TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.1K photos
1.5K videos
211 files
4.09K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Oromia 🕊 " ሰው በየሄደበት ይገደል ነበር በጣም ትልቅ ችግር ውስጥ ነው ያለፍነው አሁን ከሰላም በላይ ምን ጥቅም አለ ? ሰላምን የሚበልጥ ነገር የለም ! " - ነዋሪዎች 🟢 " ክልሉን ወደ መደበኛ ሁኔታ ለማምጣት እንዲህ ያሉ እምርጃዎች ይበረታታሉ " - አቶ ሽመልስ አብዲሳ " የሰላም ስምምነቱን የተቀበልነው የህዝባችንን ስቃይ ከተመለከትን በኃላ ነው፤... ስምምነቱ ለኦሮሞ ህዝብ ትልቅ እፎይታ…
" በመርሕ ደረጃ መጥፎ ሰላም ጥሩ ጦርነት ባይኖርም የስምምነቶች ግልጽነት ማጣት ውጤቱን የተገላቢጦሽ ሊያደርገው ይችላል ! " - የትብብሩ ፓርቲዎች

መኢአድ፣ ኢሕአፓ፣ ዐማራ ግዮናዊ ንቅናቄና እናት ፓርቲ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የጋራ መግለጫ ልከዋል።

ፓርቲዎቹ ፤ " አገራችን በሰላም እጦት፣ ሕዝባችን ለዓመታት በዘለቀ ጦርነት ቁምስቅሉን እያየ እንዳለ ምሥክር መቁጠር አይሻም። " ብለዋል።

" በተለይ በብዙ ተስፋና ጉጉት ተጠብቆ የነበረው ' ለውጥ ' የኋልዮሽ መሄድ ከጀመረ ወዲህ ሰላም ማደር ብርቅ፣ ፍጅትና ትርምስ ጌጣችን ከኾነ ሰነበተ " ሲሉ ገልጸዋል።

" ከዚህ ቀደም ኤርትራ በረሃ ከኦነግ ጋር በክልል አመራሮች ደረጃ ግልጽነት የጎደለው ስምምነት ከተደረገ በኋላ ሕዝብ ደስታውን ሳያጣጥም የሰላም ተፈራራሚው ኃይል " ቃል የተገባልኝ አልተፈጸመም " በሚል ሰበብ ተመልሶ ጫካ ከገባ ወዲኽ እንደ አገር ባጠቃላይ በተለይም ደግሞ የኦሮሚያ ክልል ያየው ቁምስቅል ተነግሮ የሚያልቅ አይደለም " ሲሉ ገልጸዋል።

ከሰሞኑ መንግሥት ' ኦነግ ሸኔ ' እያለ የሚጠራው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት የተወሰነ ቡድን ሰላም መፈረሙ በመንግሥት የመገናኛ ብዙሃን በስፋት መዘገቡን የገለጹት ፓርቲዎቹ " መጥፎ ሰላም የለም በሚል ጥቂቶች እንኳን የሰላም አካል መኾናቸውን በበጎ የምንመለከተው ነው " ብለውታል።

ከዚኹ ጋር ተያይዞ " የታጣቂ ቡድኑ መሪ ናቸው የተባሉ ግለሰብና የተወሰኑ ወጣቶች ከክልል አመራሮች ጋር ስምምነት ሲፈራረሙ ታይተዋል " ብለዋል።

" ከስምምነቱ ማግስትም አዲስ አበባ በተለያዩ አካባቢዎች ለሦስት ቀናት በዘለቀ ተኩስ ስትናጥ ከርማለች " ያሉት ፓርቲዎቹ " በተኩሱ እስከ አኹን አንዲት እናት በጥይት ተመትተው ሕይወታቸው ማለፉን አረጋግጠናል " ብለዋል።

ይኸው ድርጊት በተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞች እንደተከሰተ ገልጸዋል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ ሂደቱ ጥርጣሬን እንዳጫረባቸው ጥርጣሬያቸው የሚነሳውም ከስምምነቱ ግልጸኝነት ማጣት ብቻ ሳይሆን ከእንዲህ ዓይነት ክስተቶች ጭምር መሆኑን ገልጸዋል።

" ስምምነቱ መሣሪያ ማውረድን አይጨምርም ወይ ? " ያሉት ፓርቲዎቹ " የከተማ አስተዳደሩ ርችት እንኳን እንዳይተኮስ ሲከለክል እንዳልከረመ እንዴት ሙሉ ትጥቅ ተይዞ መግባትንና ለቀናት ጭምር የድልነሺነት ብሥራት በሚመስያመስል መልኩ ተኩስን ሊፈቅድ ቻለ ? " ሲሉ ጠይቀዋል።

በተጨማሪ ፦

° ' ከተማ ውስጥ ኹከት ለመፍጠር የመጡ ' በሚል በመታወቂያ ማንነት በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ኪሎ ሜትሮችን ተጉዘው የመጡ ነብሰ ጡሮችና አረጋውያን ጭምር ከአዲስ አበባ መግቢያ ክብረ ነክ በኾነ መንገድ ሲመልስ የነበረ ኃይል አኹን የት ሄዴ ?

° ከዚኹ መሐል ሲገድል ሲቀማ የነበረ በውል ተጣርቶ ተጠያቂነት አይኖርም ወይ ?

° መንግሥት የሰላም ስምምነት ፈጸመ ከተባለው ግለሰብና ቡድን ጋር ከዚኽ ቀደም የነበረው ግንኙነት ምን ነበር ?

° ታንዛኒያ ድረስ ኹለት ጊዜ አድካሚ ሙከራዎች ተደርገው ጫፍ እየደረሱ የተናፈቀው ሰላም ሲጨነግፍ በአቋራጭ አዲስ አበባ እውን የኾነበት ተዓምር ምን ቢኾን ነው ?

° የአዲስ አበባ ከተማ ሕዝብ ሥነልቡናዊ ጫና እንዲደርስበት ታስቦ ተሠርቷል ወይ ? የሚሉ ጥያቄዎችን ፓርቲዎቹ አንስተዋል።

ፓርቲዎቹ ፤ የለአንድም ቀን እንኳን ሰላም መስፈን እጅጉን እንሻለን ብለዋል።

" የአንድም ሰው የሰላምን መንገድ መምረጥ ያስደስተናል " ሲሉ አክበላለዋል።

" በአንጻሩ ደግሞ በሂደቱ ዙሪያ የግልጽነት አለመኖርና የሰላሙ ዘላቂነት እጅግ ስለሚያሳስበን አጠራጣሪ ጉዳዮች ሲኖሩ ማንሳት በጎ ይመስለናል " ብለዋል።

ፓርቲዎቹ፦

➡️ የሰላም መጥፎ የለውምና የተደረሰውን ስምምነት ከነገዘፉ ችግሮቹ በበጎ እናየዋለን ብለዋል።

➡️ መንግሥት የስምምነቱን ሂደትና ዝርዝር ነጥቦች የመከራው ግንባር ቀደም ገፈት ቀማሽ ለሆነው የኢትዮጵያ ሕዝብ ይፋ እንዲያደርግ በአጽንኦት አሳስበዋል።

➡️ በአዲስ አበባ በተለያዩ አካባቢዎች ለቀናት የዘለቀው ተኩስ፣ በሰላም ስምምነት የመጣ ሳይኾን ኾን ተብሎ የሕዝብን ሥነ ልቡና ለመስለብና ለማስፈራራት የተደረገ መኾኑን ሕዝባችን እንዲያውቀው እንሻለን ብለዋል።

➡️ በዚኹ የተኩስ እሩምታ ሰበብ መገናኛ አካባቢ ለተገደሉት እናት መንግሥት ሓላፊነት የሚወስድ ኾኖ ቢያንስ ቤተሰባቸውን ይፋዊ ይቅርታ እንዲጠይቅና ተገቢውን ካሳ እንዲከፍል እንጠይቃለን ብለዋል።

➡️ መንግሥት ከሽርፍራፊ ደስታና ማስመሰል ወጥቶ ዘላቂ ሰላምን በሰጥቶ መቀበል መርኅ በገለልተኛ ታዛቢዎች አማካይነት ድርድር ለማድረግ ፈቃደኝነቱን በመግለጽና ለዚህም ተግባራዊ እርምጃ በመውሰድ በአማራና ኦሮሚያ ክልሎች ያሉ ደም አፋሳሽ ጦርነቶች ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እልባት እንዲያገኙ፣ በአፋጣኝም ተኩስ አቁም እንዲታወጅ በአጽንዖት አሳስበዋል።

#እናትፓርቲ
#መኢአድ
#ኢሕአፓ
#ዐማራግዮናዊንቅናቄ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከትግራይ ክልል የፖለቲካና የጸጥታ አመራሮች ጋር መወያየታቸው ተሰምቷል። በውይይቱ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዛዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ እንዲሁም የህወሓት ሊቀመንበር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ተገኝተው ነበር። ከነሱ በተጨማሪ የፌዴራል እና የክልል ከፍተኛ ባለስልጣናትም ነበሩ። ምንም እንኳን የውይይቱ ዝርዝር ይፋ ባይደረግም በክልሉ የሚታዩ ችግሮችን እንዴት…
#Tigray

በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ ፤ በምክትል ሊቀመንበር ጌታቸው ረዳ የሚመራውን ህወሓት " በትግራይ ህዝብ ብሄራዊ ክህደት የፈፀመ ቡድን " ሲል ፈረጀ።

በምክትል ሊቀ-መንበር ጌታቸው ረዳ የሚመራውን ህወሓት " ብሄራዊ ክህደት ፈፅሟል " ሲል የፈረጀው ማእከላዊ ኮሚቴ " ቡድኑ ከአፍራሽ ተግባሩ እንዲቆጠብ " መላው የትግራይ ህዝብ እና አባላት እንዲታገሉት ሲል ጥሪ አቅርቧል።

ማእከላዊ ኮሚቴ ፤ በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ህወሓት " የትግራይ ህዝብ መብት እና ራስን በራስ የማስተዳደር መገለጫ የሆኑት ምክር ቤቶች እንዲፈርሱ ለፌደራል መንግስት ጠይቀዋል " ሲል ገልፀዋል።

በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ በአዲስ አበባ ከኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚንስተር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) ካካሄደው ውይይት መልስ ባወጣው መግለጫው ነው ይህን ጠንከር ያለ ፍረጃ ያቀረበው።

በተጨማሪ በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ህወሓት የትግራይ ሉአላዊ ግዛት ሳይረጋገጥ ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው ሳይመለሱ የትግራይ ሰራዊት በዲሞብላይዜሽን (DDR) ምክንያት በችኮላ እንዲሰናበቱ እያደረገ ነው ብሏል።

በትግራይ በኩል የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ፈራሚን ጥያቄ ውስጥ በሚከት መልኩ ፤ " የፕሪቶሪያ ውል ፈራሚ ባለቤት ማን እንደሆነ የኢትዮጵያ መንግስት እንዲወስን " በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ህወሓት ጠይቀዋል ሲልም አክሏል።

በክልሉ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን እየተካሄደ ነው ከሚባለው ህገ ወጥ የወርቅ ማእድን ማውጣት እና ማዘዋወር ጋር ተያይዞ በኢትዮጵያን በትግራይ ክልል ከኤርትራ በሚያዋስኑዋት አከባቢዎች የአገር መከላከያ ሰራዊት እንዲሰፍር በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ህወሓት ለፌደራል መንግስት ጥያቄ እንዳቀረበም በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ ገልጿል።

እስካሁን በእነ አቶ ጌታቸው ረዳ በኩል የተሰጠ ምላሽ የለም።

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Somaliland

አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድ ሶማሊለንድ ፤ ሀርጌሳ ገብተዋል።

አዲሱ የሶማሊላንድ ፕሬዝዳንት በሶማሊ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድ ለተመራ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ልዑክ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

የሶማሊላንድ ፕሬዝዳንት አቶ አብዱረህማን መሀመድ አብዱላሂ በአቶ ሙስጠፋ የተመራውን ልዑክ በጽ/ቤታቸው ተቀብለዋቸዋል።

ልዑኩ በሀርጌሳ ቆይታው ተመራጩ አዲሱ የሶማሊላንድ ፕሬዝዳንት አቶ አብዱረህማን መሀመድ አብዱላሂ በዓለ ሲመት ላይ ይሳተፋል ተብሎ እንደሚጠበቅ የሶማሊ ክልል ቴሌቪዥን ዘግቧል።

#Ethiopia #Somaliland

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia #Somalia ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ስምምነት ላይ ደረሱ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ በቱርክ ፕሬዜዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን አሸማጋይነት በቱርክ አንካራ ስምምነት ላይ ደርሰዋል። (ዝርዝር መረጃዎችን ይጠብቁ) @tikvahethiopia
ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ምን ተስማሙ ?

በቱርክ ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን አደራዳሪነት የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) እና የሶማሊያው ፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሙሀሙድ ስምምነት ላይ ደርሰዋል።

ስምምነቱ " የአንካራ ስምምነት " ተብሏል።

ይህ ተከትሎ በወጣው የስምምነት ሰነድ የተስማሙባቸው ጉዳዮች በዝርዝር ተቀምጠዋል።

ምንድናቸው ?

➡️ የሶማሊያ እና የኢትዮጵያ መሪዎች አንዳቸው ለሌላኛቸውን ሉዓላዊነት ፣ አንድነት ፣ነፃነት እና የግዛት አንድነት ለማክበር ቁርጠኝነታቸውን ገልጸዋል።

➡️ በወዳጅነት እና በመከባበር መንፈስ ልዩነቶችን እና አከራካሪ ጉዳዮችን በመተው ፤ በመተጋገዝ ለጋራ ብልጽግና ለመስራት ተስማምተዋል።

➡️  ሶማሊያ በአፍሪካ ህብረት ተልዕኮ ውስጥ የኢትዮጵያ ወታደሮች ለከፈሉት መስዋዕትነት እውቅና ሰጥታለች።

➡️ ኢትዮጵያ የሶማሊያን የግዛት አንድነት ባከበረ ሁኔታ የባህር በር ተጠቃሚ መሆኗ / ወደ ባህር እና ' ከ ' ባህር / ሊያስገኝ የሚችለው ልዩ ልዩ ጥቅም ላይ ተማምነውበታል።

➡️ ሁለቱንም ተጠቃሚ ባደረገ ሁኔታ የንግድ ውል ይታሰራል።

➡️ ኢትዮጵያ አስተማማኝ፣ ደህንነቱ የተጠበቀና እና ቀጣይነት ያለው / ዘላቂ የባህር በር መዳረሻ / አክሰስ እንዲኖራት ስምምነት ላይ ተደርሷል
ይህም በሉዓላዊ የሶማሊያ መንግሥት ስልጣን ስር የሚተገበር ነው።

ለዚህም የሚሆን ፦
- የኮንትራንት
- የሊዝ ውልን ጨምሮ ሌሎች ሞዳሊቲዎች ላይ በቀጣይ በቅርበት አብሮ ለመስራትና ለማጠናቀቅ ተስማምተዋል።

ለነዚህ ዓላማዎች መሳካት በጥሩ እምነት ከየካቲት 2025 መጨረሻ በፊት የቴክኒካል ድርድር ለመጀመር ወስነዋል። ይህም በቱርክ አመቻችነት የሚሳለጥ ሲሆን በ4 ወራት ውስጥ ተጠናቆ ስምምነት ይፈረማል።

ለዚህም ቁርጠኝነትና ለቃል ኪዳኑ ተግባራዊ መደረግ የቱርክን እገዛ በደስታ ተቀብለዋል።

➡️ በአተገባበር ሆነ በሌሎች ጉዳዮች ላይ ያሉ ልዩነቶችን በውይይት እና በሰላማዊ መንገድ ' እንደአስፈላጊነቱ ' በቱርክ ድጋፍ ለመፍታት ቃል ገብተዋል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
#TecnoAI

ዘምኖ የሚያዘምኖ፣ ህይወቶን የሚያቀል፣ ከበርካታ አርቴፊሻል ቴክኖሎጂ ካመጣቸው ከፍ ያሉ ቴክኖሎጂዎች ጋር የሚያስተዋውቆት በኪስዎት ውስጥ ይዘውት የሚዞሩት ፕሮፌሽናል አጋዥ ቴክኖ ኤ አይ ወደ እርሶ እየመጣ ነው፡፡

ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ በመከተል የቴክኖ ቲክቶክ ገጽ ፎሎው በማድረግ እና Bio ላይ ያለውን ሊንክ ተጭነው በመመዝገብ ታህሳስ 10 በስካይላይት ሆቴል በሚካሄደው የሀገራችን ትልቁ የኤ አይ ሁነት ላይ ይሳተፉ፡፡

https://www.tiktok.com/@tecnoet

@tecno_et @tecno_et
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Ethiopia🇪🇹

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በቱርክ አንካራ ፤ ከሶማሊያው ፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሙሀሙድ ጋር ያደረጉትን የፊት ለፊት ውይይትና ድርድር አጠናቀው ጥዋት አዲስ አበባ መግባታቸውን ከጠ/ሚ ፅ/ቤት የተገኘው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ምን ተስማሙ ? በቱርክ ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን አደራዳሪነት የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) እና የሶማሊያው ፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሙሀሙድ ስምምነት ላይ ደርሰዋል። ስምምነቱ " የአንካራ ስምምነት " ተብሏል። ይህ ተከትሎ በወጣው የስምምነት ሰነድ የተስማሙባቸው ጉዳዮች በዝርዝር ተቀምጠዋል። ምንድናቸው ? ➡️ የሶማሊያ እና የኢትዮጵያ መሪዎች አንዳቸው ለሌላኛቸውን…
ሶማሊያውያኑ ምን እያሉ ነው ?

በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ሶማሊያውያን በተለይም አክቲቪስቶች " ሀሰን ሼክ ሀገራችንን ሸጠብን ፤ በዲፕሎማሲ ተበልጦ አስበላን " ማለት ጀምረዋል።

ኢትዮጵያ የሶማሊያን ሉላዓዊነት፣ አንድነት እና የግዛት አንድነት ባከበረ ሁኔታ ዘላቂነት ያለው አስተማማኝና ደህንነቱ የተጠበቀ የባህር በር ታገኛለች መባሉ የሶማሊያ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎችን አበሳጭቷቸዋል።

በማህበራዊ ሚዲያ በተለይ በX ቪላ ሶማሊያ ገጽ ስር ፤ ከወራት በፊት ሲያሞጋግሷቸው የነበሩትን ፕሬዜዳንታቸውን ሀሰን ሼክ ሙሀሙድ ላይ ውግዘት ማዝነብ ጀምረዋል።

እኚህ አስተያየት ሰጪዎች ምን እያሉ ነው ?

➡️ " ሀሰን ሼክ ባህራችንን ሸጠብን። ካደን ፤ ከሀዲ ነው "

➡️ " እንዴት በድርድሩ ላይ ሆነ በስምምነቱ ላይ ኢትዮጵያ ከሶማሌላንድ ጋር ያደረገችው የባህር በር ለማግኘት የፈረመችው የመግባቢያ ስምምነት / MoU አልተነሳም ፤ በግልጽ ቀርቷል ለምን አልተባለም "

➡️ " አዋረደን ! ለሶማሊያ ጨለማ ቀን ነው "

➡️ " ስለ ኢትዮጵያ የቀጣይ የሰላም ማስከበር ተሳትፎ (ሶማሊያ ውስጥ) ለምን አለተነሳም "

➡️ " ዘላቂነት እና አስተማማኝ የባህር በር ኢትዮጵያ ስታገኝ ሶማሊያ በምላሹ ምን ታገኛለች ? "

➡️ " ሁሉንም ኢትዮጵያ የፈለገችውን ነው የተቀበልነው፤ ኢትዮጵያ በመረጠችው መንገድ ሄዳ ፤ በዚህም በዚያ ብላ ባህር በር ስታገኝ እኛ ምን አገኘን ? " 

➡️ " ኢትዮጵያ ዲፕሎማሲው እና ድርድሩ በልጣ ባህር በር አሳካች " ... የሚሉ አስተያየቶችን በመስጠት ፕሬዜዳንታቸው ላይ ውግዘት እና የስድብ ናዳ እያወረዱ ነው።

አንዳንዶቹ ከቦታው ይነሳልን ወደማለትም ገብተዋል።

120 ሚሊዮን ህዝብ ያላት ኢትዮጵያ የባህር በር ጉዳይ " በፍጹም የማልተወው የህልውዬ ጉዳይ ነው " ብላ በይፋና በድፍረት አደባባይ ከወጣች በኃላ ጉዳዩ ከፍተኛ አጀንዳ ሆኖ ዓለም አቀፍ መወያያ መሆን ችሏል።

ከሶማሌላንድ ጋር የመግባቢያ ስምምነት (MoU) ከተፈራረመች በኃላ ሶማሊያ አኩርፋ ብዙ ስትል ከርማለች ፤ ከኢትዮጵያ ጋርም ተጎረባብጣለች።

ፕሬዜዳንቷ እና አስተዳደራቸው በየጊዜው ወደ ሚዲያ እየወጡ ፦
- ከኢትዮጵያ ጋር በፍጹም አንነጋገርም፤
- የኢትዮጵያ ወታደሮች በሰላም ማስከበር ላይ አይሳተፉም፤
- እንድንነጋገር ከፈለገች MoU ቀዳ ጥላ በይፋ ይቅርታ ትጠይቅ ይህ ካልሆነ ኢትዮጵያን አንሰማትም፤
- በኢትዮጵያ ያሉ ታጣቂዎችን እንደግፋቸዋለን / እናስታጥቃለን፤
- ኢትዮጵያ ለሶማሊያ ደሟን እንዳልገበረችላት የኢትዮጵያ እድገት እንቅልፍ ከሚነሳቸው አካላት ጋር እየሄደ ጥምረት ሲፈጥር
- ከኢትዮጵያ ለመነጋገር ቅድመ ሁኔታዎችን ሲደረድር ... ሲዝት ፣ ሲፎክር ከርሟል።

በመጨረሻ በቱርክ አሸማጋይነት አንካር ሄደው ከኢትዮጵያ ጋር ስምምነት ላይ ደርሰዋል።

በስምምነቱ ይፋዊ ሰነድ ላይ ሆነ በመሪዎች መግለጫ ምንም ቦታ ላይ ስለ ሶማሊለንዱ MoU አለመነሳቱ ፤ ማብራሪያ አለመሰጠቱ እንዲሁም በግልጽ ተሰርዟል አለመባሉን በማንሳት " ኢትዮጵያ የምትፈልገውን አገኘች " በማለት ሶማሊያውያን በፕሬዜዳንታቸው ላይ ተነስተዋል።

#TikvahEthiopia
#Ethiopia🇪🇹
#Seaaccess

@tikvahethiopia