TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.04K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
መግለጫ⬆️የሰማያዊ ፓርቲ እና የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ የጋራ መግለጫ።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች፦

📌ፈተና ያልተፈተኑ የ1ኛ እና 2ኛ ዓመት ተማሪዎች ምዝገባ- መስከረም 11 እና 12
ፈተና የሚጀመረው - መስከረም 14
የፈተና የሚጠናቀቀው - መስከረም 26
የምዝገባ ቀን - ጥቅምት 1 እና 2

📌5ኛ አመት ተማሪዎች ምዝገባ ቀን - መስከረም 23 እና 24

📌የ3ኛ ዐመት የሆልስቲክ ተፈታኝ ተማሪዎች፦

ጥቅምት 9 እና 10 የመግቢያ ቀን
ጥቅምት 12-24 የፋይናል ፈተና
ህዳር 5-10 የሆልስቲክ ፈተና
ከህዳር 11 በኋላ ባሉት ቀና ምዝገባ

©የተማሪዎች ህብረት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለወጣቶች⬇️

"ሰላም ፀግሽ! ትናንት ቀን ላይ 6 ሰዓት ገደማ ወደ 18 ማዞሪያ ዘመድ ጥየቃ ሄጄ ነበር፡፡ የሆነው ነገር አሳዝኖኛል! #እናቶች ህፃን ልጆቻቸውን ትተው እንደወጡ መግቢያ አተው፡፡ እኔም ያለ እቅዴ አደርኩ እኔ የነበርኩበት ቤት 3 ቤተሰብ አደሯል፡፡ 2 አራስ ልጅ ትተው ለጉዳይ ጠዋት የወጡ ናቸው፡፡ ሚያውቁት ሰው የሌላቸውን አስብ፡፡ እባካችሁ ወጣቶች ጊዜያዊ #ስሜት አይምራን! ሊከተል የሚችለውንም ሰከን ብለን እናስብ፡፡ ሀገር ወዳድ ዜጋ ለእናቶቹ፣ ለእህቶቹ፣ በአጠቃላይ ለወገኖቹ ሰላምና ነፃነት ቅድሚያ የሚሰጥ ነው፡፡ "ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን አብዝቶ ይባርክ፡፡" መልካም ምሽት፡፡"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ⬆️የ2011 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የምዝገባ ቀናትን ከላይ ባለው ማስታወቂያ መረጃ ማግኘት ትችላላችሁ።

©J
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዝግ የሚሆኑ መንገዶች📌ነገ በመስቀል አደባባይ ለኦነግ አመራሮች የሚደረገው አቀባበል ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ድረስ በአዲስ አበባ #ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን ፖሊስ ይፋ አደረገ።

በዚህም መሰረት፦

▪️ከቀድሞ ኢምፔሪያል ሆቴል ወደ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ፣ ከቦሌ ሚካኤል ወደ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ፣

▪️በኡራኤል፣ ባምቢስ አብዮት አደባባይ፣ ከአራት ኪሎ፣ ብሄራዊ ቤተመንግስት ወደ እስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን ከካዛንቺስ፣ ብሄራዊ ቤተ መንግስት ፍል ውሃ፣

▪️ከንግድ ማተሚያ ቤት ኦርማ ጋራዥ፣ ፍልውሃ፣ ሃራምቤ ሆቴል፣ ከቴድሮስ አደባባይ፣ ኢሞግሬሽን፣ ፣ ሀራምቤ ሆቴል፣ ስታዲየም፣

▪️ከጎማ ቁጠባ፣ ብሄራዊ ትያትር፣ ስታዲየም፣ ሜክሲኮ፣ ከሰንጋ ተራ፣ በድሉ ህንፃ ስታዲየም፣

▪️ከሰንጋ ተራ፣ በለገሃር፣ ስታዲየም፣
በቂርቆስ አዲሱ መንገድ፣ በለገሃር ስታዲየም፣

በሀራምቤ ሆቴል፣ ጋንዲ ሆስፒታል፣ ወደ መስቀል አደባባይ፣

▪️ከአጎና ሲኒማ፣ በአራተኛ ክፍለ ጦር ወደ መሰቀል አደባባይ ያሉ መንገዶች #ለጊዜው የተዘጉ መሆናቸውን አስታውቆአል።

©fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰበር ዜና📌

ከአዲስ አበባ ግጭቱ ጀርባ፦

በከተማዋ የሚታየዉ #የፀጥታ ችግር በቀን ጅቦች #ስፖንሰርነት ቅጥረኞች ያነሱት መሆኑ ታዉቋል። አለማዉ ህዝቡን በማባላት ወደ #ሥልጣን መመለስ ነዉ። ቅጥረኞች ሰልጥነዉ የተሰማሩ ከመሆናቸዉም በላይ በሞተር ሳይክል፣ በቤት መኪና እና በፕካፕ ገንዘብ እየተበተነላቸዉ መሆኑን የአይን እማኞች ገልፇል። ረብሻኞቹ ከሌላ ቦታ ተመልምሎ የመጡ ሲሆን የአዲስ አበባ ወጣት የለበትም። በብዙ ቦታዎች ደግሞ የአዲስ አበባ ህዝብ ግጭት እንዳይፈጠር ሲከላከል እንደነበር ታዉቋል። የግጭት ፕሮጄክቱ ሙሉ በሙሉ የፀረ-ለዉጥ ኃይሉ መሆኑ በተጨባጭ ማስረጃ ተረጋግጧል! ባንዲራ #ሽፋን እንጂ መነሻ አይደለም። ሁለቱንም ባንዲራ የማይወዱ ሰዎች አንዱን ደግፎ ሌላዉን የተቃወሙ ያስመስላል።

ማስታወሻ፦

1. የረብሻኞቹ ፎቶ እና ቪዲዮ ይቀረፅ
2. የመኪኖቹ ታርጋ ይመዝገብ
3. ማስረጃ ለፌዴራል እና ለአዲስ አበባ ፖሊስ አድርሱ።

Oduu Ammee📌

Jeequmsi #Finfinnee waraabeyyii guyyaatiin kan qindeeffame ta'uu barameera. Jeeqxoti bakka biraatii filatamanii leenjifamuun bobbaafaman. Makiinaan maallaqa hiraa akka jiranis barameera.

Bakka jeequmsi jirutti suuraa fi viidiyoo jeeqxotaa waraabuu fi taargaa konkolaataa qabuu hin dagatinaa!

ምንጭ፦ አቶ ታዬ ደንደአ(የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ የህዝብ ግንኙነት)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update⬆️በነገው እለት አዲስ አበባ የሚገባውን የኦነግ አመራር ለመቀበል ከምሽት ጀምሮ አብዮት አደባባይ የሚገኙት #ቄሮዎች ምግብና መጠጥ እንዳላገኙ መገለጹን ተከትሎ የአዲስ አበባ ወጣቶች ከላይ በምስሉ በምትመለከቱት መልኩ ዳቦና ውኃ ይዘው እየሄዱ ይገኛሉ። #ኢትዮጵያዊነት ይህ ነው፤ ሌሎችም የከተማችን ወጣቶች አብዮት ለሚገኙት ወገኖቻችን እንድረስላቸው።

©ኤርሚያስ ቶኩማ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሁን⬆️ሁሉም አዲስ አበባ ወጣት እና ሌላውም ነዋሪ ለመልካም ስራ እንዲነሳ ጥሪ ቀርብሏል። መስቀል አደባባይ የሚገኙ ወንድሞች እና እህቶቹን እንዲደግፍ እና ለፍቅር እንዲቆምም ጥሪ ቀርቧል።

ፍቅር ያሸንፋል!
ኢትዮጵያዊነት ይለምልም!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ለፍቅር ተነሱ! ለአንድነት ተነሱ! በፈጣሪ ዘንድ ሁላችንም አንድ የሰው ልጆች ነን! ከሀገር፣ ከባንዲራ፣ ከብሄር፣ ከክልል፣ ከዘር ከሁሉም ነገር በፊት ሰውነት ይቀድማል!

ፍቅር ያሸንፋል!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዲስ አበባ-አሁን⬆️

እንደ #አቅማችን ያዘጋጀነውን እህል ውሀ መስቀል አደባባይ ምሽቱን ለሚያሳልፉ ቄሮዎች አድርሰን ከአስተባባሪዎቹ ጋር የማስታወሻ ፎቶ ተነስተናል።

ከኛ ቀደም ብለው ይሁን ከእኛም በኋላ ከየአካባቢው የመጡ በርካታ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች የምግብና የውሀ ችግር እንዳይደርስባቸው ከፍተኛ #ትብብር እያደረጉ ነው።

አስተባባሪዎቹ እንዲህ አሉኝ "የውሀም የምግብም መስተንግዶ የአዲስ አበባ ልጆች ስላደረጉልን ተደስተናል። #ገለቶማ"
.
.
በሠላምና በፍቅር የነገው ዝግጅት እንዲጠናቀቅ ምኞቴ ነው። ቸር አምላክ ህዝብህን አደራ።

©ያሬድ ሹመቴ(የፊልም ዳይሬክተር)

@tsegabwolde @tikvahethiopia