TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.5K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ጠ/ሚር #ዐቢይ_አሕመድ በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያን እየጎበኙ ካሉት ከጀርመን ፌደራል ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ፍራንክ ዋልተር ስታይንማየር ልዑካቸውን ተቀብለው አነጋገሩ። ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ የጀርመን መንግስትን የቆየና ቀጣይነት ያለው የቴክኒክና የሞያ ዘርፍ ድጋፍ ያላቸውን አድናቆት ገልፀዋል። በማስከተልም በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ለተመዘገበው ስኬት ሶስት ዋና ዋና መሰረቶች ግለሰቦች፣ ሀሳቦች እና ተቋማት ላይ መሆኑን አካፍለዋል። ፕሬዝዳንት ፍራንክ ዋልተር ስታይንማየር በበኩላቸው የኢትዮ-ጀርመን ግንኙነት ወደ ለውጥና ትብብር ከፍ ማለቱን እና የእነዚህ ግንኙነቶችን #ለማጠናከር እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል።

ምንጭ፦ Office of the Prime Minister-Ethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ለኢፌድሪ ፕረዝዳንት ወ/ሮ ሳህለወርቅ ዘውዴ እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ም/ከንቲባ ታከለ ኡማ(ኢ/ር) የEuropean Tourism Academy Membership ሽልማት ሊሠጥ ነው፡፡

የአውሮፓ የቱሪዝም እና የንግድ ተቋም (European Council on tourism and trade) የአፍሪካ ህብረት እና የአለም አቀፍ ተቋማት መቀመጫ የሆነችውን አዲስ አበባ ከተማን "የአለም የባህል እና የቱሪዝም ከተማ" በማለት መምረጡን አሳውቋል፡፡

ተቋሙ አዲስ አበባ በአህጉር ደረጃ ባሳየችው አንፃራዊ ሰላም ፣ የተረጋጋ የንግድና ቱሪዝም እንቅስቃሴ በተጨማሪም በከተማዋ የአለም አቀፍ ተቋማት በየወቅቱ መበራከት ምክንያት ይህን ሽልማት ለመስጠት መወሰኑንም አሳውቋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ ላለው የተረጋጋ የንግድና ቱሪዝም ስርዓት መገንባት ላበረከቱት አስተዋፅዖም በEuropean Council on Tourism and Trade የሚሰጠውን "European Tourism Academic Member" የሚል ትልቅ የአባልነት እና የክብር ሽልማት ለኢፌዲሪ ፕረዝዳንት ለወ/ሮ ሳህለወርቅ ዘውዴ እና ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ታከለ ኡማ(ኢ/ር) ለማበርከት በቅርቡ ወደ አዲስ አበባ እንደሚመጣም ይጠበቃል ሲል የዘገበው የከንቲባ ጽህፈት ቤት ነው።

Via EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢትዮጵያ ክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ በ2011 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት 4 ሚሊየን 234 ሺህ 856 መቶ ተሸከርካሪዎች በማስተናገድ በአጠቃላይ ብር 124 ሚሊየን 578 ሺህ 594 መቶ ብር መሰብሰብ መቻሉን ከትራንፖርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዙ በቀን አማካይ 677,057.57 ብር መሰብሰብ ችሏል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወላይታ ሶዶ🔝

#አለን_ኢትዮጵያ የበጎ-አድራጎት ድርጀት የሰው ልጆች የለውጥ ማዕከል ህጋዊ እውቅና በማግኘት ትላንት በ19/05/01 ዓ.ም በወላይታ ሶዶ ከተማ በይፋ ሥራ ጀመረ።

"በጎ ሥራ በመስራት የህሊና እረካታ እናግኝ!!" በሚል መር ቃል አቅም ለሌላቸው አረጋዊያንና ጎዳና ተዳዳሪ ህጻናት ድጋፍ አደረገ፡፡

የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ም/ከንቲባ አቶ ሐንጀሎ ደሴ በመክፈቻው እንደተናገሩት ወላጅ አጥ የሆኑትንና አቅመ ደካማ አረጋዊያንን ማገዝ የዕቅዳችን ዋና ዐላማ ስሆን ይህን መልካም ተግባር በራሳቸው ፍቃድ በመደራጀት እየመሩ አሁን ላለበት ቁመና ያደረሱ ወጣቶችንና ባለድርሻ አካላትን ከልብ እያመሰገንኩ በቀጣይ ይህ ዛሬ በማዕከል ደረጃ አድጎ "አለን ኢትዮጵያ የሰው ልጆች የለውጥ ማዕከል" በምል የበጎ አድራጎት ድርጅት ሆኖ ሥራ መጀመሩን አበስራለው።

የዝህ ድርጅት ዋና ዓላማ በተደራጀ አግባብ ቀጣይነት ባለው መልክ ይህን መልካም ተግባር ለመደገፍ ታስቦ የተቋቋመ ስሆን ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆንና በየደረጃው ካሉ አመራሮች ጋር ሆነን ይሄን መዋቅር ለመደገፍ ብሎም ከከተማ አስተዳደር የሚጠበቀውን የትኛውንም ድጋፍ ለማገዝ ቃል እየገባው ይህ መልካም ተግባር በሁሉም ህብረተሰብ ዘንድ ልለመድ ይገባል ስል መልክቱን አስተላልፈዋል።

አቅመ ደካማ የሆኑ አረጋዊያንና ህፃናትን በየአካባቢው ህብረተሰቡ ሊደግፏቸውና ሊንከባከቧቸው እንደሚገባ ብሎም ሁሉም የህብረተሰብ አካል የዝህ ድርጅት አባል በመሆን የዜግነት ድርሻውን እንድወጣ የድርጅቱ ኃላፍ ወጣት ዘገየ ወርቁ ተናግረዋል፡፡

ምንጭ፦ ተስፋማርያም(አለን ኢትዮጵያ)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ተማሪዎች አስተማሪያቸውን #በመግደል ተጠርጥረው ተያዙ‼️

ሦስት ተማሪዎች #ሞባይል ተወስዶብናል በሚል ሰበብ በአስተማሪያቸው ላይ ከተፈጸመ ግድያ ጋር በተያያዘ ኬንያ ውስጥ ተይዘው #ታሰሩ

#ናኩሩ በተባለው የኬንያ ግዛት ሆፕዌል በተሰኘው ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የፊዚክስ መምህር የሆኑት ፒተር ኦማሪ በተማሪዎቹ ጥቃት የተፈፀመበት ባለፈው ሳምንት መጠናቀቂያ ላይ ነበር።
ተማሪዎቹ ቢያንስ አንድ ሞባይል በትምህርት ቤቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ ይዘው በመገኘታቸው በመምህሩ ተወስዶብናል በሚል ነው ድርጊቱን እንደፈፀሙ የተነገረው።

ለሥነ ሥርዓትና የፈተና ኩረጃን ለመከላከል ሲባል በኬንያ በርካታ ትምህርት ቤቶች ውስጥ የሚገኙ ተማሪዎች ሞባይል እንዳይዙ ይከለክላል።

ባለስልጣናት ለቢቢሲ እንደተናገሩት ጥቃቱ በተፈጸመበት ዕለት መምህሩ በሚያስተምሩበት ትምህርት ቤት ውስጥ የምሽት ትምህርትን #እያስተባበሩ ነበር።

የአካባቢው ምክትል አስተዳዳሪ ኤሊም ሻፊ እንደተናገሩት ከኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ 150 ኪሎ ሜትር ሰሜን ምዕራብ ርቃ በምትገኘው የናኩሩ ከተማ፤ መምህሩ በትምህርት ቤቱ ቅጥር ጊቢ ውስጥ ወደሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ሲሄዱ ነው ጭቅላታቸው ላይ ተመትተው ለሞት የበቁት።

ኬንያ ውስጥ በመምህራንና በትምህርት ቤቶች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች እየጨመሩ በመሆናቸው የሃገሪቱን ባለስልጣናት በእጅጉ እያሳሰበ ነው።

ባለፈው የፈረንጆች ዓመት በምዕራባዊ ኬንያ በምትገኘው ኪሱሙ ውስጥ አንድ መምህር ከተማሪዎቹ ጋር ጠንከር ያሉ ቃላትን ከተለዋወጠ በኋላ በተማሪዎቹ በገጀራ ተመትቶ ለሞት ተዳርጓል።

ከሁለት ዓመት በፊት ደግሞ ኪሲ በተባለ ቦታ የሚገኝ የአንድ አዳሪ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የአውሮፓ እግር ኳስ ዋንጫ ውድድርን የቀጥታ ሥርጭት በቴሌቪዥን እንዳይከታተሉ በመከልከላቸው መኝታ ክፍላቸውን በእሳት አውድመውት ነበር።

ምንጭ፦ BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዲስ አበባ🔝

ከጅግጅጋ ከተማ የመጡ የከተማው ነዋሪዎች ባሳለፍነው ቅዳሜ ከጥዋቱ 3 ሰዓት ጀምሮ አዲስ አበባ በሚገኘው ዋልታ ቴሌቪዥን ድምፃቸውን ሲያሰሙ ውለዋል።

©Daw(TIKVAH-ETH)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ለሼህ አላሙዲ #መፈታት የጠቅላይ ሚንስትሩ አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነበር" አቶ ተካ
.
.
በትውልድ ኢትዮጵያዊ እና የሳዑዲ ዜግነት ያላቸው ቢሊየነሩ ሼህ ሞሐመድ ሁሴን አሊ-አላሙዲ ትናንት ከእስር ከተለቀቁ በኋላ ከሪያድ ወደ ጅዳ በማቅናት ከቤተሰባቸው ጋር ተቀላቅለዋል።

የሳዑዲ መንግሥት ያካሄደውን የፀረ-ሙስና ዘመቻን ተከትሎ ከበርካታ ንጉሣዊ ቤተሰቦች እና ከበርቴዎች ጋር ተይዘው ከ14 ወራት በላይ በእስር ያሳለፉት አላሙዲ እንዲፈቱ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከታቸውን ጠበቃቸው አቶ ተካ አስፋው ለቢቢሲ ተናገረዋል።

አቶ ተካ ''ትናንት (እሁድ) በስልክ ተገናኝተናል። ጤናቸው በጣም ጥሩ ሁኔታ ላይ ይገኛል። ከቤተሰቦቻቸው ጋርም ተቀላቅለዋል'' ያሉ ሲሆን ወደ ኢትዮጵያ መቼ ሊመጡ ይችላሉ ተብለው ለተጠየቁት ''ወደ ኢትዮጵያ መምጣቸው አይቅርም፤ ነገር ግን መቼ እንደሚመጡ በእርግጠኝነት መናገር አልችልም'' ሲሉ የአላሙዲ ጠበቃ አቶ ተካ አስፋው ተናግረዋል።

ካለፈው ግንቦት 2009 ዓ.ም ጀምሮ አሊ-አላሙዲ ከእስር እንዲፈቱ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ጥረቶችን ሲያደርጉ እንደቆዩ የሚናገሩት አቶ ተካ ''ጠቅላይ ሚንስትራችን ከአንዴም ሁለቴ ቦታው ድረስ ተገኝተው ከሳዑዲ ባለስልጣናት ጋር ውይይት አድረገዋል። ከዚያም በኋላ በነበራቸው ግንኙነት ከፍተኛ ጥረት እንዳደረጉ ነው የምናውቀው። ለመፈታታቸው የእሳቸው ጥረት እንዳለበት ነው የተረዳነው'' ብለዋል።

የጠቅላይ ሚንስትሩ ጽ/ቤት የፌስቡክ ገጽ የባላሃብቱን ከእስር መፈታት ይፋ ባደረገበት ጽሁፍ፤ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ግንቦት 2010 ዓ.ም ሞሐመድ ሁሴን አሊ-አላሙዲ ከእስር ለማስፈታት ጥረት እየተደረገ መሆኑን እና በቅርቡም ወደ አገራቸው ይመለሳሉ በማለት በሚሊኒያም አደራሽ ያደረጉትን ንግግር አስታውሷል።

የጠቅላይ ሚንስትሩ ጽ/ቤት ጨምሮም አሊ-አላሙዲ በሰላም እንዲመለሱ መልካም ምኞታችንን አንገልጻለን በማለት አስፍሯል።

ከ14 ወራት በፊት ከአላሙዲ ጋር በሙስና ወንጀሎች ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር ውለው ከነበሩት መካከል ጥቂት የማይባሉ ከበርቴዎች መጠኑ በይፋ ያልተገለጸ ነገር ግን ካላቸው ሃብት ከፍተኛ መጠን ያለውን ገንዘብ ለሳዑዲ መንግሥት ሰጥተው ከወራት በፊት ከእስር መውጣታቸው ይታወሳል።

ከዚህ አንጻር ሼህ አላሙዲንም ከእስር ለመፈታት #ከፍተኛ ገንዘብ #ከፍለዋል ወይ ተብለው የተጠየቁት ጠበቃቸው አቶ ተካ ''ከፍለዋል ብዬ ለመናገር ይከብደኛል። የተፈቱበትን አኳኋን ዝርዝር ሁኔታ ሰለማላውቅ ይሄ ነው ብዬ መናገር አልችልም። እኔ ግን ከፍተኛ ገንዘብ ከፍለዋል ብዬ አላምንም። ጠቅላይ ሚንስትሩ ግን ለመፈታታቸው የማይናቅ አስተዋጽኦ አበርክተዋል'' ብለዋል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia