TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63K photos
1.61K videos
216 files
4.38K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ኮሎኔል ጎሹ⬆️የቀድሞ የኢትዮዽያ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር የነበሩት ኮሎኔል #ጎሹ_ወልዴ ከ32 አመት በኅላ የቀድሞ ቢሯቸውን ጎብኝተዋል።

ፎቶ፦ ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ስለሰውነት እና ስለኢትዮጵያ ሀገሬ እመክራለሁ!

ውድ የTIKVAH-ETH ቤተሰቦች ከነገ ምሽት ጀምሮ ሁላችንም ቤት ስንገባ ከቤተሰቦቻችን ጋር በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ እንወያያለን። የውይይት ርዕሱን በየቀኑ ከዚህ ቻናል እናገኛለን። ቤታችን ሆነን ቢያንስ ለ30 ደቂቃ ሁሉም የቤተሰብ አባል የሚካፈልበት ውይይት እናደርጋለን።

🔹በየዩኒቨርሲቲው ያላችሁ የኢትዮጵያ ልጆች ደግሞ በየዶርማችሁ በርዕሶቹ ላይ ውይይት ታደርጋላችሁ። በቀጥታ በስልክ መስመር እየተገናኘንም እንመክራለን።

📌ውይይቶቹን የሚያሳዩ ፎቶዎች መላክ ደግሞ እንዳይረሳ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update አቃቢ ሕግ ዛሬ በዋለ #ችሎት የብሄራዊ መረጃና ደህንነት መስሪያ ቤት ባልደረባ በነበሩት የወንጀል ተጠርጣሪ #ተስፋዬ_ኡርጌ ላይ የጀመርኩትን ምርመራ በሥራ መደራረብ ሳቢያ ማጠናቀቅ አልቻልኩም ብሏል፡፡ በባለፈው ችሎት አቃቢ ሕግ ክስ እንዲመሰርት የፌደራሉ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አሳስቦ የነበረ ቢሆንም ዛሬም እንደገና አቤቱታውን እንደገና ተቀብሎ የመጨረሻውን ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ፈቅዷል፡፡

ምንጭ፦ wazemaradio
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ⬆️

"ዛሬ ከሰአት 202 ኪ.ሜ ርዝመት የሚሸፍነውን እና 4 ተሽከርካሪዎች በትይዩ ለማስተናገድ የሚያስችል 32 ሜትር ስፋት ያለውን የሞጆ - ሃዋሳ የፍጥነት መንገድ የግንባታ ሂደት ያለበትን ደረጃ መመልከት ችያለው መንገዱ ካለዉ አጠቃላይ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ጠቀሜታ አኳያ በተያዘለት የግዜ ገደብ እና የጥራት ደረጃ #መጠናቀቅ እንደሚገባዉ የስራ #መመሪያ ሰጥተናል። በጉብኝቱ ከመንገዱ ባሻገር ኢትዮጲያውያን ሙያተኞች ከውጭ ሙያተኞች የሚቀስሙት ልምድ እና የቴክኖሎጂ ሽግግር በላቀ ደረጃ አጠናክረው መሄድ እንደሚገባቸው ነው ያሳሰብኩት።

በተመሳሳይ ማምሻውን የኢትዮጲያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ የአዲስ-አዳማ የፍጥነት መንገድ ላይ የሚገኙት ቱሉዲምቱ እና የሞጆ የክፍያ ጣቢያ ላይ ያለውን የቁጥጥር እና የክፍያ ሲስተም ተመልክተናል። ዘመናዊ በሆነ ቴክኖሎጂ እና ብቃት ያለው የሰው ሃብት በመጠቀም ደህንነቱ የተጠበቀ አገልግሎት መስጠት ተልኮውን ላደረገው ኢንተርፕራይዝ በቀጣይም ከዚህም በተሻለ ሁኔታ አገልግሎት እንዲሰጥ ሚንስትር መስሪያ ቤታችን ድጋፍና ክትትል ያደርጋል።"

@tsegabwolde @tikahethiopia
ፈጣሪ ማስተዋል ይስጠን!

ዛሬ አንዳንዶች ባሉበት ሆነው ተዋልደው ተከባብረው የሚኖሩ #ብሄሮችን ለማጋጨት ይሞክራሉ፤ ሰዎችን ለጥል ያነሳሳሉ፤ እርስ በእርስ እንዲገዳደሉ ይቀሰቅሳሉ፤ በፍቅር የሚኖረውን ህዝብ ይከፋፍላሉ፤ ወጣቱ ሰብዓዊነቱን እንዲረሳና ብሄሩን እንዲያስቀድም በሙሉ አቅማቸውን ቀን ማታ ይቀሰቅሳሉ፤ ህግን ስርዓትን አክብሮ የሚኖረውን ወጣት ተነሳ ግደል፣ አጥፋ እያሉ ይመክራሉ፤ ብሄር መስደብ፣ ማንቋሸሽ ባህል እንዲሆን ይሰራሉ፤ ወጣቱን ሳያውቀው ከፈጣሪው ጋር ያጋጫሉ፤ የተወሰነ ሰው ባጠፋው ወንጀል ሚሊዮኖች መሰደብ፣ መገለል እንዳለባቸው ምንም ሳይፈሩ ይናገራሉ።

እንዲህ የሚያደርጉ ሰዎች ብዙዎቹ ከራሳቸው ጋር የተጣሉ፣ ሰውነታቸውን የረሱ፣ ፈጣሪን የካዱ፣ እውቀት የራቃቸው፣ ማስተዋል ያልፈጠረባቸው ናቸው።

ዛሬ በብሄሮች መካከል እሳት ለመለኮስ የሚጥሩ ሰዎች የለኮሱት እሳት እራሳቸውን እንደሚያነድ፤ እራሳቸውን እንደሚፈጅ ፍፁም አላስተዋሉም።

የዛሬዎቹ የጥላቻ ነጋዴዎች #ነገን አሻግረው አላዩም። ይህ ህዝብ በጣም የተዋሀደ፣ እርስ በእርሱ የተዋለደ ህዝብ ነው። ዛሬ ብሄር ለይተው በለው የሚሉት ተራ ግለሰቦች ነገ የራሳቸው ወንድም እና እህቶች ካሉበት አካባቢ ወጥተው እንደሚማሩ ረስተውታል፤ ከአንዱ ከተማ ወደ ሌላው ከተማ ሄደው የሚማሩትን #ምስኪን ልጆችን ረስተዋቸዋል።

የብሄር ተቆርቋሪዎች መስለው የራሳቸውን ወንድም እና እህቶች የሚያጋድሉት ሰይጣኖች ናቸው። ወንድም እና እህቶቻቸው በሄዱበት ቦታ ሁሉ በቋንቋቸውና በባህላቸው እንዲሸማቀቁ ሊያደርጓቸው ያሰቡ እነሱ እውነትም የዚህች ሀገር ጠላቶች ናቸው።

እናተ የጥላቻ ነጋዴዎች...

◾️ነገ ምስኪን እህት ወንድሞቻችሁ የት ተመድበው እንደሚማሩ አታውቁምና ከጥላቻ ይልቅ ፍቅርና አንድነትን አስተምሩ።

◾️ነገ ምንም የማያውቀው ሰራተኛ የዕለት ጉርሱን ፍለገ የትኛው ከተማ እንደሚሄድ አታውቁም ከጥላቻ ይልቅ ፍቅርና አንድነትን አስተምሩ።

ሁሉም ሰላምን የሚወድ፤ ሀገሩን የሚወድ ሰው በብሄር ማካከል ጥላቻ እንዲኖር የሚሰሩትን ያግልላቸው። የማዕበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች የጥላቻ ገፆች እና ግለሰቦችን #Block አድርጓቸው።

ለወጣቱ ፍቅርን እናውርሰው። ፍቅር እንደሚያሸንፍ ደጋግመን እንገረው። #ሰውነት ከሀገር፣ ከብሄር፣ ከዘር እንደሚበልጥ እንገረው።

ፈጣሪ ማስተዋልን ይስጠን!
ፀጋአብ ወልዴ-ኢትዮጵያ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የሰላም ጉባኤ⬇️

በኢትዮጵያም ሆነ በአፍሪካ ቀንድ ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍንና የተጀመረው የአንድነት ጉዞ እንዲሳካ የምሥራቅ አጎራባች ክልሎች የተቀናጀ #ርብርብ ወሳኝ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር አፈ ጉባዔ አብዱልሰላም መሐመድ ተናገሩ፡፡

የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ወይዘሮ #ኬሪያ_ኢብራሂምን ጨምሮ የምሥራቅ ተጎራባች ክልሎች ከፍተኛ አመራሮች የሚሳተፉበት የሰላም ጉባዔ በድሬዳዋ ከተማ ከዛሬ ጀምሮ ለሁለት ቀናት ይካሄዳል፡፡

አፈ ጉባዔው እንደተናገሩት በአገሪቱ የተጀመረው ለውጥና  አገር ግንባታ እንዲሳካ የምክር ቤቱ አባላት፣ በየደረጃው የሚገኘው አመራር፣ ባለሙያዎችና ነዋሪዎች ኃላፊነት አለባቸው፡፡

የምስራቅ  ኢትዮጵያና አጎራባች ክልሎች ለዘመናት ያዳበሩትን የፍቅር፣ የመቻቻልና የአንድነት ባህላዊ እሴቶች በማጠናከር ለዘላቂ ሰላም መረጋገጥ ተቀናጅተው መስራት እንዳለባቸውም አሳስበዋል፡፡

ጉባዔው የምሥራቅ ኢትዮጵያ አጎራባች ክልሎች በተቀናጀ መንገድ በአገሪቱ ብሎም በአፍሪካ ቀንድ ሀገሮች ሰላምና ልማት እንዲረጋገጥ የተጀመሩትን ተግባራት ለማሳካትም አበርክቶው የጎላ እንደሚሆን አቶ  አብዱልሰላም አመልክተዋል፡፡

ለጉባዔው የሚያስፈልጉ የመስተንግዶ፣የመሰብሰቢያ አዳራሾች፣የእርስ በርስ ባህላዊ እሴቶችና የልምድ ልውውጥ መከወኛ ሥፍራዎች ተዘጋጅተዋል።

የድሬዳዋ ከተማ ነዋሪዎችና አገልግሎት ሰጪ  ተቋማት እንግዶችን በፍቅርና በደስታ በማድተናገድ ከተማዋ የፍቅር ተምሳሌት መሆኗን  በተግባር እንዲያስመሰክሩ አፈ ጉባዔው ጥሪ አቅርበዋል።

በጉባዔው የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሂምን ጨምሮ የምስራቅ አጎራባች ክልሎች ርዕሳነ መስተዳድር፣ አፈ ጉባዔዎች፣ ከንቲባዎች፣ የአገር ሽማግሌዎች ወጣቶችና ሴቶች ይሳተፋሉ ብለዋል፡፡

የዘንድሮውን  የብሄሮች፣ብሄረሰቦችና ሕዝቦች ቀን አስመልከቶ ነገ በምሥራቁ የአገሪቱ ክፍል ድሬዳዋ ላይ የሚጀመረው የሰላምና የአንድነት ጉባዔ በቀጣይም በምዕራብ፣በደቡብና በሰሜን የአገራቸን ክፍሎች እንደሚቀጥል መረጃዎች ያመለክታሉ።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) በአዲስ መልክ እንዲዋቀርና በድርጅቱ ውስጥ የተፈፀመው #ምዝበራ ተጣርቶ ተጠያቂ
ግለሰቦች ህግ ፊት እንዲቀርቡ ለማድረግ የሚያስችል ሰፊ ምርመራ ከተጀመረ ስንብቷል። በከፍተኛ ምስጢር ተይዞ እየተካሄደ ያለው ምርመራ እጅግ ግር የሚያሰኙና አዳዲስ መረጃዎችን አግኝቷል። ምርመራው እንደቀጠለ ሲሆን በእስካሁኑ ምርመራ ሜቴክ የንግድ
አውሮፕላን ይፋዊ ባልሆነ መንገድ መግዛቱን የሚያሳይ መረጃ ተገኝቷል። ሁለት መቶ መኖሪያ ቤቶችን በድርጅቱ ገንዘብ ገዝቶ ለግለሰቦች ሰጥቷል።

ምንጭ፦ wazemaradio
@tsegabwolde @tikvahehiopia
#UpdateSport የ2011 ዓ/ም የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የሁለተኛ ሳምንት ሶስት ጨዋታዎች ከፀጥታ ጋር ስጋት በመኖሩና በብሔራዊ ቡድን ዝግጅት ምክንያት ነው ለሌላ ጊዜ የተላለፉት። ፌዴሬሽኑ ለሌላ ጊዜ እንዲተላለፍ ከተወሰነባቸው መካከል በባህር ዳር ከነማ እና ስሑል ሽረ
መካከል ሊደረግ የነበረውን ጨዋታ ሲሆን ጨዋታው ለሌላ ጊዜ የተላለፈው ደግሞ የትግራዩ ቡድን ሽረ ከፀጥታ ጋር በተያያዘ ወደ ሌላ ጊዜ #እንዲዘዋወር ጥያቄ በማቅረቡ ነው፤ ባለሜዳው ባህር ዳር ከነማ ግን ጨዋታው #በሰላም እንዲከናወን ቅድመ ዝግጅት ማድረጉን
ቢገልፅም ፌዴሬሽኑ እንዲራዘም ውሳኔ አሳልፏል፡፡ ሌሎቹ ለሌላ ጊዜ እንዲተላለፉ የተወሰኑ ግጥሚያዎች ደግሞ ድሬዳዋ ከነማ ከደቡብ ፖሊስ ሐረር ላይ ሊያደርጉት የነበረው ጨዋታ ሲሆን ድሬዳዋ ለዋልያዎቹ እና ለ23 ዓመት በታች ቡድን አምስት ተጫዋቾች በማስመረጡ ምክንያት በተመሳሳይ ሲዳማ ቡና አራት ተጫዋቾች በማስመረጡ፤ የወላይታ ድቻ እና የሲዳማ ቡና ጨዋታም ወደ ሌላ ጊዜ መተላለፉቸው ታውቋል።

ምንጭ፦ አርትስ ቴሌቪዥን
@tsegabwolde @tikvahethiopia