ወደ ኖርዌይ ለልምድ ልውውጥ የሄዱ የሁለት የፖለቲካ ፓርቲ አባላት ወደ ሀገር ሳይመለሱ ቀሩ።
የኢዜማ እና የቦሮ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ አባላት ለልምድ ልውውጥ ከሃገር በወጡበት አለመመለሳቸው ተሰምቷል።
የቦሮ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ቦሮ) የሴቶች ጉዳይ ሃላፊ ወ/ሮ አበበች ደቻሳ እና የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) የሴቶች ጉዳይ ተጠሪ የነበሩት ወ/ሮ ቅድስት ግርማ በመስከረም አጋማሽ ለልምድ ልውውጥ ወደ #ኖርዌይ ባቀኑበት ወቅት አለመመለሳቸው ተነግሯል።
ሁለቱ አባላት ወደ ኖርዌይ ያቀኑትና ያልተመለሱት በኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የልምምድ ልውውጥ እንዲያደርጉ በተላኩበት ወቅት መሆኑን የም/ ቤቱ ጸሃፊ አቶ ደስታ ዲንቃ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
አባላቱ በጋራ ምክር ቤቱ የሴቶች ክንፍ ሰብሳቢነት እና ስራ አስፈጻሚነት ሲያገለግሉ ነበር።
አቶ ደስታ ፥ " የሴቶችን የፖለቲካ ተሳትፎ ለማጠናከር በሃገር ደረጃ ከፓርላማ አባላት ጋር እና የሲቪክ ተቋማት ጋር እየተገናኙ ብዙ ስራዎችን ሲሰሩ ነበር " ብለዋል።
ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቃላቸውን የሰጡ የኢዜማ አባል ፤ አባሏ በስራ ገበታቸው ላይ አለመኖራቸው በማስረዳት " ለምን እንዳልተመለሱ የምናውቀው ነገር የለም " ብሏል።
የቦሮ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ በበኩሉ ከልጆቿና ከባለቤቷ ጋር በፖለቲካ ምክንያት ለእስር ተዳርገው እንደነበር የገለጸ ሲሆን ለመቅረቷም ምክንያት ይህ ሳይሆን እንዳልቀረ ገልጿል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" የአእላፋት ዝማሬ/The Melody of Myriads " በአዲስ አበባ እና በድሬዳዋ በተመሳሳይ ሰዓት እንደሚካሄድ ተገለጸ።
ይህንን የገለጸው አዘጋጁ የኢትዮጵያ ጃንደረባ ትውልድ / ኢጃት ማኅበር ነው።
የኢየሱስ ክርስቶስን በዓለ ልደት ምክንያት በማድረግ የሚዘጋጀው ይህ የዝማሬ መርሐግብር በበዓሉ ዋዜማ ታኅሣሥ 28/ 2017 ዓ/ም ይካሄዳል።
በአዲስ አበባ ከተማ የዝማሬ መርሐግብሩ አምና በተካሄደበት በቦሌ ደብረ ሳሌም መድኃኔዓለም ካቴድራል (ቦሌ መድኃኔዓለም) እንደሚካሄድ ነው አዘጋጆቹ ያሳወቁት።
" የጌታችንን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን በዓለ ልደት በዝማሬ እናክብር " ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።
ሁሉም የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች የልደት በዓልን ዋዜማ በቤተክርስቲያን ተገኝተው በዝማሬ እንዲያከብሩ ተብሏል።
ከዚህ ጋር በተያያዘ አዘጋጆቹ በአዲስ አበባ እና ድሬዳዋ ሀገረ ስብከት ካዘጋጁት " የአእላፋት ዝማሬ / The Melody of Myriads " መርሐግብር ውጭ ሌላ እንዳላዘጋጁ እንዲሁም ለዚህ መርሐግብር ተብሎ የሚደረግ ምዝገባም እንደሌለና ምዕመኑ ከሀሰተኛ መረጃዎች ራሱን እንዲጠብቅ ጥሪ አቅርበዋል።
ባለፈው ዓመት በአዲስ አበባ በቦሌ ደብረ ሳሌም መድኃኔዓለም ካቴድራል በተካሄደው " የአእላፋት ዝማሬ/The Melody of Myriads " እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ኦርቶዶክሳዊ ወጣት የልደት ዋዜማን በዝማሬና በፀሎት ተቀብሎ ነበር።
መርሐግብሩ ላይ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖትና ብፁአን አባቶች ተገኝተው እንደነበር አይዘነጋም።
ከመርሐግብሩ ቀደም ብሎ ምዕመናን በተለይም ወጣቶች የተዘጋጁ መዝሙሮችን አጥንተው እንዲመጡ መዝሙሮቹ በኦንላይን ሲሰራጩ ነበር።
ዘንድሮም በተመሳሳይ ለመርሃግብሩ የተዘጋጁ መዝሙሮች በማኅበሩ የማህበራዊ ሚዲያዎች (Janderbaw Media Youtube) ተጭነው ምዕመኑ ጋር እንዲዳረሱ እየተደረገ ነው።

የመሬት መንቀጥቀጡ የቦታ ለውጥ አድርጓል ? " በአንድ አካባቢ ተደጋግሞ እየተከሰተ ነው ያለው እንጂ የቀረበ ነገር የለም " - ፕ/ር አታላይ አየለ በትላንትናው ዕለት በቀን፣ በምሽትና በለሊቱ ክፍለ ጊዜ ተደጋጋሚ የሆነ የመሬት መንቀጥቀጦች መከሰታቸው ዓለም አቀፍ ጁኦሎጂካል ተቋማት ዘግበዋል። ትላንት ምሽት 2:10 የተከሰተው እና ንዝረቱ እስከ አዲስ አበባ ከተሰማው በሬክተር ስኬል 5.0 ሆኖ ከተመዘገበው…
#Earthquake
ዛሬ ምሽቱን ንዝረቱ አዲስ አበባ ድረስ በደንብ የተሰማ ተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ አዋሽ ፈንታሌ አካባቢ ተከስቷል።
በተለይ አዲስ አበባ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ያሉ ነዋሪዎች ጠንከር ብሎ እንደተሰማቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ጠቁመዋል።
አያት፣ ጣፎ፣ አራብሳ ፣ ጀሞ ... ሌሎችም አካባቢዎች ምዝረቱ ተደጋጋሚ ጊዜ ተሰምቷል።
የአዋሽ ቲክቫህ አባላት ደግሞ የመሬት መንቀጥቀጡ በጣም እያስፈራቸው እንደመጣና ድግግሞሹ እየበዛ መሆኑን ጠቁመዋል።
" ባለፉት 48 ሰዓታት የነበረው የመሬት መንቀጥቀጥ ብዙ ነበር። ድግግሞሹ ከመጨመሩ በኃላ መጠኑን ከመጨመሩ ጋር በተያያዘ አስፈሪ ሆኗል " ብለዋል።

#Earthquake ዛሬ ምሽቱን ንዝረቱ አዲስ አበባ ድረስ በደንብ የተሰማ ተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ አዋሽ ፈንታሌ አካባቢ ተከስቷል። በተለይ አዲስ አበባ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ያሉ ነዋሪዎች ጠንከር ብሎ እንደተሰማቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ጠቁመዋል። አያት፣ ጣፎ፣ አራብሳ ፣ ጀሞ ... ሌሎችም አካባቢዎች ምዝረቱ ተደጋጋሚ ጊዜ ተሰምቷል። የአዋሽ ቲክቫህ አባላት ደግሞ የመሬት መንቀጥቀጡ በጣም እያስፈራቸው…
#Earthquake
በድጋሚ የአዋሽና አካባቢው ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት " አስፈሪ ነበር " ያሉት የመሬት መንቀጥቀጥ ከደቂቃዎች በፊት መከሰቱን ጠቁመዋል።
" የመሬት መንቀጥቀጥ ድግግሞሹ እየባሰበት ነው " ያሉ ሲሆን " አላህ ይዘንልን ምናደርገው ጠፋን " ሲሉ ገልጸዋል።
" ነገሩ አዲስ አበባ እና ሌሎችም ቦታዎች ካልተሰማ ትኩረት እያገኘ አይደለም። ድግግሞሹ እኮ ብዙ ነው በሚዲያ ከሚገለጸውም በላይ ነው። ቤታቸውን ጥለው የወጡም አሉ ፤ ብቻ በጣም ነው የፈራነው " ሲሉም ተናግረዋል።
አሁን ድጋሚ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረቱ አዲስ አበባ ድረስ ነበር።
በተለይም በአዲስ አበባ የጋራ መኖሪያ ቤቶች የሚኖሩ ነዋሪዎች ጠንከር ብሎ ተሰምቷቸዋል።
በአርባሳ ፣ ጣፎ ፣ አባዶ ፣ አያት ፣ ጀሞ ፣ ጋርመንት ... ሌሎችም ቦታዎች ንዝረቱ በደንብ ይሰማ እንደነበር የቲክቫህ አባላት ጠቁመዋል።
ከአዲስ አበባ ውጭ በሌሎች ከተሞች ንዝረቱ በደንብ እየተሰማ ነው።

#Earthquake በድጋሚ የአዋሽና አካባቢው ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት " አስፈሪ ነበር " ያሉት የመሬት መንቀጥቀጥ ከደቂቃዎች በፊት መከሰቱን ጠቁመዋል። " የመሬት መንቀጥቀጥ ድግግሞሹ እየባሰበት ነው " ያሉ ሲሆን " አላህ ይዘንልን ምናደርገው ጠፋን " ሲሉ ገልጸዋል። " ነገሩ አዲስ አበባ እና ሌሎችም ቦታዎች ካልተሰማ ትኩረት እያገኘ አይደለም። ድግግሞሹ እኮ ብዙ ነው በሚዲያ ከሚገለጸውም…
#ለጥንቃቄ🚨
የመሬት መንቀጥቀጥ ሲከሰት ምን ማድረግ አለብን ?
➡️ ከቤት ውጭ ከሆኑ ፦ ከዛፎች ፣ ከሕንፃዎች ፣ ከኤሌትሪክ ምሶሶዎች እና ሌሎች ወድቀው ጉዳት ሊያደርሱ ከሚችሉ ነገሮች መራቅ እና ገላጣ ሜዳ አካባቢ መቆየት።
➡️ በቤት ውስጥ ከሆኑ ፦ በበር መቃኖች ፣ ኮርነሮች እና ኮሪደሮች ተጠግቶ ማሳለፍ። ከእሳት ምድጃዎች፣ ከተሰቀሉ ፍሬሞች እና የግድግዳ ጌጦች፣ ከመጽሐፍ መደርደሪያዎች እንዲሁም ከመስኮት አካባቢ መራቅ። የጋዝ ምድጃዎችን በተቻለ ፍጥነት ማጥፋት ካልሆነም ከአካባቢው መራቅ።
➡️ በትልልቅ ሕንጻዎች ውስጥ ከሆኑ ፦ ከሕንጻዎቹ ለመውጣት አለመሞከር ፣ አሳንሰር (ሊፍት) በፍፁም አለመጠቀም። ከደረጃዎች አካባቢ መራቅ።
➡️ መኪና እያሽከረከሩ ከሆኑ ፦ የኤሌትሪክ መተላለፊያ ምሶሶዎችን፣ ዛፎችና ሽቦዎች አካባቢ አለመቆም፣ የኤሌትሪክ መስመር ምሶሶዎች እና ሽቦዎች ተሽርካሪው ላይ ከወደቁ ከመኪናው ለመውጣት አለመሞከር፣ በተቻለ ፍጥነት ገላጣ ወደሆነ አካባቢ መኪናን ማቆም።
#Ethiopia
#የአአእሳትናአደጋስራአመራርኮሚሽን

ለሊት 7:13 ላይ በሬክተር ስኬል 4.8 የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ እንደተከሰተ የጀርመኑ ጂኦ ሳይንስ እና የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ መረጃ ያመላክታል።
የመሬት መንቀጥቀጡ የተመዘገበው ከአቦምሳ 39 ኪ/ሜ ርቀት ላይ ነው።
ይህ ባለፉት ሰዓታት ከተመዘገበው ከፍተኛው ሲሆን በሬክተር ስኬል 4.0 ፣ 4.5 ፣ 4.6 ፣ 4.7 ... የሆኑ የመሬት መንቀጥቀጦች ቀን፣ ምሽት እና ለሊቱን በተከታታይ ተመዝግበዋል።
የነዚህ የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረቶች አዲስ አበባ እና የተለያዩ የክልል ከተሞች ጠንክረው ተሰምተዋል።
በተለይ በህጻዎች ላይ ያሉ ሰዎች ጠንከር ያለ ንዝረት ተሰምቷቸዋል።
በሌላ በኩል ፤ በመሬት መንቀጥቀጥ ምክንያት በከሰም ቀበና ቤቶች እና ንብረት ላይ ወድመት መድረሱን ነዋሪዎች ጥቆማቸውን በፎቶ አስደግፈው ልከዋል።

#BankOfAbysinia
ዘመናዊ ፖስ ማሽኖቻችን ባሉባቸው የግብይት ቦታዎች ሰልፍ አይታሰብም!
#POSMachine #contactless #DigitalPayments #CashlessTransactions
#BanksinEthiopia #AddisAbaba #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ