TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ለአዲስ አበባ ነዋሪዎች!

በአቃቂ መሿለኪያ ድልድይ የሚያልፍበት ወንዝ ሙላት ምክንያት የሚፈጠሩ እንግልቶችን ለማስቀረት ህብረተሰቡ የተለያዩ የመንገድ #አማራጮችን እንዲጠቀም የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ያሳስባል፡፡

አማራጮችን ለመጠቆም ያህል፡-

1. ወደ ምስራቅ አዲስ አበባ መሄድ የሚፈልጉ ተሽከርካሪዎች ከደቡብ አፍሪካ ዩኒቨርሲቲ አደባባይ ወደ ቱሉ ዲምቱ ማሳለጫ (ወደ ጎሮ የሚወስደውን ውጫዊ የቀለበት መንገድ) መጠቀም ይችላሉ።

2. ወደ መሃል አዲስ አበባ ለመሄድ የሚፈልጉ ተሸከርካሪዎች ዋናውን አቃቂ ድልድይ መጠቀም ይችላሉ።

3. ወደ ምዕራብ አዲስ አበባ መሄድ የሚፈልጉ ተሸከርካሪዎች ከደቡብ አፍሪካ ዩኒቨርሲቲ አደባባይ በግራ በኩል ወደ ለቡ የሚወስደውን ውጫዊ የቀለበት መንገድ መጠቀም ይችላሉ።

4. ከአዲስ አበባ ወደ ምስራቅ አቅጣጫ የሚጓዙ ተሸከርካሪዎች በላይ አብ ሞተርስ አለፍ ብሎ ወደ ቱሉ ዲምቱ ኮንዶሚኒየም በመታጠፍ መስቀለኛ መንገዱን መጠቀም ይቻላሉ።

እንደሚታወቀው ቃሊቲ ቀለበት መንገድ አደባባይ - ቱሉ ዲምቱ አደባባይ መንገድ ለረጅም ጊዜ የከተማው የምስራቅ መውጫ በር በመሆን በማገልገሉ ምክንያት በመጎዳቱ እና የሚያስተናግደውም የትራፊክ መጠን በከፍተኛ ሁኔታ በማደጉ ወቅቱ የሚጠይቀውን አገልግሎት መስጠት እንዲችል ማስተር ፕላኑን ጠብቆ እንደ አዲስ በመገንባት ደረጃውን የማሻሻል ስራ እየተከናወነ ይገኛል፡፡

በዚህ አጋጣሚ የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በክረምት ወራት በሚጥለው ከፍተኛ መጠን ያለው ዝናብ በመንገዶች ላይ በሚፈጥረው #የጎርፍ ችግር ምክንያት በነዋሪዎች እንቅስቃሴ ላይ ለሚፈጠረው መስተጓጎል ይቅርታ እየጠየቀ አሽከርካሪዎች ከምን ጊዜውም በላይ ሲያሽከረክሩ ቅድመ ጥንቃቄ በማድረግ እና ሌሎች የመንገድ አማራጮች በመጠቀም ከጎርፍ ስጋትና ከእንግልት እንዲድኑ ይመክራል፡፡

©የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን
@tsegbwolde @tikvahethiopia
#የድሬዳዋ ቤተሰቦቻችን እንኳን በደህና መጣችሁልን!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ለሳምንታት ተዘግቶ የቆየው የምስራቁ የኢትዮጵያ ክፍል የኢንተርኔት አገልግሎት በዛሬው ዕለት መስራት ጀምሯል።

#አሰበ
#ሀረማያ
#ድሬዳዋ
#ጅግጅጋ
#ሀረር...እንዲሁም በሁሉም የምስራቁ የኢትዮጵያ ክፍል የምትገኙ ቤተሰቦቻችን እንኳን በደህና መጣችሁ! እንኳን በሰላም ተገናኘን!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ሜቴክ ፕሮጀክቱን ተነጠቀ⬇️

በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፓሬሽን (ሜቴክ) በግምባታ ሂደት ላይ የነበረዉና ይጠናቀቃል ተብሎ ከታቀደለት ጊዜ በኋላም መጠናቀቅ ያልቻለዉ የኦሞ ኩራዝ አንድ የስኳር ፋብሪካ ፕሮጀክት ከሜቴክ መነጠቁን ዋልታ የዉስጥ ምንጮቼ ገልፀውልኛል ብሎ ዘግቧል፡፡

ከኩራዝ አንድ #በኋላ ግንባታቸዉ በቻይና ኩባንያዎች የተጀመሩት የኩራዝ አንድና #ሁለት ፕሮጀክቶች ግንባታቸዉ #ተጠናቆ ማምረት የጀመሩ ሲሆን #በሜቴክ ግንባታዉ የተጀመረዉ ኩራዝ አንድ ግን ግንባታዉ እስካሁን #አልተጠናቀቀም፡፡

©ዋልታ ሚዲያ እና ኮሚኒኬሽን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ነገ ቅዳሜ ነሐሴ 19 ቀን 2010 ዓ.ም ከዘጠኝ ሰዓት ጀምሮ ከሃገር ውስጥ የመገናኛ ብዙሃን ጋዜጠኞች በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ለሚቀርቡላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያ ይሰጣሉ።

@tsegabwolde @tikvhethiopia
#update ጌትፋም ሆቴል⬆️

በአሁን ሰዓት የአክቲቪስት ታማኝ በየነ አቀባበል ስነ ስርዓትን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ እየተሰጠ ይገኛል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አዲስ አበባ⬆️

በምክትል ከንቲባ ኢንጂነር #ታከለ_ኡማ ሰብሳቢነት የሚመራው እና የፌደራል ፖሊስ ፣ የአዲስ አበባ እና የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽኖችን ያካተተው የፀጥታ ግብረሀይል ሳምንታዊ ውይይት አድርጎል። በተለይ በመዲናዋ የአዲስ አመት በዓል ያለምንም #የፀጥታ ችግር እንዲከበር በሚደረጉ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ላይ ተወያይተዋል።

ህብረተሰቡ የሚመለከታቸውን #አጠራጣሪ ነገሮች #ለፖሊስ በማሳወቅ አካባቢውን በንቃት እንዲጠብቅ ግብረሀይሉ #አሳስቧል

ግብረሀይሉ በህገወጥ መንገድ ወደ አዲስ አበባ የገቡ 300 የሚሆኑ ሞተር ሳይክሎችን በቁጥጥር ስር እንዲውሉ አድርጎል። በተመሳሳይ ከቀናት በፊት በርካታ ቁጥር ያለው ህገወጥ የጦር መሳሪያ በቁጥጥር ስር መዋሉ ይታወሳል።

©የአዲስ አበባ ኮሚኒኬሽን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ESAT አዲስ አበባ⬆️

በአሜሪካ መቀመጫውን ያደረገው የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን እና ራድዮ ዛሬ በጌትፋም ሆቴል በነበረው የአክቲቪስት ታማኝ በየነ የአቀባበል ስነስርዓት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተገኝቶ ነበር።

©ስንታየሁ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update⬆️የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን የሩዋንዳ አቻቸውን 4 - 2 (በፍፁም ቅጣት ምት) በማሸነፍ ለፍፃሜ ጨዋታ ማለፍ ችሏል።

እንኳን ደስ አላችሁ! እንኳን ደስ አለን!
@tsegabwolde @tikvahethiopia