TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ETV ZENA Live! የህዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የመክፈቻ ስነ ስርዓት‼️
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በአዲሱ የትምህርትና ስልጠና ፍኖተ ካርታ ዙሪያ የሚደረገዉ ዉይይት በሰላሌ ዩኒቨርሲቲ እንዲሁም በሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ከአካዳሚክ ስታፎችና ከአስተዳደር ሰራተኞች ጋር በጥሩ ሁኔታ እየተካሄደ ይገኛል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update የሕዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባ ዛሬ መስከረም 28 ቀን 2011 ዓ.ም. በፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ንግግር ተከፍቷል። ፕሬዳንት ዶክተር #ሙላቱ_ተሾመ ዛሬ ባደረጉት ንግግር ከኤርትራ ጋር ለተፈጠረው ሰላም ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #ዓብይ_አህመድ እና ለኤርትራ ፕሬዚዳንት አቶ #ኢሳያስ_አፈወርቂ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሊደመጥ የሚገባው‼️ወንዶች ሕፃናት ላይ በተመሳሳይ ፆታ የሚደርስ ፆታዊ ጥቃት እየጨመረ መጥቷል፣ ይህም ሥነልቦናዊ እና ማህበራዊ ቀውሱን እያሰፋው ነው ተብሏል።

ምንጭ፦ ሸገር FM 102.1
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከዲላ⬆️

"በዛሬ ቀን(28/01/2011) በ ጌደኦ ዞን በዲላ ከተማ ለጌህድድ (ጌደኦ ህዝቦች ድምክራስያዊ ድርጅት) አመራሮችና የተደረገዉ የአቀባበል ስነ-ስርዓት በሠላም ተጠናቋል ። አዳኔ ደስታ ከዲላ።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update⬆️በአሰላ ከተማ መናኸሪያ ዉስጥ ከ70 በላይ ሰለታማ መሳሪያዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተሰምቷል።

ምንጭ፦ አሀዱ ሬድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ወይዘሮ #ሎሚ_በዶ የጨፌ ኦሮሚያ አፈ ጉባዔ በመሆን በዛሬው እለት ተመርጠዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሀዘን መግለጫ⬆️የመቀለ ዩኒቨርሲቲ በዶክተር ደረጀ አሰፋ ድንገተኛ ሞት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገልጿል። ለወዳጅ ዘመዶቻቸውና ቤተሰቦቻቸው መፅናናትን ተመኝቷል።

▪️ዶ/ር ደረጀ የቀድሞው የደህንነት ሀላፊ አቶ #ጌታቸው_አሰፋ ወንድም ነበሩ።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ማከም እንጅ አንዳይታከም የተፈረደበት የኢትየጵያ ሐኪም"

እንደሚታወቀዉ የኢትዮጵያ ህዝብ ዘርፈ ብዙ የጤና ችግሮች ያሉበትና በቂ የህክምና ባለሙያ ባለመኖሩ ምክንያት በህክምና እጦት በየቀኑ ብዙ እናቶች፣ ህፃናትና አባቶች እንደሚሞቱ አልያም
በህመም እንደሚሠቃዩ ምስክር መጥራት አያሻም። ይህንን ችግር ለመቅረፍም መንግስት ጥረት እያደረገ ይገኛል። ነገር ግን አንድ ነገር የተዘነጋ ይመስላል። ይህም የጤና ባለሙያው በቂ ትኩረት ያለማግኘቱ ነዉ። ከነዚህም ዉስጥ ዋነኛው የጤና ዋስትና ነው። መቸስ ጤናው ከተጓደለ ባለሙያ ጤና መፈለግ ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ ይሉት አይነት ብሂል ነው። እንደሚታወቀዉ የሌላ መስሪያቤት ሠራተኞች ለምሣሌ ቴሌ፣ አየር መንገድ፣ ባንኮችና ሌሎችም አስከ ውጭ ሀገር የሚደርስ የህክምና ወጪ እንደሚሸፈንላቸው ያደባባይ ሚስጢር ነዉ። ታዲያ የጤና ዋስትና የሆነው የጤና ባለሙያ የጤና እክል ሲደርስበት ማን ዋስትና ይሁነው? ለዚህም ህያው ምስክር ካስፈለገ የዶ/ር ኑሩ አህመድን ጉዳይ ማንሳት በቂ ነው።

ዶ/ር ኑሩ አህመድ ሰይድ በባህርዳር ዩኒቨርስቲ ቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት ሐኪም ሲሆን ላለፉት 6 አመታት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል ሳይማር ያስተማረውን ህብረተሠብ ሲያገለግል ቆይቷል። በቅርብ ጊዜም ይህ የህዝብ ልጅ በበጎ ፈቃደኝነት ወደ ታች ወርዶ ማህበረሰቡን ለማገልገል ካለው ቀናኢነት የተነሳ ከአማራ ክልል ጤና ቢሮ ጋር በመተባበር በዳንግላ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ከ 200 ለሚበልጡ ታካሚዎች የቀዶ ህክምና አገልግሎት የሠጠ ሲሆን በዚያው በማገልገል ላይ እያለም ሰኔና ሰኞ እንዲሉ በደረሰበት አሠቃቂ የመኪና አደጋ የህብለ ሠረሠር(spinal cord) ጉዳት ስለደረሰበት አካሉን ማንቀሳቀስ የማይችልበት ደረጃ ላይ ይገኛል።

በዚህም ምክኒያት #በሀገር ውስጥ ህክምና ሲያደርግ ቢቆይም በቂ እንዳልሆነና ውጪ ሄዶ እንዲታከም የሐኪሞች ቦርድ ወስኗል።

ሆኖም ግን ውጪ ሄዶ ለመታከም ከ 80,000$ (2,240,000 ብር) በላይ ገንዘብ የሚያስፈልግ በመሆኑና እሱም ሆነ ቤተሠቡ ለማሟላት አቅም ስሌላቸዉ ላለፉት 4 ወራት የአልጋ ቁራኛ ሆኖ
ከፍተኛ የሞራል ጉዳት ደርሶበታል። የዶ/ሩ ጉዳት የሱና የቤተሰቡ ጉዳት ብቻ ሳይሆን የ 30,000 ዜጎች ጉዳት ነው። የሱ ጉዳት የጤና ሚኒሰቴር ጉዳት ነው። የሱ ጉዳት የህክምና ማህበሩ ጉዳት ነው። ሆኖም ግን ይህንን ተረድቶ የሚደርስለት አካል እስካሁን አልተገኘም።

የጤና ሚነኒስትሩ ክቡር ዶ/ር አሚር አማን፣ ሚኒሰትር ዲኤታው ደ/ር ከበደ ወርቁ፣ የህክምና ማህበሩ ፕሬዘዳንት ደ/ር ገመቺስ ማሞ እንዲሁም የባ/ዳር ዩኒቨርሲቲ አመራር አካላት በወቅቱ በአካልም ሆነ በስልክ ውጪ ልከው እንደሚያሳክሙት ቃል ቢገቡም ቃላቸው ከፖለቲካ ፍጆታ ሊያልፍ አልቻለም። እንዲያውም በአጓጉል ተስፋ በመደለል ሌሎችን አማራጮች እንዳናይ ተደርገን ከቆየን በሇላ ለሀኪም ማሳከሚያ የሚሆን በጀት የለንም በማለት በሱና ቤተሰቡ እንዲሁም የስራ ባልደረቦቹ ላይ ከፍተኛ የሞራል ውድቀትና የተቆርቋሪ ማጣት ስሜት ውስጥ እንድንገባ አድርጎናል።

የተከበሩ ዶ/ር አሚር፣ ዶ/ር ከበደ፣ ዶ/ር ገመቺስ፣ ዶ/ር ወንድማገኝ:-

ይህ የፖለቲካ ጥያቄ አይደለም። ይህ የብሔር/የሐይማኖት ጥያቄ አይደለም። ይህ የሰብአዊነት ጥያቄ ነው። ይህ የሕዝብን ልጅ ውለታ የመመለስ ጥያቄ ነው። ይህ የሙያ ግዴታን የመወጣት ጉዳይ ነው። ይህ ቃልን የመጠበቅና ለሚወክሉት ማህበረሰብ የመታመን ጉዳይ ነው። ይህ ሙያውንና ሙያተኛውን የማክበርና የማስከበር ጥያቄ ነው።

ይሄኔ ህክምና ፈላጊው ያንድ ባለስልጣን ቤተሰብ (በቅርቡ ከሜቴክ ሁለት ሚለዮን ብር ወጪ ተደርጎ የታከመውን ያንድ የስራ ሃላፊ ልጅ ልብ ይሏል) ወይም የሚዲያ ሠው (የኛው ንፉግ ጤና ሚኒስቴር አፈሩ ይቅለለውና ለጋሽ ፍቃዱ ተ/ማርያም የቲቢ አምባሳደር ስለነበረ ብቻ የህክምና ወጪውን እንደሚሸፍን ገልፆ እንደነበር ይታወሳል) ቢሆን ኖሮ ምን ሊደረግ እንደሚችል ለርሶ መንገር ለቀባሪ ማርዳት ነው።

ማጠቃለያ፦

1ኛ.ለኛው ባልደረባ ዋስትና ሳይኖርህ ለሌላው ዋስትና ለመስጠት ለምትተጋው/ጊው የጤና ባለሙያ ነው:- ዶ/ር ኑሩ አንተ/ች ነህ/ሽ; ጉዳቱ ያንተ/ቺ ነው; ክህደቱ ላንተም/ችም ነው። ስለሆነም ዶ/ር ኑሩን ተረባርበን እናድን በቀጣይም ለመብታችን እንታገል።

2ኛ. ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ:- መተሳሰብ መተዛዘን ባህልህ ነው በተራህ ለሀኪምህ ሀኪም ሆነህ አለኝታነትህን አሳየው።

3ኛ. ለባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ:- ሃምሣ ሎሚ ላንድ ሰው ሸክሙ ለሃምሣ ሰው ጌጡ ነው እንዲሉ ሁላችንም ብንረባረብ እላለሁ። ቸር ያሠማን። አመሠግናለሁ!

"ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን በቂ ነው"
ዶ/ር ኑሩን መርዳት ለምትፈልጉ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር:- ዶ/ር ኑሩ አህመድ ሰይድ 1000063812057 ወይንም ሩቅያ
አህመድ ሰይድ 100094030475

ስልክ ቁጥር፦
+251913885341
+251912125583
ኢሜል [email protected]

#ሼር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዜና እረፍት‼️የኢታብ ሳሙና ፋብሪካ ባለቤት አቶ #እስክንድር_ተስፋዬ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጨፌ ኦሮሚያ በዛሬው እለት እያካሄደ ባለው 4ኛ ዓመት 5ኛ የስራ ዘመን 3ኛ አስቸኳይ ጉባኤ የተለያዩ #ሹመቶችን አፀደቀ።

በዚህም መሰረት፦

1.ዶክተር ግርማ አመንቴ፦ በምክትል ርእሰ መስተዳደር ማእረግ የግብርና ዘርፍ ሀላፊ

2. አቶ አህመድ ቱሳ፦ በምክትል ርእሰ መስተዳደር ማእረግ የኢኮኖሚ ዘርፍ ሀላፊ

3. ወይዘሮ ጠይባ ሀሰን፦ በምክትል ርእሰ መስተዳደር ማእረግ የማህበራዊ ዘርፍ ሀላፊ

4. አቶ አሰግድ ጌታቸው፦ የርእሰ መስተዳድር ጽህፈት ቤት ሀላፊ

5. አቶ ዳባ ደበሌ፦ የግብርና እና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ ሀላፊ

6. ዶክተር ኢንጂነር ፍቃዱ ፉፋ፦ የከተማ ልማትና ቤቶች ቢሮ ሀላፊ

7. አቶ ሙላቱ ጽጌ፦ የንግድ ቢሮ ሀላፊ

8. ዶክተር ሚልኬሳ ሚደጋ፦ የመሬት አስተዳደር እና አጠቃቀም ቢሮ ሀላፊ

9. አቶ ገረመው ሁሉቃ፦ የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሀላፊ

10. ወይዘሮ ሙና አህመድ፦ የሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶች ቢሮ ሀላፊ

11. አቶ አድማሱ ዳምጠው፦
የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሀላፊ

12. አቶ ጥላሁን ወርቁ፦ የኢንተርፕራይዝና ኢንደስትሪ ልማት ቢሮ ሀላፊ

13. ወይዘሮ ፈቲያ መሃመድ፦ የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ሀላፊ

14. አቶ ኤባ ገርባ፦ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ቢሮ

15. ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ፦ የገቢዎች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር

16. አቶ ተሾመ ግርማ ፦ ጠቅላይ አቃቤ ህግ

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጨፌ ኦሮሚያ በዛሬ ውሎው የኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትዎርክ (ኦቢኤን) ዋና ዳርዬክተር እና የቦርድ አባላት #ሹመትን አፅድቋል።

በዚህም መሰረት፦

1. ጋዜጠኛ #መሃመድ_አደሞ፦ የኦቢኤን ዋና ዳይሬክተር

2. አቶ ሽመልስ አብዲሳ፦ የኦቢኤን ቦርድ ሰብሳቢ

3. ወይዘሮ ሌሊሴ ነሜ፦ የኦቢኤን የኦርድ አባል

4. ዶክተር ደረጄ ገረፋ፦ የኦቢኤን የኦርድ አባል

5. አቶ አድማሱ ዳምጠው፦ የኦቢኤን የኦርድ አባል

6. ረዳት ፕሮፌሰር ምህረቱ ሻንቆ

7. ኢንጂነር ወርቁ ጋቸና፦ የኦቢኤን የኦርድ አባል

8. ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ፦ የኦቢኤን የኦርድ አባል በመሆን ተሹመዋል።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Forwarded from Kirubel Niguse
በተመጣጣኝ ዋጋ የሚፈልጉትን ነገሮች ለገበያየት 👇
#አልባሳት
#ጫማዎች
#ኤሌክትሮኒክስ
#ሰዐቶች
#ቦርሳዎች.. 👇
@onlinesaleandbuystore
🛑የሌለን የለም ብቻ ነው!
JOIN ብለው ቤተሰብ ይሁኑ ።
👇👇👇
https://t.iss.one/joinchat/AAAAAEPkyxEP1snCoAkFGw
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)