TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#አእላፋትዝማሬ #TheMelodyofMyriads
በአዲስ አበባ አእላፋት የተሳተፉበት " የአእላፋት ዝማሬ / The Melody of Myriads " መርሐግብር በቦሌ በድብረ ሳሌም መድኃኔዓለም ተከናውኗል።
ይህ ዘንድሮ ለ2ኛ ጊዜ የተከናወነው መርሐግብር ከአምናውን የላቀ የምእመን ቁጥር የተገኘበት እንደሆነ በስፍራው በመገኘት ለመገንዘብ ችለናል።
መርሐግብሩ ላይ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት እንዲሁም ብፁአን አባቶች ተገኝተው ነበር።
የዝማሬና የምስጋና መርሐግብሩ የልደት በዓልን በማይገባ ቦታ የሚያሳልፉ በእግዚአብሔር ቤት ሆነው እንዲያሳልፉ ለማድረግ ዓላማ ያነገበ ነው።
የፎቶ ባለቤት ፦ ሚኪ ፎቶግራፊ
የቪድዮ ባለቤት ፦ ጃንደረባው ሚዲያ
@tikvahethiopia

" አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ትልቅ የሀገር ባለዉለታ ነበሩ ! " - አዋሽ ባንክ
ከአዋሽ ባንክ መስራቾች አንዱ የነበሩት አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን አስመልክቶ አዋሽ ባንክ የሀዘን መግለጫውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ልኳል።
ባንኩ ፥ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ የመጀመሪያው የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ እንዲሁም የባንኩ የመጀመሪያው ፕሬዝዳንት ነበሩ ብሏል።
" በህልፈተ ህይወታቸው የአዋሽ ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ፣ የማኔጅመንት አባላት እና መላዉ ሰራተኞች የተሰማንን ከፍተኛ ሀዘን እንገልጻለን " ሲል ገልጿል።
" አቶ ቡልቻ ደመቅሳ በህይወት በነበሩበት ዘመን የትላልቅ ስኬቶች ባለቤት የነበሩና ትልቅ የሀገር ባለ ዉለታ ነበሩ " ሲልም ገልጿል።
" በኢትዮጵያ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ውስጥ ጉልህ ስፍራ የነበራቸው ሰው ነበሩ። የሀገራችን የፋይናንስ ምክትል ሚንስትር ሆነው ያገለገሉ፤ እንዲሁም በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ውስጥ በተለያየ የኃላፊነት ደረጃ የሰሩ ትልቅ የሀገር ሃብት ነበሩ " ሲል አክሏል።
በአቶ ቡልቻ ደመቅሳ ህልፈተ ህይወት ሀዘኑን የገለጸው አዋሽ ባንክ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው፣ ለቤተሰቦቻቸው፣ እንዲሁም ለመላዉ የሀገራችን ህዝቦች መጽናናትን ተመኝቷል።

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች መልካም የልደት በዓል እንዲሆንላችሁ እንመኛለን።
" ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋል። " (ሉቃ. 2÷11)
መልካም የልደት በዓል !
Ayyaana Qillee Gaarii!
ርሑስ በዓል ልደት!
#TikvahEthiopiaFamily

#China #Tibet
ለሊቱን እና ጥዋት ላይ በዓለም በተለያዩ ሀገራት የተለያየ መጠን ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ ተመዝግቧል።
ከነዚህ ውስጥ እጅግ የከፋው እና የ53 ሰዎችን ህይወት የቀጠፈው የመሬት መንቀጥቀጥ በቻይና ፤ ቲቤት ግዛት ደርሷል።
የቻይና የመሬት መንቀጥቀጥ ኔትዎርክ ሴንተር በሬክተር ስኬል 6.8 የተመዘገበ ነው ብሏል።
የአሜሪካው ጂኦሎጂካል ሰርቬይ ግን የመሬት መንቀጥቀጡ በሬክተር ስኬል 7.1 የተመዘገበ ነው ሲል አመልክቷል።
በሬክተር ስኬል 6.8 ሆነ ከዛም በላይ የመሬት መንቀጥቀጥ እጅግ ጠንካራና አደገኛ ከፍተኛ የሆነ ውድመት ሊያደርስ የሚችል ነው።
በቲቤት 6 የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተቶች የተመዘገቡ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ ከፍተኛ 7.1 ነው።
በመሬት መንቀጥቀጡ ህንጻዎች ፣ መኖሪያ ቤቶች ተደርምሰዋል።
ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን የቻይና ሚዲያዎችን ዋቢ በማድረግ በትንሹ 53 ሰዎች እንደሞቱ ነገር ግን ከፍርስራሽ ስር ያሉ ሰዎች ሊኖሩ ይችላሉ በዚህም የሟቾች ቁጥር ሊጨምር ይችላል ብለዋል።
የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች የነፍስ አድን ስራ ላይ ተሰማርተዋል።
አደጋው ተራራማ በሆኑ የገጠራማ ክፍሎች የደረሰ ሲሆን ዋና ወደሚባሉ ከተሞች እንኳን አልተጠጋም።
የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረቱ በሰሜን ህንድ እና በኔፓል ዋና ከተማ ካታህማዱ ሌሎችም ቦታዎች በእጅጉ ተሰምቷል።
ባለስልጣናት ዜጎቻቸው እንዲረጋጉ እና ቀጣይ ለሚመጣው ሾክ ራሳቸውን እንዲያዘጋጁ አሳስበዋል።
ስፍራው በተደጋጋሚ ጊዜ የመሬት መንቀጥቀጥ የሚያስተናግድ ነው።
የመሬት መንቀጥቀጥ ቅፅበታዊ ፣ ለመገመት እና ለመተንበይ የሚያስቸግር የት ቦታ እንደሆነ እንጂ መቼ እንደሚፈጠር የማይታወቅ በመሆኑ ሁሌም ጥንቃቄ ማድረግ ንቁ ሆኖ መጠበቅ ይገባል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ከተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ያሰባሰበ ሲሆን ቪድዮዎቹና ፎቶዎቹን ከቲቤት እና ኔፓል የማህበራዊ ትስስር ገጾች ነው የወሰደው።
የመሬት መንቀጥቀጥ ሲከሰት ምን ማድረግ አለብን ? የሚወሰዱ የጥንቃቄ እርምጃዎችን ያንብቡ : https://t.iss.one/tikvahethiopia/93267?single

#ነዳጅ የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በነበረበት ይቀጥላል ተብሏል። የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ፤ የታህሳስ ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በህዳር ወር በነበረበት የመሽጫ ዋጋ እንዲቀጥል በመንግሥት መወሰኑን አሳውቋል። ሚኒስቴሩ " የነዳጅ ማደያዎች እና ኩባንያዎች ያልተገባ የነዳጅ ክምችት ከመያዝ እና የዋጋ ጭማሪ ከማድረግ ተቆጥበው ውሳኔውን ተግባራዊ በማድረግ ህብረተሰቡን…
#ነዳጅ
ቤንዚን በሊትር 101.47 ብር ሲገባ ናፍጣ በሊትር 98.98 ብር ሆኗል።
ዛሬ በነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ጭማሪ ተደርጓል።
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከዛሬ ታኅሣሥ 29 ቀን 2017 ዓ/ም ከምሽቱ 12 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ ተግባራዊ የሚሆን የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ መወሰኑን አሳውቋል።
በዚሁ መሰረት ፦
➡ አንድ ሊትር ቤንዚን 101.47 ብር
➡ አንድ ሊትር ናፍጣ 98.98 ብር
➡ አንድ ሊትር ኬሮሲን 98.98 ብር
➡ የአውሮፕላን ነዳጅ 109.56 ብር
➡ አንድ ሊትር ከባድ ጥቁር ናፍጣ 105.97 ብር
➡ አንድ ሊትር ቀላል ጥቁር ናፍጣ 108.30 ብር ሆኖ እንዲሸጥ ተወስኗል።
#ነዳጅ #ኢትዮጵያ