TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
" እናንተም ከኢትዮጵያ ሕዝብ ነው የወጣችሁት፣ አታንገላቱን ወዴት እንደሚሄድ ንገሩን ብንል ምላሽ አላገኘንም ! ” -  ወ/ሮ ስንታየሁ ዓለማየሁ የቀድሞ የሰላም ሚኒስትር እና የኦሮሚያ ክልል ም/ቤት አባል አቶ ታዬ ደንደአ ፍርድ ቤት በዋስ እንዲለቀቁ ከፈቀደላቸው እና ዛሬ ከቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ከወጡ በኃላ በር ላይ ተይዘው እስካሁን ወዳልታወቀ ስፍራ ተወስደዋል። አቶ ታዬ ደንደአ በዋስ እንዲለቀቁ የወሰነው…
#Update

የቀድሞው የሰላም ሚኒስትር አቶ ታዬ ደንደዓ ዛሬ መኖርያ ቤታቸዉ ገቡ።

ከቤተሰቦቻቸው ጋርም ተቀላቅለዋል።

ትናንት አመሻሹን ከቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ተለቀው ቤተሰቦቻቸውን ሳይቀላቀሉ ከማረሚያ ቤቱ በራፍ በጸጥታ ኃይሎች መወሰዳቸው ይታወሳል።

በኃልም የተወሰዱት ሜክሲኮ የወንጀል ምርመራ እነደነበር ታውቋል።

ዛሬ እኩለ ቀን ደግሞ ሜክሲኮ ከሚገኘው የወንጅል ምርመራ ማዕከል ተለቀው ቤታቸው መድረሳቸውን ባለቤታቸው ወ/ሮ ስንታየሁ ዓለማየሁ ለዶይቼ ቬለ ሬድዮ ተናግረዋል፡፡

ወ/ሮ ስንታየሁ " ጠዋት ቤተሰብ ሜክሲኮ ምግብ አድርሶላቸው ከተመለሰና ደህንነታው ከጠየቀ በኋላ ዛሬ እኩለ ቀን ምሳ ሰዓት ከማቆያው እንዲወጡ ተወስኖ 7 ሰዓት ግድም መኖራቸው ቤት ደርሰዋል " ብለዋል።

ባለፈው ሰኞ በፍርድ ቤት በ20 ሺህ ብር ዋስትና ክሳቸውን ከውጪ መከታተል እንዲችሉ በታዘዘው መሰረት ትናንት ከቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ቢለቀቁም ለምን ወደ ሜክሲኮ የወንጀል ምርመራ ማዕከል እንደተወሰዱ ግን ቤተሰብ እንዳልተረዳ ነው የተነገረው፡፡

መረጃው የዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የሪል_ስቴት_ልማት_እና_የማይንቀሳቀስ_ንብረት_ግብይትና_ግመታ_አዋጅ_1.pdf
የሪል እስቴት ልማት እና የማይንቀሳቀስ ንብረት ግብይትና ግመታ ረቂቅ አዋጅ ፀደቀ።

የህ/ተ/ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው ስብሰባ ረቂቅ አዋጁ ላይ ከተወያየ በኋላ ረቂቅ አዋጁ፤ አዋጅ ቁጥር 1357/2017 ሆኖ በሁለት ተቃውሞና በአንድ ድምፀ ተዓቅቦ በአብላጫ ድምጽ አፅድቋል።

ዛሬ በምክር ቤት የፀደቀው ረቂቅ አዋጅ የሪል ስቴት አልሚ ድርጅት ያለደንበኛው ፍላጎትና ፈቃድ አጠቃላይ ግንባታው ቢያንስ 80 በመቶ ያልተጠናቀቀ ቤት ለደንበኞች ሊያስተላልፍ እንደማይችል አስቀምጧል።

በተጨማሪ በሪል ስቴት ልማት ላይ የሚሳተፍ ማንኛውም አካል #የውሸት_ማስታወቂያ ማስነገር እንደማይችልም አስቀምጧል።

ውድ ቤተሰቦቻችን ትላንት ያያዝነውን ሙሉ ሰነዱን በዚህ ያገኙታል👇
https://t.iss.one/tikvahethiopia/92613

@tikvahethiopia
#DStvEthiopia

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ቀጥለዋል 💥

⚽️ Fulham vs Brighton ከምሽቱ 04:30 በSS Liyu በሜዳ ፓኬጅ
⚽️ Bournemouth vs Tottenham ከምሽቱ 05:15 በSS Premier League በሜዳ ፓኬጅ

👉እነዚህን ድንቅ ፍልሚያዎች ጨምሮ ሌሎች የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎችን በቀጥታ በዲኤስቲቪ ሱፐርስፖርት ይመልከቱ።

ዲኤስቲቪ ያስገቡ ፣ ደንበኝነትዎን ያራዝሙ!
👇
https://bit.ly/3RFtEvh

ደንብና ሁኔታዎች ተፈፀሚነት አላቸው! ለበለጠ መረጃ
👇
www.dstv.com/en-et

#PremierLeagueallonDStv #ሁሉምያለውእኛጋርነው
TIKVAH-ETHIOPIA
" በምክር ቤት የተሾሙትን አመራር በግርግር ነው ከፅህፈት ቤቱ ያወጣው " - በድብረጽዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት ትላንት ምሽት መግለጫ አውጥቷል። ደርጅቱ በመግለጫው ለአቶ ጌታቸው ረዳ ሰጥቷቸው የነበረው የፕሬዜዳንት ውክልና አንስቶ በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት መሰረት እንዴት እና በማን እንዲሚተኩ ከፌደራል መንግስት እየተወያየበት እንደሚገኝ…
#Tigray

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከትግራይ ክልል የፖለቲካና የጸጥታ አመራሮች ጋር መወያየታቸው ተሰምቷል።

በውይይቱ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዛዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ እንዲሁም የህወሓት ሊቀመንበር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ተገኝተው ነበር።

ከነሱ በተጨማሪ የፌዴራል እና የክልል ከፍተኛ ባለስልጣናትም ነበሩ።

ምንም እንኳን የውይይቱ ዝርዝር ይፋ ባይደረግም በክልሉ የሚታዩ ችግሮችን እንዴት በጋራ መፍታት እንደሚገባ ውይይት መደረጉ ተገልጿል።

በውይይቱ በተለዩ አንኳር ጉዳዮች ላይ በተቀመጡ የጋራ አቅጣጫዎች መሠረት በጋራ ለመስራትና የክልሉ ህዝብ የፀጥታ፣ የመልካም አስተዳደር እና የልማት ፍላጎት ለማሟላት አስቻይ ሁኔታ ለመፍጠር መግባባት ላይ መደረሱ ተገልጿል።

በተለይ ከመኖሪያቸው የተፈናቀሉ ዜጎች ወደቀያቸው የሚመለሱበትን ሁኔታና ታጣቂዎችን ወደ መደበኛ ህይወት የመመለስ ሂደት በትኩረት የሚሰራበት እና የሚሳለጥበት ሁኔታ ላይ መግባባት ላይ መደረሱ ተገልጿል።

በተጨማሪ በክልሉ ያሉ የተፈጥሮ ሃብቶች አጠቃቀም ህጋዊ  በሆነ አግባብ የህዝብንና የሀገርን ጥቅም የሚያስጠብቅ እንዲሆን፣ ለህዝብ የሚቀርቡ የመንግስት አገልግሎቶች የሚሻሻሉበትና የህዝብን ፍላጎት የሚመጥኑ እንዲሆኑ ቀጣይነት ያለው ጠንካራ ስራ እንዲሰራ መግባባት ላይ ተደርሷል።

በዚሁ ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ውይይት ላይ ጊዚያዊ አስተዳደሩ ክልላዊ ምርጫ እስኪካሄድ ድረስ ያለበትን ሃላፊነት ለመወጣት በሚያስችለው አግባብ ላይም አቅጣጫ ተቀምጧል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በህወሓት አመራሮች መካከል የተፈጠረው መከፋፈል ወደየት እያመራ ነው ? በሚል ብዙዎችን ማስጋቱ ይታወቃል።

በተለይ ሰሞኑን በአቶ ጌታቸው እና በደብረጾን (ዶ/ር) ቡድኖች መካከል ጠንከር ያሉ የመግለጫና የሚዲያ ምልልሶች ሲደረጉ ሰንብተዋል።

ከመግለጫና የሚዲያ ምልልስ ባለፈ በደብረፅዮ ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት በምክር ቤት አማካኝነት የጊዜያዊ አስተዳደሩን ሹመኞች በማንሳት የራሱን ሲሾም በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ጊዜያዊ አስተዳደር በበኩሉ በደብረጽዮን በሚመራው ቡድን የሚሾሙ ሹመኞችን በማንሳት የራሱን አመራሮች ሲመድብ ነበር።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#አፈሳ 🔵 “ ወጣቶች እየታፈሱ ነው። የሚታፈሱትም ያለ ፍላጎታቸው ወደ ግዳጅ ሊላኩ ነው ” - የኦሮሚያ ክልል ነዋሪዎች 🔴 “ ያገኘናቸው በጣም በርካታ ግኝቶች አሉ ” - ኢሰመኮ በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ወጣቶች “ በመንግስት ፀጥታ አካላት ” እየታፈሱ መሆኑን፣ በዚህም እንዲህ አይነት ድርጊት በሚፈጸምባቸው ቦታዎች ወጣቶች በነጻነት የመንቀሳቀስ መብታቸው እንደተገደበ ነዋሪዎች በቲክቫህ ኢትዮጵያ…
#EHRC

ኦሮሚያ ክልል ውስጥ ህጻናት እና የአእምሮ ህሙሟን ጨምሮ በርካቶች በግዳጅ ተይዘው እንደነበር በምርመራ ተረጋግጧል።

ሕፃናትን ጨምሮ ሰዎችን ከሕግ ውጪ የያዙ እና ገንዘብ እንዲከፍሉ ያስገደዱ የኦሮሚያ ክልል መንግሥት የአስተዳደር እና የጸጥታ አካላት ላይ የተሟላ ምርመራ በማድረግ ተጠያቂነት ሊረጋገጥ ይገባል ሲል የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አሳውቋል።
 

በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የክልሉ የአስተዳደር እና የጸጥታ አካላት " የመከላከያ ሰራዊት አባል ለመሆን የሚፈልጉ ዜጎችን ምልመላ እናከናውናለን " በሚል የሰራዊቱን አሠራር እና መስፈርቶች በጣሰ ሁኔታ ሕፃናትን ጨምሮ ሰዎችን በግዳጅ ስለመያዛቸው እና የተያዙትን ለመልቀቅ ቤተሰቦቻቸው ገንዘብ እንዲከፍሉ ስለማስገደዳቸው ኮሚሽኑ ከነዋሪዎች መረጃዎች ደርሰውት ነበር።

ይህ ተከትሎ በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች ከኅዳር 4 እስከ 20 ቀን 2017 ዓ.ም. ድረስ ክትትል እና ምርመራ አከናውኗል።

በዚህ ክትትል እና ምርመራ በኦሮሚያ ክልል ፦
- በአዳማ፣
- በቢሾፍቱ፣
- በጅማ እና በሻሸመኔ ከተሞች የሚገኙ እጩ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ማቆያ ስፍራዎችን በመጎብኘት፤ በማቆያ ስፍራዎቹ ውስጥ የሚገኙ ሰዎችን እና ቤተሰቦቻቸውን በማነጋገር፤ እንዲሁም የሚሊሻ እና የፖሊስ ተቋማትን ጨምሮ ከክልል እስከ ቀበሌ መዋቅር ያሉ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችን በማወያየት ስለጉዳዩ መረጃዎችንና ማስረጃዎችን አሰባስቧል።

ምንም እንኳን ሀገር መከላከያ ስርዓቱን እና ህጉን ተከተለ መልኩ መስፈርቱን ለሚያሟሉ ሀገር መከላከያን እንዲቀላቀሉ ማስታወቂያ ቢያወጣም ፤ እንዲሁም የኦሮሚያ ክልል አስተዳደር የምልመላ ሂደቱን በመከላከያ ሚኒስቴር መስፈርቶች መሠረት እንዲያከናውን የተጠየቀ ቢሆንም የክልሉ የአስተዳደር አካላት እና የጸጥታ ኃይሎች አባላት በመከላከያ ሚኒስቴር ከተገለጸው የምልመላ መስፈርት ውጪ ሕፃናትን ጨምሮ በርካታ ሰዎችን " የመከላከያ ሰራዊትን እንዲቀላቀሉ " በሚል በግዳጅ እንደያዙ ተረጋግጧል።

በአንዳንድ የክልሉ አካባቢዎች በዚህ አግባብ የተያዙ ሰዎችን ለማስለቀቅ ቤተሰቦቻቸው ከፍተኛ ገንዘብ እንዲከፍሉ ማስገደዳቸውም በኢሰመኮ ምርመራ ተረጋግጧል።

ኢሰመኮ ክትትል እና ምርመራ ባደረገባቸው አንዳንድ አካባቢዎች ከክልሉ አመራሮች ጋር በመተባበር " የመከላከያ ሰራዊትን እንዲቀላቀሉ " በሚል ተይዘው የነበሩ ሕፃናትን እና የአእምሮ ሕሙማንን ጨምሮ በግዳጅ የተያዙ በርካታ ሰዎችን ለማስለቀቅ ተችሏል።

በወቅቱ ኢሰመኮ ያነጋገራቸው የክልሉ የሰላም እና ጸጥታ ቢሮ እንዲሁም በጅማ እና በሻሸመኔ ከተሞች የሚገኙ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ችግሩ መኖሩን አምነዋል።

የማቆያ ስፍራዎችን በመፈተሽ የእርምት እርምጃዎችን በመውሰድ ላይ መሆናቸውን እና ድርጊቱን በፈጸሙ የመንግሥት ኃላፊዎች እና የሚሊሻ አባላት ላይ እርምጃ እንደሚወስዱ ለኢሰመኮ ገልጸዋል።

ኢሰመኮ ክትትል ባደረገባቸው አንዳንድ አካባቢዎች የመከላከያ ሰራዊት አመራሮችም ከመስፈርት ውጪ የተደረገ ምልመላ መሆኑን በመግለጽ በክልሉ የጸጥታ አካላት የተያዙ ሰዎች ከማቆያ ስፍራዎች እንዲለቀቁ ያደረጉ መሆኑን ተገንዝቧል።

ይህ የምርመራ ሪፖርት በመጠናቀር ላይ በነበረበት ወቅት በተለይም ኅዳር 14 እና 15 ቀን 2017 ዓ.ም. በኦሮሚያ ክልል ሲከናወን የቆየው የመከላከያ ሰራዊት አባላት ምልመላ ሥራ መጠናቀቁን እና ሰራዊቱ በፈቃደኛነት የተመዘገቡ እና የምልመላ መስፈርቶችን የሚያሟሉ ምልምሎችን ለይቶ ወደ ማሰልጠኛ ተቋማት እንዲገቡ ማድረጉን ኢሰመኮ ተገንዝቧል።

(ኢሰመኮ የላከልን ሙሉ የምርመራ ሪፖርት ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#EHRC ኦሮሚያ ክልል ውስጥ ህጻናት እና የአእምሮ ህሙሟን ጨምሮ በርካቶች በግዳጅ ተይዘው እንደነበር በምርመራ ተረጋግጧል። ሕፃናትን ጨምሮ ሰዎችን ከሕግ ውጪ የያዙ እና ገንዘብ እንዲከፍሉ ያስገደዱ የኦሮሚያ ክልል መንግሥት የአስተዳደር እና የጸጥታ አካላት ላይ የተሟላ ምርመራ በማድረግ ተጠያቂነት ሊረጋገጥ ይገባል ሲል የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አሳውቋል።   በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ…
🔈 በሻሸመኔ ከተማ ኢሰመኮ ባደረገው ክትትል እና ምርመራ ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች መሆኑን የገለጹ ሕፃናት " ወታደራዊ ስልጠና ትገባላችሁ " በሚል ወደ ማቆያ አዳራሾች እንዲገቡ መደረጋቸውን አረጋግጧል።

በሁሩፋ ክፍለ ከተማ፣ ሀሌሉ ወረዳ ውስጥ በማቆያ አዳራሽ ከነበሩ እና ኢሰመኮ ካነጋገራቸው 32 ሰዎች መካከል 14ቱ ዕድሜያቸው ከ15 እስከ 16 ዓመት መሆኑን የገለጹ ሲሆን አንድ ሕፃን ደግሞ ዕድሜው 11 ዓመት መሆኑን ገልጿል።

ከት/ቤት ሲወጡ #ከነዩኒፎርማቸው ፤ ሀሌሉ ወረዳ ወደ ሚገኘው ማቆያ አዳራሽ እንዲገቡ የተደረጉ የ5ኛ ክፍል ተማሪ የሆኑ ሁለት የ15 ዓመት ሕፃናት ወደ አዳራሽ ከገቡ ሁለት ሳምንት እንደሆናቸው ገልጸው የገቡበትን ሁኔታም አስረድተዋል።

ሕፃናቱ ፤ “ ከትምህርት ቤት ስንመለስ መከላከያ ለሚገቡ 25,000 ብር ይሰጣል ብሎ አንድ ግለሰብ በባጃጅ አሳፈረን፤ ከዚያ 010 ቀበሌ (ሀሌሉ ወረዳ) ወደ ሚገኘው አዳራሽ ገባን፤ ነገር ግን ከገባን በኋላ መውጣት አልቻልንም  ” ሲሉ ነው የገለጹት።

በጅማ ከተማ ኢሰመኮ ያነጋገረው የ14 ዓመት ሕፃን ስለተያዘበት ሁኔታ ሲያስረዳ፦

“ ኅዳር 2 ቀን 2017 ዓ.ም. ከምሽቱ 2፡30 ሰዓት አካባቢ ወደ ቤት እየሄድኩ እያለሁ መንገድ ላይ ቆመው የነበሩ ሚሊሻዎች ባትሪ አብርተውብኝ አስቆሙኝ፤ መታወቂያ ሲጠይቁኝ ዕድሜዬ ገና 14 ዓመት ነው፤ የ7ኛ ክፍል ተማሪ ነኝ መታወቂያ የለኝም ብዬ ስመልስ፣ ቀበሌ ሄደህ ጉዳይህ ይጣራል በማለት ወደ ቀበሌ ወስደው ብዛታቸው ከ20 በላይ ከሚሆኑ ወጣቶች መካከል ቀላቅለውኝ ሄዱ። ለመከላከያ ሰራዊት አባልነት መያዜንም ወጣቶቹ ናቸው የነገሩኝ። በማግስቱ በድብቅ ለቤተሰቦቼ ደውዬ ካሳወቅኩ በኋላ ለመውጣት ችያለሁ ” ብሏል።

#EHRC #OROMIA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
#Myanmar (Burma) #ማይናማር " በህይወት እወጣለሁ ብዬ አላሰብኩም ነበር " - ሽኩር  (የአይን ምስክር) " ስሜ ሽኩር ይባላል። የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ዓለምን ባመሰቃቃላ ግዜ እኔ ሥራ ካጡ ሰዎች አንዱ ነበርኩ። በአገራችን ያለው የኢኮኖሚ ሁኔታ ጉዳዩን የበለጠ አባብሶት የነበረ ቢሆንም ለመኖር ሲባል ለ 7ወር የህል በመምህርነት አገልግያለሁ። ነገር ግን ገቢዬ ፍላጎቴን ለማሟላት በቂ አልነበረም።…
" አሁንም በርካታ ሰዎች ከኢትዮጲያ እየጎረፉ ይገኛሉ  !! " - በስፍራው የሚገኝ የአይን ምስክር

በርካታ የሀገራችን ወጣቶች " ታይላንድ ስራ አለ " እየተባሉ ወደ ማይናማር ድንበር ቦታ ተወስደው ካምፕ ውስጥ እንዲገቡ እየተደረጉና በዓለም አቀፍ የኦንላይ ማጭበርበር ተግባር ላይ እንዲሰማሩ እየተደርጉ መሆኑን ቲክቫህ ኢትዬጵያ ለረጅም ጊዜ ማሳወቁ ይታወሳል።

አሁንም በርካታ ወጣቶች እዛው ናቸው።

ከአደገኛው ስፍራ ለመውጣት እገዛ ይፈልጋሉ።

ለዛሬ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል የሆነ እና በደላሎች ተታሎ ባልፈለገው ተግባር ላይ ተሰማርቶ እየተሰቃየ የሚገኝን አንድ ወጣት ምስክርነት እናቀርባለን።

ከማይናማርና ሜሱት ድንበር ፦

" ስሜ ይቆየኝ ፤ እኔ ኤዢያ ውስጥ በማይናማር እና በሜሱት ድንበር ላይ ነኝ።

ወደዚህ የደረስኩት በደላሎች ቅብብሎሽ ነው።

ስራ ያለው ታይላንድ ከተማ ላይ ነው ብለውኝ ነበር የመጣሁት ግን አንድ ቀን ታይላንድ አደረኩ በቀጣይ ቀን ወደ ሜሱት መጣሁ።

ስሄድ በVisit Visa 15 ቀን ነበር ለታይላንድ የከፈልኩት አሁን ግን እሱም ቀኑ አልቋል።

የጠበኩት ስራ ሌላ ነበር እያሰሩን ያሉት ሰዎችን በበየነ መረብ (ኦንላይን) ማጭበርበር ነው።

በርካቶች ማጭበርበር ስላልቻሉ ታግተዋል።

እኔ እዚህ ከመጣሁ 3 ወሬ ነው ነገ ምን እንደሚያደርጉኝ አላቅም በጣም አምባገነን እና ጨካኝ ናቸው።

ቻይኖች ናቸው የሚያሰሩን እኛንም በየቀኑ እያስጠነቀቁን ነው።

እዚህ ግቢ ፎቶ መውሰድ የተከለከለ ነው። በየቦታው በየመቀመጫው የCCTV ካሜራ እያንዳንዱን ሰው ይቆጣጠራል።

ፎቶ ሲያነሳ / ቪድዮ ሲቀርጽ የተገኘ ሰው 7 አመት የጫካ እስር እና 100 ሺህ የታይላንድ ባት ይቀጣል።

አሁንም በርካታ ሰዎች ከኢትዮጲያ እዚህ እየጎረፉ ይገኛሉ ፤ በየቀኑ ከ30 በላይ የሀገሬ ልጆች ወደዚህ ስፍራ ይመጣሉ። እባካችሁ በጭራሽ ወደዚህ እንዳትመጡ።

ለመምጣት እንዳያስቡት ጭምር ነው የማስጠነቅቀው።

እኛንም የኢትዮጵያ መንግስት እጁን ከቶ ያስወጣን ከዚህ ጉድ።

ይሄን መረጃ የምሰጠው እኔ የአይን ምስክር ስለሆንኩ ነው።

እኔን እግዚአብሔር ያውጣኝ ከዚህ።

ለሌሎች እኔ ያየሁትን ስቃይ እንዲያዩ አልመኝም።

በርካታ ኢትዮጵያን እና የምስራቅ አፍሪካ ሰዎች በቃ የአውሮፓ ሲቀር በርካቶች እዚህ ናቸው። እኔ ለሀገሬ ልጆች ይሄን መረጃ አድርሼ ለመታደግ ከቻልኩ ብዬ ነው።

ወጣት እያለቀ ነው እየተበዘበዘ በሰው ሀገር እኔን ጨምሮ የደላላ ስልክ እና የቴሌግራም ዩዘርኔም አለኝና ፎቶም አለኝ ለሚፈለገው አካል ማጋራት እችላለሁ። "


🚨 ከላይ ያለው ምስል ያሉበት ግቢው ነው። ግቢው ሶስት ሲሆን KK1 , KK3 , KK2 ይባላሉ። በጣም ሰፊ እና ማንም የማይደርስበት ነው።

ወጣቶችን ከተለያዩ ሀገራት በደላሎች አታለው ወስደው ምንድነው የሚያሰሯቸው ? በዝርዝር ያንብቡ : https://t.iss.one/tikvahethiopia/90728

@tikvahethiopia
#ArbaMinch : ላለፉት በርካታ ዓመታት አርባ ምንጭ ላይ ሲገነባ የቆየው የጋሞ አደባባይ ተመርቋል።

" አደባባዩ በዞኑ የሚገኙ ህዝቦችን ባህል እና ትዉፊት በሚወክል መልኩ ነው የተሰራው " ሲል የዞኑ አስተዳደር ገልጿል።

ለዚህ አደባባይ ከ122,000,000 ብር (መቶ ሃያ ሁለት ሚሊዮን ብር) በላይ ወጪ እንደተደረገበት ነው የተነገረው።

@tikvahethiopia
@HibretBanket

Experience 25+ YEARS OF BANKING

At Hibret Bank, we are committed to exceeding your expectations.

Hibret Bank
United, We prosper!


📞  For more information call our free call center - 995. 
🤳 To receive new information join our Telegram page. https://t.iss.one/HibretBanket
🌐 Visit our other social media pages and wesite on   linktr.ee/Hibret.Bank