TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
61.9K photos
1.58K videos
216 files
4.29K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Architecture

በፍልስጤም ሀገር ለሚገነባ ትምህርት ቤት በተዘጋጀ ዓለም አቀፍ የአርክቴክቸራል ዲዛይን ውድድር ላይ ኢትዮጵያውያኑ ፦
➡️ አርክቴትክት ዳንኤል ዋጁ
➡️ አርክቴርክት ቢንያም በውቀቱ
➡️ አርክቴክት ፍሬዘር አብርሃ ከ231 ተወዳዳሪ አርክቴክቶች መካከል " የጣልያንን ተወዳዳሪዎች " በመከተል የ2ኛ ደረጃ በመያዝ አጠናቀዋል።

አርክቴክቶቹ " Mobile school as an emergency Response in Palestine " በተሰኘ ርዕስ በተዘጋጀው በዚህ ውድድር ከአፍሪካ ብቸኛ የደረጃ ተወዳዳሪ መሆን እንደቻሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ከዚህ በፊት ለተከታታይ 5 የተለያዩ ዓለም አቀፍ ውድድሮችን ለ3 አመት ያክል የሞከሩ ሲሆን በነሱም የተለያዩ ውጤቶችን አስመዝበው እንደነበር ከ3 አመት በኋሏ ግን በአምላክ እርዳታ ለዚህ ከፍተኛ ስኬት መብቃታቸውን ገልጸዋል።

ወጣቶቹ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላኩት መልዕክት " በሃገራችን ኢትዮጵያም ብሎም በአፍሪካ ብዙ እምቅ ችሎታ ያለቸው ወጣቶች አንዳሉም በጥቂቱ ማሳየት በመቻላችን እጅግ ደስተኞች ነን " ብለዋል።

በውድድሩ ላይ በአርክቴክቸር ሙያ የታወቁ ሎሬቶች እና ባለሙያዎች በዳኝነት ተሳትፈዋል።

ከዚህ ዓለማቀፍ ውድድር 2ኛ በመሆን በማጠናቀቃቸው የ2000 ዩሮ እና የእውቅና ሰርተፍኬት ተሸላሚ በመሆን የሃገራቸውን ስም አስጠርተዋል።

(ያሸነፉበትን ስራ ከላይ ይመልከቱ)

@tikvahethiopia
ቪድዮ፦ በአስደንጋጩ አውሮፕላን አደጋ እስካሁን 151 ሰዎች ሞቱ።

በደቡብ ኮሪያ ውስጥ በማረፍ ላይ የነበረ አንድ አውሮፕላን ባጋጠመው አደጋ እስካሁን ድረስ 151 ሰዎች መሞታቸው ተሰምቷል።

" ጄጁ " የተባለው አየር መንገድ ንብረት የሆነው አውሮፕላን ከባንግኮክ መጥቶ በደቡብ ኮሪያው ሙዋን አየር ማረፊያ ሲያርፍ ነበር መንገዱን ስቶ የአውሮፕላኑ የፊተኛው ክፍል በእሣት ሲያያዝ የታየው።

ምንም እንኳ እስካሁን ድረስ የአደጋው መንስዔ ባይታወቅም የእሣት አደጋ አገልግሎት " ምናልባት ከወፍ ተጋጭቶ አሊያም ባለው ከባድ የአየር ፀባይ ምክንያት ሊሆን ይችላል " ብሏል።

አውሮፕላኑ 181 ሰዎች አሳፍሮ ነው ከታይላንድ የተነሳው።

አብዛኛዎቹ ደቡብ ኮሪያዊያን መሆናቸውን መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

እስካሁን አንድ ተሳፋሪና አንድ የበረራ ሠራተኛ በሕይወት ሲተርፉ ሌሎች ከአደጋው የተረፉ ሰዎችን የማዳን ሥራው መቀጠሉን ቢቢሲ ኒውስ ፣ ቲአርቲ ወርልድና ሮይተርስ ዘግበዋል።

ቪድዮ ፦ ከማህበራዊ ሚዲያ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Earthquake : ዛሬ ቅዳሜ ምሽት ጨምሮ ቀን ላይ ተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ እንደነበር የአፋር ቲክቫህ ኢትዮጵያ አባላት ገልጸዋል። የመሬት መንቀጥቀጥ ድግግሞሹ እየጨመረ ነው ብለዋል። አንድ የቤተሰባችን አባል፥ " አላህ መፍትሄውን ይስጠን ፤ ያረጋጋው እንጂ እጅግ በጣም ያስፈራል ፤ የዓለሙ ፈጣሪ አላህ መጨረሻችንን ያሳምረው " ሲል ገልጿል። መሬት መንቀጥቀጡ እየፈጠረ ያለው ንዝረት በተለያዩ…
" ከ30 በላይ የመኖሪያ ቤቶች ጉዳት ደርሶባቸዋል " - አቶ አብዱ ዓሊ

በአፋር ክልል ጋቢ ረሱ ዞን በተደጋጋሚ እየተከሰተ ባለው የመሬት መንቀጥቀጥ ከ30 በላይ የመኖሪያ ቤቶች ጉዳት ደርሶባቸው ነዋሪዎች ሌላ አማራጭ እንዲፈልጉ ማስገደዱ ተነግሯል።

በአዋሽ 7 ከተማ አሥተዳደር፣ በአዋሽ ፈንታሌ እና አሚባራ ወረዳዎች በሚገኙ የተወሰኑ ቀበሌዎች የመሬት መንቀጥቀጥ በተደጋጋሚ እየተከሰተ መሆኑን የዞኑ ዋና አሥተዳዳሪ አብዱ ዓሊ ገልጸዋል፡፡

በዚህም እስከ አሁን በአዋሽ ፈንታሌ ወረዳ ሳቡሬ እና ዶኾ ቀበሌዎች ከ30 በላይ የመኖሪያ ቤቶች ላይ ጉዳት መድረሱን አረጋግጠዋል፡፡

ጉዳት በደረሰባቸውና ሌሎችም ሥጋት ባለባቸው መኖሪያ ቤቶች ያሉ ወገኖችን ከአካባቢያቸው ሳይርቁ ቀለል ባለ ባህላዊ ቤት እንዲኖሩ እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡

በሰው ላይ የተመዘገበ ጉዳት ባይኖርም በሰብል የተሸፈኑ ማሳዎች እና የመኪና መንገዶች ላይ የከፋም ባይሆን የመሰነጣጠቅ አደጋ መድረሱን ገልጸዋል።

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የኤፍ ኤም ሲ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Video
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በደቡብ ኮሪያ ፣ ሙዋን በደረሰው አሰቃቂ የአውሮፕላን አደጋ አውሮፕላኑ ውስጥ ከነበሩት 181 ሰዎች 177 ሰዎች መሞታቸው መረጋገጡን " ሮይተርስ " ዘግቧል።

የቀሩት ሁለት ሰዎች በህይወት ይገኛሉ የሚለው ተስፋ እየተሟጠጠ ነው ተብሏል።

ንብረትነቱ የ " ጄጁ አየር መንገድ " በሆነው Boeing 737-800 የአውሮፕላን አደጋ በህይወት የተረፉት ሁለት ሰዎች ሲሆኑ እነሱም የበረራ ሰራተኞች ናቸው። የደረሰባቸው ጉዳት ለህይወታቸው የሚያሰጋ አይደለም ተብሏል።

ምንም እንኳ የአደጋው መንስኤ እየተመረመረ ቢሆንም ባለስልጣናት ግን  " ከወፍ ተጋጭቶ ነው " ብለዋል። ከአደጋው ቀደም ብሎ የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች አውሮፕላኑን የወፎች ጥቃት ስጋት እንዳለ አሳውቀው ነበር ተብሏል።

ከአደጋው በህይወት ከተረፉ የበረራ አባላት መካከል እንደተሰማው ከአደጋው ቀደም ብሎ የወፎች ጥቃት እንደነበር መጠቆሙን " ዘጋርዲያን " ዘግቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Earthquake አዋሽ አካባቢ በተደጋጋሚ እየተከሰተ ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ መቀጠሉን የአካባቢው ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እየገለጹ ናቸው።

ትላንት ምሽት እንዲሁም ዛሬ ጥዋት አካባቢ ጠንከር ያለ የመሬት መንቀጥቀጥ እንደነበር ጠቁመዋል።

እንደ ' አሜሪካ የጂኦሎጂካል ሰርቬይ ድረገጽ ' መረጃ  ዛሬ እሁድ ከአዋሽ 33 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሬክተር ስኬል 4.8 የተለካ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቶ ነበር።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በደቡብ ኮሪያ ፣ ሙዋን በደረሰው አሰቃቂ የአውሮፕላን አደጋ አውሮፕላኑ ውስጥ ከነበሩት 181 ሰዎች 177 ሰዎች መሞታቸው መረጋገጡን " ሮይተርስ " ዘግቧል። የቀሩት ሁለት ሰዎች በህይወት ይገኛሉ የሚለው ተስፋ እየተሟጠጠ ነው ተብሏል። ንብረትነቱ የ " ጄጁ አየር መንገድ " በሆነው Boeing 737-800 የአውሮፕላን አደጋ በህይወት የተረፉት ሁለት ሰዎች ሲሆኑ እነሱም የበረራ ሰራተኞች ናቸው። የደረሰባቸው…
#ካናዳ

በካናዳ፣ ሀሊፋክስ ኤርፖርት ሲያርፍ የነበረ አንድ የመንገደኞች አውሮፕላን በእሳት መያያዙ ተሰምቷል።

73 መንገደኞችን እና የበረራ ሰራተኞችን የያዘው በፒኤኤል አየር መንገድ የሚሰራው የኤር ካናዳ በረራ ቁጥር 2259 አውሮፕላን በሚያስደነግጥ አኳኋን ሊቆም ችሏል።

በህይወት ላይ የደረሰ ጉዳት እንደሌለ ተነግሯል።

ከሴንት ጆንስ ተነስቶ ሀሊፋክስ ኤርፖርት ሲያርፍ የነበረው አውሮፕላን የቴክኒክ ችግር እንዳጋጠመው ነው የተነገረው።

አውሮፕላኑ ሲያርፍ ከማረፊያው መንገድ ወጥቶ በእሳት ተያይዟል።

ለሲቢሲ ኒውስ ቃላቸውን የሰጡ አንድ መንገደኛ ፥ " አውሮፕላኑ በሚያርፍበት ወቅት አንዱ ጎማ በትክክል አልተዘረጋም ነበር ፤ በጣም የሚያስፈራ ድምጽም ነበር " ብለዋል።

አንዱ የአውሮፕላን ክፍል በእሳት መጋየቱን ነው የጠቆሙት።

የክስተቱ ምክንያቱ እየተመረመረ ነው ተብሏል።

@tikvahethiopia
#Tigray

በወርቅ ማዕድን ቁፋሮ እና ዝውውር ዙሪያ መረጃዎች በማሰባሰብ ላይ የነበሩ የትግራይ ቴሌቪዥን ጋዜጠኞች በታጣቂዎች መታገታቸውን ተቋሙ አስታወቀ።

የታገቱት ጋዜጠኞች ብዛት 3 እንደሆነ የገለፀው የሚድያ ተቋሙ ሞባይላቸው ከአገልግሎት ውጪ መደረጉን ጨምሮ ገልጿል። 

ትግራይ ቴሌቪዥን " በትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን ከህገ-ወጥ የወርቅ ማዕድን ፍለጋ እና ዝውውር ጋር ተያይዞ የሚነሳው ጉዳይ ለማጥራት የተሰማሩ ጋዜጠኞች ናቸው በታጣቂዎች የታገቱት " ሲል አሳውቋል።

ሦስት አባላት የያዘ የጋዜጠኞች ቡድን ዛሬ ታህሳስ 20/ 2017 ዓ.ም ከረፋዱ 3:00 ጀምሮ በአስገዳ ወረዳ ' ሜይሊ ' ተብሎ ከሚጠራ ልዩ ቦታ በምትገኘው መንደር ነው የታገቱት ተብሏል።

ጋዜጠኞቹ በአከባቢው ስላለው ህገ-ወጥ የወርቅ ማዕድን ቁፋሮና ዝውውር በማስመልከት በአካል ቦታው ድረስ በመሄድ የአከባቢውን ነዋሪዎች ፣ አርሶ አደሮችና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች ሲያነጋግሩ እንደሰነበቱ የገለፀው የትግራይ ቴሌቪዥን " የጋዜጠኞች ቡድኑ በስራ እያለ በታጣቂዎች ሊታገት እና ሊታሰር ችሏል " ሲል አመልክቷል።

የታገቱት የጋዜጠኞች ቡድን ከረፋዱ 4:00 ጀምሮ ሞባይላቸው ከአገልግሎት ውጪ በመደረጉ ምክንያት ያሉበት ሁኔታ እና ድህንነታቸው ማረጋገጥ እንዳልተቻለ አመልክቷል።

ጋዜጠኞቹን የሚመለከት መረጃ ለመጠይቅ በአከባቢው ለሚገኙ የመንግስት አመራሮች ተደጋጋሚ የስልክ ሙከራ ቢያደርግም እንዳልተሳከለት የትግራይ ቴሌቪዥን አሳውቋል።

እገታውን ስለፈጸሙ ታጣቂዎች ማንነት በዝርዝር የተባለ ነገር የለም።

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የትግራይ ቴሌቪዥን ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray በወርቅ ማዕድን ቁፋሮ እና ዝውውር ዙሪያ መረጃዎች በማሰባሰብ ላይ የነበሩ የትግራይ ቴሌቪዥን ጋዜጠኞች በታጣቂዎች መታገታቸውን ተቋሙ አስታወቀ። የታገቱት ጋዜጠኞች ብዛት 3 እንደሆነ የገለፀው የሚድያ ተቋሙ ሞባይላቸው ከአገልግሎት ውጪ መደረጉን ጨምሮ ገልጿል።  ትግራይ ቴሌቪዥን " በትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን ከህገ-ወጥ የወርቅ ማዕድን ፍለጋ እና ዝውውር ጋር ተያይዞ የሚነሳው ጉዳይ ለማጥራት…
#Update

ማንነታቸው ባልታወቁ  ታጣቃዎች የታገቱት ሦስት የትግራይ ቴሌቪዥን ጋዜጠኞች በትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን አስገደ ወረዳ ሜይሊ ተብሎ በሚጠራ ቦታ በሚገኝ እስር ቤት እንደሚገኙ የትግራይ ቴሌቪዥን ማረጋገጡን አስታውቋል።

ጋዜጠኞቹ ከህገ-ወጥ የወርቅ ማዕድን ፍለጋ እና ዝውውር ጋር ተያይዞ ስለሚነሳው ጉዳይ ለማጥራት በተሰማሩበት ነው በታጣቂዎች መታገታቸው የተበገረው።

አሁን ላይ ጋዜጠኞቹ እስር ቤት እንዳሉ ተነግሯል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Somalia #Djibouti ከቀናት በፊት ኤርትራ አስመራ የነበሩት የሶማሊያው ፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሙሀመድ ዛሬ ጅቡቲ ገብተዋል። ወደ ጅቡቲ ያቀኑት በፕሬዜዳንት ኢስማኤል ኡማር ጌሌህ ግብዣ እንደሆነ ተነግሯል። ሁለቱ መሪዎች በሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ እንደሚወያዩ ተገልጿል። @tikvahethiopia
#Update : ጅቡቲ የሚገኙት የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞትዎስ (ዶ/ር) ከጅቡቲው ፕሬዚዳንት እስማኤል ኦመር ጊሌ ጋር ተገናኝተው ውይይት አድርገዋል።

የውይይቱ ዓላማ የትውውቅ እና በሁለቱ ወንድማማች ሀገሮች መካከል ያለውን የቆየ ወዳጅነት ለማጠናከር ነው የተባለ ሲሆን በውይይታቸው የሁለትዮሽና አህጉራዊ ጉዳዮችን አንስተው መምክራቸውን በጅቡቲ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ የተገኘው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ማንነታቸው ባልታወቁ  ታጣቃዎች የታገቱት ሦስት የትግራይ ቴሌቪዥን ጋዜጠኞች በትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን አስገደ ወረዳ ሜይሊ ተብሎ በሚጠራ ቦታ በሚገኝ እስር ቤት እንደሚገኙ የትግራይ ቴሌቪዥን ማረጋገጡን አስታውቋል። ጋዜጠኞቹ ከህገ-ወጥ የወርቅ ማዕድን ፍለጋ እና ዝውውር ጋር ተያይዞ ስለሚነሳው ጉዳይ ለማጥራት በተሰማሩበት ነው በታጣቂዎች መታገታቸው የተበገረው። አሁን ላይ ጋዜጠኞቹ…
#Update

" ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቃዎች ታግተዋል " የተባሉት  3 የትግራይ ቴሌቪዥን ጋዜጠኞች ሜይሊ ተብሎ በሚጠራ ቦታ በሚገኝ እስር ቤት እንደሚገኙ የትግራይ ቴሌቪዥን ከደቂቃዎች በፊት ማረጋገጡ ይታወሳል።

አሁን ከስፍራው በተገኘው መረጃ ሦስቱ ጋዜጠኞች ከእስር ተለቀዋል።

የጋዜጠኞቹ መፈታት በማስመልከት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ የደረሰው መረጃ እንደሚያመለክተው ፥ ጋዜጠኞቹ መረጃ በማሰባሰብ ስራ እያሉ በአከባቢው በሚገኙ ፓሊስ እና ሚሊሻዎች ነው የተያዙት።

ጋዜጠኞቹ በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ ከወረዳው የፀጥታ እና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት መካከል በተደረሰ መግባባት ከሰዓታት እስር ሊለቀቁ ችለዋል። 

ጋዜጠኞቹ በአከባቢው ያለውን ህገ-ወጥ የወርቅ ማዕድን ቁፋሮና ዝውውር የሚመለከት የምርመራ ዘገባ በመስራት ላይ እንደነበሩ ለወረዳው የፀጥታ እና አስተዳደር አካላት የተናገሩ ሲሆን የጋዜጠኞች እስር እና እንግልት በክልሉ ካለው የፓለቲካ ቀውስ ትስስር አለው ተብሏል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
  
@tikvahethiopia 
" የሰላም ችግር ከሁሉም በፊት ቀድሞ መፍትሔ ማግኘት አለበት " - ፕ/ር መረራ ጉዲና

ባለፈው ሳምንት የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ ፓርቲ (ኦፌኮ) አዲሱን ዋና ፅ/ቤቱን በአዲስ አበባ አስመርቋል።

የቀድሞ ሜክሲኮ የሚገኘው ዋና ፅ/ቤቱ በኮሪደር ልማት ምክንያት በመፍረሱ አዲሱን ቢሮ ቀበና አደባባይ አከባቢ ከፍቶ ስራ አስጀምሯል።

በዚህ ወቅት የኦፌኮ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ንግግር ያደረጉ ሲሆን " አሁንም ሀገራችን ትልቅ ችግር ውስጥ ናት " ብለዋል።

የሰላም ችግር ከሁሉም በፊት ቀድሞ መፍትሔ ማግኘት እንዳለበትም ገልጸዋል። ለዚህ ደግሞ ወደጦርነት የሚመሩትን የፖለቲካ ችግሮች በውይይት መፍታት እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል።

" የኦሮሞ ህዝብ ፍላጎትም ሆነ የሌሎች ብሔር ብሔረሰቦች ፍላጎት ዘላቂ ሰላም ፣ ጠንካራ የዲሞክራሲ ስርዓት እና በኢኮኖሚ የበለፀገች ኢትዮጵያን ማየት ነው " ያሉ ሲሆን፤ " ይሄን ከግብ ለማድረስ ኦፌኮ'ን ጨምሮ ሌሎች የተቃዋሚ ፖርቲ ህብረቶች ትግላቸውን ማጠናከር አለባቸው " ሲሉ ተናግረዋል።

በወቅቱ ተገኝተው የነበሩ የተለያዩ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች " ህዝቡ ላይ እየደረሰ ያላውን ችግር ለመፍታት ህብረታችንን በደንብ በማጠናከር እና ህዝቡን ከጎን በማሰለፍ አንድላይ መቀጠል ይኖርብናል " ብለዋል።

ኦፌኮ አዲሱን ዋና ፅ/ቤቱን ስራ ባስጀመረበት ወቅት " በአገሪቱ ውስጥ ባለው ወቅታዊ ሁኔታ እና በቀጣዩ ትግል አቅጣጫ ላይ ዝርዝር ውይይት ተደርጓል " ያለ ሲሆን " በዚህ መሠረት በጦርነቱ ጉዳት፣ በኢኮኖሚ ውድቀት ምክንያት የማህበራዊ መቃወስና ወደ መፍረስ እየተኬደ ካለው መንገድ ኢትዮጵያን ለመታደግ ትኩረት ይሰጣል " ብሏል።

#OFC #AddisAbaba

@tikvahethiopia