#update የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ህግን ተከትለው የሚሰሩ የሪል ስቴት አልሚዎችን እንደሚደግፍ ነገር ግን ህገወጥ የሆኑት ላይ #ዕርምጃ እንደሚወስድ አስታወቀ፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ትናንት ከሪል ስቴት አልሚዎች በመከሩበት መድረክ ላይ እንደተናገሩት፤ የሪልስቴት ዘርፉ የከተማውን የቤት ችግር ለመቅረፍ እንደ አጋዥ ፕሮጀክት የሚጠቅም መሆኑን ገልጸው፤ የከተማ አስተዳደሩ ህግን ተከትለው የሚሰሩ የሪል እስቴት አልሚዎችን እንደሚደግፍ ነገር ግን ህገወጥ የሆኑት ላይ ዕርምጃ እንደሚወስድም አሳስበዋል፡፡
Via epa
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via epa
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አራተኛው ዙር የህዝብና ቤት ቆጠራ‼️
አራተኛው ዙር የህዝብና ቤት ቆጠራ ሊጀመር መሆኑን የማዕከላዊ እስታስቲክስ ኤጀንሲ ገለጸ።
ቆጠራው የሚጀመረው ከመጋቢት 29 እስከ ሚያዚያ 20 ሲሆን ቤት ለቤት በመሄድ እንደሚደረግ ተገልጿል።
የማዕከላዊ አስታስቲክስ ዋና ዳሬክተር አቶ #ቢራቱ_ይገዙ እንደለጹት፣ ለቆጠራው የሚያስፈልጉ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ተጠናቀዋል።
የአሁኑን ቆጠራ ከሌሎች ጊዜያቶች ቆጠራ የሚለየው የዲጂታል ቴክኖሎጂን ተጠቅሞ ተግባራዊ የሚደረግ መሆኑ ነው ብለዋል።
ከዚህ ቀደም ቆጠራው ሲካሄድ በአርብቶ አደር አካባቢና በአንዳንድ የአገሪቱ አካባቢዎች ከተያዘው የመደበኛ ጊዜ ዘግይቶ የሚደረግ ሲሆን በአሁኑ ግን በተመሳሳይ ጊዜ ለማካሄድ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መጠናቀቃቸው ነው የተገለጸው።
በተጨማሪም ባለፉት የቆጠራ ጊዜያቶች አንድ ቋንቋ ብቻ በመጠቀም ቆጠረው ይካሄድ የነበረ ሲሆን በአሁኑ ገድሞ አምስት የክልል ቋንቋዎቸን በመጠቀም ቆጠራው እንደሚካሄድም ተጠቁሟል።
ለዚህም ስራ በሁሉም ክልሎች 1መቶ 82ሺህ በላይ ለሆኑ ባለሙያዎች ይሳተፋሉ ተብሏል ሲል የዘገበው ኢዜአ ነው።
ምንጭ፦ ኢዜአ

አሳ ዛኝ ዜና‼️
በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን ጃማ ወረዳ በጫነው አሸዋ ላይ 31 ሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ ሲኖትራክ ተሽከርካሪ ተገልብጦ የሰዎች ህይወት እና ንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱ ተገለፀ።
የጃማ ወረዳ ፖሊስ ጽህፈት ቤት የትራፊክ አደጋ መርማሪ እንደገለጹት ሲኖትራክ ተሽከርካሪው በቶ ከተባለ ስፍራ በጫነው አሽዋ ላይ 31 ሰዎችን አሳፍሮ ወደ ደጎሎ ከተማ በመጓዝ ላይ እያለ ነበር አደጋው ያጋጠመው።
ተሽከርካሪው በዛሬው እለት ከጠዋቱ 12 ሰዓት ገደማ 14 ቀበሌ ልዩ ቦታው ዝግባ ከሚባል ስፍራ ሲድርስ እስካሁን ባልታወቀ ምክንያት በግምት 60 ሜትር ከሚሆን ገደል ውስጥ በመግባቱ አደጋውም መከሰቱንም አስረድተዋል።
በአደጋው የ7 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በ13 ሰዎች ላይ ከባድ እንዲሁም በ11 ሰዎች ላይ ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱን ዋና ሳጅን ተስፋው ነጋ አስታውቀዋል።
ቀላል የአካል ጉዳት የደረሰባቸው በጃማ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ሲሆን ከባድ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው 13 ሰዎች ወደ ደሴ ሪፈራል ሆስፒታል ሪፈር መላካቸውን ዋና ሳጅን ገልጸዋል፡፡
ዋና ሳጅን ተስፋው አሸዋና ድንጋይ ላይ ሰዎችን መጫን እየተለመደ እየመጣ በመሆኑ በቀጣይ ባለሀብቶችና ሹፌሮች ከዚህ ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ማሳሰባቸውን ከጃማ ወረዳ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ምንጭ፦ fbc

Alert ቴፒ‼️
በቴፒ ከተማ ከትንላንት ጀምሮ ዳግም #ያገረሸው #አለመረጋጋት ዛሬም ቀጥሏል። ዛሬም በተለያዩ የከተማይቱ አካባቢዎች ተደጋጋሚ የጥይት ድምፅ እየተሰማ እንደሚገኝ በከተማው የሚኖሩ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ገልፀዋል። ነዋሪዎች በከተማው ያለው ውጥረት ወደ ሌላ ደረጃ ሳይሸጋገር የኢትዮጵያ መንግስት መፍትሄ እንዲፈልግ ጠይቀዋል። ከትላንት ጀምሮ በተፈጠረው አለመረጋጋት ሳቢያ ስለደረሰው ጉዳት የተረጋገጡ መረጃዎችን ሳገኝ ወደእናተ አደርሳለሁ።

የትራንስፖርት ታሪፍ ጭማሪ አልተደረገም‼️
ዛሬ በስራ ላይ የሚውለውን የነዳጅ ዋጋ መጨመር ተከትሎ ምንም አይነት #የትራንስፖርት_ታሪፍ ጭማሪ #እንደማይኖር የፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን ገለፀ።
የአዲስ አበባም ሆነ የክልሎች የትራንስፖርት ታሪፍ ባለበት እንደሚቀጥልም ባለስልጣኑ አስታውቋል።
በባለስልጣኑ የፖሊሲ ጥናትና የእቅድ ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ዳይሬክተር አቶ ፍስሃ መብራቱ እንደገለፁት፥ ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆነውን የነዳጅ ዋጋ ማሻሻያ ተከትሎ ምንም አይነት የትራንስፖርት ታሪፍ ጭማሪ አልተደረገም።
በህዳር ወር የነዳጅ ማስተካከያ በተደረገበት ወቅት የአገር አቋራጭ ትራንስፖርት ታሪፍ ላይ ማስተካከያ ስለተደረገና የአዲስ አበባውም የዛሬ አመት አካባቢ መሰረታዊ ማስተካከያ ያደረገ ስለሆነ የሚኖር ማስተካከያ አለመኖሩን ነው ያስታወቁት።
የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ አካላት ይህንን አውቀው ምንም አይነት ጭማሪ ማድረግ እንደሌለባቸው ባለስልጣኑ ማሳሰቢያ ሰጥቷል።
ህብተረተሰቡ በቀድሞው ታሪፍ መሰረት የአገልግሎት ክፍያውን እንዲፈፅም አሳውቀዋል።
የንግድ ሚኒስቴር ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ የነዳጅ ምርቶች መሸጫ ዋጋ ላይ ማስተካከያ ማድረጉ ይታወቃል።

ማስታወሻ🗓ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር #አብይ_አህመድ በነገው እለት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው የምክር ቤት አባላት ለሚያቀርቡላቸው ጥያቄዎች #ማብራሪያ ይሰጣሉ።
Via elu
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via elu
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የተቃውሞ ሰልፉ ሳይካሄድ ቀረ‼️
በቅርቡ በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት የጸደቀውን የስደተኞች አዋጅ #በመቃወም በጋምቤላ ክልል ተወላጆች ዛሬ በአዲስ አበባ ይካሄዳል ተብሎ የነበረው ሰልፍ ፍቃድ ባለማግኘቱ ሳይካሄድ ቀርቷል። ረፋድ 3፡30 ገደማ ከ35 እስከ 40 የሚሆኑ የጋምቤላ ክልል ተወላጆች በመስቀል አደባባይ ቢሰባሰቡም ፍቃድ ያገኙበትን ደብዳቤ ለጸጥታ አስከባሪ ፖሊሶች ማቅረብ ባለመቻላቸው ወደ ቤታቸው ተመልሰዋል። የጸደቀው አዋጅ በጋምቤላ ክልል ከፍተኛ ስጋት መፍጠሩ እና፣ ህዝቡ ተወያይቶ #መግባባት ላይ ያልደረሰበት መሆኑ ሰልፍ ለማድረግ እንዲነሳሱ እንዳደረጋቸው በቦታው የጀርመን ድምፅ ራድዮብያነጋገራቸው ወጣቶች ተናግረዋል። በተመሳሳይ ዛሬ በጋምቤላ ከተማ ሊካሄድ የነበረው ሰልፍም የከተማ አስተዳደሩ አሁን ያለው የክልሉ የጸጥታ ሁኔታ ሰልፍ ለማድረግ የሚያስችል ባለመሆኑ ፈቃድ አልሰጥም በማለቱ አለመከናወኑን የጀርመን ድምፅ ራድዮ በስልክ ያነጋገራቸው የከተማዋ ነዋሪ #አረጋግጠዋል።
ምንጭ፦ የጀርመን ድምፅ ራድዮ

#update ጅቡቲ በተካሄደው 15ኛው የሚኒስትሮች የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ ላይ የተካፈሉ የኢትዮጵያ ልዑካን ከሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ። ፕሬዚዳንት #ኢስማኤል_ኡመር_ጌሌ ለልዑካን ቡድኑ በጅቡቲ ቤተ መንግስት አቀባባል አድርገውላችዋል። ልዑካኑ ከፕሬዚዳንቱ ጋር በነበራቸው ቆይታም በሁለተዮሽና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ መወያየታቸው ነው የተገለፀው። ከጥር 21 ቀን እስከ 23 ቀን 2011 ዓ.ም በጅቡቲ ሲካሄድ የቆየው15ኛው የሚኒስትሮች የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ በዛሬው ዕለት ተጠናቋል። በዚህ ስብሰባም በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ የሚመሩ ከአስር በላይ ሚኒስትሮችና ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ተሳትፈዋል።
ምንጭ፦ ኢ.ፕ.ድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምንጭ፦ ኢ.ፕ.ድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኦሮሚያ ክልል‼️
በኦሮሚያ ክልል ለመንግስት ሰራተኞች #አዲስ የስራ ምደባ እየካሄደ መሆኑን የክልሉ የፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ አስታወቀ።
የቢሮው ሀላፊ ዶክተር #ቢቂላ_ሁሪሳ በዛሬው እለት በሰጡት መግለጫ፥ አዲሱ የመንግስት ሰራተኞች ምደባ ያላቸውን #አቅም፣ #እውቀት እና #ስነ_ምግባርን መሰረት አድርጎ እየተካሄደ መሆኑን አስታውቀዋል።
በአዲስ መልክ በተዋቀሩ መስሪያ ቤቶች ውስጥም ሁሉም ሰራተኞች በሚመጥናቸው ስራ ዘርፍ ላይ ተወዳድረው እንዲመደቡ እየተደረገ መሆኑንም ሀላፊው ገልፀዋል።
ዶክተር ቢቂላ ሁሪሳ በመግለጫቸው፥ በፖለቲካው መስክ የመጣው ለውጥ ብቻ በሁሉም ደረጃ ያለውን የህብረተሰብ ክፍል ተጠቃሚ ማድረግ ስለማይችል የህዝቡ ፈጣን የሆነ አገልግሎት ለመስጠት የመንግስትን አደረጃጃት ከመሰረቱ ማስተካከል ለአንድ ዓመት በተደረገ ጥናት የመንግስት መስሪያ ቤቶች እንደ አዲስ እንዲደራጁ መደረጉን አንስተዋል።
አዲሱ አደረጃጀትም በመንግስት መስሪያ ቤቶች ውስጥ #መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት እቅድ ተይዞበት እየተሰራ ነው ብለዋል ሀላፊው።
በዚህም የመንግስት እና የህዝብን ሀብት በአግባቡ በመጠቀም ህዝቡ ቀልጣፋ አገልግሎትን በቅርበት እንዲያገኝ ለማድረግ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።
በአሁኑ ወቅትም እንደ አዲስ በተደራጁ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ውስጥ አቅምን፣ እውቀትን ፣ ችሎታን እና ስነ ምግባርን መሰረት በማድረግ እንዲሁም ግልጽ እና ተአማኒ በሆነ መልኩ የሰራተኞች ምደባ እየተካሄደ መሆኑንም ዶክተር ቢቂላ አስታውቀዋል።
እየተካሄደ ባለው የሰራተኞች ምደባ ማንኛውም ሰራተኛ ከመንግስት ስራ ውጭ #እንደማይሆን የገለጹት ሀላፊው፥ ሰራተኞች በአግባቡ እንዲሰሩና እና ውጤታማ በሚያደርጋቸው የስራ መስክ ላይ እንደሚመደቡን ገልፀዋል።
“ማንኛውም ሰራተኛ ከስራ ውጭ ልሆን እችላለሁ የሚል #ስጋት_ሊገባው_አይገባም” ያሉት ዶክተር ቢቂላ፥ ምደባው እስኪጠናቀቅ ድረስም ባሉበት ሆነው በትእግስት እንዲጠባበቁ መልእክት አስተላልፈዋል።
አዲሱ የመንግስት ሰራተኞች ምደባ እስከ ጥር 30 2011 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ እንደሚጠናቀቅም ገልፀዋል።
በአዲሱ ምደባ መሰረት የሚመደቡ የመንግስት ሰራተኞችም በአዲስ መንፈስ ለህዝቡ ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት በሚችሉበት ቦታ ላይ አቅጣጫና ስልጠና ከተሰጠ በኋላ ወደ ስራ የሚገባ መሆኑንም አክለው ገልፀዋል።

440 ተጠርጣሪዎች በነፃ ተለቀቁ‼️
#ኮማንድ_ፖስቱ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል 3 ወረዳዎች ላይ በቁጥጥር ስር ካዋላቸዉ 528 ተጠርጣሪዎች 440 የሚሆኑትን በነፃ አሰናበተ፡፡
ኮማንድ ፖስቱ በአሶሳና በባምባሲ ወረዳዎች እንዲሁም በማዖና ኮሞ ልዩ ወረዳ ለፀጥታ ችግር ምክንያት ናቸዉ ያላቸዉን 528 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ማዋሉ ይታወሳል፡፡
ከታህሳስ 11 2011 ዓ.ም ጀምሮ በቁጥጥር ስር ካዋላቸዉ ተጠርጣሪዎች መካከል 440 የሚሆኑት ማስረጃ ያልተገኘባቸዉ በመሆኑ በነፃ መለቀቃቸውን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሰላምና ፀጥታ ግንባታ ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ #ብርሃኑ_አየለ ለኢቢሲ ተናግረዋል፡፡
ከተለቀቁት መካከል 33ቱ ሴቶች ሲሆኑ የተቀሩት ወንዶች መሆናቸዉን አቶ ብርሃኑ ገልፀዋል፡፡
በነፃ የተለቀቁት ተጠርጣሪዎች በህገ መንግስት ዓለማዎች፣ መርሆችና ዕሴቶች እንዲሁም በአብሮነትና የሰላም ግንባታ ላይ የተሃድሶ ስልጠና ወስደዉ የተለቀቁ መሆናቸዉም ተገልጿል፡፡
ቀሪዎቹ ተጠርጣሪዎች 21 የሚሆኑት ማሰረጃ የተጠናቀቀባቸዉ ሲሆን 67 የሚሆኑት ተጠርጣሪዎች ደግሞ ጉዳያቸዉ በሂደት የሚጣራባቸዉ ናቸዉ ተብሏል፡፡
ምንጭ፦ etv

#update የአዋሽ ወልድያ ሃራ ገበያ የባቡር ፕሮጀክት የመጀመሪያው ምዕራፍ የሆነው ከአዋሽ እስከ ኮምቦልቻ ያለው 270 ኪሎ ሜትር የባቡር መንገድ ግንባታ 97 በመቶ #መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ገልጿል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia