TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ትልቅ የሀገር ባለዉለታ ነበሩ ! " - አዋሽ ባንክ

ከአዋሽ ባንክ መስራቾች አንዱ የነበሩት አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን አስመልክቶ አዋሽ ባንክ የሀዘን መግለጫውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ልኳል።

ባንኩ ፥ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ የመጀመሪያው የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ እንዲሁም የባንኩ የመጀመሪያው ፕሬዝዳንት ነበሩ ብሏል።

" በህልፈተ ህይወታቸው የአዋሽ ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ፣ የማኔጅመንት አባላት እና መላዉ ሰራተኞች የተሰማንን ከፍተኛ ሀዘን እንገልጻለን " ሲል ገልጿል።

" አቶ ቡልቻ ደመቅሳ በህይወት በነበሩበት ዘመን የትላልቅ ስኬቶች ባለቤት የነበሩና ትልቅ የሀገር ባለ ዉለታ ነበሩ " ሲልም ገልጿል።

" በኢትዮጵያ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ውስጥ ጉልህ ስፍራ የነበራቸው ሰው ነበሩ። የሀገራችን የፋይናንስ ምክትል ሚንስትር ሆነው ያገለገሉ፤ እንዲሁም በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ውስጥ በተለያየ የኃላፊነት ደረጃ የሰሩ ትልቅ የሀገር ሃብት ነበሩ " ሲል አክሏል።

በአቶ ቡልቻ ደመቅሳ ህልፈተ ህይወት ሀዘኑን የገለጸው አዋሽ ባንክ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው፣ ለቤተሰቦቻቸው፣ እንዲሁም ለመላዉ የሀገራችን ህዝቦች መጽናናትን ተመኝቷል።

@tikvahethiopia
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች መልካም የልደት በዓል እንዲሆንላችሁ እንመኛለን።

" ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋል። " (ሉቃ. 2÷11)

መልካም የልደት በዓል !
Ayyaana Qillee Gaarii!
ርሑስ በዓል ልደት!

#TikvahEthiopiaFamily

@tikvahethiopia
#China #Tibet

ለሊቱን እና ጥዋት ላይ በዓለም በተለያዩ ሀገራት የተለያየ መጠን ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ ተመዝግቧል።

ከነዚህ ውስጥ እጅግ የከፋው እና የ53 ሰዎችን ህይወት የቀጠፈው የመሬት መንቀጥቀጥ በቻይና ፤ ቲቤት ግዛት ደርሷል።

የቻይና የመሬት መንቀጥቀጥ ኔትዎርክ ሴንተር በሬክተር ስኬል 6.8 የተመዘገበ ነው ብሏል።

የአሜሪካው ጂኦሎጂካል ሰርቬይ ግን የመሬት መንቀጥቀጡ በሬክተር ስኬል 7.1 የተመዘገበ ነው ሲል አመልክቷል።

በሬክተር ስኬል 6.8 ሆነ ከዛም በላይ የመሬት መንቀጥቀጥ እጅግ ጠንካራና አደገኛ ከፍተኛ የሆነ ውድመት ሊያደርስ የሚችል ነው።

በቲቤት 6 የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተቶች የተመዘገቡ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ ከፍተኛ 7.1 ነው።

በመሬት መንቀጥቀጡ ህንጻዎች ፣ መኖሪያ ቤቶች ተደርምሰዋል።

ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን የቻይና ሚዲያዎችን ዋቢ በማድረግ በትንሹ 53 ሰዎች እንደሞቱ ነገር ግን ከፍርስራሽ ስር ያሉ ሰዎች ሊኖሩ ይችላሉ በዚህም የሟቾች ቁጥር ሊጨምር ይችላል ብለዋል።

የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች የነፍስ አድን ስራ ላይ ተሰማርተዋል።

አደጋው ተራራማ በሆኑ የገጠራማ ክፍሎች የደረሰ ሲሆን ዋና ወደሚባሉ ከተሞች እንኳን አልተጠጋም።

የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረቱ በሰሜን ህንድ እና በኔፓል ዋና ከተማ ካታህማዱ ሌሎችም ቦታዎች በእጅጉ ተሰምቷል።

ባለስልጣናት ዜጎቻቸው እንዲረጋጉ እና ቀጣይ ለሚመጣው ሾክ ራሳቸውን እንዲያዘጋጁ አሳስበዋል።

ስፍራው በተደጋጋሚ ጊዜ የመሬት መንቀጥቀጥ የሚያስተናግድ ነው።

የመሬት መንቀጥቀጥ ቅፅበታዊ ፣ ለመገመት እና ለመተንበይ የሚያስቸግር የት ቦታ እንደሆነ እንጂ መቼ እንደሚፈጠር የማይታወቅ በመሆኑ ሁሌም ጥንቃቄ ማድረግ ንቁ ሆኖ መጠበቅ ይገባል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ከተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ያሰባሰበ ሲሆን ቪድዮዎቹና ፎቶዎቹን ከቲቤት እና ኔፓል የማህበራዊ ትስስር ገጾች ነው የወሰደው።

የመሬት መንቀጥቀጥ ሲከሰት ምን ማድረግ አለብን ? የሚወሰዱ የጥንቃቄ እርምጃዎችን ያንብቡ :
https://t.iss.one/tikvahethiopia/93267?single

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ነዳጅ የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በነበረበት ይቀጥላል ተብሏል። የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ፤ የታህሳስ ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በህዳር ወር በነበረበት የመሽጫ ዋጋ እንዲቀጥል በመንግሥት መወሰኑን አሳውቋል። ሚኒስቴሩ " የነዳጅ ማደያዎች እና ኩባንያዎች ያልተገባ የነዳጅ ክምችት ከመያዝ እና የዋጋ ጭማሪ ከማድረግ ተቆጥበው ውሳኔውን ተግባራዊ በማድረግ ህብረተሰቡን…
#ነዳጅ

ቤንዚን በሊትር 101.47 ብር ሲገባ ናፍጣ በሊትር 98.98 ብር ሆኗል።

ዛሬ በነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ጭማሪ ተደርጓል።

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከዛሬ ታኅሣሥ 29 ቀን 2017 ዓ/ም ከምሽቱ 12 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ ተግባራዊ የሚሆን የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ መወሰኑን አሳውቋል።

በዚሁ መሰረት ፦

አንድ ሊትር ቤንዚን 101.47 ብር

አንድ ሊትር ናፍጣ 98.98 ብር

አንድ ሊትር ኬሮሲን 98.98 ብር

የአውሮፕላን ነዳጅ 109.56 ብር

አንድ ሊትር ከባድ ጥቁር ናፍጣ 105.97 ብር

አንድ ሊትር ቀላል ጥቁር ናፍጣ 108.30 ብር ሆኖ እንዲሸጥ ተወስኗል።

#ነዳጅ #ኢትዮጵያ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
የነዳጅ ዋጋ ምን ያህል ብር ጨመረ ?

ቤንዚን በሊትር 91 ብር ከ14 ሳንቲም ሲሸጥ የነበረ ሲሆን አሁን 10 ብር ከ33 ሳንቲም ጨምሮ 101 ብር ከ47 ሳንቲም ገብቷል።

ናፍጣ ደግሞ በሊትር 90 ብር ከ28 ሳንቲም ሲሸጥ የነበረ ሲሆን  8 ብር ከ7 ሳንቲም ጨምሮ 98 ብር ከ98 ሳንቲም ሆኗል።

በሌሎች የነዳጅ ምርቶች ላይም በትንሹ ከ8 ብር በላይ ተጨምሯል።

ከሁሉም በላይ በአውሮፕላን ነዳጅ ላይ የተጨመረው ከፍ ያለ ሲሆን በሊትር  31 ብር ከ8 ሳንቲም ጭማሪ ተደርጎ 77 ብር ከ76 ከነበረበት ወደ 109 ብር ከ56 ሳንቲም ገብቷል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የነዳጅ ዋጋ ምን ያህል ብር ጨመረ ? ቤንዚን በሊትር 91 ብር ከ14 ሳንቲም ሲሸጥ የነበረ ሲሆን አሁን 10 ብር ከ33 ሳንቲም ጨምሮ 101 ብር ከ47 ሳንቲም ገብቷል። ናፍጣ ደግሞ በሊትር 90 ብር ከ28 ሳንቲም ሲሸጥ የነበረ ሲሆን  8 ብር ከ7 ሳንቲም ጨምሮ 98 ብር ከ98 ሳንቲም ሆኗል። በሌሎች የነዳጅ ምርቶች ላይም በትንሹ ከ8 ብር በላይ ተጨምሯል። ከሁሉም በላይ በአውሮፕላን ነዳጅ ላይ የተጨመረው…
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ቪድዮ፦ ይህ እጅግ ረጅም የነዳጅ ሰልፍ በልደት በዓል ዋዜማ አዲስ አበባ ላይ የነበረ ነው። ከሰሞኑን የነዳጅ ማደያዎች እንዲህ ነበሩ።

አንዳንዶቹ " ቤንዚን የለም !! ፤ ናፍጣ የለም !! " እያሉ ሲለጥፉ ነበር።

ዜጎች ነዳጅ ለማግኘት ረጅም ሰልፍ ተሰፍለው እየዋሉ ስራቸው ሲበደል ፤ ሲጉላሉ ከርመዋል። ዛሬ ግን የነዳጅ ዋጋ ጨምሯል።

ሁሌም የወር መጨረሻ በመጣ ቁጥር ከወትሮ የተለየ ሰልፍ ፤ መጉላላት ይኖራል " የነዳጅ ዋጋ ሊጨምር ነው " በሚል። የነዳጅ ቦቴዎች መንገድ ላይ ሆን ብለው ይዘገያሉ።

ከሰሞኑን " የነዳጅ ዋጋ ሊጨምር ነው "  በሚል አፋር ላይ በየጥሻው ውስጥ ገብተው ተደብቀው የነበሩ በርካታ ቦቴዎች ከተደበቁበት እንዲወጡ ተደርገው ወደ መዳረሻቸው እንዲሄዱ ስለመደረጋቸው መነገሩ ይታወሳል።

@tikvahethiopia
#Abyssiniabank

አይዞን ለበዓል እኛ አለን።

ከአፖሎ እንዴት አነስተኛ ብድር መውሰድ እንደሚቻል ለማየት ሊንኩን ይጠቀሙ፡ https://t.iss.one/apollodigitalproduct/220

ለአንድሮይድስልኮች https://play.google.com/store/apps/details?id=com.boa.apollo&hl=en&gl=US
ለአፕል ስልኮች  https://apps.apple.com/us/app/apollo-digital/id1601224628

#Apollodigitalbank #Apollodigitalproduct #poweredbybankofabyssinia #BankofAbyssinia #የሁሉም_ምርጫ #The_Choice_For_all
TIKVAH-ETHIOPIA
🔈#ኮሬ “ ሰሞኑን በጎርካ ወረዳ ቆሬ ቀበሌ ንጹሐን ዜጎች በታጣቂዎች ተገድለዋል ” - የዞኑ አካል 🔴 “ እስካሁን ድረስ ነዋሪዎቹ በየቀኑ ይገደላሉ። የአንዳንዱ ግድያ ይገለጻል ፤ የአንዳንዱ አይገለጽም ሰው ተሰላችቶ ” - በሕዝብ እንደራሴዎች ም/ቤት የዞኑ ህዝብ ተወካይ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ ኮሬ ዞን የንጹሐን በታጣቂዎች ግድያ ባለመቆሙ ዞኑ እና በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት የዞኑ ተወካይና…
🚨#ኮሬ

ታጣቂዎች አደረሱት በሚባል ጥቃት ከዘጠኝ ዓመታት በላይ የንጹሐን ግድያ ልጓም ባልተገኘለት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን አሁንም “ ንጹሐን ተገድለዋል ” ተብሏል።

ስማቸው እንዲነገር ያልፈለጉ የዞኑ አካል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል፣ “ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት ባለፉት 48 ሰዓታት ብቻ የሁለት ሰዎች ህይወት አልፏል ” ብለዋል።

በዞኑ ኬረዳና ጀሎ በተሰኙት ቀበሌዎች  አንታዮ ዦላና አድማሱ አሰፋ የተባሉ ሰዎች ታጣቂዎቹ ሰነዘሩት በተባለ ጥቃት መገደላቸውን ከቤተሰቦቻቸው መረጋገጡን ነው የገለጹት።

አቶ አንታዮ ዦላ የተገደሉት ከትላንት በስቲያ ታኀሳስ 28 ቀን 2017 ዓ/ም ከቀኑ 11 ሰዓት ተኩል ኬረዳ ቀበሌ መሆኑን አስረድተው፣ “ ገዳዮቹ ከጋላና ወረዳ ሻሞሌ ሽዳ ታጥቀው ወደ ኮሬ ዞን ዘልቀው ገብተው ነው ” ብለዋል።

“ በዚሁ ቀበሌ ጥቃት ከመፈጸም ተጨማሪ የቤት እንስሳትን ዘርፈዋል ” ብለው፣ “ አድማሱ አሰፋ ደግሞ ታኀሳስ  29 ቀን 2017 ዓ/ም ከቀኑ 6:30 ገደማ ጄሎ ቀበሌ ተገድሏል ” ሲሉ ገልጸዋል።

“ ገዳዮቹ የጋላና ወረዳ የቡልቶ ጃልደሳ ታጣቂዎች ወደ ኮሬ ዞን ዘልቀው በመግባት ጥቃት ፈጽመው ነው ” ብለዋል።

“ ባለፉት ቀናት ጥቃት ለመሰንዘር ከፍተኛ እንቅስቃሴ እንደነበር ከህዝብ አስተያየት መረጃ መመልከት ተችሎ ነበር። መረጃዎቹ ከጃሎ፣ ኬረዳ፣ ዞቀሣ፣ ጋሙሌ፣ ሻሮ፣ ጎልቤ፣ ቆቦ፣ ዶርባዴ ቀበለያት ተሰባስበዋል” ነው ያሉት።

የንጹሀን ጥቃቱ እንዲቆም ለመንግስት አሳስበው እንደሆን በቅርቡ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ ያቀረበላቸው በሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት የዞኑ ሕዝብ ተወካይ አምዛዬ አወቀ (ዶ/ር)፣ በፓርላማ ቢያሳውቁም ድርጊቱ እንዳልቆመ ገልጸው ነበር።

“ ነዋሪዎቹ በየቀኑ ይገደላሉ። የአንዱ ግድያ ይገለጻል፤ የአንዱ አይገለጽም ሰው ተሰላችቶ” ብለው፣ “መንግስት ትኩረት ቢሰጥ ኖሮ ያ አካባቢው የሚያስቸግር አይደለም ጠባብ ቦታ ነው ገላና ሸለቆና ነጭ ሳር ፓርክ እነዚህ ሽፍቶች የሚንቀሳቀሱበት ነው ” ብለው ነበር።

ከዚህ ቀደም ስለጉዳዩ የጠየቅናቸው በክልሉ ምክር ቤት የቀድሞ አማሮ ምርጫ ክልል ተወካይ አቶ ዜናነህ አዱላ በበኩላቸው፣ “ አካባቢው ከ2009 ዓ/ም ጀምሮ በጸጥታ ችግር የወደቀ ነው ” ማለታቸው ይታወሳል።

“ በአካባቢው ላይ ከመንግስት ተቃርኖ የሚንቀሳቀሰው የሸኔ ታጣቂ መኖሩ ሁኔታውን አባብሶታል” ብለው፣ “ ‘መንግስት ቸልተኛ ሆኗል’ የሚል ግምገማ አለን ” ሲሉ ተናግረው ነበር።

ከወራት በፊት ቃሉን የሰጠን ዞን ኮሚኒኬሽን “ ባለፉት ዓመታት ከ300 በላይ ንጹሐን በታጣቂዎች ተገድለዋል ” ማለቱ አይዘነጋም።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
“ ቅልጥ አለቱ በመሬት ውስጥ የሚያደርገዉ እንቅስቃሴና ወደ ላይ የመውጣት ግፊቱ እንደቀጠለ ነው።  ግን ቀዝቅዞ እዛው ሊቀር፣ ከመሬት በላይ ሊፈነዳ ይችላል ” - ኤሊያስ ሌዊ (ዶ/ር) በአዋሽ ፈንታሌና ዶፈን ቮልካኖዎች መካከል የሚከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ጠንከርና ከፍ እያለ መምጣቱ በተደጋጋሚ ተገልጿል። ሰሞኑንም በተደጋጋሚ እየተከሰተ ተስተውሏል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ ለመሆኑ ምን መደረግ አለበት?…
#Earthquake

በአፋር ክልል አዋሽና አካባቢው እየተከሰተ ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ አሁንም ድረስ ቀጥሏል።

ትላንት ቀን እንዲሁም ለሊቱን ተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል።

የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ በመዘገበው ብቻ በሬክተር ስኬል 4.5 ፣ 4.7 ፣ 5.3 የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል።

ከሁሉም ከፍ ያለው ለሊት የተከሰተው በሬክተር ስኬል 5.3 ሲሆን የመሬት መንቀጥቀጡ አዋሽ እና አካባቢው በርካታ ሰዎችን ከእንቅልፋቸው ቀስቅስቋል።

ንዝረቱ አዲስ አበባ እና ሌሎች ከተሞችም ተሰምቷል።

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦፊዚክስ ፣ ስፔስ ሳይንስ እና አስትሮኖሚ ተቋም ዳይሬክተር ኤልያስ ሌዊ (ዶ/ር) ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ሰጥተው በነበረው ቃል ፤ ቅልጥ አለት መሬት ውስጥ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል። ይህ እንቅስቃሴ በፈንታሌ እና በዶፈን ተራራዎች መካከል ሲሆን የሚታየው ርዕደ መሬት የዛ ውጤት ነው።

የዛ እንቅስቃሴ የፈጠረው መንቀጥቀጥ ሞገድ በመሬት ውስጥ ተጉዞ ነው አዲስ አበባ ድረስ የሚሰማው።

@tikvahethiopia