TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.1K photos
1.5K videos
211 files
4.09K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
" ጉዳዩ ዓለም አቀፍ የወንጀል ገጽታ ያለው ነው " -  የውጭ ጉዳይ ሚኒሰቴር የታገቱት ኢትዮጵያውያን ጉዳይ ከምን ደረሰ ? የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው ፦ " በህገወጥ ዓለምአቀፍ ደላሎች ተታለው ወደ ማይናማር ፣ ታይላንድ፣ ቻይና ድንበር አዋሳኝ አካባቢዎች ወደሚገኙ ህገወጥ ካምፓች ተወስደው የሚገኙ ዜጎችን ለማስመለስ በመንግስት የተጀመሩ ጥረቶች ቀጥለዋል። ጉዳዩ…
#Update

🚨“ በጣም ብዙ ችግር ነው እየደረሰባቸው ያለው። ጣታቸው የተቆረጠ አሉ ” - የወላጆች ኮሚቴ

ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ከሰጠው መግለጫ በመነሳት፣ “ አንዳንድ ሚዲያዎች መንግስት በማይናማር የታገቱ ዜጎችን አስለቀቀ ” በማለት መዘገባቸው ስህተት መሆኑን ጉዳዩን የሚከታተሉ የታጋች ቤተሰቦች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

የታጋቾቹ ቤተሰቦች በዝርዝር ምን አሉ ?

“ አጋቾች  ያገቷቸውን ልጆቻችንን ‘መንግስት አስለቀቀ’ መባሉ ትክክል አይደለም።

አጋቾቹ ሲቀጧቸው የተጎዱ፣ በህመም ሳቢያ መስራት የማይችሉ ልጆችን ከካምፕ አውጥተው ታይላንድ ድንበር ሲጥሏቸው ሰብአዊ መብት ላይ የሚሰሩ ኤን.ጂ.ኦ አንስተው ታይላንድ በመውሰድ አሳክመው ህንድ ካለው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጋር በመሆን ነው ኢትዮጵያ እንዲገቡ ያደረጓቸው።

አንዳንድ ሚዲያዎች የዘገቡትና መንግስትም ድፍን ባለ መልኩ የሰጠውን መግለጫ መነሻ በማድረግ ማይናማር ያሉ ልጆች የተለቀቁ የመሰላቸው
አድማጮች እንኳን ደስ አላችሁ ’ የሚለን በዝቷል። እውነታው ይሄ አይደለም።

ይህን ጉዳይ ህዝብ ይረዳው። ማይናማር ከታገቱት ልጆች መካከል እንዲለቀቁ በተደረገ ጥረት ማንም አልተለቀቀም።

ታይላንድ ያሉት ናቸው እንጂ ማይናማር ያሉት አይደሉም የወጡት። ዋሽተው ነው። ዜናውን አካብደውታል። እኛን ምንም ተስፋ አልሰጡንም። ‘አትምጡ’ ነው ያሉን ” ሲሉ አስረድተዋል።

የወላጆች ኮሚቴ በበኩሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል ምን አለ ?

በዚህ መልኩ (ታጋቾች ተለቀዋል በሚል) የዘገቡት ሚዲያዎች ሁለት፣ ሦስት ጊዜ ድምፅ እንዲሆኑን ጠይቀናቸው ሳለ ‘ እንከሰሳለን ’ ብለው ነው የፈሩት። አሁን ግን ያልተወራውን ማስተላለፍ ከኢቲክስ ውጪ ነው። በጣም ቅር ብሎናል። እውነታውን አሳውቁልን።

በታይላንድና በማይናማር ድንበር ያሉት ልጆች እንጂ ወጡ የተባሉት ከማይናማር ግዛት ካሉት ጋር እንደማይገናኝ በህንድ የሚገኘው ኢትዮጵያ ኤምባሲ ነግሮናል።

የኤምባሲው ሰዎች ‘እኛ የሚመለከተን ታይላንድ አካባቢ ያለውን ብቻ እንጂ የማይናማሩ የሚመለከተው ቶኪዮ ያለው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ነውና ማይናማር ያሉትን አንድም ነገር አልሰራንም’ ብለው ቃል በቃል ነው የነገሩን።

ከኢትዮጵያ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር አምባሳደር ነብያት ጌታቸው በመግቢያ ንግግራቸው ያስተላለፉት ትክክለኛውን ‘ታይላንድ አካባቢ ያሉትን’ ብለው ነው።

ነገር ግን አንዳንድ ሚዲያዎች በስቃይ ላይ ያሉ ልጆችን መንግስት እያስወጣ እንዳለ አድርገው ነው መግለጫውን የዘገቡት። ይህ ቅር አሰኝቶናል።


ሌሎች አገራት እኮ ዜጎቻቸውን ያስወጡት ከትራደሽናል ሊደሮች፣ ከኤምባሲዎች ጋር ሆነው በመስራት ነው። የኛዎቹ ግን ይህን ለማድረግ ፈቃደኛ አይደሉም።

አንዱን ኢትዮጵያዊ የመራቢያ አካሉን የዘር ፍሬ ነቅለውታል። በጣም ብዙ ችግር ነው እየደረሰባቸው ያለው። ጣታቸው የተቆረጠ አሉ።

አሁንም ቢሆን የኢትዮጵያ መንግስት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተነጋግሮ በችግር ላይ ያሉ ልጆችንን  ካሉበት ስቃይ እንዲታደጋቸው በአጽንኦት እንጠይቃለን ” ብሏል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ከተራ2017

የ2017 ዓ/ም የጥምቀት ከተራ በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ በቤተክርስቲያኗ ሥርዓት እና ትውፊት ተከብሮ ውሏል።

ዛሬ ታቦታት ከየአብያተክርስቲያናቱ ወጥተው ወደ የማደሪያቸው ባህረ-ጥምቀት ገብተዋል።

በነገው ዕለት በመላው ሀገሪቱ የጥምቀት በዓል ይከበራል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ቪድዮ  ፦ #ሀማስ እና #እስራኤል የተኩስ አቁም ለማድረግ መስማማታቸው መነገሩን ተከትሎ ፍልስጤማውያን ደስታቸውን ለመግለፅ በጋዛ አደባባይ ወጥተዋል። " አላሁ አክበር ! አላሁ አክበር ! " ይህ በስምምነቱ መረጃ የተደሰቱ ፍልስጤማውያን ድምፅ ነው። በርካቶች የሰላም ወሬ በመንፈሱ በደስታ አልቅሰዋል ፤ አንብተዋል ፤ ፈጣሪ ቀጣዩን ጊዜ ደግሞ የሰላም ያደርግላቸው ዘንድ ተማፅነዋል። ፍልስጤማውያን ስምምነቱን…
#Peace🏳

ጋዛ ተኩስ አቁም ነገ ተግባራዊ ይሆናል።

የተኩስ አቁሙ ነገ ተግባራዊ እንደሚሆን የኳታር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሳውቋል።

የእስራኤል መከላከያ ሚኒስቴር ነገ በሀገሩ ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 2 ሰዓት ተኩል ላይ የተኩስ አቁሙ ተግባራዊ እንደሚሆን አረጋግጧል።

የጠቅላይ ሚኒስቴር ቤኒያሚን ኔታንያሁ ዛሬ ቅዳሜ የተኩስ አቁሙን አፅድቋል።

ተኩስ አቁሙ ስራ ላይ ሲውል 1,904 ፍልስጤማውያን ከእስራኤል እስር ቤቶች እንደሚለቀቁ የእስራኤል መንግሥት አሳውቋል።

ሀማስ ደግሞ ከ98 እስራኤላውያን ታጋቾች መካከል 33ቱን ለ6 ሳምንታት በሚዘልቀው የተኩስ አቁም ወቅት ይለቃል።

ግብፅ ሰብዓዊ እርዳታ ወደ ጋዛ ለመላክ እየተዘጋጀች ነው።

በሌላ በኩል ግን ሀማስ እና እስራኤል የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ መድረሳቸው ከተገለጸ በኃላ 122 ፍልስጤማውያን በእስራኤል መገደላቸውን የጋዛ የሰላማዊ ሰዎች ጥበቃ ኤጀንሲ ገልጿል።

እስካሁን በ15 ወራት ጦርነት የተገደሉት ፍልስጤማውያን ቁጥር 46,899 ደርሷል። 110,725 ሰዎች ታጎድተዋል።

መረጃው ከዶቼ ቨለ የተገኘ ነው።

@tikvahethiopia
" በተራሮቹ ላይ የተከሰተው እሳት ከመስፋፋቱና ከፍተኛ ችግር ከማስከተሉ በፊት ህብረተሰቡ እንዲሳተፍ እና አስፈላጊው ድጋፍ እንዲደረግ ጥሪ እናቀርባለን " - ወረዳው

በኦሮሚያ ክልል፣ በምዕራብ አርሲ ዞን ወንዶ ወረዳ " ጎቱ ኦኖማ " በተባለው አከባቢ ከሰዓት 10 ሰዓት አከባቢ በተራሮች ላይ የእሳት ቃጠሎ መነሳቱን የወረዳው ኮሚኒኬሽን ቢሮ አስታውቋል።

የእሳቱ መከሰት መንስዔው በድርቅ ምክንያት የተከሰተ ነው ያለው ቢሮው የተከሰተውን ቃጠሎ በህብረተሰቡ ተሳትፎ ለማጥፋት እየተሞከረ ነው ሲል አስታውቋል።

ሆኖሞ የተከሰተውን የእሳት አደጋ ተከትሎ በማኅበራዊ ሚዲያው በ 'እሳተ ገሞራ' የተከሰተ ነው በሚል የተሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ ነው ሲል ገልጿል።

በተራሮቹ ላይ የተከሰተው እሳት ከመስፋፋቱ እና ከፍተኛ ችግር ከማስከተሉ በፊት ህብረተሰቡ እንዲሳተፍ እና አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርግም ቢሮው ባወጣው መረጃ ጠይቋል።

Via @tikvahethmagazine
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update : ቲክቶክ በመጪው እሁድ በአሜሪካ አገልግሎቱን እንደሚያቆም አስታውቋል። ቲክቶክ የተጣለበት እገዳ ተግባራዊ ከመሆኑ በፊት መንግሥት ጣልቃ ካልገባ በስተቀር ከመጪው እሁድ ጀምሮ መተግበሪያውን በአሜሪካ ለማቆም እንደሚገደድ ገልጿል። ኩባንያው በሰጠው መግለጫ ዋይት ሃውስ እና የፍትህ ዲፓርትመንት " ቲክቶክ በቀጣይነት እንዲቀጥል ለማህበራዊ ሚዲያው መሰረታዊ የሚባሉ ግልጽነት እና ማረጋገጫ መስጠት…
አሜሪካ ቲክቶክን ዘጋች።

' ቲክቶክ ' የተባለው የአጫጭር ቪድዮ ማጋሪያ እስከ ዛሬ እሁድ ድረስ እንዲሸጥ ካልሆነ ግን እንዲታገድ የወጣው ህግ ተግባራዊ ሆኗል።

በዚህም ቲክቶክ በመላ አሜሪካ ውስጥ ከዛሬ ጀምሮ እንዳይሰራ ተደርጓል።

መተግበሪያው ገና እግዱ ተግባራዊ የሚሆንበት ሰዓት ሳይደርስ ቀደም ብሎ (ከሰዓታት በፊት) ነው የዘጋው።

በቲክቶክ ተጠቃሚዎች ስክሪን ላይ ፥ " ቲክቶክን ለማገድ የወጣው ህግ ተግባራዊ ሆኗል በዚህም አሁን ቲክቶክን መጠቀም አይችሉም " የሚል ፅሁፍ ነው የሚታየው።

ቲክቶክ ትራምፕ ስልጣናቸውን ተረክበው ወደ ቢሮ ሲገቡ መፍትሄ ለማበጀት አብረዋቸው እንደሚሰሩ እንደጠቆሟቸው በማመልከትም እስከዚያው ድረስ ተገልጋዮቹ እንዲጠባበቁት ጠይቋል።

ትራምፕ ቲክቶክ መተግበሪያ ካልተሸጠ እንዲታገድ የሚለው ህግ እንዲዘገይ ጠይቀው የነበረ ቢሆንም ከመታገድ ሊያድነቱ አልቻሉም።

ፕሬዜዳንታዊ ስልጣናቸውን ሲረከቡ ምን ሊያደርጉ ይችላሉ ? የሚለው በቀጣይ ይታያል።

ቲክቶክ 170 ሚሊዮን ተጠቃሚዎች ነበሩት።

@tikvahethiopia
#ጥምቀት

እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ አደረሳችሁ ! በዓሉ በደስትና በረከት የተሞላ እንዲሆን ከልብ እንመኛለን።

መልካም የጥምቀት በዓል !

#TikvahEthiopiaFamily

@tikvahethiopia
#ጥምቀት

የ2017 ዓ/ም የጥምቀት በዓል በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን በተለያዩ ሃይማኖታዊ እና መንፈሳዊ ስነ-ስርአቶች እየተከበረ ይገኛል።

ዛሬ ጥዋት የእምነቱ ተከታዮች በቤተክርስቲያን በመሰባሰብ በዓለ ጥምቀቱን በማህሌት ፣ በቅዳሴ፣ በመንፈሳዊ መዝሙሮች እና በተለያዩ መርሃ ግብሮች አክብረዋል።

በተለይም በአዲስ አበባ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሊቀ-ጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነኢየሱስ በተገኙበት ልደታ ማሪያም ካቶሊክ ካቴድራል ቤተክርስቲያን ተከብሯል።

ፎቶ፦ Pax Catholic TV

@tikvahethiopia