TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
214 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update አዲስ አበባ⬆️

"ጥላቻን መቀነስ(-) ይቅርታን ማባዛት(*) ያለንን ማካፈል (፥) በፍቅር መደመር (+) ብለን ተነስተን ከጠበቅነው በላይ #ድጋፍ አግኝተናል። ከአርቲስቶች፣ ከአትሌቶች፣ ከወጣቶች፣ ከዲያስፓራው እና በተለያየ አካባቢ የሚገኙ ተጽእኖ ፈጣሪዎች ጋር ውይይት አድርገን #ውጤታማ ስራ ተሰርቷል። በዛሬው እለትም በተመሳሳይ በተለያየ ዘርፍ ከተሰማሩ ባለሀብቶች ጋር ውይይት በማካሄድ ላይ እንገኛለን።"

©ምክትል ከንቲባ ዳግማዊት ሞገስ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ⬆️ዛሬ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ሉሜ ወረዳ #የተከሰከሰው የመከላከያ ሰራዊት አውሮፕላን በፎቶው የትመለከቱትን ይመስላል። በዚህ አደጋ የ18 ዜጎቻችን ህይወት አልፏል።

ፎቶ፦ ኢቲቪ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ዶክተር #አብይን ጨምሮ የበርካቶችን ስሜት የነካው እና ያስለቀሰው በሱማሌ ክልል ተወላጅ በሆነ ወጣት ላይ የክልሉ መንግስት የፈፀመው ግፍ።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰበር ዜና⬆️ሜድሮክ ኢትዮጲያ ለአዲስ ተስፋ ቀመር የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ማስፈጸሚያ እና አቅመ ደካሞችን ለመደገፍ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባዘጋጀው የእራት ግብዣ ላይ የ23 ሚሊየን ብር #ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገብቷል።

©ምክትል ከንቲባ ዳግማዊት ሞገስ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለ10ኛ ክፍል ተማሪዎች📌ማትሪክ ዛሬ ወጥቷል እየተባለ የሚወራው ውሸት ነው። ምንም የወጣ ወይም ይፋ የተደረገ የ10ኛ ክፍል ውጤት የለም።

▪️በለፈው ሳምንት ከመንግስት እንደሰማነው የ10ኛ ክፍል ውጤት እንዲሁም የ12ኛ ክፍል ማለፊያ ነጥብ ከነሀሴ 25-30 ባሉት ቀናት ውስጥ ይወጣል። ነገ የሚወጣ ከሆነ ተከታትዬ አሳውቃችኋለሁ።

📌በተለያዩ ገፆች ላይ የምታገኟቸውን ሀሰተኛ መረጃዎች ከመቀበል ተቆጠቡ። እንዲሁም ለሰዎች ከማጋራት ተቆጠቡ። በርካታ ሰዎች በተማሪዎች ስም መነገድ እና ማጭበርበር ጀምረዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ማሰታወቂያ⬆️

የዜግነት ለውጥ ያለባችሁ ተማሪዎች በሙሉ፦ ኢትዮጵያዊ ዜግነት ለሌለው ተማሪ በዩኒቨርሲቲ ምደባ ስለማይመደብ የዜግነት ለውጥ ያለባችሁ ተማሪዎች ከት/ቤታችሁ ኢትዮጵያዊነትን የሚገልፅ ደብዳቤ በማፃፍ በኢሜል [email protected] ወይም በፋክስ ቁጥር 0111232883 መላክ ያለባችሁ መሆኑን እንሳውቃለን፡፡ 

የተማሪዎች ፊልድና ዩኒቨርሲቲ ምርጫ ስትሞሉ ድጋፍ ለምትፈልጉ ት/ቤት ተወካዮች በክፍሉ ባለሞያዎች ስልክ ቁጥሮች ብቻ ይደዉሉ !!!! 

የክፍሉ ስልክ = 0111260971
አቶ ሹምዬ አበራ = 0910964274
ወ/ሮ ሙሉወርቅ ተስፋዬ = 0911571491

#ማሳሰቢያ ፡ መስመሩ ሲያዝ ደግመው ይሞክሩ እንጅ ወደማይመለከትዉ ኣካል ደውለው መልስ ባይጠብቁ እንመክራለን።

©neaea
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አማራ ክልል⬇️

በአማራ ክልል በዚህ ዓመት በትራፊክ አደጋ የ1 ሺህ 1 መቶ ሀምሳ ሁለት(1152) ሰዎች ህይወት ማለፉ ተሰማ፡፡ ባለፈው አመት በክልሉ በታራፊክ አደጋ ምክንያት ህይወታቸው ከጠፋ ሰዎች ቁጥር አንፃር የዘንድሮው በልጦ ተገኝቷል። ባለፈው ዓመት በትራፊክ አደጋ 1 ሺህ ዘጠና ስድስት(1096) ሰዎች ህይወታቸው ያለፈው፡፡

በሌላ በኩል⬇️

▪️በክልሉ በዚህ አመት 8 መቶ 57(857) ተሸከርካሪዎች አደጋ አድርሰዋል። ባለፈው ዓመት ደግሞ 7መቶ 96(796) ተሸከርካሪዎች አደጋ አድርሰዋል፡፡

የችግሩን አሳሳቢነት ለማሳወቅ ፣ ለመጠየቅ እና እውቅና ለመፍጠር ከህጻን እስከ አዋቂ የሚሳተፍበት #ሰልፍ ነገ በዋና ከተማዋ #ባህርዳር መዘጋጀቱን ከአማራ ክልል የመንገድ ትራንስፖርት ቢሮ ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የሴኔጋል ፕሬዝዳንት ማኪ ሳል በሴኔጋል ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ግለሰቦች የሚሰጠውን "Royal Order of the Lion" የተሰኘውን የክብር ሽልማት ለአለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር #ቴድሮስ_አድሃኖም መስጠታቸው ተሰምቷል፡፡

©etv
@tikvahethiopia @tsegabwolde