TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.2K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
እንኳን አደረሳችሁ!!

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ ለክርስትና እምነት ተከታዮች ያስተላለፉት መልዕክት።

መልካም የገና በዓል።

#PMOEthiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የሚኒስትሮች ም/ቤት ታሕሳስ 27 ቀን 2011 ዕለት ባካሄደው 60ኛ መደበኛ ስብሰባ በአስር የተለያዩ ስምምነቶችና በማጽደቂያ ረቂቅ አዋጆች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ።

ምንጭ:- ጠ/ሚ ጽ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በትግራይ ክልል ምዕራባዊ ዞን ዳንሻ ከተማ አካባቢ ያረፈች የአየር ሀይል ሊኮፍተር በአካባቢው ወጣቶች ታግታ ነበር ወጣቶቹ ሂሊኮፍተሯ በአካባቢው ያረፈችበት #ምክንያት እንዲነገራቸው በመጠየቃቸው ነው ሂሊኮፍተሯ የታገተችው። ነገር ግን ከአካባቢው ባለስልጣናት ጋር ውይይት ከተደረገ በኅላ ሂሊኮፍተሯ በሰላም ተለቃለች።

ምንጭ፦ ኢትዮጵያ ላይቭ ሀፕዴት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፌደራል ፖሊ ስ‼️

በአንዳንድ አካባቢዎች የሚነሱ ግጭቶችን ከሕብረተሰቡ ጋር #በመወያየትና #በመተማመን ለመፍታት ጥረት እየተደረገ መሆኑን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጄነራል #እንዳሻው_ጣሰው ለኢዜአ እንደገለጹት ፖሊስ በተለያዩ ቦታዎች የሚነሱ ግጭቶችን ለማስቆም እርምጃ ከመውሰድ ይልቅ በውይይቶች እንዲፈቱ እያደረገ ነው።

በአንዳንድ ቦታዎች ግጭቶች ሲፈጠሩ ከመስመር የወጡና የተበላሹ ጉዳዮች እንዲስተካከሉ ለማድረግ በየደረጃው ውይይቶች እየተካሔዱ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ሕዝቡን ወዳልተፈለገ አቅጣጫ የሚመሩ አካላት እንዲስተካከሉም በየደረጃው የሚገኙ የፀጥታና ባለድርሻ አካላት እየሰሩ መሆኑንም ጠቁመዋል።

ይህ የሚሆነው እነዚህ ተሰሚነት ያላቸው አካላት ለህብረተሰቡ ቅርብ በመሆናቸው ችግሩ በእነርሱ አማካኝነት እንዲፈታና የተባባሰ ግጭት እንዳይመጣ መሆኑን አመልክተዋል።

በአሁኑ ወቅት በሕብረተሰቡና በፖሊስ መካከል መተማመንን የሚሸረሽሩ ተግባራትን ለመከላከል ለውጡን ተግባራዊ ማድረግ የግድ መሆኑን ጠቁመዋል።

የፌዴራል ፖሊስ ከሕብረተሰቡና በየደረጃው ካሉ የፀጥታ መዋቅር አደረጃጀት ጋር በመሆን ሰላምና ደሕንነት ለማስጠበቅ እየሰራ መሆኑን አንስተዋል።

በአንዳንድ አካባቢዎች ሕብረተሰቡን ነፃ ለማውጣት ነው የምንታገለው በማለት የሚንቀሳቀሱ አካላት መኖራቸውን ጠቅሰው ከተነሱበት ዓላማ ውጭ በሕገ-ወጥ መንገድ ወደ ዝርፊያ ሲገቡ መስተዋሉን ነው የጠቆሙት።

በተለያዩ ቦታዎች ፖሊስ ለሚያከናውነው ሰላምን የማስከበር፣ ሕገ-ወጦችን በቁጥጥር ስር የማዋልና ፀጥታ የማስፈን ስራ ሕብረተሰቡ ድጋፍ እያደረገ መሆኑንም አመልክተዋል።

በተለይ ሕገ-ወጥ የጦር መሳሪያ መስፋፋት ጋር ተያይዞ ሕብረተሰቡና ፖሊስ በሚያደርገው ክትትል አዘዋዋሪዎች በቁጥጥር ስር እየዋሉ ሲሆን ይሕ ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባው ጠይቀዋል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"መንግስት ሀገር መምራት አልቻለም፣ አቅም አጥሮታል፣ የምትሉ ወገኖች መግረፍና ማሰር ነው ያልቻልነው እንጂ መምራት የምንችልና ለውጥ ያመጣን መሆኑን ዓለም መስክሮልናል'' ጠ/ሚር ዶ/ር #ዐቢይ_አህመድ ከመላ ሀገሪቱ ከተውጣጡ መምህራን ጋር ባደረጉት ውይይት ከተናገሩት የተወሰደ...

@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለገና በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያለ በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር እና የጤና እንዲሆንላችሁ ይመኛል!!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዶ/ር አሚር አማን🔝

"ኮተቤ በሚገኘው ትምህርት ለተቸገሩ በጎ አድራጎት ማህበር በመገኘት እሁድን አብረን አሳልፈናል። ይህ ድርጅት ቤተሰቦቻቸው አቅም ለሌላቸው ህፃናት የነፃ ትምህርትና የምግብ እርዳታ እንዲሁም ለወላጆች የአቅም ግንባት ስልጠና እየሰጠ ያለ ነው።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዲስ አበባ ፖሊ ስ‼️

በዓሉ በሰላም እንዲከበር የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ለጸጥታ አካላቱ የተለመደ #ትብብሩን አጠናክሮ እንዲቀጥል የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጥሪ አስተላልፏል።

ህብረተሰቡ የፖሊስ አገልግሎትን ለማግኘትም ሆነ #አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙ ጥቆማ ለመስጠት በ991 ወይም 816 ነፃ የስልክ መስመሮችን እና 011-1-11 01 11፤011-1-26 43 59 011-1 01 02 97 ፤011-8-69 88 23፤011-8-69 90 15 መጠቀም እንደሚቻል ኮሚሽኑ አሰታቋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአቶ #ጌታቸው_አሰፋ ጉዳይ፡ ፖለቲካዊ ወይስ ሕጋዊ መፍትሄ?
.
.

የትግራይ ክልል አሳልፌ #አልሰጥም ቢል በቀጣይ ምን ሊከሰት ይችላል?

የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ አቶ ብርሃኑ ፀጋዬ አቶ ጌታቸውን ለመያዝ ሰው #መግደል የለብንም ማለታቸው ይታወሳል። አቶ #አብረሃም አቶ ጌታቸውን ለመያዝ የኃይል እርምጃ ሊወሰድ እንደማይገባ ይናገራሉ።

"አንድን ሰው ለመያዝ ተብሎ ወደ ጦርነት ይገባሉ ብዬ አላስብም የፌደራል መንግሥትም ፖለቲካውን ለማስተካከል ሲል ዝምታን ይመርጣል ፤ የትግራይ ክልልም የራሱን ህዝብ የራሱን ደህንነት ይጠብቃል ብየ አስባለሁ።" ይላሉ።


https://telegra.ph/የአቶ-ጌታቸው-አሰፋ-ጉዳይ-ፖለቲካዊ-ወይስ-ሕጋዊ-መፍትሄ-01-07