TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.9K photos
1.61K videos
216 files
4.37K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update አሜሪካውያን በአጋማሽ ምርጫው ‹በትራምፕ ላይ ይፈርዳሉ› እየተባለ ነው፡፡ አሜሪካውያን በምርጫ ዘመን አጋማሽ ላይ እያካሄዱ ባለው ምርጫ በትራምፕ አስተዳደር ላይ ፍርድ ይሰጣሉ እየተባለ መሆኑን ሲኤንኤን
ዘግቧል፡፡ ከሁለት ዓመታት በፊት በአዋዛጋቢ ምርጫ ወደ ቤተ መንግሥት የገቡት ዶናልድ ትራምፕ በዚህ ምርጫ እንደሚፈተኑ ነው የተገለጸው፡፡ አሁን ያለው የምርጫ ሂደት ውጤቱን ለመተንበይ አስቸጋሪ እንዳደረገውም ተዘግቧል፡፡ ‹ምናልባትም እንደ ዛሬ ሁለት ዓመቱ ዋና ምርጫ ያልተጠበቀ ውጤት ሊያስከትል ይችላል› የሚሉም አሉ፡፡

ምንጭ፦ CNN
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፕሬዘዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋቂ ጋር ተወያዩ‼️
#Update ፕሬዝዳንት #ሳህለወርቅ_ዘውዴ የኢትዮጵያ ርዕሰ ብሔር ሆነው መመረጣቸው ለአህጉር ጥሩ ዜና እንደሆነ የአፍሪካ ኀብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር #ሙሳ_ፋኪ ተናገሩ። ሚስተር ፋኪ ዛሬ በብሔራዊ ቤተ መንግስት ከኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ጋር በአህጉሪቱ ሰላምና ፀጥታ እንዲሁም አጀንዳ
2063 በተሰኘው የአፍሪካ ህብረት የልማት መርሃ ግብር ትግበራ ዙሪያ ውይይት አካሂደዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምዕራብ ኦሮሚያ‼️

በምዕራብ ኦሮሚያ ያጋጠመውን የፀጥታ ችግር ለመቅረፍ እየሰራ መሆኑን የኦሮሚያ ክልል መንግስት አስታውቋል።

የኦሮሚያ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሀላፊ አቶ #አድማሱ_ዳምጠው በዛሬው እለት በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መግለጫ
ሰጥተዋል።

አቶ አድማሱ በመግለጫቸውም፥ የክልሉ መንግስት ህዝቡን መሰረት አድርጎ በፖለቲካ እና በኢኮኖሚው ዘርፍ እየሰራ ያለው ስራ ውጤት እያስመዘገበ ይገኛል ነው ያሉት።

ይሁን እንጂ በአሁኑ ወቅት በክልሉ በተወሰኑ አካባቢዎች ያለው የፀጥታ ሁኔታ #አሳሳቢ መሆኑን እና በአፋጣኝ መፍትሄ ሊሰጠው የሚገባ መሆኑን አንስተዋል።

በተለይም በምእራብ ኦሮሚያ በሚገኙ ዞኖች ያለው የፀጥታ ሁኔታ መሻሻል ያለበት መሆኑን የክልሉ መንግስት ይገነዘባል ያሉት አቶ አድማሱ፥ በዚህ ላይም እየሰራ መሆኑን አንስተዋል።

አቶ አድማሱ አክለውም፥ የክልሉ መንግስት የኦሮሞ ህዝብ ትጥቅ መፍታት አለበት የሚል አቋም እንደሌለው እና ማንኛውንም አካል በመማረክ የማስተዳደር ፍላጎት እንደሌለውም ተናግረዋል።

በአሁኑ ወቅትም የክልሉ መንግስት በኦሮሞ ስም ተደራጅተው ከሚንሰቃቀሱ አካላት ጋር ሰለማዊ በሆነ መንገድ በመወያየት እየሰራ ይገኛል ያሉት አቶ አድማሱ፥ ወደ ፊትም ትኩረት ሰጥቶ የሚሰራበት ጉዳይ መሆኑን ገልፀዋል።

የኦሮሞ ህዝብ ጥያቄ በጠብመንጃ ሳይሆን በውይይት፣ በመደማመጥና በመከባበር የሚፈታ መሆኑን በመግለጽ፥ የክልሉ መንግስትም የኦሮሞን ህዝብ ጥያቄ በመመለስ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር የሚወያይ መሆኑንም አስታውቀዋል።

አባ ገዳዎች እና የሀገር ሽማግሌዎች አሁን እየመጣ ያለውን ለውጥ ጠብቀው በማስቀጠል የበኩላቸውን እንዲወጡም አቶ አድማሱ ጥሪ አቅርበዋል።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር‼️

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በአዲሱ መዋቅር መሰረት አምስት ቋሚ #ተጠሪዎችን ሾሟል።

በዚህም መሰረት፦

• አምባሳደር #ወይንሽት_ታደሰ- የአፍሪካ እና የመካከለኛው ምስራቅ አገሮች ጉዳዮች ቋሚ ተጠሪ

• አምባሰዳር #ማህሌት_ኃይሉ- የአውሮፓ፣ የአሜሪካ፣ የኤዥያ እና የባለብዙ ወገን ጉዳዮች ቋሚ ተጠሪ

• አምባሳደር ዶክተር በጋለ ቶሎሳ- የዳያስፖራ እና ቆንስላ ጎዳዮች ቋሚ ተጠሪ

• አምባሳደር ነጋ ፀጋዬ- የኃብት ማኔጅመንትና አገልግሎት ቋሚ ተጠሪ

• አምባሳደር ደዋኖ ከድር- የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ ጉዳዮች ቋሚ ተጠሪ ሆነው ተሹመዋል።

አምባሳደር ወይንሸት በሲዊዲን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ቋሚ መልእክተኛ እና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር እንዲሁም በአፍሪካ ህብረት የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛን ሲያገለግሉ የነበሩ ሲሆን፥ አምባሳደር ማህሌት ኃይሉ ደግሞ በኒውዮርክ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ቋሚ መልዕክተኛ ጽህፈት ቤት ምክትል የሚስዮን መሪ በመሆን አገልግለዋል፡፡

አምባሳደር ዶክተር ቦጋለ ቶሎሳ በኩባ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኤምባሲ ልዩ መልእክተኛ እና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር እንዲሁም ወደ ዋናው መስሪያ ቤት ተመልሰው የቆንስላ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄነራል ሆነው አገልግለዋል።

አምባሳደር ነጋ ፀጋዬ በፈረንሳይ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ልዩ መልእክተኛ እና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሆነው ያገለገሉ ሲሆን፥ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ዳይሬክተር ጄነራል በመሆንም ሰርተዋል።

አምባሳደር ደዋኖ ከድር ደግሞ በኩባ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ልዩ መልእክተኛ እና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሆነው ቆይተዋል፤ ሁለቱም በተለያየ ወቅት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው አገልግለዋል።

ቋሚ ተጠሪዎች የመስሪያ ቤቱን የዕለት ተዕለት ስራ የመከታተልና ውሳኔ የማሳለፍ ሃላፊነት የሚኖራቸው ሲሆን በተለያዩ አገሮች በስፋት ይሰራበታል፡፡

በቀጣይም የዳይሬክተር ጀኔራሎች እና ሌሎች የሃላፊነት እርከኖች ድልድል ይፋ እንደሚያደርግም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

ምንጭ፦ OBN
@tsegabwolde @tikvahethiopia
🕊1
ኮሎኔል ጎሹ⬆️የቀድሞ የኢትዮዽያ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር የነበሩት ኮሎኔል #ጎሹ_ወልዴ ከ32 አመት በኅላ የቀድሞ ቢሯቸውን ጎብኝተዋል።

ፎቶ፦ ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ስለሰውነት እና ስለኢትዮጵያ ሀገሬ እመክራለሁ!

ውድ የTIKVAH-ETH ቤተሰቦች ከነገ ምሽት ጀምሮ ሁላችንም ቤት ስንገባ ከቤተሰቦቻችን ጋር በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ እንወያያለን። የውይይት ርዕሱን በየቀኑ ከዚህ ቻናል እናገኛለን። ቤታችን ሆነን ቢያንስ ለ30 ደቂቃ ሁሉም የቤተሰብ አባል የሚካፈልበት ውይይት እናደርጋለን።

🔹በየዩኒቨርሲቲው ያላችሁ የኢትዮጵያ ልጆች ደግሞ በየዶርማችሁ በርዕሶቹ ላይ ውይይት ታደርጋላችሁ። በቀጥታ በስልክ መስመር እየተገናኘንም እንመክራለን።

📌ውይይቶቹን የሚያሳዩ ፎቶዎች መላክ ደግሞ እንዳይረሳ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update አቃቢ ሕግ ዛሬ በዋለ #ችሎት የብሄራዊ መረጃና ደህንነት መስሪያ ቤት ባልደረባ በነበሩት የወንጀል ተጠርጣሪ #ተስፋዬ_ኡርጌ ላይ የጀመርኩትን ምርመራ በሥራ መደራረብ ሳቢያ ማጠናቀቅ አልቻልኩም ብሏል፡፡ በባለፈው ችሎት አቃቢ ሕግ ክስ እንዲመሰርት የፌደራሉ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አሳስቦ የነበረ ቢሆንም ዛሬም እንደገና አቤቱታውን እንደገና ተቀብሎ የመጨረሻውን ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ፈቅዷል፡፡

ምንጭ፦ wazemaradio
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ⬆️

"ዛሬ ከሰአት 202 ኪ.ሜ ርዝመት የሚሸፍነውን እና 4 ተሽከርካሪዎች በትይዩ ለማስተናገድ የሚያስችል 32 ሜትር ስፋት ያለውን የሞጆ - ሃዋሳ የፍጥነት መንገድ የግንባታ ሂደት ያለበትን ደረጃ መመልከት ችያለው መንገዱ ካለዉ አጠቃላይ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ጠቀሜታ አኳያ በተያዘለት የግዜ ገደብ እና የጥራት ደረጃ #መጠናቀቅ እንደሚገባዉ የስራ #መመሪያ ሰጥተናል። በጉብኝቱ ከመንገዱ ባሻገር ኢትዮጲያውያን ሙያተኞች ከውጭ ሙያተኞች የሚቀስሙት ልምድ እና የቴክኖሎጂ ሽግግር በላቀ ደረጃ አጠናክረው መሄድ እንደሚገባቸው ነው ያሳሰብኩት።

በተመሳሳይ ማምሻውን የኢትዮጲያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ የአዲስ-አዳማ የፍጥነት መንገድ ላይ የሚገኙት ቱሉዲምቱ እና የሞጆ የክፍያ ጣቢያ ላይ ያለውን የቁጥጥር እና የክፍያ ሲስተም ተመልክተናል። ዘመናዊ በሆነ ቴክኖሎጂ እና ብቃት ያለው የሰው ሃብት በመጠቀም ደህንነቱ የተጠበቀ አገልግሎት መስጠት ተልኮውን ላደረገው ኢንተርፕራይዝ በቀጣይም ከዚህም በተሻለ ሁኔታ አገልግሎት እንዲሰጥ ሚንስትር መስሪያ ቤታችን ድጋፍና ክትትል ያደርጋል።"

@tsegabwolde @tikahethiopia