TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59K photos
1.5K videos
211 files
4.08K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
መላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ምዕመናን በሙሉ እንኳን ለ2017 ዓ/ም የጥምቀት #ከተራ በዓል አደረሳችሁ ! መልካም በዓል ! @tikvahethiopia
#ከተራ2017 : በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት እና ትውፊት መሰረት የከተራ በዓል እየተከበረ ይገኛል።

በገጠርም በከተማም ያሉ ታቦታት ከየአብያተክርስቲያናቱ ወጥተው ወደ የማደሪያቸው ባህረ-ጥምቀት በማምራት ላይ ይገኛሉ።

በተለያዩ የባህል አልባሳት ያሸበረቁ ምዕመናን፣ ካህናት፣ ዲያቆናትና መዘምራን ታቦታቱን አጅበው ወደየማደሪያቸው በመሸኘት ላይ ይገኛሉ።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፎቶዎቹን ከተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ማሰባሰቡን ይገልጻል

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ከተራ2017 : በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት እና ትውፊት መሰረት የከተራ በዓል እየተከበረ ይገኛል። በገጠርም በከተማም ያሉ ታቦታት ከየአብያተክርስቲያናቱ ወጥተው ወደ የማደሪያቸው ባህረ-ጥምቀት በማምራት ላይ ይገኛሉ። በተለያዩ የባህል አልባሳት ያሸበረቁ ምዕመናን፣ ካህናት፣ ዲያቆናትና መዘምራን ታቦታቱን አጅበው ወደየማደሪያቸው በመሸኘት ላይ ይገኛሉ። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፎቶዎቹን…
#ጎንደር

በታሪካዊቷ እና ጥንታዊቷ ጎንደር ሁሉም ታቦታት ፒያሳ በመገናኘት ወደ ማደሪያ ቦታቸው እየተጓዙ ይገኛሉ።

የጥምቀት ከተራ በዓል በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ እየተከበረ ይገኛል።

ጎንደር የጥምቀት በዓል እጅግ በጣም በደማቅ ሁኔታ ከሚከበርባቸው የሀገራችን አካባቢዎች አንዱ ሲሆን ለዘንድሮው በዓል በርካታ እንግዶች በዓሉ ላይ ለመታደም ጎንደር ተገኝተዋል።

ፎቶ፦ ማህበረ ቅዱሳን እና ፋኖስ ፒክቸርስ

@tikvahethiopia
ሞሐ የለስላሳ መጠጦች ኢንዱስትሪ አክሲዮን ማህበር፣ ለደንበኞቹ ካዘጋጃቸው በርካታ ሽልማቶች
ውስጥ አንዱ ቢዋይዲ የኤሌክትሪክ መኪና ዕጣ፣ በመቀሌ ለዕድለኛ ወጥቷል፡፡
ዕድለኛው አሸናፊ አቶ የማነ ነጋሽ ፣ ሽልማታቸውን ጥር 10 ቀን 2017ዓ.ም. በመቀሌ ከተማ በተከናወነ
ልዩ የሽልማት ፕሮግራም ተረክበዋል፡፡
ከዚህ በፊት በአዲስ አበባ እና በድሬዳዋ ከተማ ነዋሪ የሆኑ ዕድለኞች ሚሪንዳ እና ፔፕሲ ጠጥተው
ቢዋይዲ የኤሌክትሪክ መኪና ዕጣ ማሸነፋቸው ይታወሳል፡፡
ወጋገን ባንክ !

በወጋገን ካርድ በፖስ ማሽኖቻችን ክፍያ ሲፈፅሙ ተመላሽ እንዳለው ሰምተዋል ?

በወጋገን ክፍያ ካርድዎ ለአጠቃቀም ምቹ፣ ፈጣን እና አስተማማኝ በሆኑት የወጋገን ፖስ ማሽኖች ተጠቅመው በሆቴሎች እና ሬስቶራንቶች ፣ሱፐር ማርኬቶች፣ ሆስፒታሎች ፣ የገበያ ማዕከላት እንዲሁም በተለያዩ የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላገኙት አገልግሎት እና ለገዙት ዕቃ  ክፍያ ሲፈፅሙ የገንዘብ ተመላሽ ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡

ልብ ይበሉ !

እስከ ጥር 28 ቀን 2017 ዓ.ም በወጋገን የክፍያ ካርድዎ በፖስ ማሽኖቻችን ክፍያዎን ሲፈፅሙ ግብይትዎ ቀልጣፋ፣ ምቹ እና አስተማማኝነቱ እንደተጠበቀ ሆኖ የተመላሽ ገንዘብ ተጠቃሚ ይሆናሉ።

ዛሬውኑ ፈጥነው የወጋገን ካርድዎን ይውሰዱ

ለበለጠ መረጃ ወደ ደንበኞች ግንኙነት ማዕከል በ866 ነፃ የስልክ መስመር ይደውሉ! በተጨማሪም ከስር የተቀመጠውን ሊንክ በመጫን የማህበራዊ ሚዲያዎቻችንን ይቀላቀላሉ https://linktr.ee/WegagenBank
TIKVAH-ETHIOPIA
" ጉዳዩ ዓለም አቀፍ የወንጀል ገጽታ ያለው ነው " -  የውጭ ጉዳይ ሚኒሰቴር የታገቱት ኢትዮጵያውያን ጉዳይ ከምን ደረሰ ? የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው ፦ " በህገወጥ ዓለምአቀፍ ደላሎች ተታለው ወደ ማይናማር ፣ ታይላንድ፣ ቻይና ድንበር አዋሳኝ አካባቢዎች ወደሚገኙ ህገወጥ ካምፓች ተወስደው የሚገኙ ዜጎችን ለማስመለስ በመንግስት የተጀመሩ ጥረቶች ቀጥለዋል። ጉዳዩ…
#Update

🚨“ በጣም ብዙ ችግር ነው እየደረሰባቸው ያለው። ጣታቸው የተቆረጠ አሉ ” - የወላጆች ኮሚቴ

ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ከሰጠው መግለጫ በመነሳት፣ “ አንዳንድ ሚዲያዎች መንግስት በማይናማር የታገቱ ዜጎችን አስለቀቀ ” በማለት መዘገባቸው ስህተት መሆኑን ጉዳዩን የሚከታተሉ የታጋች ቤተሰቦች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

የታጋቾቹ ቤተሰቦች በዝርዝር ምን አሉ ?

“ አጋቾች  ያገቷቸውን ልጆቻችንን ‘መንግስት አስለቀቀ’ መባሉ ትክክል አይደለም።

አጋቾቹ ሲቀጧቸው የተጎዱ፣ በህመም ሳቢያ መስራት የማይችሉ ልጆችን ከካምፕ አውጥተው ታይላንድ ድንበር ሲጥሏቸው ሰብአዊ መብት ላይ የሚሰሩ ኤን.ጂ.ኦ አንስተው ታይላንድ በመውሰድ አሳክመው ህንድ ካለው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጋር በመሆን ነው ኢትዮጵያ እንዲገቡ ያደረጓቸው።

አንዳንድ ሚዲያዎች የዘገቡትና መንግስትም ድፍን ባለ መልኩ የሰጠውን መግለጫ መነሻ በማድረግ ማይናማር ያሉ ልጆች የተለቀቁ የመሰላቸው
አድማጮች እንኳን ደስ አላችሁ ’ የሚለን በዝቷል። እውነታው ይሄ አይደለም።

ይህን ጉዳይ ህዝብ ይረዳው። ማይናማር ከታገቱት ልጆች መካከል እንዲለቀቁ በተደረገ ጥረት ማንም አልተለቀቀም።

ታይላንድ ያሉት ናቸው እንጂ ማይናማር ያሉት አይደሉም የወጡት። ዋሽተው ነው። ዜናውን አካብደውታል። እኛን ምንም ተስፋ አልሰጡንም። ‘አትምጡ’ ነው ያሉን ” ሲሉ አስረድተዋል።

የወላጆች ኮሚቴ በበኩሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል ምን አለ ?

በዚህ መልኩ (ታጋቾች ተለቀዋል በሚል) የዘገቡት ሚዲያዎች ሁለት፣ ሦስት ጊዜ ድምፅ እንዲሆኑን ጠይቀናቸው ሳለ ‘ እንከሰሳለን ’ ብለው ነው የፈሩት። አሁን ግን ያልተወራውን ማስተላለፍ ከኢቲክስ ውጪ ነው። በጣም ቅር ብሎናል። እውነታውን አሳውቁልን።

በታይላንድና በማይናማር ድንበር ያሉት ልጆች እንጂ ወጡ የተባሉት ከማይናማር ግዛት ካሉት ጋር እንደማይገናኝ በህንድ የሚገኘው ኢትዮጵያ ኤምባሲ ነግሮናል።

የኤምባሲው ሰዎች ‘እኛ የሚመለከተን ታይላንድ አካባቢ ያለውን ብቻ እንጂ የማይናማሩ የሚመለከተው ቶኪዮ ያለው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ነውና ማይናማር ያሉትን አንድም ነገር አልሰራንም’ ብለው ቃል በቃል ነው የነገሩን።

ከኢትዮጵያ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር አምባሳደር ነብያት ጌታቸው በመግቢያ ንግግራቸው ያስተላለፉት ትክክለኛውን ‘ታይላንድ አካባቢ ያሉትን’ ብለው ነው።

ነገር ግን አንዳንድ ሚዲያዎች በስቃይ ላይ ያሉ ልጆችን መንግስት እያስወጣ እንዳለ አድርገው ነው መግለጫውን የዘገቡት። ይህ ቅር አሰኝቶናል።


ሌሎች አገራት እኮ ዜጎቻቸውን ያስወጡት ከትራደሽናል ሊደሮች፣ ከኤምባሲዎች ጋር ሆነው በመስራት ነው። የኛዎቹ ግን ይህን ለማድረግ ፈቃደኛ አይደሉም።

አንዱን ኢትዮጵያዊ የመራቢያ አካሉን የዘር ፍሬ ነቅለውታል። በጣም ብዙ ችግር ነው እየደረሰባቸው ያለው። ጣታቸው የተቆረጠ አሉ።

አሁንም ቢሆን የኢትዮጵያ መንግስት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተነጋግሮ በችግር ላይ ያሉ ልጆችንን  ካሉበት ስቃይ እንዲታደጋቸው በአጽንኦት እንጠይቃለን ” ብሏል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ከተራ2017

የ2017 ዓ/ም የጥምቀት ከተራ በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ በቤተክርስቲያኗ ሥርዓት እና ትውፊት ተከብሮ ውሏል።

ዛሬ ታቦታት ከየአብያተክርስቲያናቱ ወጥተው ወደ የማደሪያቸው ባህረ-ጥምቀት ገብተዋል።

በነገው ዕለት በመላው ሀገሪቱ የጥምቀት በዓል ይከበራል።

@tikvahethiopia