TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.2K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update 🔴" በ104.4 የመቐለ ኤፍኤም ያጋጠመው ችግር በመግባባት እንዲፈታ አድርጊያለሁ  ስልጣን መረከብ የሚፈልግ አካል እና ግለሰብ ህግ እና ስርዓት ያክብር  " - የመቐለ ከተማ ፓሊስ  " ሬድዮ ጣቢያችን ለሁለት የተሰነጠቁ ቡድኖች መጫወቻ እንዲሆን አንፈቅድም " - የመቐለ FM አመራር ጥሪ 21 / 2017 ዓ.ም ከረፋዱ 4:00 ሰዓት 5 ታጣቂዎች አስከትሎ የመቐለ ኤፍ ኤም ሬድዮ ጣቢያን…
#Update

" ህጋዊ ስራ አስኪያጅ እኔ ነኝ ወደ ስራ ቦታየ እንዳልገባ ፓሊስ ከልክሎኛል " - የ104.4 ኤፍ ኤም መቐለ ሹመኛ መሆናቸውን የሚናገሩት ዘመንፈስ ቅዱስ ፍስሃ

" ሹመኛ ነኝ " ያሉት በሊቀ-መንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት በመቐለ ከተሾመው ከንቲባ በኋላ ህዳር 2017 ዓ.ም የኤፍ ኤም ሬድዮው ስራ አስኪያጅ ሆኖው መመደባቸው የገለጹት ዘመንፈስቅዱስ ፍስሃ የከተማዋ ፓሊስ ወደ ስራ ቦታቸው እንዳይገቡ መከልከሉ " አግባብ " አይደለም ብለዋል።

ለኤፍኤም ሬድዮ ጣብያው የከተማዋን ምክር ቤት እና አሰራር በጣሰ መልኩ ከመስከረም 2017 ዓ.ም ወዲህ ሦስት ስራ አስኪያጆች መመደባቸው የገለፁት ዘመንፈስቅዱስ ፍስሃ ይህ አካሄድ እንዲታረምና ወደ ስራቸው እንዲገቡ ጠይቀዋል።

ከተመደቡበት ወርሃ ህዳር 2017 ዓ.ም ሦስቴ ወደ ስራ ገበታቸው ለመግባት ያደረጉት ጥረት በኤፍ ኤም ሬድዮው በሚገኙ አመራሮች መስተጓጉሉም አምርረው የነቀፉት ዘመንፈስቅዱስ ከጥር 22/2017 ዓ.ም በኋላ ወደ ስራ ገበታቸው ለመግባት ያደረጉት ጥረት ከዛ በፊት አይተዋቸው የማያውቁ ታጣቂዎች ተመድበው  እንደተደናቀፋባቸው በምሬት ተናግረዋል። 

104.4 የመቐለ ኤፍኤም ከተማዋ ባቋቋመው ቦርድ የሚመራ እንደሆነ የጠቀሱም ሱሆን " ቦርዱ እኔ ህጋዊ ስራ አስኪያጅ አድርጎ ሹመኛል ስለሆነም ስራዬን እንድሰራ በጣብያው ያሉ ህገ-ወጦች ስርዓት መያዝ አለባቸው " ብለዋል።

ጥር 22/2017 ዓ.ም በ104.4 ኤፍ ኤም መቐለ ቅጥር ግቢ " እኔን ነኝ ህጋዊ ሹመኛ ... እንተ አይደለህም " በሚል በተፈጠረ ግርግር ፓሊስ ደርሶ በውይይት መፍታቱ መዘገባችን ይታወሳል።

የወዝግቡ መነሻ ለሁለት ከተከፈሉት የህወሓት አመራሮች የሚያያዝ ሆኖ በጣብያው የሚገኙ አመራሮች የጊዚያዊ አስተዳደሩ ቅቡልነት ያላቸው ፤ አዲሱ ተሿሚ ደግሞ በድብረፅዮኑ ህወሓት ድጋፍ ያላቸው ናቸው።

በ2001 ዓ.ም የተቋቋመው 104.4 የመቐለ ኤፍ ኤም በአገሪቱዋ የሚድያ ህግ የተቋቋመ እና በየአመቱ ተገቢ ክትትልና ቁጥጥር የሚደረግበት መሆኑ ይታወቃል ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
" ህዝቡ ያለፈው አልበቃ ብሎት የትናንት ቁስሉ ሳይሽር አሁንም በሽብር እና በጦርነት ወሬ ስሜት ወስጥ ይገኛል ! " - የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚንስትር 

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) ለትግራይ ህዝብ በተለይ ደግሞ ለልሂቃን መልእክት እና ምክር አስተላልፈዋል። 

ጠቅላይ ሚንስትሩ ጥር 26/2017 ዓ.ም በፅሁፍ ባስተላለፉት ጠንካራ መልእክት እና ምክር ትግራይን እና ህዝብዋን " የጥንታዊ እና ገናና ታሪክ ባለቤት የኢትዮጵያ ዋልታና መከታ " ሲሉ ገልፀዋቸዋል።

" የትግራይ ህዝብ ታሪክ የማያረጅ እና የማይደበዝዝ በደማቅ ቀለም የተፃፈ ነው " ያሉ ሲሆን " ክልሉ ለህዝባቸው እና አገራቸው የሚጠቅሙ በርካታ ሊቃውንት ፣ የሃይማኖት መሪዎች ፣ ፓለቲከኞች ፣ የአገር ሽማግሌዎች ያፈራ ነው " ሲሉ ፅፈዋል።

የትግራይ ህዝብ የዘመናት ተጋድሎዎች ያወሱ እና ያወደሱት ጠቅላይ ሚንስትሩ " የአገር ፍቅር ስሜት የትግራይ ህዝብ መለያ እና መገለጫ ነው " ብለዋል።

" ቢሆንም መጥፎ አጋጣሚ ሆኖ በተለይ ባለፉት አንድ መቶ ዓመታት ከማእከላይ መንግስቱ ለተደጋጋሚ ጊዜዎች ግጭት ውስጥ በመግባት ትግራይ የጦርነት አውድማ ፤ ህዝቡም ደግሞ የሁሉም ዓይነት ችግሮች ተጋላጭ እና ተጠቂ መሆኑን " ጠቅላይ ሚንስትሩ አውስተው " የሚያጋጥሙ እና የሚፈጠሩ ችግሮች ከውግያ በመለስ የሚፈቱበት አማራጭ አልነበረም ወይ ? " ሲሉ ጠይቀዋል።

" ህዝቡ ያለፈው አልበቃ ብሎት የትናንት ቁስሉ ሳይሽር አሁንም በሽብር እና በጦርነት ወሬ ስሜት ወስጥ ይገኛል ፤ ይህንን ዓይነት አደጋ የሚፈጥር ችግር እንዴት መፍታት እና ማስወገድ እንደሚቻል በግልፅ መነጋገር እንደሚያስፈልግ ለአስተዋይ የሚሰወር አይደለም " ብለዋል።

" ስለሆነም በፓለቲካ ፣ በንግድ ፣ ፀጥታ ፣ አካዳሚ እና ሚድያ እና በሌሎች የስራ ዘርፎች የተሰማራችሁ የትግራይ ልሂቃን ወገኖች የትግራይ ህዝብ እስከ ዛሬ የተሰቃየው የከፈለው ዋጋ ይብቃው ፤ ልዩነትን በመነጋገር እና በውይይት የመፍታት ባህልንና ልምድ ታጠቁ " ሲሉ መክረዋል።

ልሂቃኑ ከፌደራል መንግስት እና ሌሎች ሃይሎች ያላቸው ልዩነት በአገሪቱ ህገ-መንግስት በዴሞክራሲያዊ መንገድ በመግባባት ለመፍታት ዝግጁ እንዲሆኑ ጠቅላይ ሚንስትሩ ጥሪ አቅርበዋል።

" የፌደራል መንግስት በሁሉም አጀንዳዎች ለመነጋገር ፤ የሃሳብ ልዩነት ደግሞ እንደልዩነት በማክበር ፣ በሚያግባቡ አገራዊ ርእሰ ጉዳዮች በመስማማት ለመስራት የሚያስችል ምቹ ሁኔታ መኖሩ የትግራይ ህዝብ እና ልሂቃኑ መገንዘብ አለባችሁ " ብለዋል።

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) በመልእክታቸው ማሳረግያ " ሰላም እና ብሩህ መፃኢ ለትግራይ ህዝብ ፣ ግጭት እና ጦርነት ይብቃ ! " የሚል መልካም ምኞታቸው አስተላልፈዋል።

@tikvahethiopia            
#እናትፓርቲ

እናት ፓርቲ የአዲስ አበባ ፋይናንስ ቢሮ ከሚያዝያ 2015 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ ያደረገው የጣሪያ ግድግዳ/ ንብረት ግብር መመርያ እንዲቆም የመሠረተው ክስ በፍርድ ቤት ተቀባይነት አግኝቶ መመሪያው "ተፈጻሚ ሊሆን አይገባም" ሲል ፍርድ ቤት ጥር 9 ቀን ብይን መስጡቱን ፓርቲው አስታውቋቃ።

ፓርቲው የወጣው መመርያ " ሕግን ባልተከተለ መንገድ እና የከተማ አስተዳደሩ ባልተሰጠው ሥልጣን የወጣ በመሆኑ " መመሪያው እንዲሻሻል ሲል በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አስተዳደር ችሎት ክስ መስሮቶ መቆየቱን ገልጿል።

ፍ/ቤቱ የአዲስ አበባ ፋይናንስ ቢሮ ያቀረባቸውን ሦስት መቃወምያዎች ውድቅ አድርጎ ወደ ፍሬ ነገር ክርክር ከገባ በኋላ ጉዳዩን መርምሮ መመሪያው " ተፈጻሚነት ሊኖረው አይገባም " የሚል ውሳኔ መስጠቱን፤ የውሳኔውን አፈጻጸም እንደሚከታተልም ፓርቲው አስታውቋል።

(ፓርቲው የላከው መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
Some wait for opportunities. Others create them. Which one are you? The Jasiri Talent Investor Program invites bold, innovative thinkers ready to take action. Don’t miss out on our 8th Cohort. Click the link to start your application, https://bit.ly/4aGlAm8.

#Jasiri4Africa
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የአፖሎ አካውንት በመክፈት ወይም የአፖሎን መተግበርያ ለሌሎች በማጋራት አንዲሁም ገንዘብ ተቀማጭ በማድረግ የተለያዩ ሽልማቶችን ያሸንፉ።

የመርሃ ግብሩን ዝርዝር መረጃ ከዚህ በታች ያግኙ፡፡
https://t.iss.one/BoAEth/1525


አፖሎን በማውረድ ተሳታፊ ይሁኑ፡
ለአንድሮይድ ስልኮች: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.boa.apollo&hl=en&gl=US
ለአፕል ስልኮች: https://apps.apple.com/eg/app/apollo-digital/id1601224628
ለህዋዌ ስልኮች ፡https://appgallery.huawei.com/app/C108966741

#መጣሁልሽ #አምሮኛል_መጣሁልሽ #ApolloWinBig #DepositAndWin #JoinApolloGetRewarded
#Ethiotelecom

የካቲት 07 ይጠናቀቃል፤ ፈጥነው የኢትዮ ቴሌኮም የአክሲዮን ባለቤት ይሁኑ!!

💁‍♂️ የአክሲዮን ሽያጩ በቴሌብር ሱፐርአፕ https://onelink.to/uecbbr ይከናወናል፤ የመሸጫው ጊዜ ገደብ ከመጠናቀቁ በፊት የኢትዮ ቴሌኮም የቀጥታ ድርሻ ባለቤት ይሁኑ!!

🗓 እስከ የካቲት 07/2017 ዓ.ም ብቻ!

📖 የደንበኛ ሳቢ መግለጫውን https://teleshares.ethiotelecom.et/ ያንብቡ፡፡

ለተጨማሪ መረጃ ወደ 128 ይደውሉ !

#telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#መቄዶንያ❤️ 🔵 “ የጎዳና ኑሮ ከባድ ነው፣ የ85 ዓመት እናቶች ተደፍረው የመጡበት አጋጣሚዎች አሉ። ጎዳና ላይ ሰዎች በብርድ ምክንያት ይሞታሉ” - የክብር ዶክተር ቢኒያም በለጠ 🔴 “ ኢትዮጵያዊያን እባካችሁ ወደ ቀልባችን እንመለስ። ሰውን በመግደል፣ በማፈናቀል የምናገኘው ጥቅም የለም። ሰውን በመርዳት ግን ጥቅም ይገኛል ” - ቀሲስ ታጋይ ታደለ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ከመቄዶንያ በጎ…
#መቄዶንያ

“ ህንፃው ለማጠናቀቅ ገንዘብ ተቸግረናል። ለማጠናቀቅ ወደ 5 ቢሊዮን ብር ያስፈልገናል ” - መቄዶንያ

መቄዶንያ የአረጋዊያንና የአእምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል በሚያስገነባው ሆስፒታል ጭምር ያለው ህንፃ ለማጠናቀቅ የገንዘብ እጥረት ስለገጠመው እርዳታ እንዲያደርግ ጥሪ አቀረበ።

ከየካቲት 1 ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮ “ በሰይፉ ኢቢኤስ የዩቱብ ቻነል ” ድጋፍ ማድረጊያ መርሀ ግብር ስለሚጀመር ደጋጎች ሁሉ ድጋፍ እንዲያደርጉ በአንጽንኦት ተጠይቋል።

ይህ የተባለው ዛሬ በመቄዶኒያ በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ነው።

የመቄዶንያ መስራች የክብር ዶክተር ቢኒያም በለጠ ደግሞ፣ “ ይህን ህንፃ ጀምረነዋል። ለማጠቀቅ ገንዘብ ተቸግረናል። 5 ቢሊዮን ብር ያስፈልገናል ” ብለዋል።

ህንፃው ምን የማጠቃለያ ስራዎች ቀርተውት ነው ድጋፍ ያስፈለገው ? ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ ላቀረበላቸው ጥያቄ፣ “ ሴራሚክ የባኞ ቤት እቃዎች፣ 7 ሊፍቶች፣ የኤሌክትሪክ ፊኒሽንግ እቃዎች ገና ናቸው ” ሲሉ መልሰዋል።

በመቄዶንያ ምን ያክል የአእምሮ ህሙማን አሉ? ስንል ላቀረብንላቸው ጥያቄ ደግሞ፣ “ ወደ 2,500 የአእምሮ ሆሙማን፤ ከ2,000 በላይ ዳይፐር ተጠቃሚዎች፣ ከዚያ ውጪ ያሉት አረጋዊያን ናቸው ” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

የክብር ዶክተር ቢኒያም በለጠ፣ “ በ44 ቅርንጫፍ ከ8,000 በላይ ሰዎች አሉ። በየጊዜው ሰው እየጨመረ ነው የሚሄደው። ህክምና የሚፈልጉ ሰዎች ጭምር ናቸው ያሉት ” ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

መቄዶንያ የአረጋዊያንና የአእምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል ከ8,000 በላይ ወገኖችን ከጎዳና በማንሳት በ44 ቅርንጫፎች በቀን ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ በማውጣት ሰብዓዊ ድጋፍ የሚረዳ ማዕከል ነው።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
" ከአደጋው በህይወት የተረፈ የለም " - የሶባ ቦሩ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን

በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን ሶባ ቦሩ ወረዳ በወርቅ ቁፋሮ ስራ ላይ የነበሩ 8 ሰዎች ላይ አፈር ተደርምሶባቸዉ የሁሉም ሕይወት ማለፉን የወረዳዉ መንግስት ኮሚኒኬሽን ኃላፊ አቶ አሸናፊ ድንቆ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

አደጋው በትላንትናው ዕለት ከቀኑ 9 ሰዓት አከባቢ ' ቃንጣቻ ' ተብሎ በሚጠራዉ ቀበሌ በባህላዊ መንገድ የወርቅ ማዕድን በማዉጣት ስራ ላይ በነበሩ 8 ሰዎች ላይ መድረሱን ኃላፊዉ ገልጸዋል።

በአከባቢዉ የሚስተዋለዉ ባህላዊ የወርቅ አወጣጥ ስርዓትና በቸልተኝነት የሚደረጉ ሽሚያዎች ለናዳዉ ምክንያት ሊሆን ይችላል ያሉት ኃላፊዉ ሟቾቹ ሁሉም ወንዶች መሆናቸው አስታዉቀዋል።

የአስከሬን ፍለጋዉ ሂደት ፈታኝ እንደነበር ገልጸው አደጋዉ ከደረሰበት ሰዓት አንስቶ እስከ ምሽቱ አምስት ሰዓት ድረስ በሰዉ ሃይልና በማሽን በመታገዝ የፍለጋ ስራዉ መከናወኑንና በዛሬው ዕለት የሁሉም የቀብር ሥነ ስርዓት መፈፀሙን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልፀዋል።

አቶ አሸናፊ የጉጂ ዞን ሰባ ቦሮ ወረዳ በወርቅ ፣ ታንታሌም ፣ አምርላንድን በመሳሰሉ የማዕድን ሃብቶች የበለፀገ አካባቢ መሆኑንና ከሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች የመጡ በርካታ ሰዎች በማዕድን ማዉጣት ስራ ላይ ተሰማርተው እንደሚሰሩ ገልፀዉ ከዚህ ቀደም አከባቢዉ ላይ መሰል አደጋዎች ተከስተዉ እንደማያውቁም ተናግረዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ከ5 ሺህ በላይ ሰራተኞች ውላቸው እንዲቋረጥ መመሪያ ተሰጠ።

ጤና ሚኒስቴር በሲዲሲ እና ዩኤስኤይድ (USAID) ድጋፍ የተቀጠሩ ከ5 ሺህ በላይ ስራተኞችን ውል እንዲቋረጥ መመሪያ ሰጠ።

ጤና ሚኒስቴር ከአሜሪካ መንግሥት በሲዲሲ (CDC) ወይም ዩኤስኤይድ (USAID) አማካኝነት በተገኘ የበጀት ድጋፍ የሚከናወን ማንኛውም ስራም ሆነ ክፍያ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ከጃንዋሪ 24 ,2025 ጀምሮ እንዲቋረጥ ማሳሰቢያ እንደደረሰው ገልጿል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የተመለከተው እና በጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ ተፈርሞ ለሁሉም የክልል ጤና ቢሮዎች የተሰራጨው ደብዳቤ " በጤና ሚኒስቴር ድጋፍ የተቀጠሩ እና ተቋማችሁ ከCDC ወይም USAID ጋር በሚያደርገው ውል መሰረት የተቀጠሩ ሰራተኞችን በተመለከተ ስራ ላይ እንዲውል አሳስባለሁ " ይላል።

ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ የደብዳቤውን #ትክክለኛነት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጠዋል።

ሚኒስትር ዴኤታው በሰጡን ተጨማሪ ማብራሪያ በመላው ሃገሪቱ በሲዲሲ እና ዩኤስኤይድ አማካኝነት በኮንትራት እያገለገሉ ያሉ ሰራተኞች ቁጥር 5 ሺህ እንደሚሻገር ገልጸዋል።

ሚንስትሩ " ሰው እንዲዘጋጅ ነው እንጂ የአሜሪካ መንግሥትም ሃሳቡን ሊቀይር ይችላል የተቀየረ ነገር ካለ የሚቀጥል ይሆናል አሁን ባለው ሁኔታ ግን ድጋፉን ካቋረጠ ሌላ መፍትሄ ማፈላለግ ያስፈልጋል " ብለዋል።

" ለዚህ ደግሞ ሰራተኞቻችን እንዲዘጋጁ ከመንግስት ጋርም ንግግር እየተደረገ ነው ያለው የመንግስት ሰራተኞች ስራውን እንዲያስቀጥሉ የCDC እና USAID ሰራተኞች ስራውን እንዲያቆሙ ተወስኗል " ብለዋል።

ሚኒስትር ዴኤታው በዝርዝር ምን አሉ ?

" እኛን በዋናነት የሚመለከተን በጀቱ በቀጥታ በእኛ በኩል ስለሚመጣ የሲዲሲ ሰራተኞችን ነው ዩኤስኤይድ ግን ቅጥር የሚያከናውነው በራሱ በኩል ነው ውሉንም የሚያቋርጡት ራሳቸው ናቸው።

የአሜሪካ መንግሥት ሃሳቡን ቀይሮ ሌላ መረጃ የሚያስተላልፍ ከሆነ እኛም ሌላ መረጃ የምናስተላልፍ ይሆናል አሁን ባለው የአሜሪካ መንግስት ውሳኔ ግን ኮንትራታቸውን ማቋረጥ አስፈላጊ በመሆኑ ይህንን ደብዳቤ አስተላልፈናል።

ከ5 ሺ በላይ ይሆናል ትክክለኛ ቁጥራቸውን ለማወቅ መረጃ የመሰብሰብ ስራ እየሰራን ነው ሁሉም በኮንትራት ናቸው ኮንትራታቸው በየአመቱ ይታደሳል ስራቸውም ከኤች አይ ቪ ጋር የተገናኙ ስለሆነ አብዛኞቹ የቆዩ ሰራተኞች ናቸው።

በጣም አስፈላጊ በመሆናቸው ነበር በዚህ ያህል በጀት ተቀጥረው ሲሰሩ የነበረው 15 እና 20 ዓመት የሞላቸውም አሉ ስራው ላይ ችግር ሊያመጣ ይችላል።

በአንድ ጊዜ ይሄን ያህል ሰው ከሴክተሩ ከተቀነሰ ችግር ሊፈጠር ይችላል ዋናው ነገር ግን ስራው እንዳይስተጓጎል ሃላፊነቱን ላለው የመንግስት ሰራተኛ እያስተላለፉ መሄድ ያስፈልጋል።

ቀላል ስራ አይደለም የሚጠብቀን የሚቻለውን ሁሉ እናደርጋለን።

የመጨረሻ ውሳኔዎችን አልሰማንም ከአሜሪካ መንግሥት በየጊዜው የተለያዩ ውሳኔዎች እየተላለፈ ስለሆነ ዛሬ ሌላ ነገ ሌላ ነው የሚባለው ሁሉም የአፍሪካ ሃገራት ተመሳሳይ ነገር ነው እያደረጉ ያሉት ከሁሉም ጋር ውይይት እየተደረገ ነው።

የዓለም ጤና ድርጅትም በቦርድ ደረጃ ከሁሉም የአፍሪካ ሃገራት ጋር ውይይቶችን እያደረገ ይገኛል።

ሰራተኞችም እንዲያውቁ እኛም ጫናውን ለማሳወቅ እና መፍትሄው አብሮ ለመፈለግ እንዲቻል ለመንግሥትም አሳውቀናል ስራ እንዳይጎዳ ከፍተኛ ጥንቃቄ ይደረጋል።

በዚሁ ከቀጠለ ሌላም ከባባድ ውሳኔዎች ሊወሰን ይችላል የመድኃኒት ግዢ እና ሌሎችም ድጋፎች ሊቋረጡ ይችላሉ አይታወቅም እንዳይቋረጥ እና እንዲቀጥል እኛም እንደሃገር የምንችለውን ጫና እናደርጋለን።

በውስጥ አቅም በውስን የሰው ሃብት ባለን በጀት ስራዎች እንዳይስተጓጎሉ በሽታዎች ተመልሰው ከፍ እንዳይሉ አስፈላጊውን እርምጃ መውሰድ ያስፈልጋል ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይቶችን እያደረግን እንገኛለን በሚቀጥሉት ጊዜያት የሚመጡ ውጤቶችን እና ቀጣይ ውሳኔዎችን እናሳውቃለን " ብለዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
ከወልደያ ቆቦ የሚያስኬደው የሃሚድ ውሃ ወንዝ የብረት ድልድይ ወደ መቐለ የደንጋይ ከሰል ጭኖ በሚሄድ መኪና ተሰብራል።

ጉዳትም ድርሷል።

የአማራ ክልል የመንገድ ቢሮ ጉዳቱን በተመለከተ ለፌዴራል የመንገዶች አስተዳደር በደብዳቤ ሪፖርት አድርጓል።

ከወልድያ - ቆቦ - አላማጣ ባለው ዋናው የአስፓልት መንገድ ከቆቦ ከተማ 14 ኪ.ሜ ርቀት ወደ ወልድያ በኩል በሚወስደው በሮቢትና ጎብየ ከተማ መካከል የሚገኝው " የሃሚድ ውሃ ወንዝ " ላይ 50 ሜትር ርዝመት ያለው ተገጣጣሚ የብረት ድልድይ በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ከዛሬ 8 ዓመት በፊት ተገንብቶ አገልግሎት ሲሰጥ እንደነበር አስታውሷል።

አሁን ላይ የብረት ድልድዩ ከፍተኛ የትራፊክ ፍሰት የሚበዛበት ከመሆኑ የተነሳና በከባድ ጭነት ምክንያት በደረሰበት ጉዳት የተሰበረ መሆኑን ጠቁሟል።

በዚህም ወልድያ ወደ ቆቦ እና አላማጣ የሚወስደው የአስፓልት መንገድ ሙሉ በሙሉ አገልግሎት ማቆሙን ቢሮው ገልጿል።

በአካባቢው ብቸኛ ስለሆነና ተለዋጭ መስመር መግቢያና መውጫ መንገድ ባለመኖሩ የትራንስፓርት አገልግሎት፣ የኢኮኖሚና ማህበራዊ መስተጋብር ሙሉ በሙሉ መቋረጡን አመልክቷል።

የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር በአካባቢው የተፈጠረውን ችግር ግምት ውስጥ በማስገባት ጉዳት የደረሰበትን የሃሚድ ውሃ ወንዝ የብረት ድልድይ በአፋጣኝ የጥገና ስራ እንዲያደርግለትና ክፍት እንዲሆን ጠይቋል።

@tikvahethiopia