TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ግብር

የግብር ግዴታቸውን ለመወጣት የሄዱ ጠበቆች ነጋዴ የሚያቀርበውን ሂሳብ መዝገብ ካላቀረባችሁ አትስተናገዱም በሚል መጉላላት እየደረሰባቸዉ ነው።

የኢትዮጵያ ፌዴራል ጠበቆች ማሕበር የበጀት ዓመቱን የግብር ግዴታቸውን ለመወጣት የሄዱ ጠበቆች " ነጋዴ የሚያቀርበውን ሂሳብ መዝገብ አይነት ከተመዘገበ ካፒታል ጋር ካላቀረባችሁ አትስተናገዱም " በሚል መጉላላት እየደረሰባቸው እንደሚገኝ አስታውቋል።

ቅሬታዉን ለፍትህ ሚኒስትር ያቀረበዉ ማህበሩ  ከጥብቅና አገልግሎት አሰጣጥ እና ከግብር አከፋፈል ጋር በተያያዘ በተደጋጋሚ ሲያጋጥም የቆየውን ችግር በዘላቂነት እንደሚቀርፍ የታመነበት ዝርዝር መመሪያ ሳይወጣና በሥራ ላይ እንዲውል ሳይደረግ የ2016 በጀት ዓመት የግብር መክፈያ ወቅት ተጀምሯል ብሏል።

ይህን ተከትሎ ፍትህ ሚኒስትር ለገንዘብ ሚኒስትር እና ለአዲስ አበባ ከተማ ገቢዎች ቢሮ ደብዳቤዉ ጽፏል።

በዚህም የጠበቆችን ታክስ አከፋፈል በተመለከተ ዝርዝር መመሪያ ወጥቶ ችግሩ ወጥ በሆነ መልኩ በዘላቂነት እስከሚፈታ ድረስ ከዚህ ቀደም በነበሩ ዓመታት ሲስተናገዱበት በቆየው ነባር አሰራር የ2016 በጀት ዓመት የግብር ግዴታቸውን እንዲወጡ እንዲደረግ ጠይቋል።

በዚህ ምላሽ ሊያገኙ እንደሚችል በተገለፀበት ደብዳቤ  ጠበቆች " ነጋዴ የሚያቀርበውን ሂሳብ መዝገብ አይነት ከተመዘገበ ካፒታል ጋር ካላቀረባችሁ አትስተናገዱም " በሚል የሚደርስባቸዉን መጉላላት ሊቀርፍ ይችላል የሚል እምነት ተጥሎበታል።

#CapitalNewspaper #Ethiopia

@tikvahethiopia
#ግብር

🔴 " አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ አዲስ መመሪያ አውጥቶ መክፈል የማንችለውን ግብር እየጠየቀን ነው " - መኪና አስመጪዎች

🔵 " የግብር ስወራው ተጨባጭ እንደሆነ በሸጡት መኪና ልክ ዋጋ እንደማይቆረጥ የተረጋገጠ ነው " - የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ

በአዲስ አበባ ከተማ ያሉ ተሽከርካሪ አስመጪዎች፣ " በ2015 ዓ/ም ተጠንቶ ተግባራዊ እንዳይሆን በሚል ቆይቶ ነበር " የተባለ መመሪያ ተግባራዊ በማድረግ የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ከአቅም በላይ የሆነ ግብር እየጠየቃቸው መሆኑን በመግለጽ ቅሬታቸውን በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል አሰምተዋል።

" በ2015 ዓ/ም ነበር ጥናቱ የተጠናው ፤ ከዛ 'ተግባራዊ አይሁን፣ ትክክል አይደለም' ተብሎ የተቀመጠ ጥናት ነው አሁን መመሪያ ተደርጎ በትዕዛዝ የወረደው " ሲሉ ነው የተናገሩት።

አስመጪዎቹ ስለዝርዝር ቅሬታቸው ምን አሉ ?

" አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ አዲስ መመሪያ አውጥቶ መክፈል የማንችለውን አላስፈላጊ ግብር እየጠየቀን ነው። ይሄን የሚያደገው 'ሲስተም አዘጋጅቻለሁ' በሚል ነው።

አዲሱ ሲስተም የስሪት፣ የተመረተበትና የመጣበት አገር ይጠይቃል፣ በጥናት መልክ ተዘጋጅቶ ተግባራዊ እንዲሆን ብሎ በአዲስ አበባ በሁሉም ቅርንጫፎች ኤክስኤል ሰርቶ አውርዶ ሥሩ ብሏል።

'ከጉምሩክ ዴክላራሲዮን ላይ ሒሳቡ ሲሰላ ከ45 በመቶ በላይ የሆነ ትርፍ እያተረፋችሁ ነው’ በሚል ነው አዲስ አሰራር ያመጣው።

ይህ መመሪያ ከገቢዎች ሚኒስቴር የተለዬ፣ ፌደራልና ክልል ላይ የሌለ፣ በአዲስ አበባ ብቻ፣ የመኪና አስመጪዎችን ብቻ በተመለከተ የተዘጋጀ መመሪያ ነው።

በዚህ መመሪያ መሠረት የተጠየቅነው
ግብር አላስፈላጊ፣ ከህግ አግባብ ውጪ የሆነ ነው። ምክንያቱም ግብር በህግ ነው እንጂ በጥናት አይደለም የሚከፈለው። 

ግብር ሲከፈል ህግ ተረቆ፣ በተወካዮች ምክር ቤት ጸድቆ ነው። ለአዲስ አበባና ለድሬዳዋ ከተማ አስተዳደሮች የግብር መመሪያ የሚያወጣው  ደግሞ ገቢዎች ሚኒስቴር ነው።

ይሄን አዲስ መመሪያ ግን የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ በራሱ በደብዳቤ መልኩ ነው ወደታች ያወረደው ከአሰራር ውጪ በሆነ መልኩ


እስከዛሬ ጉምሩክ ባስቀመጠው መሠረት ከፍተኛው ጣራ 9% ተደርጎ እኛም 4ም፣ 5ም% አተረፍን ብለን አቅርበን ነበር የምንፈፍለው።

አሁን ግን ቢሮው ሌላ የራሱን ሰንጠረዥ አዘጋጅቶ ለ11ዱም ክፍለ ከተሞች ይህንን መመሪያ አወረደ በትዕዛዝ መልክ። መመሪያው የወረደው ‘ከ45 በመቶ በላይ እያተረፋችሁ ነው የዚህን
ግብር ክፈሉ’ በሚል ነው።

ከዚህ ቀደሙ
ግብር ጋር ሲነጻጸር 5% አትርፌአለሁ ብለሸ አሳውቆ ግብር ሲከፍል የነበረን ሰው ‘45% ታተርፋለህ’ ማለት በጣም ብዙ እጥፍ ነው። የህግ አግባብ የለውም አሰራሩ። 

በፌደራል ደረጃ ንግድ ፈቃድ አስመጪዎች ያላቸው መኪና መሸጫ አላቸው። የእነርሱ በኖርማሉ ነው፣ እነርሱን አይመለከትም መመሪያው። ክልል ያሉትንም በተመሳሳይ አይመለከትም። 

አዲስ አበባ ውስጥ ሆነው ክፍለ ሀገርም ሆነው የክፍለ ሀገር ፈቃድ አውጥተው (ለምሳሌ የክልል፣ የፌደራል ፈቃድ ያላቸው) ከኛ ጋር ተመሳሳይ መኪና የሚሸጡ አሉ።

እነርሱን ግን ይሄ አዲሱ የግብር መመሪያ አይመለከትም። አንድ ከተማ ውስጥ ተመሳሳይ አይነት መኪና እየሸጡ እያሉ
ይሄ ትልቅ ልዩነት ነው የሚያመጣው።

የፌደራል ገቢዎች የማያውቀውን ተመን እንዴት አንድ የከተማ አስተዳደር በራሱ ያወጣል? ይሄ አሰራር የህግ ግራውንድ የለውም። ቅሬታችን ይሰማልንና ትግበራው ይስተካከልልን”
ብለዋል።

አዲስ አበባ ያሉ ተሽከርካሪ አስመጭዎች ከዚህ ቀደም ያልነበረ አሰራር ወርዶ ከመጠን ያለፈ ግብር ተጠየቅን ለሚለው ቅሬታቸው ያላችሁ ምላሽ ምንድን ነው ? ስንል ለአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ጥያቄ አቅርበናል።

የቢሮው ኃላፊ አቶ ቢኒያም ምክሩ ምን ምላሽ ሰጡ?

" በሚቆረጠው ደረሰኝና ገበያ ላይ ባለው ዋጋ መካከል ያለው ልዩነት በጣም ሰፊ ነው፡፡ ይህንን ለማስተካከል ነው ጥናቱ የተጠናው።

የግብር ስወራው ተጨባጭ እንደሆነ በሸጡት መኪና ልክ ዋጋ እንደማይቆረጥ የተረጋገጠ ነው።

ምንም የተጣሰ የህግ ክፍተትም የለውም። ከተማው በማንዴቱ ነው የሰራው። ዋናው ዓላማ ግን ከፍተኛ የሆነ የታክስ ስወራ ስላለ ያን ለማስቀረት ነው።

ከተማው ማንኛውም መኪና የሚገዛ ሰው ስንት ብር ነው የገዛው? በትክክል በገዛውና በከፈለው ገንዘብ ልክ ደረሰኝ ተሰጥቶታል ወይ? በስት አካውንት ነው ገንዘብ እንዲያስገባ የሚጠየቀው? የሚለው የአደባባይ ምስጢር ነው። 

ስለዚህ የግብር ስወራው ተጨባጭ እንደሆነ በሸጡት መኪና ልክ ዋጋ እንደማይቆረጥ የተረጋገጠ ነው።

እዚህ ላይ ልዩነት አለኝ የሚል ማንኛውም ሰው መጥቶ ልንወያይ እንችላለን በራችን ክፍት ነው "
ብለዋል።

(ኃላፊው፣ ቅሬታ አቅራቢዎቹ በገለጹት መሠረት ላቀረብንላቸው ጥያቄዎች የሰጡን ሙሉ ማብራሪያ በቀጣይ ይቀርባል)

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ግብር 🔴 " አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ አዲስ መመሪያ አውጥቶ መክፈል የማንችለውን ግብር እየጠየቀን ነው " - መኪና አስመጪዎች 🔵 " የግብር ስወራው ተጨባጭ እንደሆነ በሸጡት መኪና ልክ ዋጋ እንደማይቆረጥ የተረጋገጠ ነው " - የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ በአዲስ አበባ ከተማ ያሉ ተሽከርካሪ አስመጪዎች፣ " በ2015 ዓ/ም ተጠንቶ ተግባራዊ እንዳይሆን በሚል ቆይቶ ነበር " የተባለ መመሪያ ተግባራዊ…
#ግብር #ተሽከርካሪዎች

የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ከተሽከርካሪ አስመጪዎች ለቀረበበት ቅሬታ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጠው ሙሉ ምላሽ ምንድን ነው?

" አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ላይ ያሉ ዋና ዋና የሚባሉ የታክስ ስወራ አለባቸው የሚባሉ ዘርፎች ተለይተው ጥናት ተደርጓል፡፡

አንዱ ከቋሚ ንብረት፣ ከቤት፣ ከሪልስቴት ጋር ሽያጭ ጋር፣ ሌላው ደግሞ ከመኪና ጋር የተገናኘ ጥናት ነው፡፡ 

እነዚህ ጥናቶች 2015 ዓ/ም ተጠንተው ተጠናቀው 2016 ዓ/ም ሚያዝያ ጀምረው ተግባራዊ እንዲደረጉ በከተማ አስተዳደሩ ተወስኖ ሰርኩላር ተላልፏል፡፡ 

የቤትና መኪና ሻጮችን በተመለከተ ማለት ነው፡፡ የቤት ወዲያውኑ ተግባራዊ ተደርጓል፡፡ ከመኪናም ሽያጭ ጋር በተገናኘ የመኪና ሽያጭ በሚከናወንበት ጊዜ ሁለት ቢሮዎች ናቸው በዋናነት
ግብር የሚሰበስቡት፡፡ 

አንዱ የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ነው፡፡ ሁለተኛው ደግሞ በትራንስፖርት ቢሮ ውስጥ ያለው የከተማው የአሽከርካሪና ተሸከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ነው፡፡ 

በጥናት እንዲጠና የተደረገው  ከተማው የሚሸጡ ተሽከርካሪዎች የሚሸጡበት ዋጋና ተሸጠዋል ተብሎ ለገቢወዎች ቢሮ በሚቀርበው የገንዘብ መጠን መካከል በጣም ሰፊ የዋጋ ልዩነት በመኖሩ ነው።

ጥናቱን ከፌደራልም ከአዲስ አበባም የተለያዩ ባለሙያዎች ናቸው ያጠኑት፡፡ በገበያው ዋጋና ለገቢዎች ቢሮ በሚቀርበው ሪፖርት መካከል በጣም ሰፊ ሆነ የዋጋ ልዩነት እንዳለው ጥናቱ አሳይቷል።

10 ሚሊዮን ብር የሚሸጥ መኪና በ3 ሚሊዮን ብር፣ በ6 ሚሊዮን ብር የሚሸጥ መኪና በ1 ሚሊየን ብር እየሆነ ያለው፡፡ በሚቆረጠው ደረሰኝና ገበያ ላይ ባለው ዋጋ መካከል ያለው ልዩነት በጣም ሰፊ ነው፡፡  

ይህንን ለማስተካከል ነው ጥናቱ የተጠናው። ጥናቱ በወቅቱ የነበረውንም የዋጋ ግሽበት ከውጭ ምንዛሬ ጋር የተያያዘውንም ጉዳይ ግምት ውስጥ ያስገባ ነው። 

ስለዚህ ተግባራዊ መደረግ የነበረበት አምና ነው፡፡ 2016 ዓ/ም በዚሁ ነው መሰራት የነበረበት፡፡ ነገር ግን በተለያየ ምክንያት 2016 ዓ/ም ሳይተገበር ቆይቷል፡፡ 

ከተማ አስተዳደሩ ‘2016 አለመተግበሩ ትክክል አይደለም፡፡ በ2016 ዓ/ም የግብር ዘመን ላይ ተግባራዊ አልተደረገም፡፡ አሁን ግን የ2017 ዓ/ም
ግብር በሚከፈልበት ጊዜ ህጉ መከበር አለበት’ የሚል አሰራር ስለተቀመጠ ያንን አሰራር ነው የተገበርነው፡፡ 

በተከታታይ አስመጭዎቹ ሰዎችን ወክለው የሂሳብ ባለሙያዎቹ ጭምር መጥተው በተሰራው ፎርሙላ ላይ ቁጭ ብለን አንድ በአንድ ተወያይተናል፡፡ ተግባብተናል ብዙ ልዩነት አልነበረም።

በውይይታችን በተለይ ቴክኒካል የሆነውን ነገር የሒሳብ ባለሙያዎቻቸው ባሉበት ተወያይተን እነሱን የሚያከስር እንዳልሆነ ነገር ግን የግብር ስወራውን ለመከላከል የተዘጋጀ ፎርሙላ እንደሆነ ከውጭ ምንዛሬ ጋር ያለውንም ችግር ግምት ውስጥ እንዳስገባ በመድረኩ ላይ ተግባብተናል፡፡ 

አንድ ሰው መኪና ሲገዛ ደረሰኙን ይዞ ታርጋ ለመውሰድ ወይም ለማዞር በሚሄድበት ጊዜ አምና ጭምር መኪና ሻጮቹ የሰጡትን ደረሰኝ አሽከርካሪና ተሽከርካሪ ባለስልጣን ‘አልቀበልም’ እያለ በፎርሙላው መሰረት እየሰራ ትክክለኛውን እያሰላ ከመኪና ገዥዎቹ አስፈላጊውን ክፍያ ሲቀበል ነው የነበረው፡፡ 

ሻጮቹ የሸጡት የገንዘብ መጠን ገዢው ታርጋ ለመሸጥ በሚሄድበት ጊዜ ተቀባይነት እንዳላገኘ እዛ በትክክለኛው ዋጋ የስም ዝውውር እንደፈጸመ ያውቃሉ፡፡ ስለዚህ አምናም እነሱ ላይ አለመተግበሩ ካልሆነ በስተቀር አዲስ የመጣ ነገር አይደለም፡፡  

ምንም አስመጪዎቹን የሚጎዳ፣ የሚያከስር ነገር የለውም፡፡ በጣም መሠረታዊ ሚባሉ ጉዳዮችን ግምት ውስጥ ያስገባ አሰራር ነው፡፡

እንደ ጉዳት እየወሰዱት ያለው አምና ስንከፍል በነበረው አይነት ብቻ እንክፈል ለምን ተጨማሪ ክፍያ እንከፍላለን? ከሚል አስተሳሰብ የመነጨ ጥያቄ ነው፡፡ 
ይሄ ደግሞ ተቀባይነት የለውም፡፡ የታክስ ስወራን መከላከል ያስፈልጋል፡፡ የከተማ አስተዳደሩ በከተማው የሚሰራውን ይህን ሁሉ ልማትና ህዝብ ጥያቄ የሚመልሰው ከተማዋ ከምታመነጨው ገቢ ነው፡፡ 

እዚህ ገቢ ውስጥ የግብር ስወራውን የመከላከል የገቢዎች ቢሮ ኃላፊነት አለበት፡፡ የዋጋ ጥናትን በተመለከተ በግልጽ በታክስ አስዳደር አዋጁ ላይ ስልጣን ለገቢዎች ቢሮ ተሰጥቷል፡፡ ግልጽ ነው፡፡

አዋጁም ይሄ በዋናው የፌደራል የታክስ አስተዳደር አዋጅ የሚባል አለ በሱ አዋጅ ላይ በግልጽ የተቀመጠ፣ አንቀጽ 3 ላይ ለገቢዎች ቢሮ ተሰጠ ስልጣን አለ "
ብሏል።

አንዱ የአስመጪዎቹ ቅሬታ መመሪያውን ማውረድ ያለበት የገቢዎች ሚኒስቴር ነው እንጂ ቢሮው አይደለም የሚል ነውና የቢሮው ምላሽ ምንድን ነው ? ሲንል ለቢሮ ኃላፊው ተጨማሪ ጥያቄ አቅርበናል።

ምን ምንላሽ ተሰጠ ?

" አይ አይልም። የአዲስ አበባ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የተሰጠ ስልጣን በታክስ አስተዳደር ተቀምጧል። የፌደራል ግብር ከፋይ የሚባሉ አሉ። አዲስ አበባ ላይ ደግሞ የአዲስ አበባ ግብር ከፋይ አለ። 

በአዲስ አበባም ሆነ በየትኛውም የሀገሪቱ ክልል ላይ PLC የሆኑ ግብር ከፋዮች ለፌዴራል መንግስት ነው ግብር የሚከፍሉት። እነሱን የተመለከተ አሰራር ሊያወርድ ይችላል ፌደራል መንግስት። 

የአዲስ አበባ ከተማ ግብር ከፋዮችን በተመለከተ አሰራር መዘርጋት፣ ዋጋ ማጥናት፣ በዋጋ ጥናቱ መሰረት ግብር እንዲሰበስቡ የማድረግ ስልጣን ደግሞ ለከተማ አስተዳደሩ ገቢዎች ቢሮ መሆኑ በአዋጁ በግልጽ ተቀምጧል። "

" ግብር የሚከፈለው ህግ ወጥቶ በህግ ደረጃ ነው እንጂ ጥናት ተጠንቶ አይደለም፣ ይሄ ጥናት ደግሞ 2015 ዓ/ም ላይ ‘ተጠንቶ አይሆንም ትክክል አይደለም’ በሚል ነበር ቆይቶ የነበረው፣ አሁን ለአዲስ አበባ መኪና አስመጪዎች ብቻ በሚል ጥናትን መሰረት ተድርጎ የወጣ፣ ህግን መሰረት ያላደረገ ነው " የሚል ቅሬታም ቀርቧል። የቢሮው ምላሽ ምንድን ነው? ለሚለው ጥያቄ ምላሽ ትጥቷል።

ቢሮው በምላሹ ምን አለ ?

" በታክስ አስተዳደር አዋጁ ላይ በግልጽ የተቀመጠው በማንኛውም ምርት፣ አገልግሎት፣ ሽያጭ በሚከናወንበት በማንኛውም እቃ ላይ የገቢዎች ቢሮ ዋጋ ማጥናት፣ ዋጋን Set የማድረግ፣ በዚህ ዋጋን በመቀነስ የሚመጣን የግብር ስወራ ለመከላከል ዋጋ መተመን እና በዚያ መሰረት ግብር ማስከፈል እንደሚችል ተቀምጧል።  

ስለዚህ መመሪያም፣ ሌላ አዋጅም አያስፈልገውም አሰራር ብቻ ነው መዘርጋት የሚያስፈልገው። ይጠናል ያ የተጠናው ጥናት ወደ አሰራር ይቀየርና ተግባራዊ ይደረግ ተብሎ ለየቅርንጫፍ ይወርድና ነው ተግባራዊ የሚደረገው።  

ይሄ ነው አሰራሩ። ምንም የተጣሰ የህግ ክፍተትም የለው። ከተማው በማንዴቱ ነው የሰራው። "

(ገቢዎች ሚኒስቴር በጉዳዩ ዙሪያ ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ ከሆነ በቀጣይ የምናቀርብ ይሆናል)

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia