TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.5K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETH-ከዩኒቨርሲቲዎች የሚመጡላትን የቅበላ ቀናት የሚያቀርብ ይሆናል። በመሆኑም ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ትክክለኛ ገፃችሁን እና ድረ ገፃችሁን ጎብኙ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ የወንጀል ችሎት በሰኔ 16ቱ የቦንብ ጥቃት የተከሰሱ በእነ ጌቱ ግርማ 5 ግለሰቦች ክስ ላይ የክስ መቃወሚያ ለመስማት ለጥቅምት 16 ተለዋጭ ቀጠሮ ያዘ᎓᎓

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Forwarded from Deleted Account
Forwarded from Deleted Account
የምስራች!!!

🇪🇹 በሀገራችን ምርት እንጠቀም! እንኩራ!

የRingAround App ይሞክሩን
https://https://ringaround.lpages.co/et-tikvah-downloadringaroundapp

በውጭ ሀገር ለምትኖሩ ኢትዮጵያውያን!

ሳያመልጣችሁ በሀገራችን የቴክኖሎጂ ጠቢባን ተዘጋጅቶ የቀረበውን አለም አቀፉን የRingAround Appን በስልካችሁ ላይ ቶሎ በመጫን ወደ ሀገር ቤት ይደውሉ!
#update አቶ ሌንጮ ለታ⬇️

#ኦነግ ትጥቅ አልፈታም በማለት ለተጀመረው ሰላማዊ የፖለቲካ ሂደት እንቅፋት መሆን የለበትም መንግስትም በጉዳዩ ላይ ግልፅ መረጃ ማቅረብ አለበት ሲሉ የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር ሊቀመንበር አቶ ሌንጮ ለታ ተናገሩ።

አዲስ አበባ በሚገኘው አሐዱ በተባለው ሬድዮ ከአቶ #በቀለ_ገርባ ጋር እንግዳ ሆነው የቀረቡት አቶ #ሌንጮ_ለታ በሀገሪቱ የተጀመረው ለውጥ ሁሉን አካታችና የማይቀለበስ እንዲሆን ሁሉም አካል በሀላፊነት መንቀሳቀስ አለበት ብለዋል። የኢትዮጵያ መንግስት ከኦነግ ጋር የደረሰበትን ስምምነት ይፋ ማድረግ አለበት ያሉት አቶ ሌንጮ ለታ የኦነግ መሪ አቶ ዳውድ ኢብሳ ከምን ተነስተው ትጥቅ አንፈታም እንዳሉ መረዳት ይቸግረኛል ብለዋል።" ወጣቶች ባዶ እጃቸውን ወጥተው ታንክ ፊት ቆመው ሲታገሉ የኦነግ ሰራዊት የት ነበረ? አሁንስ ትጥቅ አልፈታም ማለት ማንን ለመውጋት ነው?" ሲሉ ጠይቀዋል።

ምንጭ፦ ዋዜማ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የዕድል ሎተሪ ወጣ!

በርካቶች በጉጉት ሲጠብቁት የነበረው ዕድል ሎተሪ ጥቅምት 02/2011 ዓ.ም ከምሽቱ 12፡00 በብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ዕድል አዳራሽ በህዝብ ፊት ወጥቷል፡፡ በዚህም መሰረት የወጡት የአሸናፊ ቁጥሮች እንደሚከተሉት ሆነዋል፡፡

🔹3,000,000 ብር የሚያስገኘው የ1ኛ ዕጣ ቁጥር 0863185
🔹2,000,000 ብር የሚያስገኘው የ2ኛ ዕጣ ቁጥር 0735433
🔹1,000,000 ብር የሚያስገኘው የ3ኛ ዕጣ ቁጥር 1167564
🔹500,000 ብር የሚያስገኘው የ4ኛ ዕጣ ቁጥር 0265137
🔹250,000 ብር የሚያስገኘው የ5ኛ ዕጣ ቁጥር 1234506
🔹125,000 ብር የሚያስገኘው የ6ኛ ዕጣ ቁጥር 0278147
🔹7ኛ ዕጣ ቁጥር 0036098
🔹8ኛ ዕጣ ቁጥር 50717
🔹9ኛ ዕጣ ቁጥር 02651
🔹10ኛ ዕጣ ቁጥር 0977
🔹11ኛ ዕጣ ቁጥር 5864
🔹12ኛ ዕጣ ቁጥር 810
🔹13ኛ ዕጣ ቁጥር 69
🔹14ኛ ዕጣ ቁጥር (የማስተዛዘኛ ዕጣ) ደግሞ 9 በመሆን ወጥቷል፡፡

አስተዳደሩ ዕድለኞችን እንኳን ደስ አላችሁ እያለ ዜናውን ለጓደኞቻችሁ በማጋራት (share በማድረግ) ለሌሎች እንዲደርስ አድርጉ፡፡ እናመሰግናለን!

የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር
ጥቅምት 02/2011 ዓ.ም

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የዕድል ሎተሪ ማውጫ‼️
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ህይወት ፋና ሆስፒታል⬆️ሐረማያ ዩኒቨርስቲ ሕይወት ፋና ስፔሻላይዝድ ዩኒቨርስቲ ሆስፒታል የማህጸንና ጽንስ ህክምና ስፔሻሊስ ሐኪሞች መስከረም 30 ቀን 2011 ዓ.ም 7 ኪሎ የሚመዝን Ovarian Cancer በቀዶ ጥገና በማውጣት ኦፕሬሽኑ በተሳካ ሁኔታ ተካሄዷል።

ምንጭ፦ Hiwot Fana Specialized University Hospital
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቅርቡ ማጣራት በጀመረባቸውና ያለ ስራ ታጥረው የተቀመጡ መሬቶችን ለልማት የማዋል ስራ ላይ ሁሉም ቦታዎች ለተደራጁ ወጣቶች ይሰጣሉ የሚለው መረጃ ከእውነት የራቀ ነው ሲል የከተማ አስተዳደሩ ለሽገር FM ገልጿል። የአዲስ አበባ ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ እንደተናገረው በቦሌ ክፍለ ከተማ በሚገኙ ወረዳዎች በመንግስት ታጥረው የሚገኙ ቦታዎች በማህበር ለተደራጁ ወጣቶች ይሰጣሉ በሚል #የሀሰት_መረጃ እየተሰራጨ በመሆኑ ነዋሪዎች በሀሰተኛ መረጃ መደናገር የላባቸውም ብሏል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ዛሬ አጋሮ ውጥረት ነግሶባት ውላለች። በከተማይቱ የአንድ ሰው ህይወት ማለፉንም ሰምተናል። መልዕክታቸውን የላኩ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት እንዳሉት መንግስት በአጋሮ ያለውን የመልካም አስተዳደር ችግር ይይልን ብለዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update ቱጃሩ ተጠለፋ⬇️

የታንዛንያ ፖሊሶች በአፍሪካ ከሁሉም ወጣቱ ቢሊዮነር ቱጃር የሚባሉት ሰው #መጠለፋቸውን ተከትሎ የዋና ከተማዋን የዳሬሰላምን እና ዙሪያዋን #ድንበሮች ዘግተዋል።

የአርባ ሰባት ዓመቱ መሃመድ ዴውጂ ትናንት ሃሙስ ጠዋት የአካል እንቅስቃሴ ስፖርት ሊሰሩ ወደ አንድ ሆቴል ሊገቡ ሲሉ ጨንበል ያጠለቁ ሁለት ታጣቂዎች እንደጠለፉዋቸው የዳሬሰላም ፖሊስ አዛዥ ላዛሮ ማምቦሳሳ ገልፀዋል።

ኮሎሲየም ሆቴል እና የስፖርት ክለብ የሚገኘው ኦይስተር ቤይ በሚባለው የዳሬሰላም የባለለፀጎች አካባቢ ነው -የፖሊስ አዛዡ እንዳሉት ታጣቂዎች ወደሰማይ ከተኮሱ በኋላ ዴውጂን አፋፍሰው መኪና ውስጥ አስገብተው ተፈትልከዋል። ፖሊሶች ዋና ተጠርጣሪዎች ያሏቸውን ሁለት ነጮች እየፈለጉ ናቸው።

እኚህ ባለጸጋ በአሥር ሃገሮች በግብርና በመድን ዋስታና በትራንስፖርትና እና የምግብ ኢንዱስትሪ ዘርፍ የሚሰራው /METL/ ግሩፕ የተባለው ኩባኒያ ባለቤት ሲሆኑ ከሁለት ዓመታታ በፊት ፎርብስ መጽሄት የሃብታቸው መጠን እንድ ነጥብ አምስት ቢሊዮን ዶላር መሆኑን አውጥቶ ነበር፡፡ ለእኚህ ሰው መጠለፍ “ኃላፊ ነኝ” ያለ ወገን እስካሁን ብቅ አላለም።

ምንጭ፦ VOA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የመረጃ መደራረብ እና መሰልቸት እንዳይኖር ቻናላችን ለዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ብቻ ይህን ገፅ አዘጋጅቷል! ገፁ ለቀጣይ 1 ወር ብቻ የሚቆይ ነው!

https://telegram.me/TIKVAHUNIVERSITY