TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.5K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ከሀረር🔝

"ፀግሽ ዛሬ ሀረር ፈዲስ የሚባል አካባቢ የስላሴ ቤተክርስቲያን ሲመረቅ የሙስሊም አባቶች ተገኝተው ነበር። #ኢትዮጵያዊነት" ሶል ከሀረር

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ🔝

አፍሪካ ለተጠናከረ የንግድና የህዝቦች እንቅስቃሴ ዲጂታል እድሎችን በኢ-ገቨርናንስ ማእቀፍ ስር በአፋጣኝ መጠቀም እንዳለባት ጠቅላይ
ሚኒስትር ዶ/ር #ዐቢይ_አሕመድ አሳሰቡ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ያሉት የአፍሪካ ህብረትና የተባብሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ዛሬ ባዘጋጁት የጎንዮሽ ስብሰባ ላይ ነው፡፡

ስብሰባው "ዲጂታል ማንነት ለ2030 የልማት አጀንዳና ለአፍሪካ ህብረት አጀንዳ 2063" በሚል ርእስ ተካሂዷል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው በተለይም ዲጂታል ምጣኔ ሀብት እያሳየ የሚገኘውን እድል ከግምት ውስጥ በማስግባት የአፍሪካን ልማት በትክክለኛ ህገ ደንቦች የሚመራ ዲጂታል አሰራር ከፍ ማድረግ ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ አስምረውበታል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የተባብሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ዲጂታል ማንነት ኢኒሼቲቭ አማካሪ ቦርድ ተባባሪ #ሊቀመንበር ናቸው።

ምንጭ፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ታላቁ ሩጫ🔝ለ18ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ በተካሄደው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በወንዶች የ5ኪሜ የሩጫ ውድድር ሀጎስ ገብረመድህን ከመስፍን ኢንዱስትሪያል ኢንጂነሪንግ 1ኛ ወጥቷል፡፡ በሴቶች የ5ኪሜ ውድድር ደግሞ ፎቴን ተስፋዬ ከመሰቦ 1ኛ ወጥታለች።

ምንጭ፦ etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አስተያየታችሁን አድርሱ!!

ዛሬ ቀኑን ሙሉ በTIKVAH-ETH መረጃዎችን ቀነስ ማስታወቂያዎችን ገታ አድርገን የእስከዛሬው ቆይታችን ላይ እንነጋገራለን። አዳዲስ ሀሳቦች ይቅረቡ እና እንነጋገር። ቻናላችን ከ200,000 በላይ ኢትዮጵያዊየያንን ያቀፈ ነው። በቀን እስከ 60,000 የሚደርሱ ኢትዮጵያዊያን ቤታቸውን ይጎበኛሉ።

ማንኛውም አስተያየት መላክ ይቻላል! አስተያየቱ በጨዋ ቋንቋ ልንማማርበት ይሁን!!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሲዳማ ባህል አዳራሽ🔝በሲዳማና ወላይታ ሕዝብ መካከል ተፈጥሮ የነበረውን ችግር ይፈታል ተብሎ የታመነበት የዕርቅና #ሰላም_ኮንፈረንስ በሀዋሳ ሲዳማ ባህል አዳራሽ በመካሄድ ላይ ነው።በዕርቁ ሥነ ሥርዓት ላይ የመንግስት ኃላፊዎች፣ የኃይማኖት አባቶች፣የባህል ሽማግሌዎችና አባ ገዳዎች የተገኙ ሲሆን ፕሮግራሙም በተያዘለት መርሃ ግብር መሠረት ቀጥሎ ይገኛል።

ምንጭ፦ የሲዳማ ዞን ባህል፣ቱሪዝም የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ
@tsegabwolde @tikvahethiopia