#አቢሲንያ_ባንክ
በረቀቀ ቴክኖሎጅ የተዘጋጀውን የሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያ
- በ5 የቋንቋ አማራጭ
- ከአቢሲንያ ወደ አቢሲንያ አካውንት ያለምንም ክፍያ እና ያለገደብ ገንዘብ ለማስተላለፍ
- ኪውአር ስካን አገልግሎት
ለማግኘት ዛሬውኑ ወደ አቅራቢያዎ ቅርንጫፍ በመሄድ አገልግሎቱን ያግኙ #Mobilebanking #Unlimited_Transfer #withinBoa #bankofabyssinia #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ

የሁሉም ምርጫ !
ሸሪዓውን መሠረት አድርገውና ሁሉንም የማህበረሰብ ክፍል አካተው፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ በተመሰከረለት የአይማል ኮር ባንኪንግ ሲስተም እየታገዙ ዳጐስ ያሉ ጥቅሞችን ለአስቀማጮች የሚያስገኙትን፤ የሴቶች (ዘህራህ)፣ የወጣቶች (ፊትያህ)፣ የባለውለታዎች (ሙስኒን)፣ የሃጅ እና ዑምራ፣ የዕድር (ጀሚአህ)፣ የዕቁብ (ሱንዱቅ) እና የጊዜ ገደብ ተቀማጭ ሙዷረባህ ትርፍ አጋሪ ሂሳቦችን በመክፈት፤ ከባንካችን ጋር ኢንቨስት አድርገው በተሻለ ትርፍና በከፍተኛ ጥቅም የወደፊት ህልምዎን እውን ያድርጉ!
አቢሲንያ አሚን
ዕሴትዎን ያከበረ!
#AbyssiniaAmeen #IFB #bankofabyssinia #አቢሲኒያአሚን #Banking #BanksinEthiopia #AddisAbaba #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ

#Ethiopia
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 44ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ።
ካሳለፋቸው ውሳኔዎች አንዱ የውጭ ዜጎች የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለቤት ወይም ባለይዞታ የሚሆኑበትን አግባብ ለመደንገግ የወጣው ረቂቅ አዋጅ ነው።
ምክር ቤቱ " ይህ የዜጎችን የመሬት ይዞታ የማግኘትና የመጠቀም መብት በማያጣብብ መልኩ ለውጭ ዜጎች ህጋዊ አሠራር መዘርጋቱ ፦
- የውጭ ካፒታል በሀገራችን ሥራ ላይ እንዲያውሉ ለማበረታታት፣
- የቤት ልማት እና ተደራሽነትን ይበልጥ ለማነቃቃት፣
- የመኖሪያ ቤት ፍላጎት እና አቅርቦት ሚዛን ለማስጠበቅ
- ለዜጎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር ትልቅ ጠቀሜታ ይኖረዋል " ብሏል።
በረቂቅ አዋጁ ላይ ከተወያየ በኋላ ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡
ምክር ቤቱ ሌላ ከወሳናቸው ጉዳዮች አንዱ ለአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ ንግድ ቀጣና ስምምነት የዕቃዎች ቀረጥ ምጣኔ ቅነሳን ለማስፈፀም በቀረበ ረቂቅ ደንብ ላይ ነው።
" ስምምነቱ በአባል ሀገራት መካከል ንግድ እንዲስፋፋ፣ የገበያ ትስስሩ እንዲጠናከር፣ የእሴት ሠንሰለቱ እንዲጎለብት እና የኢኮኖሚ ትራንስፎርሜሽን ማበረታታት የሚያስችል ነው " ብሏል።
" በአባል ሀገሮች መካከል የሚደረጉ ግብይቶች በታሪፍ ምክንያት ሳይደናቀፉ የእቃዎች ፍሰት የተሳለጠ እንዲሆን ከአባል አገራት በሚመጡ እቃዎች ላይ የጉምሩክ ታሪፍ ምጣኔ ለይቶ መወሰን አስፈላጊ መሆኑን በመወያዬት ደንቡ በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ተፈፃሚ እንዲሆን " ሲል በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡
(ተጫማሪ ምክር ቤቱ የወሰናቸውን ውሳኔዎች ከላይ ይመልከቱ)
@tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ተደረገ። የ2017 ትምህርት ዘመን ኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ / የ12ኛ ክፍል ፈተና የሚሰጥበት መርሃ ግብር ይፋ ተደርጓል። የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ይፋ ባደረገው መርሃ ግብር ፈተናው ከሰኔ 23/2017 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ሐምሌ 8/2017 ዓ/ም የሚሰጥ ይሆናል። በወረቀት የሚፈተኑ የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች ሰኔ 21…
የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ሆኗል።
የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተና መቼ ይሰጣል ?
➡️ በወረቀት ፈተናቸውን የሚወስዱ ተፈታኞች ፦ ሰኔ 23 ፣ ሰኔ 24 እና ሰኔ 25/2017 ዓ/ም
➡️ በበየነ መረብ (ኦንላይን) /ፈተናቸውን የሚወስዱ የ1ኛ ዙር ተፈታኞች ፦ ሰኔ 23 ፣ ሰኔ 24 እና ሰኔ 25/2017 ዓ/ም
➡️ በበየነ መረብ (ኦንላይን) /ፈተናቸውን የሚወስዱ የ2ኛ ዙር ተፈታኞች ፦ ሰኔ 26 ፣ ሰኔ 27 እና ሰኔ 30/2017 ዓ/ም
የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተና መቼ ይሰጣል ?
➡️ በወረቀት ፈተናቸውን የሚወስዱ ተፈታኞች ፦ ሐምሌ 1 ፣ ሐምሌ 2 እና ሐምሌ 3/2017 ዓ/ም
➡️ በበየነ መረብ (ኦንላይን) /ፈተናቸውን የሚወስዱ የ1ኛ ዙር ተፈታኞች ፦ ሐምሌ 1 ፣ ሐምሌ 2 እና ሐምሌ 3/2017 ዓ/ም
➡️ በበየነ መረብ (ኦንላይን) /ፈተናቸውን የሚወስዱ የ2ኛ ዙር ተፈታኞች ፦ ሐምሌ 4 ፣ ሐምሌ 7 እና ሐምሌ 8/2017 ዓ/ም
#Ethiopia #NationalExam #Grade12
#TikvahEthiopiaFamily

የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ሆኗል። የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተና መቼ ይሰጣል ? ➡️ በወረቀት ፈተናቸውን የሚወስዱ ተፈታኞች ፦ ሰኔ 23 ፣ ሰኔ 24 እና ሰኔ 25/2017 ዓ/ም ➡️ በበየነ መረብ (ኦንላይን) /ፈተናቸውን የሚወስዱ የ1ኛ ዙር ተፈታኞች ፦ ሰኔ 23 ፣ ሰኔ 24 እና ሰኔ 25/2017 ዓ/ም ➡️ በበየነ መረብ (ኦንላይን) /ፈተናቸውን የሚወስዱ የ2ኛ ዙር…
#NationalExam
በዘንድሮ የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና 608 ሺህ ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚወስዱ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።
ከሰኔ 23 እስከ ሐምሌ 8 ቀን 2017 ዓ/ም የሚሰጠው አገር አቀፍ ፈተና ላይ 608 ሺህ ተማሪዎች ይቀመጣሉ ተብሎ ነው የሚጠበቀው።
ፈተናው በወረቀት እና በበየነ መረብ ይሰጣል።
ፈተናውን በወረቀት የሚወስዱ ተማሪዎች እንደ ቀደሙት ዓመታት ሁሉ ሙሉ በሙሉ ወደ ዩኒቨርሲቲዎች ገብተው ይወስዳሉ።
ፈተናውን በበይነ መረብ የሚወስዱት ደግሞ ፦
- በዩኒቨርሲቲዎች፣
- በመንግስት እና በግል ትምህርት ቤቶች፣
- በጤና እና መምህራን ማሰልጠኛ ኮሌጆች
- በቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ውስጥ ባሉ ኮምፒዩተሮች ይፈተናሉ። ተማሪዎቹ ግቢ ማደር ሳይጠበቅባቸው ከቤታቸው እየተመላለሱ ነው ፈተናውን የሚወስዱት።
በበይነ መረብ የሚሰጠው ፈተና በሁለት ዙር ሲሆን ይህም የሆነው በበይነ መረብ የመፈተን አቅምን እና የተፈታኝ ተማሪዎችን ቁጥር ለመጨመር እንዲሁም ያለውን የመሰረተ ልማት አቅም ለማሳደግ እንደሆነ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ለኤፍ ኤም ሲ በሰጠው ቃል አስረድቷል።
#Ethiopia #NationalExam #Grade12 #ኤፍኤምሲ

Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#አቢሲንያ_ባንክ
በጉርሻ 1.6 ሚሊዮን ብዙ ነው? ግን እውነት ነው! ክፍያዎችን በአቢሲንያ ባንክ በመቀበል ብቻ ቢዝነስ የሚደጉም ጉርሻ!!
#Banking #BanksinEthiopia #AddisAbaba #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ

#ፋይዳ #National_ID
" እያንዳንዱ ሰው መታወቅ አለበት " - ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
ባለፉት 2 እና 3 ዓመታት በተሰራው ስራ ከ15 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ለፋይዳ / ብሔራዊ መታወቂያ መመዝገባቸውን ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።
ይህን የገለጹት " ቴክ-ቶክ " ከተሰኘ የቴሌቪዥን ፕሮግራም ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ነው።
ባለፉት 2 እና 3 ዓመታት በተሰራው ስራ አሁን ላይ ከ15 ሚሊዮን በላይ ዜጎች የፋይዳ / ብሔራዊ መታወቂያ እንዳወጡ የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) እስከ መጪው መስከረም ወር ድረስ 20 ሚሊዮን ይጠጋል ተብሎ እንደሚታሰብ ተናግረዋል።
በሚቀጥለው ዓመት ፋይዳ መታወቂያ ያላቸው ዜጎችን ቁጥር ወደ 60 እና 70 ሚሊዮን ለማድረስ እንደሚታሰብ ጠቁመዋል።
" በቀጣይ 2 እና 3 ዓመታት ውስጥ እያንዳንዱ ሰው የሚታወቅ ከሆነ እንደ ሀገር ለብዙ ነገር ለፕላኒንግ፣ ለገቢ፣ ለንግድ ፣ ለመተማመን ያግዛል " ብለዋል።
" ፋይዳ ፋይዳው የጎላ ነው " ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፋይዳ ፦
- የሚፈጸሙ ህገወጥ ንግዶችን ለመከላከል
- መጭበርበሮችን ለመቀነስ
- ያልተስተካከለውን የንግድ ስርዓት ለማሻሻል
- ለኢኮኖሚው
- መተማመንን ለመገንባት
- ለአጠቃላይ የንግድ ስርዓቱ
- ለሰላም እና ደህንነቱ
- ወጥቶ ለመግባቱ
- አገልግሎት ለማግኘቱ ... በአጠቃላይ በሁሉም መስክ ያለው ሚና ከፍተኛ እንደሆነ አስረድተዋል።
ፋይዳ ብዙ ሴክተሮችን የሚነካ መሆኑን በመጠቆም " እያንዳንዱ ዜጋ ሊኖረው የሚግባ ነገር ነው " ሲሉ ገልጸዋል።
እያንዳንዱ ሰው መታወቅ እንዳለበትም አስገንዘበዋል።
" ፋይዳን የተገበሩ ሀገራት ተጠቅመዋል የተዘናጉ ሀገራት ደግሞ የደረሰባቸው ጉዳት አለ " ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) " አፍሪካ ውስጥ የሞከሩ ሀገራት አሉ በትክክል ግን በእኛ በዲጂታል አይዲ መልክ አይደለም የሞከሩት እኛ የጀመርነውን ዲጂታል አይዲ ለመማር ብዙ የአፍሪካ ሀገራት በገንዘብ ውልም ጭምር ጥያቄ እያቀረቡ ነው ያሉት ፤ እኛም የሚሳካልን ለሌሎችም ትምህርት የሚሆን ስራ እንደምንሰራ ተስፋ አደርጋለሁ ጥቅሙም ከፍተኛ ነው " ብለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA
#Digital_ID #National_ID #Ethiopia

የውጭ ባንኮች መቼ ይገባሉ ?
የውጭ ባንኮች ከሚቀጥለው ዓመት አጋማሽ ላይ ወደ ኢትዮጵያ በመግባት ኢንዱስትሪውን እንደሚቀላቀሉ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ አቶ ማሞ ምሕረቱ አመልክተዋል።
የውጭ ባንኮችን ሥራ ለማስጀመር በተያዘው ዕቅድ መሠረት የመጀመሪያዎቹ የውጭ አገር ባንኮች በ2025 መጨረሻ ወይም በመጪው በጀት ዓመት አጋማሽ ወደ ሥራ እንደሚገቡና ለዚህም አስፈላጊ የሆኑ ዝግጅቶች መደረጋቸውን አቶ ማሞ ገልጸዋል።
በቀጣዩ ዓመት የውጭ ባንኮች ወደ ኢትዮጵያ መግባት እውን ቢሆንም የትኞቹ የውጭ ባንኮች ሊገቡ እንደሚችሉ ግን የብሔራዊ ባንክ ገዢ አልገለጹም።
የውጭ ባንኮች እንዳይገቡ እንቅፋት ይሆናቸዋል ተብለው ይጠቀሱ የነበሩ አንዳንድ መመሪያዎች የውጭ ባንኮች ይገባሉ ተብሎ ከተጠቀሰው ጊዜ ቀደም ብሎ የሚስተካከሉ መሆኑ ተነግሯል።
የውጭ ባንኮች ቢግቡ አይቀበሏቸውም ተብለው ሲጠቀሱ ከነበሩ መመሪያዎች መካከል በአሁኑ ወቅት ባንኮች በአስገዳጅነት እንዲገዙ የሚገደዱት ቦንዶችና የ18 በመቶው የብድር ገደብ ጣሪያ ይገኙባቸዋል፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ እነዚህ መመሪያዎች እንደሚሻሩና ለዚህም ቀነ ገደብ መቀመጡን ይፋ እንዳደረጉ ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል።
ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የሪፖርተር ጋዜጣ ነው።

#Ethiopia #France
የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ለማድረግ አውሮፓ ይገኛሉ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ ፈረንሳይ የገቡ ሲሆን ከፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር ተገናኝተው መወያየታቸው ተነግሯል።
ውይይታቸው የሁለቱን ሀገራት ግንኙነቶች እና ትብብሮች በሚያጠናክሩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ እንደሆነና ፍሬያማ እንደነበር ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) ከውይይቱ በኃላ ገልጸዋል።
በፈረንሳይ ለተደረገላቸው አቀባበል እና በታኅሳስ ወር በአዲስ አበባ ከነበረው ውይይት ቀጥሎ ዛሬ ስለተካሄደው ውይይት አመስግነዋል።
" ትብብራችን በብዙ ጠቃሚ ዘርፎች የቀጠለ ሲሆን የንግድ ትስስሮቻችንን የበለጠ ማሳደግ ከቅድሚያ የትኩረት ማዕከሎቻችን አንዱ ነው " ሲሉም አክለዋል።

ኢትዮጵያ የቢትኮይን ኩባንያዎችን ትኩረት ለምን ሳበች ? በአዲስ አበባ የሚገኘው የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፓርክ፣ ዋነኛው የቢትኮይን ኩባንያዎች መዳረሻ ሆኗል፡፡ ካለፈው አንድ አመት ጀምሮ 10 ኩባንያዎች በዚሁ ፓርክ ውስጥ መሰረተልማት ገንብተው እየሰሩ መሆናቸውን፣ የአይቲ ፓርኩ ሐላፊ አቶ ሔኖክ አሕመድ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል፡፡ በሌሎች የሀገሪቱ አካባቢዎችም በዚሁ ስራ ላይ የተሰማሩ አለምአቀፍ…
#Crypto #Ethiopia
ኢትዮጵያ እያደገ የመጣውን የክሪፕቶ ካምፓኒዎች የሀይል ፍላጎት ማሟላት ትችላለች ?
" አሁን ያሉትን የክሪፕቶ ካምፓኒዎች የሀይል ፍላጎት ለማሟላት ጥረት እናደርጋለን፡፡ አዳዲስ ካምፓኒዎች መቀበል ግን አቁመናል " - አቶ ሞገስ መኮነን
➡️ " ሁሌም ቅድሚያ የምንሰጠው ለሀገር ውስጥ ፍላጎት ነው፡፡ በሀገር ውስጥ የሀይል እጥረት ሲያጋጥም፣ ለክሪፕቶ ከረንሲ ካምፓኒዎች የሚቀርበው ሀይል ሙሉ በሙሉ ሊቋረጥ እንደሚችል አስገዳጅ ስምምነት አለ ! "
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል፣ ከዚህ በኋላ አዳዲስ የክሪፕቶከረንሲ ካምፓኒዎችን ላለመቀበል መወሰኑን አስታወቀ፡፡
የተቋሙ የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሞገስ መኮነን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃለመጠይቅ፣ " የክሪፕቶ ካምፓኒዎች የኤሌክትሪክ ሀይል ፍላጎት ከፍተኛ በመሆኑ፣ ያሉትን ካምፓኒዎች ፍላጎት ማሟላት እንጂ፣ ከእንግዲህ አዳዲስ ካምፓኒዎችን አንቀበልም " ብለዋል፡፡
በተቋሙ የሀይል አቅርቦት ለሀገር ውስጥ ፍላጎት ቅድሚያ እንደሚሰጥም ገልፀዋል፡፡
አቶ ሞገስ መኮነን በዝርዝር ምን አሉ ?
" በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያ የክሪፕቶ ከረንሲ ካምፓኒዎች እንቅስቃሴ እየተስፋፋ ነው፡፡ ይህ ኢንቨስትመንት ሁለት አመት ሆኖታል፡፡
ኢትዮጵያ ላይ ትኩረት ያደረጉበት ምክንያት፣ እኛ ጋር የኤሌክትሪክ ሀይል ዋጋ ከሌሎች ጎረቤት ሀገራት ጋራ ሲነፃፀር ዝቅተኛ በመሆኑ ነው፡፡ በዛ ላይ ከታዳሽ የሀይል ምንጭ የሚገኝ መሆኑ ነው፡፡
አሁን በአጠቃላይ 36 የክሪፕቶከረንሲ ካምፓኒዎች አሉ፡፡ ስራ የጀመሩና ስራ ለመጀመር በሒደት ላይ የሚገኙ፡፡ እነዚህ ካምፓኒዎች ከፍተኛ የሀይል መጠን እንደሚፈልጉ ይታወቃል፡፡ ነገር ግን እኛ ቅድሚያ የምንሰጠው ለሀገር ውስጥ ፍላጎት ማሟላት ነው፡፡
የህዝቡና የአምራቹ ዘርፍ የሀይል ፍላጎት ሳይሟላ፣ ለክሪፕቶ ካምፓኒዎችም ይሁን ለውጭ ሀገራት የሚቀርብ ሀይል የለም፡፡ ሁሌም ቢሆን ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ የሀገር ውስጥ ፍላጎት መሟላት ነው፡፡ የሀገር ውስጥ አምራች ኢንዱስትሪውም ቅድሚያ ይሰጠዋል፡፡
የማኑፋክቸሪንግ ዘርፉ ከፍተኛ የሰው ሀይል የሚቀጥር ስለሆነ በሀይል አቅርቦት በኩል ቅድሚያ ያገኛል፡፡ በዚህም በማኑፋክቸሪን ዘርፉ ያሉ ባለሀብቶች ደስተኞች እንደሆኑ እናውቃለን፡፡ ለሀገር ውስጥ ፍላጎት ቅድሚያ ስለሚሰጥ ነው እንደዛ የሆነው፡፡
የሀገር ውስጥ ፍላጎት በሚጨምርበት ጊዜ ለጎረቤት ሀገራት የሚላከው ሀይል ይቋረጣል፡፡ ለክሪፕቶ ካምፓኒዎች የሚቀርበውም ሀይል እንደዚሁ ሊቋረጥ ይችላል፡፡
አሁን ላይ የሀይል እጥረት ችግር የለብንም እንጂ እንዲህ አይነት ችግር ቢያጋጥመን፣ ለነሱ የምናቀርበውን ሀይል እስከማቋረጥ የሚያደርስ ውል አለን፡፡ የውጭ ምንዛሪ ፍላጎታችንንና የሀገር ውስጥ የሀይል ፍላጎትን በዚህ መልኩ ነው የምናጣጥመው፡፡ ከክሪፕቶ ካምፓኒዎች ዶላር ለማግኘት ተብሎ የሀገር ውስጥ የሀይል ፍላጎት አይጎዳም፡፡
የክሪፕቶ ካምፓኒዎቹ የሀይል ፍላጎት ከ 100 እስከ 400 ሜጋዋት ይደርሳል፡፡ እኛ የምንሰጣቸው ግን ከ20 እስከ 30 ሜጋዋት ብቻ ነው፡፡ አሁን ያሉት የክሪፕቶ ካምፓኒዎች እየቆዩ ያሉት የሚፈልጉትን የሀይል መጠን ስለሚያገኙ ሳይሆን ወደፊት እናገኛለን ብለው ተስፋ ስለሚያደርጉ ነው፡፡ እያደገ ከሚሔደው የሀይል ልማት መጠቀም ይፈልጋሉ፡፡
በርግጥ አሁን እየተሰሩ ያሉት ስራዎች የማመንጨት አቅማችንን እያሳደጉት ነው ያሉት፡፡ ሀይል የማመንጨት አቅማችን ሲያድግ የክሪፕቶ ካምፓኒዎችንም ፍላጎት ማሟላት እንችል ይሆናል፡፡ አሁን ባለው ኹኔታ ግን ከሀገር ውስጥ ፍጆታ የተረፈንን ነው የምናቀርብላቸው፡፡
አሁን ላይ የማመንጨት አቅማችን ወደ 6ሺህ ሜጋዋት ቢደርስም መሰረተልማቶቻችን ተቀብለው ማሰራጨት የሚችሉት 4ሺህ ሜጋዋት ያህሉን ብቻ ነው፡፡ አሁን ባለን መሰረተልማት ማቅረብ የምንችለው ይህን ነው፡፡ የ2 ሺህ ሜጋዋት ትርፍ አለን፡፡ ይህንን ትርፍ የማመንጨት አቅም ለተጠቃሚው ለማድረስ ግን በየአመቱ የመሰረተ ልማት ማስፋፊያ ስራዎች ይከናወናሉ፡፡ ህብረተሰቡ ጋር ካልደረሰ የእኛ ማመንጨት ብቻውን ትርጉም የለውም፡፡
የሀገር ውስጥ ፍላጎትን ከማሟላት ባሻገር፣ የገጠር ኤሌክትሪክ ማስፋፋት ስራም እንደቀጠለ ነው፡፡ ይህን የምናደርገው ከዋናው ብሔራዊ የሀይል ቋት/ግሪድ ጋር በማገናኘትና ከመስመር ውጪ ባሉ አካባቢዎች በሚሰሩ ስራዎች አማካኝነት ነው፡፡ ህብረተሰቡ ተጠጋግቶ በሚኖርባቸው አካባቢዎች ከዋናው መስመር ሀይል እንዲያገኙ እናደርጋለን፡፡
በገጠሩ አካባቢና በሀገሪቱ ዳርቻ የሚገኙ አካባቢዎች ደግሞ አኗኗኗቸው የተራራቀ ስለሆነ ከግሪድ ውጪ ካሉ አማራጮች ለምሳሌ ከፀሀይ ሀይል እና ከሌሎችም ምንጮች የሀይል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ይደረጋል፡፡
የኤሌክትሪክ ሀይል አቅርቦትን ለማስፋፋት የፋይናንስ እጥረት አለብን፡፡ 85 በመቶ የሚሆነው የኤሌክትሪክ መሰረተልማት ከውጪ ነው የምናስገባው፡፡ ይህን ለማድረግ የሚያስፈልገን የገንዘብ አቅም ከአለምአቀፍ አበዳሪዎችና ለጋሾች ነው የምናገኘው፡፡ የፋይናንስ እጥረቱን ከተለያዩ ምንጮች ነው የምናሟላው፡፡ ነገር ግን ያለብንን የፋይናንስ እጥረት ለመቅረፍ ሲባል ለክሪፕቶ ካምፓኒዎች ቅድሚያ ሰጥተን የሀገር ውስጥ ፍላጎትን አንጎዳም፡፡
በሌላ በኩል፣ ተቋማችን ለክሪፕቶ ካምፓኒዎች ሀይል በማቅረብ የውጭ ምንዛሪ ማግኘቱ መጀመሩ የውጭ ምንዛሪ ምንጩን እንዲያሰፋ ረድቶታል፡፡ በሌላ አባባል ከክሪፕቶ ካምፓኒዎች የሚገኘው የውጭ ምንዛሪ መሰረተልማትን ለማስፋፋት አስተዋፅኦ እያደረገ ነው፡፡ ስለዚህ ለክሪፕቶ ካምፓኒዎች ከምናቀርበው ሀይል የሚገኘው ገቢ የኤሌክትሪክ ሀይልን ወደ ህብረተሰቡ ለማድረስ እያገዘን ነው፡፡ የውጭ ምንዛሪ የሚፈልጉ እቃዎች እንገዛበታለን ከዚህ በፊት ያሉብንን አዳዎች እንከፍልበታለን፡፡
ከዚህ በኋላ ግን የክሪፕቶ ካምፓኒዎችን ተቀብለን አናስተናግድም፡፡ አሁን ያሉትን ካምፓኒዎች የሀይል ፍላጎታቸውን ለማሟላት ጥረት እናደርጋለን፡፡ "