባለበት ወቅት ነው ብሏል፡፡

ለተጠቀሰው ችግር ዋነኛው መንስኤ የኢሕአዴግ አመራር ውስጥ የተፈጠረው #አለመግባባት እና የውጭ ኃይሎች ጣልቃ ገብነት መሆኑንም መግለጫው ይናገራል፡፡

‹‹የክህደት ዘመን ላይ ደርሰናል›› የሚለው የሕወሓት መግለጫ ትችቱን እንደሚከተለው ያቀርባል፡፡

‹‹በስመ ለውጥ ለአገራቸው ክብርና ሉዓላዊነት መረጋገጥ ዕድሜ ልካቸውን የደከሙና የለፉ የሚረገሙበትና የሚብጠለጠሉበት፣ በአገሪቱ ታሪክ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ በዜጎች ላይ የተለያዩ በደሎችና ግፍ የፈጸሙ፣ እንዲሁም የአገራቸውን ሉዓላዊነት አሳልፈው የሰጡ ብቻ ሳይሆን፣ ከሌሎች የኢትዮጵያ ጠላቶች ጋር አብረው አገርና ሕዝብ የወጉ የሚመሠገኑበትና ክብር የሚሰጥበት የክህደት ዘመን ላይ ደርሰናል፤››

ይሁን እንጂ የአገሪቱ ሁኔታ ሕወሓት ካወጣው መግለጫ በተቃራኒ እንደሆነ በርካቶች ይገልጻሉ።

ከምንጊዜውም የተሻለ ዴሞክራሲ የሰፈነበት፣ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች የቆሙበትና ቀደም ሲል ለተፈጸሙ ጥሰቶችም ፍትሕ የተሰጠበት መሆኑን የአገሪቱ የፖለቲካ ልሂቃን፣ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎችና የተለያዩ የውጭ መገናኛ ብዙኃንና ዓለም አቀፍ ተቋማት ሳይቀሩ በይፋ እየተናገሩ ናቸው።

በተለያዩ አካባቢዎች የሚስተዋሉ ግጭቶችና የዜጎች መፈናቀል መኖር እርግጥ ቢሆንም፣ የፖለቲካ ሽግግር ከዚህ የፀዳ ሊሆን እንደማይችል ነገር ግን ይህ ችግር እየደበዘዘ መሄድ እንዳለበትና በአሁኑ ወቅትም መረጋጋት መኖሩን ያስረዳሉ።

ሕወሓት በፖለቲካ ማዕከሉ ላይ የነበረው ተፅዕኖ በመቀነሱ የመገፋት ስሜት ሊጫነው እንደሚችል፣ ይኼንንም የሚያባብሱ የፖለቲካ ትግሎች በኢሕአዴግ ውስጥ መቀጠላቸው በግልጽ የሚታይ ቢሆንም፣ ጉዳዩን ከሕዝብ ጋር ማገናኘት ስህተት እንደሆነ በርካታ የፖለቲካ ልሂቃን በተለያዩ መድረኮች በተደጋጋሚ የሚያነሱት ሐሳብ ነው።

የካቲት 13፣ 2011

ምንጭ - ሪፖርተር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጥያቄ -- ለለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ አስተዳደር፦

ይህ ሁሉ ህገወጥ ቤት ሲሰራ በወቅቱ የነበሩ አመራሮች አሁን የት ናቸው?? ዜጎች በተሳሳተ ቦታ ላይ ሀብት ንብረታቸው ሲያፈሱ ዝም ብለው የተመለከቷቸው በወቅቱ የነበሩት አስተዳዳሪዎች ዛሬ የት ናቸው?? ይህ ሁሉ ኪሳራ እስኪደርስ ድረስ ዝም ብለው የተመለከቱት አካላትስ ተጠያቂ ይሆናሉ??

@tsegabwolde @tikvahethiopia
Audio
የቤቶችና ኮንስትራክሽ ሚንስቴር‼️

በኢትዮጵያ ከተሞች ያለውን ስር የሰደደ የቤት ችግር ለመቅረፍ መንግሥት 7 አይነት አማራጮችን እንደሚከተል የቤቶችና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ደኤታ አቶ ካሳሁን ጎፌ አስታወቁ።

የከተማ ቤቶች በኢትዮጵያ ስኬቶች፣ ተግዳሮቶችና የወደፊት አቅጣጫዎች በሚል ርዕስ የፖሊሲ ጥናትና ምርምር ተቋም አጥኚ የሆኑት ዶክተር ዘመንፈስ ገብረእግዚአብሔር ጥናታዊ ፅሑፍ አቅርበዋል።

በጥናታዊ ፅሑፉ ላይ እንደተመለከተው የቤቶች ልማት ውዝፍ ችግሮች ያሉበት እና በየአመቱ አዳዲስ ፍላጎቶች የሚፈጠሩበት፣ ሆኖም በዚህ ልክ የቤቶች አቅርቦት የሌለበት ነው ብለዋል።

Via VOA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በምዕራብ ኦሮሚያ በነበረው #ሁከት ተሳትፈዋል የተባሉ የመንግስት አመራሮች እየተመረመሩ ነው!
.
.
.
በምዕራብ ኦሮሚያ ዞኖች ባለፉት ወራት በነበረው የፀጥታ ቀውስ ሀላፊነታቸውን አልተወጡም ተሳትፎም አድርገዋል ተብለው የተጠረጠሩ አንድ መቶ ያህል የክልሉ አመራሮችና የፀጥታ አካላት ላይ ምርመራ እየተካሄደ ሲሆን ስምንት መቶ የሚጠጉ ፖሊሶችም ስልጠና እንዲወስዱ እየተደረገ ነው።

ባለፉት ወራት የምዕራብ ወለጋ፣ ምስራቅ ወለጋ ፤ ሆሮ ጉዱሩ እና ቄለም አካባቢዎች በኦሮሞ ነፃነት ግንባር ታጣቂዎችና በመንግስት የፀጥታ ሀይሎች መካከል ከፍተኛ ግጭት እንደነበረ ይታወሳል። በዚህ ግጭት ደግሞ የዞኑ አመራሮችን ከመግደል እስከ ባንኮች ዘረፋ የሚደርስ ሰፊ ወንጀል መፈጸሙ በክልሉ መንግስት መግለጫ የተሰጠበት እንደነበርም አይዘነጋም፡፡በተለይ አባቶርቤ ተብሎ የሚጠረ ህቡዕ ቡድን የተለያዩ ግለሰቦችን በመግደል ድርጊት ተሰማርቶ እንደነበርም መንግስት ራሱ ይፋ አድርጓል።

አሁን አካባቢው ላይ በኦሮሞ ዲሞክራቲክ ፓርቲ (ኦዲፒ) እና በኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) መካከል የተፈጸመውን እርቅ ተከትሎ አንጻራዊ ሰላም የወረደ መስሏል፡፡ ሁለቱን ወገኖች በማሸማገል ስራ ላይ የነበሩት አባ ገዳዎች እና ሃደ ሲንቄዎችም( እናቶች) ውጥረት እና ግጭት ሲንጣቸው በነበሩ ዞኖች ተንቀሳቅሰው ባሳለፍነው ሳምንት ሁኔታውን መቃኘታቸው ይታወቃል፡፡ ታጥቀው የነበሩ የኦነግ አባላትንም ትጥቅ በማስፈታት ወደተዘጋጀላቸው ካምፕ እንዲገቡ እየተደረገ ነው። ከሁሉም በላይ ግን የጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ እና የክልሉ ርእሰ መስተዳድር አቶ #ለማ_መገርሳ አካባቢው ድረስ በመጓዝ ያደረጉት ጉብኝት እና ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር የነበራቸው ውይይት ይበልጥ በስፍራው የሰላም አየር መንፈስ መጀመሩን ለማመላከት የታሰበ ይመስላል፡፡

አሁን ይህ ውጤት ይገኝ እንጂ ለወራት የተስተዋለውን ግጭት ያባባሰው እና ለቁጥጥር አዳጋች ያደረገው ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉ የክልሉ የጸጥታ አካላት #በሁከቱ መሳተፋቸው መሆኑን ዋዜማ ሬድዮ መረጃ አግኝቻለሁ ብሏል፡፡ በተለይ አባቶርቤ ተብሎ ሲንቀሳቀስ በነበረው የህቡዕ ቡድን ውስጥም ሆነ አከባቢው ላይ በነበረው ሁከት የቀጥታ ተሳትፎ ነበራቸው ተብለው የተጠረጠሩ ከ800 በላይ የኦሮሚያ ክልል የፖሊስ አባላት በአሁኑ ወቅት አምቦ በሚገኘው ሰንቀሌ ወታደራዊ ማሰልጠኛ የተሃድሶ ስልጠና እየተሰጣቸው እንደሚገኝም ጭምር ነው ራድዮ ጣቢያው አረጋግጫለሁ ብሎ የዘገበው፡፡

ዋዜማ ራድዮ ከምንጮቼ ሰማሁ እንዳለው ይበልጥ #ሁከቱን_በመምራት በማደራጀትና በማስተባበር #አባቶርቤ በተሰኘው ቡድን ውስጥም በቀጥታ በመሳተፍ ደግሞ በ100 ግለሰቦች ላይ ምርመራ እየተካሄደባቸው ይገኛል፡፡ ከነዚህ መካከልም #የዞን_አመራሮች እና #በፖሊስ_አመራርነት ደረጃ የሚገኙ መኖራቸው ጭምርም ታውቋል፡፡

አካባቢውን ያረጋጋሉ ተብለው ከአዲስ አበባ የተላኩት የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አመራርም #ተጠርጥረው በምርመራ ላይ ናቸው፡፡

ምንጭ፦ ዋዜማ ራዲዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አቶ ኢሳያስ በዋስ እንዲወጡ ተወሰነ‼️

ፍርድ ቤቱ መርማሪ ፖሊስ አቶ #ኢሳያስ_ዳኘው በዋስ ሊለቀቁ አይገባም በሚል ያቀረበውን ይግባኝ ውድቅ አደረገ። በከባድ የሙስና ወንጀል የተጠረጠሩት አቶ ኢሳያስ ዳኘው በተጠረጠሩበት ወንጀል በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 10ኛ የወንጀል ችሎት ቀርበው ጉዳያቸውን ሲከታተሉ ከቆዩ በኋላ በ50 ሺህ ብር ዋስ እንዲወጡ #ተፈቅዶላቸዋል

መርማሪ ፖሊስም ግለሰቡ በዋስ መውጣት የለባቸውም በሚል ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ያቀረበው ይግባኝ ውድቅ ተደርጎበታል።

በመሆኑም ከዚህ ቀደም በተወሰነው መሰረት በ50 ሺህ ከሃገር እንዳይወጡ በተጣለ እገዳ #በዋስ እንዲለቀቁ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔውን አፅንቷል።

አቶ ኢሳያስ ዳኘው በኢትዮ ቴሌኮም የኤን ጂ ፒ ኦ ዳይሬክተር ሆነው በሚሰሩበት ወቅት ለሜቴክ የተሰጠን ውል በማሻሻልና ክፍያ እንዲፈጸም በማድረግ በመንግስት ላይ ጉዳት እንዲደርስ አድርገዋል በሚል በከባድ የሙስና ወንጀል ነበር የተጠረጠሩት።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀዋሳ-የሲዳማ ሪፈረንደም ሰልፍ‼️

#የሲዳማ_ክልል_ጥያቄ የሕዝቤ ውሳኔ ቀን መዘግየት አስመልክቶ በቀን 14/6/2011 ዓ.ም በሀዋሳ ከተማ የሚካሄደው ሰልፍ በሰላማዊ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት #ማጠናቀቁን የሲዳማ ዞንና የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ኃላፊዎች በጋራ በሰጡት መግለጫቸው አስታውቀዋል።

የሰልፉ ዓላማ የሲዳማ ሕዝብ በክልልነት የመደራጀት መብት አስፈላጊውን ሕጋዊ ቅድመ ሁኔታዎችን በማጠናቀቅ በቀን 12/3/2011 ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ቢቀርብም እስከ አሁን ድረስ ሕዝቤ ውሳኔ የሚካሄድበት ቀን ተወስኖ ምላሽ ባለመሰጠቱና በመዘግየቱ የሚካሄድ ሰልፍ መሆኑን ለማወቅም ተችሏል።

"ሕገ መንግስታዊ መብታችን ይከበር" በሚል መሪ ቃልና ሌሎች መፈክሮችን በመያዝ በዕለቱ ከጧቱ 1:00-6:00 ሰዓት ድረስ መነሻውን ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ያደረገ በሲዳማ ዞን አስተዳደር- በአሮጌው መናኸሪያ -በተስፋዬ ግዛው ሕንጻ-በመሳይ ሆቴል አቋርጦ በሀዋሳ ዓለም አቀፍ ስታዲዬም ማሳረጊያ የሚደረግ ይሆናል።

በሰልፉ ላይ ከሲዳማ ዞን ሁሉም ወረዳዎች የተወጣጡ ሰልፈኞች የሚሳተፉ መሆኑን በመግለጽ ሰልፉም በሰላማዊ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ ፖሊስ ከተለያዩ ፀጥታ አካላትና ከሰልፉ አስተባባሪዎች ጋር በመሆን አስፈላጊውን ዝግጅት ማጠናቀቁን በመግለጫው አክሏል።

ኀብረተሰቡም ይህን ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት፣ የራሱንና የአካባቢውን ሰላምና ፀጥታ በመጠበቅና በማስጠበቅ ረገድ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣና ማንኛውንም ዓይነት አጠራጣሪ ሁኔታ ሲያጋጥም ለፀጥታ አካላት ፈጥኖ ጥቆማ በመስጠት እንዲተባበርም ጥሪ ቀርቧል።

ከዚህም በተጨማሪ: በሰላማዊ ሰልፉ መነሻ-መድረሻ እንዲሆኑ በተፈቀዱ መንገዶች ላይ ማንኛውም ዓይነት የተሽከርካሪ እንቅስቃሴ የማይፈቀድ መሆኑንና የሰላማዊ ሰልፍ ትዕይንት እስኪጠናቀቅ ድረስ ለትራፍክ እንቅስቃሴ ዝግ እንደሚሆን ተገልጿል።

ከዚህ ውጭ በቡድንም ሆነ በተናጠል የከተማውን ኀብረተሰብ ሰላማዊ እንቅስቃሴና የሰላማዊ ሰልፉ ሠላማዊ ህደቱን ማወክ የተለያዩ #የጦር_መሳሪያዎችን ይዞ መገኘት፣በሰልፉ ወቅት በሕግ #የተከለከሉ ድርጊቶች መፈፀም በጥብቅ የተከለከሉ ሲሆን ተፈጽሞም ሲገኙ የፀጥታ አካሉ አስፈላጊውን ሕጋዊ #እርምጃ ለመውሰድ የሚገደድ መሆኑን ኃላፊዎቹ በመግለጫቸው አጽንኦት ሰጥተዋል።

በማጠቃለያም ሕዝባዊ ትዕይንቱ በሰላም እንዲጠናቀቅ ኀብረተሰቡ ከፀጥታ አካላት ጋር በትብብር እንዲሰራ በድጋሚ ጥሪ በማቅረብ ኃላፊዎቹ መግለጫቸውን አጠቃለዋል።

ምንጭ፦ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀዋሳ~ጥብቅ ማስጠንቀቂያ‼️

#በቡድንም ሆነ #በተናጠል የሀዋሳ ከተማ ኀብረተሰብን #ሰላማዊ እንቅስቃሴና የሰላማዊ ሰልፉ ሠላማዊ ሂደቱን ማወክ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎችን ይዞ መገኘት፣ በሰልፉ ወቅት በሕግ #የተከለከሉ ድርጊቶች መፈፀም በጥብቅ #የተከለከለ ሲሆን ተፈጽሞም ሲገኝ የፀጥታ አካሉ አስፈላጊውን ሕጋዊ #እርምጃ ለመውሰድ የሚገደድ መሆኑን ገልጿል።

#ሲዳማሪፈረንደም2011 #ሀዋሳ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Alert ~ ሸዋሮቢት‼️

"ሰላም ፀግሽ እንዴት ነህ #ሽዋሮቢት ላይ ችግር አለ መንገድ ተዘግቷል፤ ወጣቶች አስፓልት ላይ ጎማ እያነደዱ ነው። ምክንያቱ ደግሞ እናትና ህፃን ልጅ በአሰቃቂ ሁኔታ ተገለው መገኘታቸው ነው። ተዟዙሬ እንዳጣራሁት #የብሄርም #የሃይማኖትም ግጭት #የለበትም ገዳዩ ተይዟል ወጣቶቹ ደግሞ #ይሰጠን ይገደል ነው ጥያቄያቸው ነገሩ ወደባሰ ደረጃ ሳይደርስ በቂ የፖሊስ ሃይል መድረስ ይኖርበታል። እየተቀጣጠሉ ያሉት ጎማዎች ብዙ እና ረጅም መንገድ ላይ ነው ዋናው ግን የሃይማኖትም የብሄርም ግጭት አይደለም!!!" ሠአሌው ምህረት

@tsegabwolde @tikvahethiopia
Mbirr

በትላንትናው ዕለት በማዕበራዊ ድረገፅ በተለይም "Think Tank" በተባለው ድረገፅ Mbirrን የተመለከተ መረጃ ተሰራጭቶ በርካቶች ሲቀባበሉት አምሽተዋል። በሀገራችን ውስጥ የሚነገሩ ሀሰተኛ ወሬዎችን ከምንጩ እያጣራ በማቅረብ የሚታወቀው አለም አቀፉ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት ይህንን መረጃም አጣርቶ የደረሰበትን በፌስቡክ ገፁ ይፋ አድርጓል።

ጋዜጠኛው የMBirr ሀላፊ የሆኑትን እና በኢሜይሉ ላይ የተጠቀሱትን አቶ #እንደሻውን በስልክ አነጋግሮ ያገኘው ምላሽ ይኸ ነው፦

"ይህ fabricated (የፈጠራ) የሆነ መረጃ ነው። አንተም እንዳየኸው ሰዉ ዝም ብሎ ነው ሼር እያረገው ያለው። እንደዚህ አይነት ኢሜይል አልተላከምም፣ አልተላከም።"

በተጨማሪ...

ጋዜጠኛ ኤልያስ የMbirr ኮርፖሬት ኮሚኒኬሽን ሀላፊ የሆነችውን እየሩሳሌም ሀድጉን ስለጉዳዩ ጠይቋት ይህን መልስ ሰጥታለች፦

"Hello Elias, The #fake_news article posted on Ethio Think Tank was categorically untrue, and resulted from the impersonation of one of our employee's email accounts. We have demanded that they retract the article immediately. We request that all news media refrain from publishing this fake news article."

ምንጭ፦ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት (https://www.facebook.com/Elias-Meseret-5172433­22140049/)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሳዛኝ ዜና‼️

አክሱም ሽረ እንደስላሴ መስመር ላይ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ7 ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡

የትራፊክ አደጋው ከሽረ እንደስላሴ ወደ አክሱምና ከአክሱም ወደ ሽረ እንደስላሴ  ሲጓዙ የነበሩ ተሽከርካሪዎች #በመጋጨታቸው ያጋጠመ ነው ተብሏል፡፡

በትራፊክ አደጋው በ15 ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት ያጋጠመ ሲሆን በአምስት ሰዎች ላይ ደግሞ ቀላይ አካል ጉዳት አጋጥሟል፡፡

የትራፊክ አደጋው ልዩ ስሙ አዲግዳድ በተባለ ቦታ ላይ በትናትናው ዕለት እንዳጋጠመ ነው ተገለፀው፡፡

ምንጭ፡-Dimtsi Weyane
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኢንጂነር አይሻ መሃመድ‼️

#የመከላከያ_ሰራዊት_ቀን የሰራዊቱን አቅም በማሳየት እና የሰራዊቱ ሞራል በመገንባትም ጭምር ከፍተኛ ሚና እንደተጫወተ የመከላከያ ሚኒስትር ኢንጅነር #አይሻ_መሃመድ አስታወቁ።

ሚንስትሯ በሰጡት የማጠቃለያ መግለጫ 7ተኛው የኢፊዲሪ የመከላከያ ሰራዊት ቀን በስኬት ተጀምሮ በስኬት እንደተጠናቀቀ ተናግረዋል።

ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት የተውጣጡ አባላት ያሉት ኮሚቴ ተዋቅሮ በአሉን እንዴት እናስኪድ በሚለው ጉዳይ ላይ መግባባት ላይ ተደርሶ ወደ ስራ እንደተገባ ሚንስትሯ አስታውሰዋል።

በተለያዩ ቦታዎች የተደረጉት የፓናል ውይይቶች እና የተለያዩ ዝግጅቶች ህብረተሰቡንና የመከላከያ ሰራዊት አባላትን የበለጠ እንዲቀራረቡ እንዳደረገም ተገልጿል፡፡

በአሁኑ ሰአት የመከላከያ ሰራዊተ በአንዳንድ የሃገሪቱ ክፍሎች ህገ መንግቱን የማስከበር ስራ በመስራት ላይ እንደሚገኝ እና የሕብረተሰቡን ሰላም ለመጠበቅ የሃገሪቱን ሉአላዊነት ከውስጥም ከውጭም ለማስጠበቅ ከመቼውም ጊዜ በላይ እይተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ ነው መከላከያ ሚኒስትሯ የገለፁት።

ምንጭ፦ EBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አንዳንድ #ተራ የሚመስሉ #ንግግሮች በሰዎች ላይ ከባድ ተፅእኖን ይፈጥራሉና ዘወትር መልካም ንግግር እንናገር።

#የጥላቻ_በር_ይዘጋ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Fake Pages Alert‼️

ከላይ በምስሉ ላይ የ'ራይት' ምልክት የተደረገበት(ከ28ሺ በላይ ተከታይ ያለድ ገፅ) ትክክለኛው የጉለሌ ፖስት ገፅ ሲሆን ሌሎቹ ፌክ ገፆች ናቸው።

Via Gulale Post
https://www.facebook.com/Elias-Meseret-517243322140049/
@tsegabwolde @tikvahethiopia