TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#የጠፋ_መታወቂያ

የአዲስ አበባ አስተዳደር ወሳኝ ኩነት ምዝገባ እና መረጃ ኤጀንሲ #ለጠፋ_መታወቂያ_አገልግሎት ለመስጠት ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታውቋል።

ኤጀንሲው ይህንን ያሳወቀው ዛሬ ለአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ በሰጠው ቃል ነው።

የአዲስ አበባ የወሳኝ ኩነት ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ፤ " ለጠፋ መታወቂያ አገልግሎት ለመስጠት ዝግጅት አጠናቀናል " ያሉ ሲሆን " ይህንንም በቀጣይ ሳምንት ውስጥ ወደ ተግባር ለማስገባት እየተሰራ ይገኛል " ብለዋል፡፡

በሌላ በኩል ፤ በአዲስ አበባ ተቋርጦ የቆየው የመታወቂያ እድሳት አገልግሎት ባለፈው ህዳር 1 ቀን በድጋሚ ከጀመረ ወዲህ  ከ250 ሺ በላይ ተገልጋዮች አገልግሎቱን ማግኘት መቻላቸውን ኤጀንሲው አሳውቋል።

ኤጀንሲው " አዲስ የአገልግሎት ምዕራፍ " በሚል ህዳር 1 ቀን 2015 ዓ/ም በተጀመረ የመታወቂያ አገልግሎት የተገልጋዮችን መጉላላት ለመቀነስ ቅዳሜ እና እሁድን ጨምሮ ከስራ ሰዓታት ውጪ አገልግሎት ሲሰጥ መቆየቱን ገልጿል።

በእድሜና በጤና እክል ምክንያት በአካል ተገኝተው መገልገል ላልቻሉ ዜጎችም የቤት ለቤት አገልግሎት ሲሰጥ መቆየቱን ኤጀንሲው ለአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ተናግሯል።

በአዲስ አበባ ከተማ ከመታወቂያ አገልግሎት ጋር በተያያዘ አገልግሎቱ ተቋርጦ መቆየቱ በርካቶች ብዙ ጉዳያቸው እንዲስተጓጎል አድርጎ ቆይቷል ፤ የእድሳት አገልግሎት ከተጀመረ በኃላም የቲክቫህ ቤተሰብ አባላትን ጨምሮ ሌሎችም ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር የተያያዘ ቅሬታ እንዳላቸው ፤ ሰዓታቸውም በዚሁ ጉዳይ እየጠፋና አንዳንዳችም እየተጉላሉ ስለመሆኑ ይገልፃሉ።

በ " መታወቂያ እድሳት " አገልግሎት ጉዳይ ምን ገጠማችሁ ? ምን በጎ ጎንና ክፍተት ያለባቸውን ተግባራት ታዘባችሁ ? @tikvahethiopiaBOT

@tikvahethiopia