TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ቄሱ የአሲድ ጥቃት ተፈፀመባቸው‼️

በመካከላኛው አሜሪካ የኒካራጓ ዋና መዲና በሆነችው ማናጓ የ59 ዓመቱ ቄስ በተፈፀመባቸው የአሲድ ጥቃት ክፉኛ እንደተጎዱ ተዘገበ። ቄስ #ሚጌል_ጉቫራ ጥቃቱ የተፈፀመባቸው በሜትሮፖሊታን ካቴድራል ውስጥ አማኞች የሰሩትን ኃጢያት ኑዛዜ ተቀብለው ሲጨርሱ ነበር።

በአሲዱ ፊታቸው፣ ክናዳቸው ላይና ትከሻቸው አካባቢ ቃጠሎ ያጋጠማቸው ሲሆን የህክምና ክትትል እያደረጉ ይገኛሉ።

በወቅቱ በቤተክርስቲያኑ ውስጥ የነበሩ አምላኪዎች ፖሊስ በአፋጣኝ እስከሚደርስ አሲዱን በመወርወር የደፋችባቸውን ሴት በቁጥጥር ስር አውለዋታል።

ፖሊስ እንዳለው ጥቃት አድራሿ ጥቃቱን ለማድረስ ምን እንዳነሳሳት እያጣራ ሲሆን፤ የአገሪቱ መገናኛ ብዙሃን እንደዘገቡት ግን ጥቃት አድራሿ በማህፀን ውስጥ ያለ ሽል የተሳለበት ካናቴራ ለብሳ የነበረች የሩሲያ ዜጋ ናት።

ቤተክርስቲያኑ ፀረ መንግሥት እንቅስቃሴዎች መደረግ ከጀመሩበት ካለፈው ሚያዚያ ጀምሮ እንቅስቃሴውን በመግታት ረገድ የሚጫወተው ሚና እዚህ ግባ የሚባል አይደለም ተብሎ በመንግሥት ወቀሳ ሲደርስበት ቆይቷል። ጥቃቱም ሆን ተብሎ የተፈፀመ እንደሆነ ፖሊስ አስረድቷል።

በተቃዋሚዎችና በፀጥታ ኃይሎች መካከል በተፈጠረ ግጭት በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሕይወታቸው አልፏል፤ በዚህም ወቅት ቤተክርስቲያኗ ለመንግሥት ተቃዋሚዎች መሸሸጊያ ሆናለች በሚል በመንግሥት ደጋፊዎች ተከቦ ነበር።

ባለፈው የፈረንጆቹ ሐምሌ ወርም የኒካራጓ ቀሳውስት መንግሥትን ለመገልበጥ ለሚታገሉ ተቃዋሚዎች መጠጊያ ሆነዋል ሲሉ ፕሬዚደንት ኦርቴጋ ተችተዋል።

"ቀሳውስቱ መፈንቅለ መንግሥት ለማካሄድ አይተኙም" ሲሉም ፕሬዚደንቱ አክለው ተናግረዋል።

ምንጭ፦ BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለሚመለከተው አካል‼️

ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የድህረ ምረቃ ተማሪዎች።

የፍትሕ ጥያቄ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በተደጋጋሚ እኛ የድህረ ምረቃ ተማሪዎች ያነሳን ቢሆንም ምንም አይነት ተገቢ መላሽ እንልተገኘም፡፡

ነገሩ እንዲህ ነው፦

በመላው የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች የ A ውጤት መነሻ 85 እንደሆነ እየታወቀ ነገር ግን የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሴኔት ለድህረ ምረቃ ተማሪዎች ከ90 በላይ የሚል ፍታዊነት የጎደለው ህግ አውጥቶ ተማሪውን እየጎዳና ከተወዳዳሪነት እያገለለ ቆይቷል፡፡

ነገር ግን እኛ ተማሪዎች አግባብነት እንደሌለው ለማሳየትና የፍትሕ ጥያቄያችን ይመለስ በማለት ይህ ፍትሐዊነት የጎደለው ህግ ከወጣበት ጊዜ ጀመሮ ስንታገል ቆይተናል፡፡

ለአብነት ያክል እስከ ኢፌዴሪ ትምህረት ሚኒስተር (MoE) ድረስ ጥያቄው የሄደ ሲሆን ት/ት ሚኒስተሩ ችግሩን አምኖበት ጥያቄውን የዩኒቨርስቲው ሴኔት እንዲፈታው አቅጣጫ አስቀምጠው ነበር። ከብዙ ትግል በሁዋላ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ እራሱን ፈትሾ ችግሩን አምኖ የA መነሻን እንደሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ከ 85 እንዲጀመር አፀደቀ፡፡

በዚህን ጊዜ የድህረ ምረቃ ተመሪዎች ጥያቄና ቅሬታ ተፈታ ተባለ፡፡ እርግጥ ነው የኛ የ3 አመት ትግል ፍሬ አፍርቷል ነገረ ግን እንደገና የኛን የ ነባር የ ድህረ ምረቃ ተማሪዎች ስሜት የሚነካ ውሳኔ ተወሰነ፡፡

አዲስ የወጣው የውጤት አሰጣጥ ነባር የድህረ ምረቃ ተመሪዎችን(ጥያቄውን ስንጠይቅ የነበርነዉን) አያካትትም ሲባል እኛ ነባር የ ድህረ ምረቃ ተማረዎች ህዳር 26 ጥዋት ደማቅ ሰላማዊ ሰልፍ አካሄደን ከሰአት መድረክ ተዘጋጅቶልን የተወያየንበት ሲሆን አምባገነናዊ በሆነ መልኩ የሴኔቱን ውሳኔ ብቻ አንፀባርቀው የተመሪውን ቅሬታ ሳይቀበሉ ቀርተዋል(academic vice president)፡፡

ይሁን እንጂ የኛ ጥያቄ መልስ አሰከሚያገኝ ድረስ ወደ ሁዋላ አንልም።

ፍትህ ለሁሉም!!!
ከ ቅሬታ አቅራቢዎች ኮሚቴ።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ናሁ ቴሌቪዥን🔝የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባል የሆነው አርቲስት ደረጄ ዛሬ እሁድ ከቀኑ 8 ስዓት በናሁ እሁድ መዝናኛ ይቀርባል። የቻናላችን ቤተሰቦችንም ዝግጅቱን እንድታዩለት ጋብዟቹዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለሚመለከተው አካል‼️

አስቸኳይ መፍትሄ እንፈልጋለን!

በሰበታ አዋስ ወረዳ ቆርኬ ገበሬ ማህበር ወይንም ወጨጫ ማርያም አካባቢ ነዋሪዎች ሰሞኑን ሰላማችን ተቃውሷል ደሀው ዜጋ ጥርሱን ነክሶ አጠራቅሞ ከቤት ኪራይ ይሻለኛል ብሎ እዚህ ተራራ ላይ መኖር ከጀመረ አመታትን አስቆጥሯል ነገር ግን አሁንም ቤታችሁ ሊፈርስ ነው እያሉ ህዝቡን ሽብር ውስጥ ከተውታል እኛ እንኳን እዚህ ከመጣን ሰባተኛ አመታችን ነው አዳዲስ ነዋሪ ከመምጣቱ በፊት ሰፈሩ የቆርቆሮ አጥር እንኳ አያውቅም ነበር ገበሬው በፍቃዱ ቤት ሰርቶ የሸጠው መሬት ነው የቀበሌዎቹ ሰራተኞች እና ታጣቂዎችም በሙስና የተጨማለቁ ናቸው አንድ ቤት ሲሰራ ከ 20 እስከ 30 ሺ ብር ይቀበላሉ ሰባት አመት ስኖር መታወቂያ የለኝም አንድ መታወቂያ ለመስጠት እስከ 2 ሺ ብር እንደሚቀበሉ አውቃለሁ እኔም ተጠይቄ ነበር ነገር ግን ትቼዋለሁ ያ አልበቃ ብሏቸው አሁን ደሞ ይህን ከእጅ ወደ አፍ የሆነ ነዋሪ የምትኖርበት መሬት ህገ ወጥ ነው እያሉ ዳታ መሰብሰብ ጀምረዋል ካርታ የለውም ነገር ግን በየወቅቱ ለመንግስት ግብር ስንከፍልበት የነበረ ወረቀት አለን ሰራቸው ምንም ግልፅ አይደለም ሊገባን አልቻለም እናም በዳታ ስብሰባው ወቅት የሙስና ጥማታቸውን እያረኩ ነው ልጁን ቅባት ቀብቶ ወደ ትምህርት ቤት መሸኘት ያቃተው ነዋሪ ለነሱ ደም እንባ እያለቀሰ እየሸጎጠ ነው ያቃተውም ምን ይከሰት ይሆን እያለ ጨቅላ ህፃናትን ይዞ ጭንቀት ላይ ነው ያለው ኢሄን መልዕክት የሚመለከተው አካል አይቶ አፋጣኝ መልስ እንፈልጋለን።

@tsegabwolde @tivahethiopia
#Update የቴዲ አፍሮ የሚሊንየም አዳራሽ የሙዚቃ ኮንሰርት በተሻለ የድምፅ እና የምስል ጥራት ለህዝብ ሊደርስ እየተዘጋጀ ይገኛል።

©ethiopikalink
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update የአፋር ብሄራዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ኢንጂነር አይሻ መሃመድን ሊቀመንበር ፤ አቶ አወል አርባን ምክትል ሊቀመንበር እንዲሆኑ መርጧል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
fixed!! ቻናሉ ላይ ከትላንት ምሽት ጀምሮ ተፈጥሮ የነበረው ችግር ተፈቷል! ሊንኩ አይሰራም ላላችሁ በሙሉ ይቅርታ እንጠይቃለን!

@tikvahethiopia
አዲስ አበባ🛬ጋዜጠኛ ሳዲቅ አህመድን እና ጋዜጠኛ አብዱረሂም አህመድን ኢትዮጵያ ገብተዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETH ላይ የነበረው የሊንክ አለመስራት ችግር ሙሉ በሙሉ ተፈቷል። @tikvahethiopia ሼር ስናደርገው አይሰራም እያላችሁ ለነበራችሁ የቻናላችን ቤተሰቦች ችግሩ ሙሉ በሙሉ መቀረፉን ለመግለፅ እንወዳለን! ለትዕግስታቹ ከልብ እናመሰግናለን!
.
.
ይህ በእንዲህ እንዳለ በማህበራዊ ሚዲያ አንዳንድ ግለሰቦች TIKVAH-ETH ቆሟል ብለው ያሰራጩት መረጃ ሀሰት መሆኑን እንድታውቁት እንፈልጋለን!

https://t.iss.one/joinchat/AAAAAENjSkUg0WenkgR_CA
BE THERE! ህዳር 27-ታህሳስ 1, 2011 ዓ.ም. ADDIS FOTO FEST!

ሸራቶን አዲስ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዲስ አበባ🔝ከተሽከርካሪ ነፃ ቀን...
ፎቶ፦ Mike(TIKVAH-ETH)
@tsegabwolde @tikvahethiopia