TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#እንድታውቁት

የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተናን በድጋሚ የሚፈተኑ ተፈታኞች በበየነ መረብ (ኦንላይን) መመዝገብ እንደሚችሉ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

ተፈታኞች በራሳቸው የሚመዘገቡበት አድራሻ https://register.eaes.et/Online እንደሆነ ተገልጿል።

ይህ የበይነ መረብ (አንላይን) ምዝገባ መተግበሪያ ራስ አገዝ (self services ) ሲሆን ተመዝጋቢዎች የሚፈልጉትን ድጋፍ በመጠየቅ ከማዕከል ማግኘት ይችላሉ ተብሏል።

(እንዴት መመዝገብ እንደሚቻል ከላይ ይመልከቱ)

(የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት)

@tikvahethiopia
#ethiotelecom #telebirr

🏑 ሁላችንም የምንሳተፍበት የዘንድሮ የገና ጨዋታ የሚደረግበት ሜዳ ቴሌብር ሱፐርአፕ ነው!! 😁

💁‍♂️ መተግበሪያው https://onelink.to/uecbbr ከሌለዎት ያውርዱ፤ በሞቀው የገና ጨዋታ ተሳታፊ ይሁኑ!

🤩 ከ15 ሚሊየኑ የዕድልዎን ለመውሰድ ታኅሣሥ 23 ይጠብቁን!!

#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
" ዝቅተኛ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ዩኒቨርሲቲዎች እኩል በጀት የሚመደብበት አሰራር አይኖርም " - ትምህርት ሚኒስቴር

ከዚህ በኃላ ዝቅተኛ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ዩኒቨርሲቲዎች እኩል በጀት የሚመደብበት አሰራር እንደሚቀር የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ተናግረዋል።

ዩኒቨርሲቲዎች የሚመደብላቸው በጀት ባስመዘገቡት ውጤት ልክ እንደሚሆን ሚኒስትሩ ይፋ አድርገዋል።

ይህን ይፋ ያደረጉት ከሰሞኑን በትምህርት ዘርፉ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን በተቀናጀ መልኩ ማሻሻል የሚያስችል ስምምነት ትምህርት ሚኒስቴር እና 47 የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የቦርድ ሰብሳቢዎችና የዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንቶች በተፈራረሙበት ወቅት ነው።

ሚኒስትሩ ፤ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትን በመሰረታዊነት ለመቀየር የትምህርት ጥራትን ማስጠበቅ ወሳኝ እንደሆነ አስገንዝበዋል።

ዩኒቨርሲቲዎች የተጣለባቸውን ሃላፊነት በብቃትና በጥራት እንዲፈፅሙ በተለይ ሙስናን ማጥፋት ግዴታ መሆኑን ፕ/ር ብርሃኑ አሳስበዋል።

" ሙስና የትውልድ ጸር በመሆኑ ለትውልዱ አርዓያ የሚሆን ዩኒቨርሲቲ መፍጠር ይገባል " ብለዋል። #ኤፍኤምሲ

@tikvahethiopia
#ethiotelecom

ኢትዮ ቴሌኮም በ67 ከተሞች የ4ጂ ሞባይል ኔትወርክ አገልግሎት ማስጀመሩን አሳውቋል።

የከተሞቹ ዝርዝር ከላይ በምስል ተያይዟል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update 🔴“ 14 ተማሪዎች ታስረዋል ”  - ድርጅቱ 🔵 “ ስማቸውን ካረጋገጡልኝ እኔ ነኝ የማስፈታቸው። ግን ስምና ዲፓርትመንት አምጡ ስንል ‘አናመጣም’ ነው የሚሉት ” - ኀብረቱ 🟢 “ የታሰሩት መፈታታቸውን እንጂ ያልተፈቱ እንዳሉ መረጃው የለኝም ” - መቐለ ዩኒቨርሲቲ ከአዲሱ የዩኒቨርሲቲዎች የምግብ ሜኑ ትግበራ ጋር ተያይዞ ተማሪዎች ቅሬታ እያነሱ መሆናቸው የሚታወቅ ሲሆን፣ የመቐለ ዩኒቨርሲቲ…
#Update

" የምግብ ጥራቱ ወርዷል ፤ መጠኑ ቀንሷል 22 ብር በነበረ ጊዜ ይሻላል ፤ የብሩ መጨመር ምንም ነገር ካላስተካከለ ትርፉ ከፍተኛ ኮስት ሸሪንግ / የወጪ መጋራት እዳ ነው " - ተማሪዎች

ከሰሞኑን በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ወጥነት ባለው መንገድ መተግበር የጀመረው የምግብ ሜኑ በተማሪዎች ዘንድ ቅሬታን የፈጠረ ሆኗል።

ምግቡ መጠኑ ቀንሷል፤ ጥራቱም 22 ብር የነበረ ጊዜ ይሻላል የሚል ቅሬታ ነው ተማሪዎች ዘንድ ያለው።

ከዚህ ባለፈ የብሩ መጨመር በተማሪዎች ኮስት ሼሪንግ / ወጪ መጋራት ላይ ከፍተኛ ጭማሪ አድርጎ ተማሪውን ባለዕዳ ከማድረግ ባለፈ አንድም የጥራት መሻሻል አይታይም ፤ ጭራሽ መጠንም ቀንሷል ብለዋል።

በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አስተዳደርና ልማት መሪ ሥራ አስፈፃሚ የሆኑት ዶ/ር ሰሎሞን አብርሃ  ስለ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የምግብ በጀት (100 ብር) ምን አሉ ?

" የምግብ በጀቱ 100 ብር ሆነ ማለት የግድ የተለየ ለውጥ ይመጣል ማለት አይደለም። የምግብ አይነቱም ሙሉ ለሙሉ አስደናቂ በሆነ መልኩ ይቀየራል ማለት አይደለም፣ ሊቀየርም አይችልም።

ድሮውንም ተማሪዎች በተመደበላቸው 22 ብር ብቻ ሲመገቡ አልቆዩም።

ከፌዴራል መንግሥት የሚመደበው 22 ብር አነስተኛ መሆኑ ስለሚታወቅ ዩኒቨርሲቲዎች በራሳቸው አካሄድ ሲያስተካክሉ ቆይተዋል።

ዩኒቨርስቲዎች ከሚመደብላቸው የተለያየ በጀት እያዟዟሩ በቀን ከ80 እስከ 150 ብር በማውጣት ተማሪዎችን ሲመግቡ ነበር።

የተማሪዎች የምግብ ሜኑ ከመሻሻሉ በፊት አንድ እንጀራን እስከ 24 ብር ድረስ የሚገዛ ዩኒቨርስቲ ነበር። ድሮ ይመደብ የነበረው በጀት አንድ እንጀራ እንኳን በቅጡ የማይገዛ ነበር።

በመሆኑም ይህ አካሄድ የዩኒቨርሲቲዎችን እንቅስቃሴ ስላስተጓጎለና የአሰራር ስርዓታቸው ላይም ችግር ስለፈጠረ፣ የምግብ ሜኑ ሲዘጋጅ ጥናት ተጠንቶ ሀገር አቀፍ የተማሪ ህብረት ተወካዮች ጭምር በአካል በተገኙበት የዩኒቨርሲቲዎች ምግብ ማሻሻያ ተደርጓል።

ተማሪዎች አሁን ካለው ሁኔታ አንፃር ማድረግ ያለባቸው የሚመደብላቸው በጀት በአግባቡ ለእነርሱ መድረሱን እና በቀን የመቶ ብሩ በጀት ተሰልቶ በሳምንት 700 ብር ወጪ መደረጉን፣ እንዲሁም ያንን ወጪ ታሳቢ ያደረገ ሜኑ መቅረብና አለመቅረቡን ማረጋገጥ ነው።

ከዚህ ጋር በተያያዘ የተማሪዎች ህብረት አደረጃጀትም ኃላፊነት በመውሰድ በአግባቡ መከታተል አለበት " ብለዋል።


ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህ የሰሎሞን አብርሃ (ዶ/ር) ንግግር የተወሰደው ለአሐዱ መሆኑን ያሳውቃል።

@tikvahethiopia
" በአማራ ክልል አጀንዳ ልየታ እንደማንሳተፍ ለኮሚሽኑ በአክብሮት እንገልጻለን " - መኢአድ እና እናት ፓርቲ

መላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) እና እናት ፓርቲ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአማራ ክልል ባቀደው አጀንዳ የማሰባሰብ ሥራ በአጀንዳ ልየታ የሚሳተፉ የፓርቲ ተወካዮችን እንዲያሳውቁ በደብዳቤ ቢጠይቃቸውም ከወዲሁ እራሳቸውን ማግለላቸውን የሚገልጽ የጋራ መግለጫ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ልከዋል።

ፓርቲዎቹ ራሳቸውን ከምክክሩ እንዳገለሉ በገለጹበት በዚሁ መግለጫ ፤ የጦርነት ችግሮች ካልተፈቱ በምክክሩ ለመሳተፍ እንደሚቸገሩ ሲያሳስቡ መቆየታቸውን አስታውሰዋል ፤ የአማራ ክልል ህዝብ በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች በአየርና በምድር በከባድ መሳሪያ እንዲሁም በድሮን ጭምር የሚደርስበት ጥቃት አለመቆሙን ጠቅሰዋል።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቢያበቃም አማራ ክልል በኮማንድ ፖስት እየተዳደረና ጦርነቱ እየተስፋፋ ያለበት፣ በርካታ ዜጎች በማንነታቸው እና በፖለቲካ አመላካከታቸው የታሰሩበት፣ የተሽከርካሪ እንቅስቃሴ አልፎ አልፎ ሙሉ በሙሉ የሚገደብበት ፣ በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ ለማድረግ ፍላጎት የራቀበት ሁኔታ መኖሩን ገልጸዋል።

" በዚህ መልክ በተጠቀሰው የአጀንዳ ልየታ ለመሳተፍ መሞከር እውነተኛ ምክክር አድርጎ ለሀገር የሚበጅ መፍትሄ ለማምጣት ሳይሆን የተጠና ተውኔት አካል ከመሆንና ራስን ከማታለል የዘለለ የሚያመጣው መፍትሄ እንደሌለው በውል እንረዳለን " ብለዋል።

በህዝቡ የሚፈደርሰው ጉዳት አለመቆሙን ጠቅሰው፣ " በክልሉ የአጀንዳ ልየታ ሥራ ማሰብ ከፈረሱ ጋሪው የቀደመበትና ኮሚሽኑ እውነተኛ ምክክር የማድረግ እንቅስቃሴ ሳይሆን የስርዓት ዓላማ ማስፈጸሚያ መሣሪያ ወደ መሆን ገባ ወይ ? እንድንል አስገድዶናል " ብለዋል።

ፓርቲዎቹ፣ የሀገራዊ ምክክሩ አካሄድ ከዐዋጁ አጸዳደቅ ጀምሮ ከታዩበት የተለያዩ የጎሉ ችግሮች ላይ ተጠደምደው ከመቆዘም ይልቅ ምክክሩ ለአገር የሚያመጣውን ውጤት በመገንዘብ " ችግሮች እየተቀረፉ ይሄዳሉ " በሚል እሳቤ በመደገፍ እንደቆዩ አስታውሰዋል።

በምክክሩ ሰላም እንዲመጣ ከተፈለገ፣ የሰሜኑ ጦርነት በፕሪቶሪያው ስምምነት እንደተቋጨ ሁሉ በአማራና ኦሮሚያ ክልሎች ጦርነቶች ተቋጭተው ወደ ምክክር መኬድ እንዳለበት፣ ይህ ካልሆነ የሀገሪቱ እጣ ፈንታ ሀገራዊ ምክክሩ ሳይሆን የጦርነቶቹ ሂደት ሊወስን እንደሚችል ምክረ ሀሳብ ሲያቀርቡ መቆየታቸውን ነው የገለጹት።

በመሆኑም፣ " ኮሚሽኑ በሰው ቁስል እንጨት ከመስደድ " ይልቅ ከዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ እና ከመንግስት ጋር ያለውን መልካም ግንኙነት ተጠቅሞና ጫና አድርጎ በገለልተኛ አካላት አሸማጋይነት እውነተኛ ሰላምን ሊያዋልድ የሚችል ድርድር እንዲደረግ አሳስበዋል።

(የትብብር ፓርቲዎቹ ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል)


@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ያለማቋረጥ እየመዘገብን ነው እስካሁን 4.9 ነው የተመዘገበው አሁንም ያለው ነገር ስናየው የሚቆም አይመስልም " - ፕ/ር አታላይ አየለ በስምጥ ሸለቆ ውስጥ የሚገኙ የሃገሪቱ አካባቢዎች ላይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተደጋጋሚ እየተሰማ ያለው ከዝቅተኛ መጠን እስከ መካከለኛ መጠን ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ በመሬት ውስጥ ያለው የማግማ እንቅስቃሴ ፈጣን (Active) በመሆኑ ምክንያት የተከሰተ እንደሆነ ሲነገር…
" ዛሬ የተመዘገበው የመሬት መንቀጥቀጥ በሬክተር ስኬል 5 ነው ፤ ካለፈው አንጻር የዛሬው ጠንካራ ነው " -  አታላይ አየለ (ፕ/ር)

ዛሬ አመሻሽ ላይ በሬክተር ስኬል 5 የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተ።

አመሻሽ 12 ሠዓት ከ26 ላይ በፈንታሌ አካባቢ በሬክተር ስኬል 5 የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አስታውቋል።

በዩኒቨርሲቲው የጂኦ ፊዚክስ ሕዋ ሣይንስ እና አስትሮኖሚ ተቋም የሴስሞሎጂ ትምህርት ክፍል ኃላፊ፣ የመሬት መንቀጥቀጥ ሣይንስ መምህርና ተመራማሪ አታላይ አየለ (ፕ/ር) ምን አሉ ?

" የመሬት መንቀጥቀጡ በተደጋጋሚ እየተስተዋለ ነው።

ባሳለፍነው ቅዳሜ ዕለትም በዚሁ አካባቢ በሬክተር ስኬል 4 ነጥብ 3 የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ ተመዝግቦ ነበር።

ካለፈው አንጻር የዛሬው ጠንከር ያለ ነው " ብለዋል። (ለኤፍ ኤም ሲ)

ከሰሞኑን በተደጋጋሚ ንዝረቱ አዲስ አበባ ድረስ የሚሰማ የመሬት መንቀጥቀጥ እየተከሰተ ሲሆን በሬክተር ስኬል የሚመዘገበው መጠንም ጨምሮ ታይቷል።

@tikvahethiopia
#አክሱም

🧕" እኛ የምንፈልገው ፍትህ ነው። ሂጃባችንን አድርገን ነው መማር የምንፈልገው። ያለ ሂጃብ ሸሪዓም አይፈቅድም አስቸኳይ እና ዘላቂ መፍትሄ ይሰጠን " - ተማሪዎች

➡️ " የአክሱም ሙስሊም ሴት ተማሪዎች በአጠቃላይ ሁሉም የሉም ከትምህርት ገበታ ላይ ወጥተዋል " - የክልሉ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት

👉 " ማንም ተማሪ በትምህርት ቤት ሃይማኖትን የሚያንጸባርቅ ነገር ማድረግ የለበትም " - የአክሱም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት

በትግራይ ፣ አክሱም ከተማ ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ላለፉት 2 ሳምንታት የራስ መሸፈኛ ሂጃብ ለብሰው ወደ ትምህርት ቤት መግባት እንደተከለከሉና በዚህም ከትምህርት ገበታ መውጣታቸውን የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት አሳውቋል።

በዚህ ዓመት ከሂጃብ መልበስ ጋር በተያያዘ በአክሱም በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ውዝግቡ የጀመረው ጥቅምት ወር ነው።

ተቋሙ ለክልል ትምህርት ቢሮ አሳውቆ አውንታዊ ምላሽ ቢሰጠውም በተግባር የተቀየረ ነገር ግን የለም።

የምክር ቤቱ ፀሀፊ ሓጂ መሓመድ ካሕሳይ ምን አሉ ?

" ፀጉራቸውን ሸፍነው ትምህር ቤት እንዲሄዱ ማየት ያልተፈቀደበት መታየት የለበትም ፀጉሯ የአንድ ሴት ይሄ ሃይማኖታዊ ግዴታ ነው።

ሃይማኖት ውስጥ ፖለቲካ አይገባም፣ ፖለቲካ በሃይማኖት አይገባም እየተባለ በአንቀጽ ተቀምጦ እያለ አሁን ፖለቲካ በሃይማኖት እየገባ ነው።

ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ከትምህርት ቤት ዩኒፎርም ጋር የሚመሳሰል የፀጉር መሸፈኛ ሂጃብ መጠቀም እንደሚችሉ በ2000 ዓ/ም የወጣ ሀገር አቀፍ መመሪያ አለ።

ስለዚህ ዝም ብለን የምናየው ነገር አይሆንም።

በአሁኑ ጊዜ በአራት ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ወጥተዋል።

ዋናው ደግሞ 3 ወር ሲማሩ የነበሩ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ለብሔራዊ ፈተና የኦንላይ ምዝገባ የሚደረግበት ወቅት ነው በዚህ ሳምንት ያልቃል የአክሱም ሙስሊም ተማሪዎች እስካሁን አልተመዘገቡም።

የአክሱም ሙስሊም ሴት ተማሪዎች በአጠቃላይ ሁሉም የሉም ትምህርት ገበታ ላይ ወጥተዋል፤ አልገቡም እስካሁን።

ችግሩ እንዲፈታ ከክልሉ ትምህርት ቢሮ እና ከአክሱም ከተማ አስተዳደር ትምህርይ ፅ/ቤት ጋር ውይይት እየተደረገ ነው " ብለዋል።


ተማሪዎች ምን ይላሉ ?

" በጦርነት ምክንያት ለ2 ዓመታት ከሌሎች  ተማሪዎች ወደኃላ ቀርተናል አሁን ደግሞ በሂጃብ ምክንያት ፈተና ሊያመልጠን ነው።

ፎርሙ እያመለጠን ነው። ሌሎች ተማሪዎች በሂጀብ ፎርም እንደሞሉ ነው የምናውቀው። እኛ የምንፈልገው ፍትህ ነው። ሂጃባችንን አድርገን ነው መማር የምንፈልገው።

ያለ ሂጃብ ሸሪዓም አይፈቅድም ፤ መፍትሄው ደግሞ በጣም አስቸኳይ እና ዘላቂ መሆን አለበት። እስካሁን መብታችን እየተከበረ አይደለም " ብለዋል።

NB. የክልል ትምህርት ቢሮ እና የአክሱም ከተማ አስተዳደር ምላሽ ለመስጠት ፍቃደኛ አልሆኑም።

የአክሱም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ምን አለ ?

ምክትል ርዕሰ መምህር ገ/መስቀል ገ/እግዚአብሔር ፦

" ' ትምህርት ቤቶች ከሃይማኖት እና ከፖለቲካ ነጻ መሆን አለባቸው ' ይላል የትግራይ ክልል የትምህርት ቤቶች አደረጃጀት መመሪያ ማንም ተማሪ በትምህርት ቤት ሃይማኖትን የሚያንጸባርቅ ነገር ማድረግ የለበትም።

ክርስቲያኑ መስቀል ወይም መጠምጠሚያ ፤ ሙስሊሙም ሂጀብ ወይም ኮፍያ ማድረግ አይፈቀድም። የትምህርት ቤቱ መለያ ዩኒፎርም ብቻ ነው መልበስ የሚገባው።

የተወሰኑ ተማሪዎች ሂጃባቸውን አናውልቅም ብለው ነበር አሁን ግን ተማሪዎች የትምህት ቤቱን መመሪያ ተከትለው እየገቡ ናቸው።

አሰራሩ ለዓመታት የቆየ ነው " ብለዋል።


አንድ በጉዳዩ ላይ ቃላቸው የሰጡ የክልል ትምህርት ቢሮ ሰራተኛ ፤ " በክልሉ ትምህርት ቤቶች ተግባራዊ እየሆነ ያለው በ1995 የወጣ መመሪያ ነው በዚያ መመሪያ ትምህርት ቤቶች የራሳቸውን መተዳደሪያ ማውጣት እንደሚችሉ ይደነግጋል " ሲሉ ተናግረዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የቪኦኤ ሬድዮ ጣቢያ ትግርኛ አገልግሎት መሆኑን ይገልጻል።

@tikvahethiopia
ፎቶ ፦ ዓመታዊው የታኅሣሥ 19 የሊቀ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል የንግሥ በዓል በሐዋሳ ከተማ ተከብሯል።

የንግሥ በዓሉ እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ኦርቶዶክሳውያን በተገኙበት ነው የተከበረው።

የሲዳማ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ በዓሉ ያለ አንዳች ኮሽታ በሰላም በከፍተኛ ድምቀት ተከብሯል ብሏል።

የፎቶ ባለቤት ፦ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር

@tikvahethiopia