TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
60.7K photos
1.54K videos
215 files
4.22K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#እንድታውቁት

" ለአጭር ደቂቃም ሆነ ለሰዓት በመንገድ ዳር መቆም አይቻልም " - የትራንስፖርት ቢሮ

ወደ አዲስ አበባ ከተለያዩ የአፍሪካ ብሎም ዓለም አገራት እንግዶች እየገቡ ናቸው።

ይህን ተከትሎ ከዛሬ ጀምሮ እስከ የካቲት 09/2017  ዓ.ም  ማታ 12:00  ድረስ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ፦
- በኤሌክትሮኒክ ታክሲ ስርዓት (ኤታስ) አገልግሎት የሚሰጡ የሜትር ታክሲ፣
- የላዳ፣
- የታክሲ እና መሰል ተሽከርካሪዎችን የሚያሽከረክሩ አሽከርካሪዎች በኮሪደር ልማት በለሙና የእንግዶች መተላለፊያ በሆኑ መንገዶች ላይ ለአጭር ደቂቃም ሆነ ለሰዓት በመንገድ ዳር መቆም እንደማይችሉ የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ አሳውቋል።

@tikvahethiopia
#Tigray

በእንዳስላሴ ሽረ ከተማ በህዝብ መዝናኛ ስፍራ በተጣለ የእጅ ቦምብ 10 ሰዎች ከባድ እና ቀላል ጉደት ደረሰባቸው።

የሰው ህይወት አለማለፉን ለመረዳት ተችሏል።

የቦምብ ጥቃቱ አድራሾች እና ግብረ አበሮቻቸው ለመያዝ የተጠናከረ ክትትል እና ምርመራ እያደረግኩ ነው ብሏል ፖሊስ።

ጥቃቱ መቼና ? የት ? እንዴት አጋጠመ ?

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ፤ በስፍራው የነበሩ የአይን እማኞችን አግኝቶ አነጋግሯል።

ጥቃቱ የካቲት 3/2017 ዓ.ም ከምሽቱ 1:40 ቀበሌ 05 በሚገኝ የአንድ ግለሰብ የመዝናኛ ስፍራ ነው የደረሰው።

የመዝናኛ ቤቱ ባለቤት ሰሞኑን ከማያወቀው ሰው በሞባይል እየተደወለ የማስፈራርያ መልእክት ይደርሰው እንደነበር ፤ የመልእክቱ አንኳር ነጥብ " እስከ 400 ሺህ ብር እንዲከፍል " ይህንን ካላደረገ ግን አደጋ እንደሚደርስበት የሚገልጽ ማስጠንቀቅያ ነው።

ግለደቡ የማስፈራርያ ዛቻውን በሰዓቱ ለፓሊስ ያደርስ እንደነበረ ነው የተነገረ ሲሆን ጥቃቱ ከመድረሱ ከአንድ ቀን በፊት ሳይቀር ዛቻውን ተጠናክሮ ቀጥሎ ነበር።

የመዝናኛ ቤቱ ባለቤት ስጋቱ አይሎበት ፓሊስ ጣብያ ድረስ በመሄድ የጉዳዩን አሳሲበነት አስረድቶ ፓሊስ በተባለው አከባቢ ከየካቲት 2/2017 ዓ.ም በመከታተል እያለ ቦምቡ መጣሉ ከከተማው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ የደረሰው መረጃ ያመልክታል።

የተጣለው ቦምብ በ10 ሰዎች ላይ ጉዳት ያደረሰ ሲሆን አንድ ሴት የምትገኝባቸው ሦስት ሰዎች ላይ  ከባድ ፡ ሰባት ሰዎች ላይ ደግሞ ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል።

የከተማው ፓሊስ ተጠርጣሪዎች ከግብረ አበሮቻቸው ጋር ለመያዝ ክትትል እና ምርመራውን አጠናክሮ መቀጠሉ ገልፆ ህዝቡ መረጃ በመስጠት ከጎኑ እንዲሰለፍ ጥሪ አቅርቧል።

ከቀናት በፊትም በከተማዋ በአስፋልት ዳር ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች አንድ ሰው ተገድሎ መገኘቱ የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ መረጃውን አጋርቶናል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
“የተነሳበትን አካባቢ ጉዳት አድርሷል። ግን አሁንም ሙሉ ለሙሉ አልጠፋም” - ባለስልጣኑ

በአፋር ክልል ሃላይዳጌ አሰቦት ብሔራዊ ፓርክ ከተነሳ ቀናት ያስቆጠረው ቃጠሎ በቁጥጥር ሥር ባለመዋሉ ለማጥፋት ርብርብ እየተደረገ መሆኑን የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ባለስልጣን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጸ።

የተቋሙ የህዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ አቶ ናቃቸው ብርሌው በሰጡን ማብራሪያ፣ የእሳት ቃጠሎ በተነሳበት አካባቢ ጉዳት እንዳደረሰ፣ የጉዳት መጠኑን የሚታወቀው ቃጠሎው ሲቆም መሆኑን ገልጸዋል።

አቶ ናቃቸው በዝርዝር ምን አሉ ?

“ በእርግጥ ብሔራዊ ፓርኩ ውስጥ ነው የእሳት ቃጠሎው የተነሳው። ምክንያቱ በሂደት የሚጣራ ቢሆንም በሰው ሰራሽ ምክንያት እንደተከሰተ ነው የሚገመተው።

በባሕሪው ብሔራዊ ፓርኩ ሳራማ ምድር (Grass land) ነው። ለመቆጣጣር አስቸጋሪ እንደነበር ነው ያገኘነው መረጃ የሚያሳየው።

በአካባቢው አውራ ጎዳና መንገድ የሚሰሩ፣ የአፋር ብሔራዊ ክልል ከአሚባራ ወረዳ ጋር በመተባበር የፍየር ብሬኪንግ (የመጥረግ፣ የመቁረጥ ስራ) በግሬደር እየተሰራ ነው።

ፋየር ብሬኪንግ ተርቷል እሳቱ ወደ ሌላኛው ክፍል እንዳይዛመት የመጥረግ ሥራ እየተሰራ ነው ” ሲሉ ተናግረዋል።

አሁንስ የእሳት ቃጠሎው በቁጥጥር ስር ውሏል ? ስንል ላቀረብነው ጥያቄ በሰጡን ምላሽ “ ከፍተኛ ጉዳት እንዳያደርስ፣ ወደልላኛው የፓርኩ ክፍል እንዳይስፋፋ ነው የቆረጣ ሥራ የሚሰራው ሳሩ ልክ የመንገድ ያክል በግሬደር እየተቆረጠ ነው ” ሲሉ መልሰዋል።

“ የተነሳበትን አካባቢ ጉዳት አድርሷል። ግን አሁንም ሙሉ ለሙሉ አልጠፋም ” ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

እስካሁን በቃጠሎው በምን ያክል ሄክታር መሬት ላይ ጉዳት እንደደረሰ ታውቋል ? ለሚለው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ “ የእሳት ቃጠሎው በቁጥጥር ስር ሲውል ወይም መጥፋቱ ሲረጋገጥ የጉዳቱ አይነቱና መጠኑ የሚታወቀው ያኔ ነው ” ሲሉ መልሰዋል።

“ እስቲል የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን የሰው ኃይል የሎጂስቲክስ ድጋፍ በማድረግ፣ ባለሙያዎችን በመመደብ በአዋሳኝ የሚገኘው የአዋሽ ብሔራዊ ፓርክ ተሽከርካሪዎችን ጭምር በመውሰድ እሳቱን ለሚያጠፉ ኃይሎች ድጋፍ እየተደረገ ነው ” ብለዋል።

ሰሞኑን በተለያዬ ፓርኮች እየተከሰቱ ያሉ የእሳት ቃጠሎን ምንነት ጠይቀናቸው በሰጡን ምላሽም፣ “ በእርግጥ እንዲህ አይነት ሁኔታዎች የሚከሰቱት ከወቅቱ ጋር ተያይዞ ነው። ከፍተኛ ሙቀት፣ ደረቅ የአየር ሁኔታ ስላለ ” ነው ያሉት።

“ እነዚህ ጥብቅ ቦታዎች በባህሪያቸው ደንም ይሁን ሳር ስላላቸው ትንሹም ቃጠሎ በቀላሉ የመስፋፋት እድል አለው። ብዙዎቹ የሚስተዋሉትም በተፈጥሮ አይደለም በሰው ሰራሽ ነው የሚሰቱት ” ብለዋል።

ማህበረሰቡ እሳት ቃጠሎ ሲያጋጥም በማጥፋት እንደሚተባበር፣ ከማህበረሰቡ ውስጥ እንዲህ አይነት ድርጊት የሚፈጽሚ አንዳንድ እንደማይጠፉ ገልጸው፣ " በጋራ ለመከላከል ሲከሰት ለማጥፋት የሚደረገውን ሁሉ ጥረት በህገ ወጦች ላይ በማተኮር ሁሉም ኃላፊነቱን ቢወስድ ” ሲሉ አሳስበዋል።

“ በአንዳንድ አካባቢዎች ሲኬድ ከግጥሽ ጋር የተያያዙ ናቸው። አዲስ ሳር እንዲያወጣላቸው የሚደረጉ ድርጊቶች አሉ። እናም የብዙኀንን ተሳትፎ ስለሚጠይቅ ሁሉም በኃላፊነት ቢከላከል ” የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል።

(ጉዳዩን ተከታትለን መረጃ የምናደርሳችሁ ይሆናል)

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
" 26 ሰዎች ወዲያ ነው ህይወታቸው ያለፈው። ቁጥሩ ሊጨምር ይችላል " - ፖሊስ

በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን ፤ ጉዳያ ቢላ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ26 ሰዎች ሕይወት ማለፉን ፖሊስ አስታወቀ።

አደጋው ከሻምቡ ከተማ ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ የነበረ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ በመገልበጡ ነው የተከሰተው፡፡

በደረሰው አደጋ የ26 ወገኖቻችን ሕይወት ወዲያው ሲያልፍ 42 ወገኖቻችን ላይ ደግሞ ከባድ ጉዳት መድረሱን የዞኑ የትራፊክ ደህንነት ሃላፊ ኢንስፔክተር አስናቀ መስፍን ተናግረዋል፡፡

በአደጋው ሕይወታቸው ያለፉ ወገኖች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችልም ሃላፊው ገልጸዋል፡፡

መረጃው የፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ነው።

@tikvahethiopia
🌍 Make the most of your stay with our ultimate visitors' plan!!

📶 Effortlessly connected.
🎁 Access exclusive deals and offers tailored just for you.
🛫🏡 Enjoy benefits both locally and around the world.
💳 Choose your preferred currency and simplify your transactions.

Get your Visitor Plan today and elevate your experience!

📍 Available at Bole International airport and all service centers.

Read more: https://bit.ly/4cXi8Uv


#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
#ExitExam

🔴" የተፈተነው ፈተና ኮንተንቱ(ይዘቱ) ህክምና ያልሆነ ነው በትምህርት ሊገኝ የማይችል ነው " - ተፈታኝ ተማሪዎች

🔵" የተማሩት ነው የሚወጣው የተፈተኑትም ይህን መሰረት አድርጎ ነው " - ትምህርት ሚኒስቴር

ሃገር አቀፍ የመውጫ ፈተና (Exit Exam)  ከጥር 26-30/2017 ዓም በ 87 የፈተና ማዕከላት መሰጠቱ ይታወሳል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያም ፈተናው ከተጠናቀቀ በኋላ " ፈተናው ለፈተና ዝግጅት ከሚያግዘው ' ብሉፕሪንት ' ውጪ ነው ይዘቱም ከተማርነው ትምህርት ጋር የማይገናኝ ነው " የሚሉ ቅሬታዎችን ከተፈታኞች ተቀብሏል።

ከተለያየ የትምህርት ክፍል ፈተናውን የወሰዱ ተፈታኞች ፈተናውን ከብሉ ፕሪንት ውጪ የመጣ መሆኑን በመግለጽ ትምህርት ሚኒስቴር ምላሽ ይስጠን ብለዋል።

ቅሬታውን ካቀረቡ ተፈኞች መካከል የሆኑ የህክምና ተማሪዎች " የመጣው ፈተና በጣም ከስታንዳርዱ የወጣ የህክምና ተማሪዎችን የማይመጥን ነበር " ብለዋል።

አክለውም " የተፈተነው ፈተና ኮንተንቱ (ይዘቱ) ህክምና ያልሆነ ነው በትምህርትም ሊገኝ የማይችል ነው " ያሉ ሲሆን " የሚመለከተውን አካል ለማናገር ብንሞክርም ከውጤት በፊት ንግግር እንደማይኖር ተነግሮናል " ሲሉ ገልጸዋል።

" ከእኛ በፊት አምና የተመረቁ ተማሪዎች የተፈተኑትን ፈተና ተመልክተናል ሰርተንም ስለገባን እናውቀዋለን ትክክለኛ ፈተና ነበር የተፈተኑት ይዘቶቹም ጥሩ ነበሩ  ዘንድሮ ምን እንደተፈጠረ አናውቅም የወጣው ፈተና ከህክምና ጋር የማይገናኝ ጥያቄ ይበዛው ነበር " ሲሉ ቅሬታቸውን አቅርበዋል።

በተጨማሪ ከጤና ተማሪዎች ውጭ የፊዚክስ ተማሪዎች ቅሬታቸውን አቅርበዋል።

የትምህርት ሚኒስቴር የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈጻሚ ኤባ ሚጀና (ዶ/ር ) ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ከብሉ ፕሪንት ውጪ ተፈትነናል የሚለው ቅሬታ " ውሸት ነው " ብለዋል።

" ከስልጠና ፕሮግራም ብቃት (Competency) ውጪ የሚዘጋጅ አንድም ጥያቄ የለም " ያሉት ስራ አስፈጻሚው የተባለው ቅሬታ " ውሸት ነው ሪፖርትም አልቀረበልንም እንደዚህ ብሎ የጠየቀንም የለም ከኮምፒተንሲ ውጭ የሚወጣ ፈተና የለም " ነው ያሉት።

አክለውም "ፈተናው ከብቃት ጋር የተገናኘ ከሁለተኛ ዓመት እስከ መጨረሻ ዓመት የተማሩት ነው የሚወጣው የተፈተኑትም ይህን መሰረት አድርጎ ነው " ብለዋል።

" ጥያቄው ከዚህ ውጪ ወጣ የሚል ቅሬታ ከሱፐር ቫይዘር፣ ፈታኝ ፣ተማሪ እንዲሁም ዩኒቨርሲቲዎች የቀረበልን አንድም ሪፖርት የለም መረጃው የለንም ሪፖርቱም አልቀረበልንም " ሲሉ ገልጸዋል።

በሌላ በኩል ሃገር አቀፉ የመውጫ ፈተና ውጤት ነገ አልያም ከነገ በስቲያ ይፋ እንደሚደረግ ከትምህርት ሚኒስቴር መስማቱን የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተማሪዎች ህብረት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል፡፡

ህብረቱ ፥ ሚኒስቴሩ ከComprehensive Nursing የመውጫ ፈተና ጋር ተያይዞ የቀረበ ቅሬታን እያጣራ እንደሚገኝ አስረድቷል።

ረቡዕ ወይም ሐሙስ አጠቃላይ የመውጫ ፈተና ውጤት ይፋ እንደሚደረግ ሚኒስቴሩ እንደገለጸለት ህብረቱ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳውቋል፡፡

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ExitExam 🔴" የተፈተነው ፈተና ኮንተንቱ(ይዘቱ) ህክምና ያልሆነ ነው በትምህርት ሊገኝ የማይችል ነው " - ተፈታኝ ተማሪዎች 🔵" የተማሩት ነው የሚወጣው የተፈተኑትም ይህን መሰረት አድርጎ ነው " - ትምህርት ሚኒስቴር ሃገር አቀፍ የመውጫ ፈተና (Exit Exam)  ከጥር 26-30/2017 ዓም በ 87 የፈተና ማዕከላት መሰጠቱ ይታወሳል። ቲክቫህ ኢትዮጵያም ፈተናው ከተጠናቀቀ በኋላ " ፈተናው…
#COC

ጤና ሚኒስቴር የሙያ ብቃት ምዘና ለመውሰድ እየጠበቁ ለሚገኙ የጤና ተመራቂዎች ምዘናው ለመስጠት ዝግጅት ማጠናቀቁን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳውቋል።

በትምህርት ሚኒስቴር ባለፈው ሳምንት የተሰጠውን የመውጫ ፈተና ወስደው ያለፉ ተማሪዎችን ዝርዝር እየጠበቀ መሆኑን ጤና ሚኒስቴር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

የመውጫ ፈተና ውጤት መገለፅን ተከትሎ፥ COC የሚወስዱ አመልካቾች (በድጋሜ ተፈታኞችን ጨምሮ) ምዝገባ እንደሚደረግ ሚኒስቴሩ አረጋግጧል።

የCOC ምዘና አመልካቾች ምዝገባ በጊዚያዊነት ከየካቲት 10/2017 ዓ.ም በኋላ ለመጀመር መታቀዱን ሚኒስቴሩ ጠቁሟል።

በዚህም ምዘናውን በየካቲት ወር መጨረሻ ወይም በመጋቢት ወር የመጀመሪያ ሳምንት ለመስጠት በጊዚያዊነት መታቀዱን ከሚኒስቴሩ ሰምተናል።

Via
@tikvahuniversity
" በአደጋው ሁለት ሰዎች ወዲያዉኑ ሲሞቱ ስራ ላይ የነበረ አንድ ተረኛ የፖሊስ አባልን ጨምሮ በሶሰት ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል ጉዳት ደርሷል" - የወላይታ ሶዶ ከተማ ፖሊስ

ትላንት ምሽት 4 ሰዓት ገደማ መነሻዉን ሻሸመኔ ያደረገ ኮድ (3)  - B311533 AA የሆነ አይሱዙ የጭነት መኪና ሶዶ ከተማ ሲደርስ ባደረሰዉ የትራፊክ አደጋ  በሰዉ ሕይወትና በንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱን የወላይታ ሶዶ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ም/ኮማንደር ሀብታሙ አሰፋ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

እንደ ፖሊስ አዛዡ ገለፃ ከኦሮሚያ ክልል አርሲ አከባቢ የግብርና ምርት / ሙሉ ቲማቲም / ጭኖ የነበረዉ ተሽከርካሪ ሶዶ ከተማ ' ሲዳር ቄራ ' በሚባለዉ አከባቢ በከተማዉ በሞተር ሳይክል ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ሁለት ሰዎችን ገጭቶ ወዲያዉ ሕይወታቸዉ አልፏል።

በተመሳሳይ መልኩ የምሽት ተረኛ የነበረ አንድ የፖሊስ መርማሪም ጥሪ ተደርጎለት በሞተር ሳይክል ጥሪ ወደተደረገለት ስፍራ ሲንቀሳቀስ ይሄዉ ተሽከርካሪ ገጭቶት ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰበት የፖሊስ አዛዡ ገልጸዋል።

አደጋ አድራሹ ተሽከሪካሪ አራት የመብራት ፖሎችን ከገጨ በኋላ ዲች ዉስጥ ገብቶ የቆመ ሲሆን በአሽከርካሪዉና ረዳቱ ላይ ቀላል የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል።

ከባድ የአካል ጉዳት የደረሰበት የፖሊስ መርማሪ በሶዶ ክርስቲያን ሆስፒታል ሕክምና እየተደረገለት ሲሆን ቀላል ጉዳት የደረሰባቸዉ ሹፌሩና ረዳቱም በኦቶና አጠቃላይ ሆስፒታል በሕክምና ላይ መሆናቸዉን የከተማው ፖሊስ አዛዥ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

አጠቃላይ በአደጋዉ 2 የሞት፣ 1 ከባድና 2 ቀላል የአካል ጉዳት እንዲሁም 7 የንብረት ጉዳት መድረሱን አሳውቀዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray በእንዳስላሴ ሽረ ከተማ በህዝብ መዝናኛ ስፍራ በተጣለ የእጅ ቦምብ 10 ሰዎች ከባድ እና ቀላል ጉደት ደረሰባቸው። የሰው ህይወት አለማለፉን ለመረዳት ተችሏል። የቦምብ ጥቃቱ አድራሾች እና ግብረ አበሮቻቸው ለመያዝ የተጠናከረ ክትትል እና ምርመራ እያደረግኩ ነው ብሏል ፖሊስ። ጥቃቱ መቼና ? የት ? እንዴት አጋጠመ ? ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ፤ በስፍራው የነበሩ የአይን እማኞችን…
" 4 ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል " - ፖሊስ

በቦንብ ፍንዳታ የተጠረጠሩ 4 ሰዎች በቁጥጥር ስር ማዋሉ ፓሊስ አስታውቋል።

ትናንት የካቲት 3/2017 ዓ.ም በትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን እንዳስላሰ-ሽረ ከተማ በአንድ የህዝብ መዝናኛ ስፍራ በተጣለ ቦምብ በ13 ሰዎች ላይ ከባድ እና ቀላል ጉዳት ደርሷል።

ሞት አላጋጠመም።

አደጋው ከተከሰተበት ጀምሮ ከክልል እስከ ወረዳ የተቀናጀ የወንጀል አጣሪ ቡድን አቋቋሞ መንቀሳቀስ መጀመሩ የጠቀሰው ፓሊስ ፤ ከፍነዳታው ጋር በተያያየ 4 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ማዋሉ አስታውቀዋል። 

የቢንጎ ማጫወቻ መሆኑ በተጠቀሰው የህዝብ መዝናኛ ማእከሉ ሰዎች በብዛት እንደሚሰባሰቡበት የጠቀሰው ፓሊስ ባለፈው ጥር ወር በተመሳሳይ ቦንብ ተጥሎ ሳይፈነዳ በመቅረቱ አደጋ አላደረሰም ብሏል።

ፓሊስ " ጥቃቱን አድርሰዋል " በማለት በጠረጠራቸው ሰዎች ላይ ውጤታማ የሆነ የማጣራት በማካሄድ ጉዳዩ ለህዝብ እንደሚያሳውቅ ገልፆ የህዝቡ ትብብር ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቋል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia            
TIKVAH-ETHIOPIA
" 26 ሰዎች ወዲያ ነው ህይወታቸው ያለፈው። ቁጥሩ ሊጨምር ይችላል " - ፖሊስ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን ፤ ጉዳያ ቢላ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ26 ሰዎች ሕይወት ማለፉን ፖሊስ አስታወቀ። አደጋው ከሻምቡ ከተማ ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ የነበረ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ በመገልበጡ ነው የተከሰተው፡፡ በደረሰው አደጋ የ26 ወገኖቻችን ሕይወት ወዲያው ሲያልፍ 42 ወገኖቻችን ላይ ደግሞ…
#Update

“ አደጋው በጣም አሰቃቂ ነው። 28 ሰዎች ሞተዋል። 45ቱ ሰዎች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል ” - የኦሮሚያ ክልል ፓሊስ ኮሚሽን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ

በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ወለጋ ዞን ጉደያ ቢላ ወረዳ ደረሰ በተባለው የትራፊክ አደጋ፣ እስካሁን የሟቾች ቁጥር 28 መድረሱን የኦሮሚያ ክልል ፓሊስ ኮሚሽን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

ኮሚሽኑ ስለአደጋው መንስኤ በሰጠን ቃል፣ “የፊት ጎማው በሮ ወጥቶ ነው። በፍጥነት ላይም ነበር። የፍሬን ቴክኒክ ችግር እንዳለም መረጃ አለ” ብሏል።

የሟቾች ቁጥር ከ26 ጨመረ እንዴ? ስንል የጠየቅናቸው የክልሉ ፓሊስ ኮሚሽን የትራፊክ አደጋና መረጃ ክፍል ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር መሰለ አበራ፣ “እስካሁን ባለው መረጃ የሟቾች ቁጥር 28 ነው” ብለዋል።

“ ከባድ አደጋ የደረሰባቸው 45 ሰዎች ናቸው። እነርሱም በባኮ ሆስፒታል ህክምና ላይ ናቸው ” ነው ያሉት።

የደረሰባቸው ጉዳት ቀላል ጭምር ነው ወይስ ከባድ ብቻ ነው ? ስንል ላቀረብነው ጥያቄ ዋና ኢንስፔክተሩ፣ “ 45ቱም ከባድ አደጋ ነው የደረሰባቸው ” ሲሉ መልሰዋል።

“ ከሻምቡ ወደ አዲስ አበባ ተሳፋሪዎችን ጭኖ ሲጓዝ የነበረ ማርሴዲስ ኮድ 3A 12661 መኪና ጉደያ ቢላ ወረዳ ጎንካ ኢጃ ቀበሌ ጅማ ወንዝ የሚባል ልዩ ቦታ ነው የፊት ጎማው በሮ ገደል የገባው ” ሲሉም የአደጋውን መንስኤ ጨምር አስረድተዋል።

አክለው፣ “ የፊት ለፊት ጎማው በሮ ወጥቶ ነው። በፍጥነት ላይም ነበር። የፍሬን ቴክኒክ ችግር እንዳለም መረጃ አለ። ፓሊስ በማጣራት ላይ ይገኛል ” ነው ያሉት።

የተሳፈሩ ሰዎች ስንት ነበሩ ? ጉዳት ሳይደርስባቸው የተረፉ ይኖሩ ይሆን? ስንል ላቀረብነው ጥያቄም፣ “ አሁን ባለው መረጃ 28 ሟች፣ 45 ከባድ ጉዳት አጠቃላይ ሹፌርና ረዳት፣ ተሳፋሪን ጨምሮ ነው። መኪያው ውስጥ የነበሩት እነዚሁ ናቸው ” ብለዋል ዋና ኢንስፔክተሩ።

“ አደጋው የደረሰበት ማርሴዲስ ተሽከርካሪ ስሪቱ በጣም የቆዬ በመሆኑ ለረጅም ርቀት መመደብ አልነበረበትም ” የሚል አስተያዬት ሲሰጥ ተስተውሏል፤ የፓሊስ አስተያዬት ምንድን ነው ? የሚል ተጨማሪ ጥያቄም አቅርበናል። 

ኢንስፔክተሩ፣ “እኛ ይሄ መረጃ አልደረሰንም። መንገድ ትራንስፓርት መረጃውን አይቶ ከመናኸሪያ የሚመድበው ስለሆነ ከትልቁ መናኸሪያ ነው ይሄ ስምሪት የሚሰጠው” ብለዋል።

“የሚመለከተው አካል፣ ፌደራል መንገድ ትራንስፓርት አይቶ ስሞሪት የሚሰጥ ስለሆነ እንደኛ እንዲህ አይነት ችግር ካለ እነርሱም ፍተሻ እንዲያደርጉና እንዲህ አይነት ርቀት ቦታም ባይመደብ ጥሩ ነው” ሲሉም አክለዋል።

የፍጥነትም ሆነ የቴክኒክ ችግር እንዲህ አይነት አደጋዎች እንዳይደገሙ ባስላለፉት መልዕክት፣ “ይሄ አሰቃቂ አደጋ ነው። እንደ ኦሮሚያ የደረሰው ከባድ አደጋ ነው። በድጋሚ እንዳይከሰት ባለ ባለንብረቶችና አሽከርካሪዎች ሳይሰማሩ በፊት የቲክኒክ ችግር ቢመረምሩ” ሲሉ አሳስበዋል።

ዋና ኢንስፔክሩ በምላሻቸው፣ “የቲክኒክ ችግር በጣም ለአደጋ ስለሚያጋልጥ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ነው መልዕክት የማስተላልፈው” ሲሉም አስገንዝበዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia