TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.1K photos
1.5K videos
211 files
4.09K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" ለ1,523 ቀናት ያህል በፕላስቲክ ቤት መኖር ይብቃን " - ተፈናቃይ ወገኖች

ዛሬ ጥዋት በመቐለ ሰላማዊ ስልፍ ተካሂዷል።

ሰላማዊ ሰልፉ " በቃን ወደ ቄያችን መልሱን " ባሉ የተፈናቃይ መጠለያዎች ውስጥ በሚገኙ ወገኖች አማካኝነት ነው የተደረገው።

የመቐለ ሮማናት አደባባይ የሚወስዱ መንገዶች ከጥዋቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ በከተማዋ ፓሊስ ከተሸከርካሪ እና ከእግረኞች እንቅስቃሴ ነፃ  እንዲሆኑ ተደርገው ነበር።

በመቐለ እና ከመቐለ ውጪ ባሉት የተፈናቃይ መጠለያዎች የሚገኙ ወገኖች " ይበቃል !! " በሚል በሦስት አቅጣጫ ወደ ሮማናት አደባባይ ተሰባስበው ድምጻቸውን አሰምተዋል።

ሰልፈኞች በሮማናት አደባባይ እንደደረሱ ፦

- ለ1523 ቀናት በፕላስቲክ ቤት መኖር ይብቃን !
- የፕሪቶሪያ ስምምነት በሙሉነት ይተግበር !
- ወደ ቤታችን መልሱን !
- ጦርነት እንጠየፋለን ፤ ሰላም እንሻለን !
- ዓለም ድምፃችንን ስሚ !
- በመቀጠል ያለው የተፈናቃዮች ሞት ይብቃ !
- ህገ- መንግስት ይከበር !  ... የሚሉ እና ሌሎች መፈክሮች አሰምተዋል።

ተፈናቃዮቹ በተወካያቸው በኩል ባሰሙት መግለጫ ፥ በመላ ትግራይ የሚገኙ ተፈናቃዮች በረሃብ እና መድሃኒት እጦት እየሞቱ መሆናቸው ጠቅሰዋል።

ለማሳያ ከመስከረም 2017 ዓ.ም ወዲህ  ብቻ በክልሉ በሚገኙ የተለያዩ የተፈናቃይ ማቆያ ጣብያዎች ይኖሩ የነበሩ ከ812 በላይ ወገኖች ህይወታቸው ማጣታቸው ገልፀዋል።

መሰል ሰለማዊ ሰልፍ የዛሬን ጨምሮ ለ3 ቀናት እንደሚኖር ተነግሯል። የዛሬው የማስጀመሪያ ስነ-ስርዓት ሰላማዊ ነበር።

የተፈናቃይ ስልፈኞቹን ጥያቄ እና የሚመለከተው የመንግስት አካል ምላሽ ካለ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ተከታትሎ ያቀርባል።

#TigraiTV #TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia   
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update እስካሁን ድረስ መቆጣጠር ባልተቻለው የአሜሪካ፣ ሎስ አንጀለስ  ሰደድ እሳት ምክንያት ቢያንስ 16 ሰዎች መሞታቸው ሲረጋገጥ ከ137 ሺህ በላይ ሰዎች ተፈናቅለዋል። የበርካታ ሰዎች ቤት ወደ አመድነት ተቀይሯል። ሰደድ እሳቱ ያደረሰው ውድመት 135 ቢሊዮን ዶላር እንደሆነ የተገመተ ሲሆን ከዚህም ከፍ እንደሚል ይጠበቃል። እሳቱን ለመቆጣጠር የሚደረገው ጥረት ቢቀጥልም ዝነኛ ወደሆነውና የአሜሪካ…
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
" መላው የሎስ አንጀለስ ግዛት በእሳት ስጋት ውስጥ ይገኛል " - ባለስልጣናት

በአሜሪካ ፤ ሎስ አንጀለስ የተነሳው ሰደድ እሳት አሁንም መቆጣጠር ያልተቻለ ሲሆን የሟቾች ቁጥርም ወደ 24 ከፍ ብሏል። 16 ሰዎች ደግሞ የገቡበት አይታወቅም።

በሎስ አንጀለስ ዙሪያ 3 አካባቢዎች መቃጠላቸውን ቀጥለዋል።

በአሁኑ ላይ ትልቁ እሣት ሚገኘው በፓሊሳድስ ሲሆን 9307 ሔክታር መሬትን ሲያቃጥል 11 በመቶውን መቆጣጠር ተችሏል።

የኢቶን እሳት በትልቅነቱ 2ኛ ደረጃ ሲይዝ ከ5665 ሔክታር በላይ አቃጥሏል። 27 በመቶው በቁጥጥር ስር ውሏል።

ከሞላ ጎደል በቁጥጥር ስር በዋለው በሃረስት እሳት 323 ሄክታር መሬት መቃጠሉ ታውቋል።

የእሳት አደጋ ሠራተኞች ትልቁን እሳት መቆጣጠር ቢጀምሩም ባለስልጣናት ግን ቀጣዮቹ ንፋሶች " አደጋ ሊያስከትሉ የሚችሉ የንፋስ ሁኔታዎች ሊሆኑ ይችላሉ መላው የሎስ አንጀለስ ግዛት በእሳት ስጋት ውስጥ ይገኛል " ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

እሳቱ በአሜሪካ ታሪክ አውዳሚው ለመሆን መቃረቡ ተገልጿል።

የግል ትንበያ ተቋም የሆነው " አኩዌዘር " በእሳት ቃጠሎ የተነሳ የደረሰው ኪሳራ ግምት ከ250 እስከ 275 ቢሊዮን ዶላር ሊደርስ ይችላል ብሏል።

ለሌላ በኩል ፥ የአደጋ ቀጠና ከሆኑ ቦታዎች ሰዎች እንዲወጡ የታዘዘ ሲሆን የወጡም አሉ።

ነዋሪዎች እንዲወጡ በታዘዙባቸው አካባቢዎች ዝርፊያ ሲፈፅሙ የነበሩ 29 ሰዎች መታሰራቸው ተነግሯል።

ሰዎች ቤታቸው ለቀው ሲወጡ ሲዘርፉ የነበሩ በርካቶች ነበሩ።

ከዚህ ባለፈ ፥ በሰደድ እሳቱን ምክንያት አከራዮች በህገወጥ መንገድ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ላይ ከፍተኛ የሆነ ጭማሬ ማድረጋቸው ተነግሯል።

እሳቱን ተከትሎ ከዚህ ቀደም ይጠየቅበት ከነበረው የቤት ኪራይ በሺዎች በመጨመር እንደተጠየቁ አንዳንዶች ገልጸዋል።

በሰደድ እሳቱ በሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ቤታቸው አመድ ሆኗል። በርካታ የተፈናቀሉ ተጎጂዎች " የማይቀምስ የቤት ኪራይ እና የሆቴል ክፍያ እየተጠየቅን ነው " ማለታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
#ብርሃን_ባንክ
መልካም ዜና ለብርሃን ቤተሰቦች በሙሉ
“በብርሃን መደጋገፍ” በሚል ፡ አዲስ የእድር አገልግሎት ጠቀም ካለ ወለድ እና  የብድር አማራጮች ጋር በብርሃን ባንክ ቀርቦሎታል። በአቅራቢያዎ ወደሚገኝ ቅርንጫፍ ጎራ ብለው ወይም በ8292 የደንበኞች አገልግሎት ቁጥር ደውለው ዝርዝር መረጃ ማግኘት ይችላሉ።
እንደ ስማችን ብርሃን ነው ሥራችን!
#Beberhanmedegagef #edir #digitalfinancialservice #berhanbank #bank #Stressfreebanking #bankinethiopia #finance
➡️ Facebook
➡️ Telegram
➡️ Instagram
➡️ Twitter
➡️ LinkedIn
➡️ YouTube
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር ዛሬ ጥር 5/2017 ዓ.ም ተፈናቃዮች " ይበቃል ወደ ቄያችን መልሱን ! " በሚል የጀመሩትን ሰላማዊ ሰልፍ የሚደግፍ መግለጫ አውጥተዋል። 

" ይበቃል ወደ ቄያችን መልሱን በሚል መሪ ቃል በተፈናቃዮች የተጠራው ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ ቀናና የሚደገፍ " ብሎታል ጊዚያዊ አስተዳደሩ በመግለጫው። 

" የተፈናቃዮች መከራ ተገቢ ምላሽ አልተሰጠውም " ያለው መግለጫው " የፌደራል መንግስት የገባው ውል እና ቃል በመተግበር ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው መመለስ አለበት " ሲል በአፅንኦት ገልጿል።

" አሁንም በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት መሰረት ከአገር መከላከያ ውጪ ያሉ ታጣቂዎች ይውጡ " ሲልም አክሏል።

" በህገ-መንግስቱ ማእቀፍ የትግራይ ግዛታዊ አንድነት ተከብሮ ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው መመለስ አለባቸው "ም ብሏል።

" የአፍሪካ ህብረት ፣ የአሜሪካ መንግስት ፣ የአውሮፓ ህብረት እና የዓለም አቀፍ ማህበረሰብ የህዝቡ ድምፅ በማዳመጥ የፕሪቶሪያ ውል በአግባቡ ተግባራዊ እንዲሆን ጫናቸው እንዲያሳድሩ " ሲልም ጥሪ አቅርቧል።

" ፅላል ስቪክ ማሕበር ማሕበረሰብ ምዕራብ ትግራይ " የተሰኘ መንግስታዊ ያልሆነ ማህበር ያስተባበረውና " ይበቃል ! " በሚል መሪ ቃል ዛሬ በመቐለ ሮማናት አደባባይ መንገድ በመዝጋት የተጀመረው የተፈናቀዮች ሰላማዊ ሰልፍ እስከ ጥር 7/2017 ዓ.ም እንደሚቀጥል ታውቋል።

ዛሬ በርካታ የመቐለ ጎዳናዎች ተዘግተው በርካታ የፖሊስ አባላትም ተሰማርተው ነው የዋሉት።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia            
#FreeNaima

" ገንዘቡን ካላገኘን በቀር እንዳንደውልላቸው አስጠንቅቀውናል። በጣም ተጨንቀናል " - ቤተሰብ

በሊቢያ ታጣቂዎች በርካታ ስደተኞችን አግተው የማሰቃየት ድርጊት እየፈጸሙባቸው ይገኛል።

ከእነዚህ ታጋቾች መካከል የሀገራችን ልጅ ነሒማ ጀማል አንዷ ናት።

ነሒማ ከኦሮሚያ ክልል፤ ሻሸመኔ በመሰደድ ነው ወደ ሊቢያ ያቀናችው።

' ሬፊዩጂስ ኢን ሊቢያ ' የተሰኘው ተቋም በኤክስ ገፁ እንዳስታወቀው ነሒማ እና ሌሎች ስደተኞች ' ኩፍራ ' በምትባለው የሊቢያ ግዛት በታጣቂዎች ቁጥጥር ሥር ይገኛሉ።

ነሒማ በፎቶዎቹና በቪዲዮዎች ላይ አፏ በጨርቅ ተለጉሞ ስቃይ ሲደርስባት ትታያለች።

የነሒማ ጀማል ቤተሰቦች ቪዲዮዎች እና ፎቶዎች ተልኮላቸው የማስለቀቂያ ገንዘብ እንዲከፍሉ ማስጠንቀቂያ ደርሷቸዋል።

የነሒማ እህት ኢፍቱ ጀማል ፤ ነሒማ ከ8 ወራት በፊት ከሻሸመኔ ከተማ የ11ኛ ክፍል ትምህርቷን አቋርጣ ወደ ሊቢያ እንደተሰደደች ለቢቢሲ አማርኛ አገልግሎት ተናግራለች።

" ፎቶዎች እና ቪዲዮዎች ይልኩልናል። ስትሰቃይ ያሳዩናል። የድምፅ መልዕክትም ልከውልናል። እህታችን ' ገንዘብ ላኩላቸው ካልሆነ ይገድሉኛል ' ስትል ይሰማል " ስትል አስረድታችለች።

ነገር ግን ኢፍቱ እንደምትለው ቤተሰቡ አጋቾቹ የጠየቁትን ገንዘብ የመላክ አቅም የለውም።

' ሬፊዩጂስ ኢን ሊቢያ ' የተባለው ሊቢያ የሚገኙ ስደተኞችን ጉዳይ የሚከታተለው ተቋም እንዳለው የ20 ዓመቷ ነሒማ ጀማል ባለፈው ግንቦት ሊቢያ ከገባች ከቀናት በኋላ ነው በታጣቂዎቹ እጅ ውስጥ የገባችው።

በቁጥጥር ሥር ከዋለች በኋላ ስቃይ ሲደርስባት እና ስትደበደብ የሚያሳዩ ፎቶዎች እና ቪዲዮዎች ለቤተሰቦቿ ተልከዋል።

ኢፍቱ እንደምትለው ቤተሰቡ የተጠየቀውን ገንዘብ ለማሰባሰብ እርዳታ ቢጠይቅም እስካሁን ድረስ ሊሞላላቸው አልቻለም።

ቤተሰቡ የነሒማን ድምፅ ከሰማ ሁለት ሳምንት እንዳለፈው እህቷ ተናገራለች።

" ገንዘቡን ካላገኘን በቀር እንዳንደውልላቸው አስጠንቅቀውናል። በጣም ተጨንቀናል " ስትል አክላለች።

' ሬፊዩጂስ ኢን ሊቢያ ' ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ስቃዩ እና ማስፈራራቱ እንደተጠናከረ እና ይህ ደግሞ ቤተሰቦች ላይ ከፍተኛ ጫና እያሳደረ እንደሆነ ገልጿል።

አጋቾቹ ለነሒማ ማስለቀቂያ የጠየቁት ገንዘብ 6 ሺህ ዶላር ነው።

የነሒማ ቤተሰብ ይህንን ሁሉ ገንዘብ ለማሰባሰብ የሚችለውን ሁሉ እያደረገ ይገኛል።

ለነሒማ ቤተሰብ የተላኩ ቪዲዮዎች በርካታ ስደተኞች በአሰቃቂ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኙ ያሳያሉ።

ነሒማ እጅና እግሯ ተጠፍሮ፤ አፏ በጨርቅ ታፍኖ ትታያለች። ስቃይ ሲደርስባት እና ደም በደም ሆና የሚያሳዩ ቪዲዮዎች እና ፎቶዎችም አሉ።

ድርጅቱ በለቀቃቸው ቪዲዮዎች እና ፎቶዎች ላይ ነሒማ ብቻ ሳትሆን 50 ገደማ ሌሎች የአጋቾቹ ሰለባዎች ከጀርባዋ ተደርድረው ይታያሉ።

የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች በሊቢያ እየተካሄደ ያለውን የባርነት ንግድ ዓለም ረስቶታል ሲሉ ዓለም አቀፉን ማኅበረሰብ እየወቀሱ ናቸው።

በእርስ በርስ ጦርነት እየታመሰች ወዳለችው ሊቢያ በስደት የተጓዙት ነሒማ እና ሌሎች ስደተኞች መጨረሻቸው ምን ሊሆን እንደሚችል አይታወቅም።

በርካታ ኢትዮጵያውያንና ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ስደተኞች ሕይወታቸውን ለመቀየር በሚል ወደ አውሮፓ በሚያደርጉት ጉዞ የሜዲቴራኒያን ባሕርን ከማቋረጣቸው በፊት ሊቢያን ይረግጣሉ።

መረጃው ከሪፊውጂስ ኢን ሊቢያና ቢቢሲ አማርኛ አገልግሎት ነው የተገኘው።

#FreeNaima

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Earthquake ከትላንት ለሊት ጀምሮ እስከ ዛሬ ምሽት 12:20 ድረስ አዋሽና አካባቢው ተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተቶች ተመዝግበዋል። የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተቶቹ አዲስ አበባ ድረስ ንዝረታቸው ተሰምቷል። ከትላንት ለሊት ጀምሮ እስከ ዛሬ ምሽት 12:20 ድረስ በተለያየ ጊዜ በሬክተር ስኬል ፦ 👉 4.6 👉 4.5 👉 5.2 👉 4.3 👉 5.2 የሆኑ የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተቶች ተመዝግበዋል።…
#Earthquake : ዛሬ ሰኞ ምሽት 5:24 ሲል በሬክተር ስኬል 4.8 የተለካ የመሬት መንቀጥቀጥ ከአዋሽ 17 ኪ/ሜ ርቀት ላይ መከሰቱን የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ አሳውቋል።

የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረቱ አዲስ አበባና ሌሎችም ከተሞች ተሰምቷል።

" አሁን ላይ ቀንሷል ቆሟል ፣ ከአሁን በኃላ ምንም ነገር አይፈጠርም " በሚል መዘናጋት ጥንቃቄ እና ትኩረት ማጣት እንዳይመጣ መጠንቀቅ ይገባል።

የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተት ቅፅበታዊ  ፣  ተገማች ያልሆነና መተንበይ የማይቻል ነገር በመሆኑ ዘውትር ነቅቶ መጠበቁ የተሻለ ነው።

@tikvahethiopia
#አቢሲንያ_ባንክ
ቅዳሜ ጥር 10 ከረፋዱ 4:30 ቀጣይ ዙር የጥያቄ እና መልስ ውድድር በቴሌግራም ቻናላችን ላይ ይደረጋል። በየሳምንቱ አስር አሸናፊዎች ይሸለማሉ! ዛሬውኑ የቴሌግራም ቻናላችንን በመቀላቀልና ቀላል ጥያቄዎችን በመመለስ ይሸለሙ!

የቴሌግራም ሊንክ 👇
https://t.iss.one/BoAEth

አቢሲንያ የሁሉም ምርጫ!
#Telegram #giveaway #contest #Boa #bankinginethiopia #banksinethiopia #bankofabyssinia #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
TIKVAH-ETHIOPIA
#ሹመት : የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩት አቶ መሐመድ እድሪስ የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሕዳር 18 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ አቶ መሐመድ እድሪስን የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር አድርገው ሾመዋቸዋል። @tikvahethiopia
#ሹመት : ሳምሶን መኮንን (ዶ/ር) የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሾሙ።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሀን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሹመትን አስመልክቶ የቀረበለትን የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ በአንድ ድምፀ ተአቅቦ በአብላጫ ድምፅ አፅድቋል።

በዚሁ መሠረት ሳምሶን መኮንን (ዶ/ር) የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሹመዋል።

ሳምሶን መኮንን (ዶ/ር) ማናቸው ?

➡️ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የስትራቴጂክ ኮሚዩኒኬሽን እና አለምአቀፋዊነት ጽህፈት ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው ሲሰሩ ቆይተዋል።
   
➡️ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በጋዜጠኝነት እና ተግባቦት የትምህርት ዘርፍ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ አግኝተዋል።

➡️ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተማሩበት የትምህርት ክፍል በአስተማሪነት አገልግለዋል።

➡️ በውጭ ቋንቋዎች የማስተርስ ዲግሪ ባገኙበት አምቦ ዩኒቨርስቲ እና በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ አስተምረዋል። 

➡️ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የ12 ዓመታት የማስተማር እና የአመራርነት ልምድ አለቸው።

➡️ የዶክትሬት ዲግሪያቸውን ከደቡብ አፍሪካ ዩኒቨርስቲ (UNISA) በኮሚዩኒኬሽን አግኝተዋል።

➡️ በተለያዩ የምርምር ህትመቶች ላይ የወጡ ጽሁፎችን በግላቸው እና በጋራ አሳትመዋል።

➡️ በብሉምበርግ የአፍሪካ ሚዲያ ኢኒሼቴቭ ስር የሚሰጠውን የፋይናንስ ጋዜጠኝነት ስልጠናን በስራ አስኪያጅነት መርተዋል በሌሎች ተቋማትም በማማከር ስራዎች ተሳትፈዋል። 

#HoPR #EthiopiaInsider

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ፎቶ ፦ የመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የሕንፃ እድሳት ተጠናቆ ጥር 6 ቀን 2017 ዓ.ም ታቦተ ሕጉ ወደ መንበረ ክብሩ እንደሚመለስ ተገልጿል። ጥር 6 ቀን 2017 ዓ.ም ታቦተ ሕጉ ወደ መንበረ ክብሩ ይመለሳል ተብሏል። ካቴድራሉ እድሳት እየተደረገለት ከሁለት ዓመታት በላይ የቆየ ሲሆን ከ1 ወር በኋላ ሙሉ ለሙሉ ለአገልግሎት ክፍት ይደረጋል። ለካቴድራሉ እድሳት እስካሁን 124,827,576…
ፎቶ ፦ የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የእድሳት ሥራ ተጠናቆ በቅዱስ ፓትርያርኩ እየተመረቀ ነው።

የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የእድሳት ሥራ ተጠናቆ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ተመርቆ ታቦተ ሕጉ ጥንታዊነቱን ጠብቆ ወደ ታደሰው ካቴድራል በመግባት ላይ ይገኛል።

በምርቃት መርሐ ግብሩ ላይ ፤ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ፣ የጠቅላይ ቤተክህነት መምሪያ ኃላፊዎችና የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የየክፍል ኃላፊዎች ፣ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ፣ ምዕመናንና ምዕመናት ተገኝተዋል።

መረጃው የቤተክርስቲያኒቱ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ነው።

@tikvahethiopia
ወጋገን ባንክ ደንበኞች የሞባይል ዋሌት አገልግሎት ከኢ-ብር ሞባይል ፋይናንሻል ሰርቪስስ ጋር በመተባበር መስጠት ጀምሯል። አገልግሎቱ የባንክ ሂሳብ የሌላቸው ግለሰቦችንም ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው።

ባንኩ አገልግሎቱን ያስተዋወቀው በሽረ ከተማ በርካታ ደንበኞች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ነው።

የባንኩ የኢንተርፕራይዝ ሰርቪስስ ም/ሥራ አስፈፃሚ አቶ የኋላሸት ዘውዱ የወጋገን ኢ-ብር የሞባይል ዋሌት አገልግሎት ደንበኞች ካሉበት ሆነው በማንኛውም ጊዜ ገንዘብ ማስተላለፍ እና ክፍያ መፈፀም እንደሚያስችላቸው ገልፀዋል፡፡

የኢ-ብር ሞባይል ፋይናንሻል  ሰርቪስስ ቦርድ ሊቀመንበር የሆኑት አቶ በዕውቀት ታፈረ በበኩላቸው ባንኮች ከቴክኖሎጂ አቅራቢ ባለድርሻ አካላት ጋር የሚያደርጉት ትብብር የባንክ ኢንዱስትሪውን ለማዘመን የሚያግዝ መሆኑን ጠቅሰዋል።

የወጋገን ኢ-ብር የሞባይል ዋሌት አገልግሎት ከፕሌይ ስቶር ወይም አፕ ስቶር የኢ-ብር መተግበሪያውን በማውረድ ወይም ወደ *602# በመደወል ደንበኞች በቅድሚያ ወጋገን ባንክን በመምረጥ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆን እንደሚችሉ ተገልጿል፡፡

https://linktr.ee/WegagenBank