TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
214 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አዳማ🔝

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #ዐቢይ_አሕመድ የ7ኛው የኢፌዲሪ ሀገር መከላከያ ሰራዊት ቀን ክብረ በዓል ወቅት በሰራዊቱ ያላቸውን ኩራት ገልፀዋል።

ጠ/ሚሩ በጦር ኃይሉ ውስጥ ግልጽነትና ሌሎች ክፍተቶችን ለመሙላት የተከናወኑ ዋና ዋና ለውጦችን በማንሳት የተመዝገበውንም ከፍተኛ ለውጥ አበረታች መሆኑን ገልጸዋል።

በዋናነትም ቁልፍ የሆነው የለውጡ መለያም ከፖለቲካ ወገንተኝነት የፀዳ ሙያዊ ብቃት ያለው ሰራዊት መገንባት ነው። መከላከያ ሰራዊቱን ከማዘመንና በሞያ ከማብቃት ጎን ለጎንም ጠ/ሚሩ የኢትዮጲያ ወጣቶች የጦር ሰራዊቱን #ዘመናዊ_ተቋማት_ግንባታና #የቴክኖሎጂ ልህቀት እርምጃ እንዲያግዙ ጥሪ አቅርበዋል።

ምንጭ፦ የጠ/ሚ ፅ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"የመከላከያ ሰራዊቱ #ለጠላቶች የፍርሃት፤ ለኢትዮጵያውያን ደግሞ #የኩራት ምንጭ ነው"- ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር #አብይ_አህመድ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
7ኛው የመከላከያ ቀን🔝ተጨማሪ ፎቶዎች ዛሬ #በአዳማ ከተማ የተከበረው 7ኛው መከላከያ ሰራዊት ቀን!

ፎቶ፦ የጠ/ሚ ፅ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
‹‹እየተገነባ ያለው #የመከላከያ_ሠራዊት ዛሬ የሁሉንም #ሉዓላዊነት የሚጠብቅ ነገ ደግሞ የሕዝብ ውክልና አግኝታችሁ ሥልጣን የምትይዙ ተረክባችሁ የምታስቀጥሉት ተቋም ነው›› ጠቅላይ ሚኒስትርና የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ዶክተር #ዐብይ_አህመድ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ የፖላንድ አምባሳደር ሚስተር አሌክሳንደር ክሮፕዊንኪን ተቀብለው አነጋገሩ፡፡ በኢትዮጵያ እና በፖላንድ መካከል የሁለትዮሽ ግንኙነት በሚጠናክርባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር አድርገዋል፡፡

ምንጭ:- የፕሬዝዳንት ፅ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
‹‹ሠራዊቱ አሁንም #መስዋትነት እየከፈለ የዜጎችን ሰላም እና ደኅንነት ለማረጋገጥ እየሠራ ነው፡፡›› ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል ሰዓረ መኮንን
.
.
የኢፌዴሪ ሀገር መከላከያ ሠራዊት ቀን ለ7ኛ ጊዜ በአዳማ ከተማ ተከብሯል፡፡ በበዓሉ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የኢፌዴሪ ሀገር መከላከያ ሠራዊት ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል #ሰዓረ_መኮንን ‹‹በዓሉን የምናከብረው በትግል መስዋትነት ከፍለው ያለፉ ሠራዊቶችን ለመዘከር፣ በክብር ለተሰናበቱት ክብር ለመስጠት እና በማገልገል ላይ ያሉ ሠራዊቶችን ለማሰብ ነው›› ብለዋል፡፡

የመከላከያ ሠራዊት ቀን ሠራዊቱ ሕገ-መንግሥታዊ ቃሉን የሚያድስበት እና ሕዝባዊ ወገንተኝነቱን የሚያጠናክርበት እንደሆነም አስታውቀዋል፡፡ ለተጀመረው ተስፋ ሰጪ ሀገራዊ ለውጥ የመለከላከያ ሠራዊት ግንባር ቀደም ባለቤት ሆኖ በተቋማዊ ለውጥ ውስጥ እንደሚገኝም ተገልጿል፡፡ ቀጣይነቱን ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት እንደሚሠሩም ጀኔራል ሰዓረ አረጋግጠዋል፡፡

ኢትዮጵያ ከኤርትራ ጋር የጀመረችው ሰላማዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንዲጎለብት የመከላከያ ሠራዊት የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ እንደሆነና ወደፊትም አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡

የመከላከያ ሠራዊት አሁንም መስዋትነት እየከፈለ የዜጎችን ሰላም እና ደኅንነት ለማረጋገጥ እየሠራ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

በበዓል አከባበሩ ላይ የጅቡቲ፣ የኬንያ፣ የሱዳን፣ የደቡብ ሱዳን፣ የቡሩንዲ፣ የሩዋንዳ እና የሌሎች ጎረቤት ሀገራት የመከላከያ ሠራዊት ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡

ምንጭ፦ AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia