TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ፎቶ⬆️ዛሬ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ሉሜ ወረዳ #የተከሰከሰው የመከላከያ ሰራዊት አውሮፕላን በፎቶው የትመለከቱትን ይመስላል። በዚህ አደጋ የ18 ዜጎቻችን ህይወት አልፏል።

ፎቶ፦ ኢቲቪ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ዶክተር #አብይን ጨምሮ የበርካቶችን ስሜት የነካው እና ያስለቀሰው በሱማሌ ክልል ተወላጅ በሆነ ወጣት ላይ የክልሉ መንግስት የፈፀመው ግፍ።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰበር ዜና⬆️ሜድሮክ ኢትዮጲያ ለአዲስ ተስፋ ቀመር የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ማስፈጸሚያ እና አቅመ ደካሞችን ለመደገፍ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባዘጋጀው የእራት ግብዣ ላይ የ23 ሚሊየን ብር #ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገብቷል።

©ምክትል ከንቲባ ዳግማዊት ሞገስ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለ10ኛ ክፍል ተማሪዎች📌ማትሪክ ዛሬ ወጥቷል እየተባለ የሚወራው ውሸት ነው። ምንም የወጣ ወይም ይፋ የተደረገ የ10ኛ ክፍል ውጤት የለም።

▪️በለፈው ሳምንት ከመንግስት እንደሰማነው የ10ኛ ክፍል ውጤት እንዲሁም የ12ኛ ክፍል ማለፊያ ነጥብ ከነሀሴ 25-30 ባሉት ቀናት ውስጥ ይወጣል። ነገ የሚወጣ ከሆነ ተከታትዬ አሳውቃችኋለሁ።

📌በተለያዩ ገፆች ላይ የምታገኟቸውን ሀሰተኛ መረጃዎች ከመቀበል ተቆጠቡ። እንዲሁም ለሰዎች ከማጋራት ተቆጠቡ። በርካታ ሰዎች በተማሪዎች ስም መነገድ እና ማጭበርበር ጀምረዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ማሰታወቂያ⬆️

የዜግነት ለውጥ ያለባችሁ ተማሪዎች በሙሉ፦ ኢትዮጵያዊ ዜግነት ለሌለው ተማሪ በዩኒቨርሲቲ ምደባ ስለማይመደብ የዜግነት ለውጥ ያለባችሁ ተማሪዎች ከት/ቤታችሁ ኢትዮጵያዊነትን የሚገልፅ ደብዳቤ በማፃፍ በኢሜል [email protected] ወይም በፋክስ ቁጥር 0111232883 መላክ ያለባችሁ መሆኑን እንሳውቃለን፡፡ 

የተማሪዎች ፊልድና ዩኒቨርሲቲ ምርጫ ስትሞሉ ድጋፍ ለምትፈልጉ ት/ቤት ተወካዮች በክፍሉ ባለሞያዎች ስልክ ቁጥሮች ብቻ ይደዉሉ !!!! 

የክፍሉ ስልክ = 0111260971
አቶ ሹምዬ አበራ = 0910964274
ወ/ሮ ሙሉወርቅ ተስፋዬ = 0911571491

#ማሳሰቢያ ፡ መስመሩ ሲያዝ ደግመው ይሞክሩ እንጅ ወደማይመለከትዉ ኣካል ደውለው መልስ ባይጠብቁ እንመክራለን።

©neaea
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አማራ ክልል⬇️

በአማራ ክልል በዚህ ዓመት በትራፊክ አደጋ የ1 ሺህ 1 መቶ ሀምሳ ሁለት(1152) ሰዎች ህይወት ማለፉ ተሰማ፡፡ ባለፈው አመት በክልሉ በታራፊክ አደጋ ምክንያት ህይወታቸው ከጠፋ ሰዎች ቁጥር አንፃር የዘንድሮው በልጦ ተገኝቷል። ባለፈው ዓመት በትራፊክ አደጋ 1 ሺህ ዘጠና ስድስት(1096) ሰዎች ህይወታቸው ያለፈው፡፡

በሌላ በኩል⬇️

▪️በክልሉ በዚህ አመት 8 መቶ 57(857) ተሸከርካሪዎች አደጋ አድርሰዋል። ባለፈው ዓመት ደግሞ 7መቶ 96(796) ተሸከርካሪዎች አደጋ አድርሰዋል፡፡

የችግሩን አሳሳቢነት ለማሳወቅ ፣ ለመጠየቅ እና እውቅና ለመፍጠር ከህጻን እስከ አዋቂ የሚሳተፍበት #ሰልፍ ነገ በዋና ከተማዋ #ባህርዳር መዘጋጀቱን ከአማራ ክልል የመንገድ ትራንስፖርት ቢሮ ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የሴኔጋል ፕሬዝዳንት ማኪ ሳል በሴኔጋል ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ግለሰቦች የሚሰጠውን "Royal Order of the Lion" የተሰኘውን የክብር ሽልማት ለአለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር #ቴድሮስ_አድሃኖም መስጠታቸው ተሰምቷል፡፡

©etv
@tikvahethiopia @tsegabwolde
"ክፉ ሰው እንጂ ክፉ ብሄር የለም!"

~ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ~

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ኢትዮጵያ ውስጥ አሁን እየታየ ያለው ለውጥ እንዲመጣ ከፍተኛ “አስተዋጽዖ አድርገዋል፤ መስዋዕትነት ከፍለዋል” ኢትዮጵያዊያን ዕውቅና ለመስጠት ሥራ መጀመሩን አንድ የሽልማት ድርጅት አስታውቋል።

ይህ ለውጥ እንዲመጣ ከሰባት ዓመት ሕፃን ልጅ እስከ አዛውንት ሕይወታቸውን ገብረዋል ያሉት የዕውቅናው ሥርዓት አዘጋጆች ዕውቅናው እነዚህንና በአመራር ላይ ያሉ ሰዎችንም እንደሚያካትት ገልፀዋል።

©VOA
@tsegabwolde @tikvahethiopia