TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
🔈#የሠራተኞችድምፅ

🔴 " ደመወዛችን ተቆርጦ 15 ,000 ብር የሚከፈላቸው 5 ,000 ብር ነው የገባላቸው፡፡ ለ6 ወራት ደመወዛችን በስርዓት እየተከፈለን አይደለም " - ሠራተኞች

🔵 " ጥሩ ቅሬታ ነው። ድርጅቱ ደመወዝ የሚከፍለው ብር ሲኖር ነው " - የናሁ ቴሌቪዥን አስተዳደር

የናሁ ቴሌቪዥን ሠራተኞች የወር መወዛቸው በወቅቱ እንደማይፈጸም፣ ጊዜው ካፈ በኋላ ራሱ ከደመወዛቸው ከግማሽ በላይ ተቆርጦ እንደሚደርሳቸው፣ ደመወዛቸው ባለመከፈሉ ብድር ጭምር እንደገቡ፣ ድርጅቱ አጥጋቢ ምላሽ በመስጠት ፋንታ እያንጓጠጣቸው መሆኑን በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል ስሞታ አሰምተዋል፡፡

ሠራተኞቹ ያቀረቡት ዝርዝር እሮሮ ምንድን ነው?

" ደመወዛችን ተቆርጦ 15 ሺሕ ብር የሚከፈላቸው 5 ሺሕ ብር ነው የገባላቸው። ላለፉት ስድስት ወራት የሰራንበት ደመወዝ በትክክል እየተከፈለን አይደለም፡፡ አሁን ለምሳሌ የጥቅምት ወር ደመወዝ ዛሬ ነው የገባልን።

ወቅቱን ተላልፎ እንኳ 13 ሺሕ ብር የሚከፈለን ሰዎች ተቆርጦ 6,500 ብር ነው የገባልን፡፡ ወሩን ሥራ ገብተናል፡፡ ግን ‘ፊርማ አልፈረማችሁም’ ተብሎ ነው የተቆረጠው፡፡ ለዜናም፣ ለጥቆማም ልናናግር ወጥተን ያረፈድነው ሰዓት አይቆጠርልንም፡፡ 

የሐምሌን ደመወዝ ራሱ ‘ከባንክ ተበደሩና ውሰዱ እኛ እንከፍላን’ ነበር ያሉን፡፡ የሐምሌ ደመወዛችን ባለመፈጸሙ አቢሲኒያ ብድር ገብተናል፡ ግን እስካሁን እለተከፈለንም፡፡ 

የነሐሴ ወር ደመወዝ ደግሞ 20 ፐርሰንት ተቀንሶ ነው የገባው፡፡ ቀሪውን ራሱ እስካሁን አልሰጡንም፡፡ የመስከረም ደግሞ ጥቅምት 20 ነው የተከፈለን፡፡ ይህ ባለበት ሁኔታ አሁን ደግሞ ደመወዛችን ከግማሽ በታች ተቆርጦ ነው የገባው፡፡ 

ከ10 ሺሕ ብር እስከ 3,000 ብር ነው የተቆረጠብን፡፡ ይህ ሲደረግ ምንም አይነት ማስጠንቀቂያ አናውቅም፡፡ ብቻ ደመወዛችን ሲገባ ግን ተቆርጧል፡፡ ስንናገርም ‘ከፈለጋችሁ ውጡ ከፈለጋችሁ ተቀመጡ’ ነው የምንባለው።

ድርጊቱ ከአቅማችን በላይ ሆኗል። እስከ ሰባት ዓመት የሰሩ ጓደኞቻችንን ‘እንዳትመጡ’ ብለዋቸዋል። አንዷ ወር ሙሉ የሠራችበት ተቆርጦ 1,000 ሺሕ ብር ነው የገባላት ከ10 ሺሕ ብር ደመወዟ። ‘ምን ታመጣላችሁ ብትፈልጉ ውጡ’ ነው የሚሉት።

ሰው ለመቀነስ ፈልገው ከሆነ እንኳ በአግባቡ ምክንያቱ ተጠቅሶ፣ ደብዳቤ ተፅፎ፣ ለሠራተኛው የሚገባው ሁሉ ተሰጥቶ ነው የሚሆነው። ከዚህ ግን ማናጀሩ ‘ኑ’ ብሎ ‘ካሁን ወዲያ እንዳትመጡ’ ነው የሚለው
" ብለዋል።

የሌሎች ደመወዝ በትክክል እየተፈጸመ ከሆነ የእናንተ ለብቻው ለምን በወቅቱና ሳይቆረጥ አልተፈጸመም? ምን የተለዬ ምክንያት ኖሮ ነው የእናንተ ብቻ እንዲህ የተደረገው? በሚል ላቀረብነው  ጥያቄ ምላሻቸው፣ " እነርሱ የሚሉት ‘አቴንዳንስ በትክክል አልፈረማችሁም’ ነው፡፡ ግን ሰዓት አልፎም ቢሆን ፈርመናል " የሚል ነው።

“ ደመወዝ ሊቆረጥ የሚችለው በተሸረረፈው ሰዓት ነው፡፡ ሦስት ቀን ያልፈረመ የአንድ ቀን ይቆረጣል ነው የሚለው ሕጉ” ሲሉ አክለው፣ " እኛ ግን ለምሳሌ 4 ሰዓት ገብተን ቢሮ ውለን የሙሉ ቀን ደመዝ ነው የሚቆረጥብን " ብለዋል።

ቅሬታው ያላቸው 14 ሰዎች እንደሆኑ፣ ከድርጅቱ ደመወዝ ያልተቆረጠባቸው አራት ወይም አምስት ሰዎች እንደሆኑ አስረድተው፣ ድርጅቱ በአግባቡ እንዲያስተዳድራቸው ጠይቀዋል። 

ሠራተኞቹ ያቀረቡትን ቅሬታ በመንገር እውነት ነው ? ከሆነ ለምን እንደህ ተደረገ ? ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ የጠየቃቸው የናሁ ቴሌቪዥን አስተዳደር አቶ ኢዶሳ ቀጀላ፣ " ጥሩ ቅሬታ ነው። ድርጅቱ ደመወዝ የሚከፍለው ብር ሲኖር ነው " የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

የድርጅቱ አስተዳደር አክለው ምን አሉ ?

" ብዙ ነገሮች ኪሳራ ላይ ስለጣሉን ብዙ ክፍያ ውጪ ላይ ስለሚያዝብንና ከከስተመሮቻችን ጋር ያሉትን ሴልሶች ቶሎ ኮሌክት ለማድረግ ስለማንችል/ ስለምንቸገር ደመወዝ ቆይተን ልንከፍል እንችላለን።

አንደኛ ደመወዝ ይቆያል። ሁለተኛ ደግሞ በአግባቡ ሥራ ያልገቡ ሰዎችን አቴንዳንሳቸው ኮሌክት ተደርጎ ይገባና ስንት ቀን ሥራ ገብተዋል? ተብሎ ነው ደመወዝ የሚከፈለው።

አሁን ‘ደመወዝ በአግባቡ አልተከፈለንም፣ ተቆረጠ’ የሚሉ ሠራተኞች በወር ውስጥ ስንት ቀን ገብተው እንደፈረሙ አቴንዳንሳቸው ታይቶ ነው ደመወዝ የተከፈላቸው እንጂ ሠራተኞች ስለሆኑ ብቻ 30 ቀናት ታስቦ አይሰጥም።

ስለዚህ የተቆረጠባቸው ሰዎች አሉ። እነርሱም በአግባቡ ያልገቡና አቴንዳንስ ያልፈረሙ ለድርጅቱ ሥራ ያልሰሩ ሰዎች ናቸው " ሲሉ ተናግረዋል።

ደመወዝ ሊቆረጥባቸው የሚገባው በሸራረፉት ሰዓት ሆኖ እያለ ሰዓት አሳልፈው ቢሮ ቢገቡም የሙሉ ቀን መቆረጡ ቅር እንዳሰኛቸው ሠራተኞቹ ገልጸዋል፤ ይህን ማድረጉ አግባብ ነው? ስንል ላቀረበው ጥያቄም ምላሽ ሰጥተዋል።

ምን አሉ ?

"አንድ ሠራተኛ ድርጅቱ በሚያውቀው መልክ ነው ገብቶ የሚወጣው እንጂ ሥራ ስለሌለ 4 ሰዓት መግባት የለም። 

የቢሮ መግቢያ ሰዓት ከ2፡30 ይጀምራል። እስከ 3፡30 እኛ እዚያ እንቆያለን አቴንዳንስ ከዚያ በኋላ ይነሳል” ያሉት የድርጅቱ አሰሰተዳዳሪ፣ “እስከ 4 ሰዓት ያልገባ ሠራተኛ ገብቶ እንዲሰራ አንፈልግም፤ አንፈቅድም።

አጋጣሚ ሆኖ ችግር ካጋጠመ ደውሎ ማሳወቅ፣ ማስፈቀድ ይኖርበታል። እንደዚህ የሚያደርጉ ሠራተኞች በጥሩ ትራት ይደረጋሉ። 

እንደፈለጉ ለሚገቡና ለሚወጡ ሠራተኞች ደመወዛቸውንም አንከፍልም፤ እሱም ብቻ ሳይሆን አስተዳደራዊ እርምጃም እንወስድባቸዋለን። ይህን ሕጉም ስርዓቱም ይፈቅዳል”
በማለት ነው የመለሱት።

ድርጅቱ ሠራተኛ ለመቀነስ ፈልጎም ከሆነ በደብዳቤ እንጅ ‘ውጡ’ ተብሎ “ተጥላልተን” መሆን የለበትም የሚል ቅሬታ ሠራተኞቹ አላቸው፤ ይህን ማድረግስ ለምን አስፈለገ? በሚል ቲክቫህ ላቀረበው ጥየያቄ፣ “ይህን አላደረግነውም” የሚል አጭር ምላሽ ሰጥተዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" አውሮፓና አሜሪካ ዜጎችን ለሥራ ለማሰማራት ለየትኛውም አካል የተሰጠ ውክልና የለም " - ሚኒስቴሩ

" ካናዳን ጨምሮ በተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት ለሥራ ዜጎችን እንልካለን፡፡ ለዚህም ከሚመለከታቸው አካላት ፍቃድ አግኝተናል " በሚል በተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ገጾች ህገ-ወጥ ማስታወቂያዎች እየተላለፉ እንደሆነ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አሳውቋል።

እየተለለፉ ባሉት ህገ-ወጥ ማስታወቂያዎች ህብረተሰቡ ላላስፈላጊ ወጪና እንግልት እየተዳረገ መሆኑን አመልክቷል።

በመሆኑ " መሰል የማጭበርበር ተግባር እየፈፀሙ የሚገኙ አካላትን በህግ ተጠያቂ ለማድረግ እየሰራሁ ነው " ብሏል።

በውጭ ሀገር ስራ ስምሪቱ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ወደ አውሮፓና አሜሪካ ዜጎችን ለሥራ ለማሰማራት ለየትኛውም አካል የሰጠው ውክልና የሌለ መሆኑን አሳውቋል።

ሚኒስቴሩ ፥ " ዜጎች በስምሪቱ ተጠቃሚ ለመሆን ህጋዊ አማራጮችን ብቻ በመጠቀም ካላስፈላጊ ወጪ፣ እንግልትና ሌሎች አስከፊ አደጋዎች ራሳቸውን እንዲጠብቁ በጥብቅ እናሳስባለን " ብሏል።

የሁለትየሽ ስምምነት የተፈረመባቸው መዳረሻ ሀገራት በ lmis.gov.et ላይ መመልከት እንደሚቻል ገልጿል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#DDR " ትጥቅ መፍታት መሸነፍ ፣ መዋረድ ወይም ራስን ዝቅ ማድረግ ማለት አይደለም። ትጥቅ መፍታት ማለት የሀገር አንድነትና ሰላም በፅኑ መሰረት ላይ ከማቆም አንፃር መታየት አለበት " - የኢፌዴሪ ሀገር መከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ ወታደራዊ አመራር  የመጀመሪያ ዙር የትግራይ የቀድሞ ተዋጊዎችን ዲሞቢላይዝድ በማድረግ ወደ  ተሃድሶ ስልጠና ማዕከላት የማስገባት ስራ በይፋዊ ስነስርዓት ተጀምሯል። ዛሬ…
#Update

" ተገደን እንጂ ወደን የገባነው ጦርነት የለም ፤ በDDR አሰራር ወደ ህዝባችን ለመቀላቀል ፍቃደኞች ነን ሁሌም ምርጫችን ሰላም ነው " - ተመላሽ ታጣቂዎች 

የብሄራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን የዲሞብላይዜሽን  እና መልሶ ማቋቋምያ ስነ-ሰርዓት በትግራይ መቐለ በይፋ ተጀምሯል።

ቅዳሜ ህዳር 14/2017 ዓ.ም በይፋ በተከናወነው የዲሞብላይዜሽን እና መልሶ ማቋቋምያ የማስጀመሪያ ስነ-ስርዓተ የክልሉ እና የፌደራል ከፍተኛ የስራ ኋላፊዎች ተገኝተው ነበር።

የብሄራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን በDDR የሚታቀፉ የትግራይን ጨምሮ በስድስት የሀገሪቱ ክልሎች የሚገኙ ከ600 ሺህ በላይ  ታጣቂዎች በሁለት ዓመት ውስጥ ዴሞብላይዝ በማድረግ  ወደ ህዝቡ እንዲቀላቀሉ አቅዶ እየሰራ እንደሆነ በማስጀመሪያ ስነ-ስርዓቱ ተገልጿል።

የብሄራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ኮሚሽነር ተመስገን ጥላሁን ምን አሉ ?

ትጥቅ መፍታትና ዴሞብላይዜሽን (DDR)  ከፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነቶች ዋነኛ እና ጎልቶ የሚጠቀስ ነጥብ ቢሆንም በሃብት እጦት ምክንያት መዘግየቱ ተናግረዋል።

በትግራይ ጦርነት የተሳተፉ 274,800 ታጣቂዎች በDDR ዴሞብላይዝ ሆነው በሁለት ዓመት ውስጥ ወደ ህዝብ ይቀላቀላሉ ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ ፦
👉 በአንድኛ ዙር 75 ሺህ 
👉 በሁለተኛ 100 ሺህ
👉 በሦስታና ዙር 53 ሺህ 800 
👉 በአራተኛ ዙር 46 ሺህ እንደሆነ አብራርተዋል።

በተካሄደው እጅግ አሰቃቂ ደም አፋሳሽ ጦርነት " በርካታ ህይወት ተቀጥፈዋል ፣ አካል ጎድሏል የሀገር እና የህዝብ ሃብት ወድመዋል " ያሉት አቶ ተመስገን ይህ እንዳይደገም እንደ ሀገር እና ህዝብ በቁርጠኝነት መስራት አለብን ሲሉ በአፅንኦት ተናግረዋል።

የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜዳን ጌታቸው ረዳ ምን አሉ ?

DDR ቀድሞ መደረግ የነበረበት ቢሆንም፤ ለፕሮጀክቱ ማስፈፀሚያ የሚሆን ሃብት ለማሰባሰብ ነው የዘገየው ፤ የዘገየም ቢሆን ዛሬ መጀመሩ ለሰላም ያለው ትርጉም ትልቅ ነው ብለዋል።

ተፈናቃዮች ባልተለመለሱበት፣ የትግራይ ሉኣላዊ ግዛቶች ከፌደራል የሀገር መከላከያ ሰራዊት ውጭ ባሉ የሀገር ውስጥና የውጭ ታጣቂዎች ተይዞ ባለበት ወቅት DDR መጀመሩ ከስጋት ወጪ ሆኖ እየተፈፀመ ባይሆንም ሁኔታዎች እየተስተካከሉ ይሄዳሉ ከሚል ተስፋ ድጋፋችን መስጠት እንቀጥላለን ሲሉ ገልጸዋል።

የDDR መተግበር የትግራይ ሰላም መቀጠል ከሀገር ሰላም መፅናት ተያይዞ መታየትና መፈፀም እንዳለበት የፌደራል መንግስት እና ለጋሾች ትኩረት አደርገው ደጋፋቸው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅብረዋል።
 
የተሰናባች ታጣቂዎች ተወካይ ነጋሽ  ገ/ዮሃንሰ ምን አሉ ?

" ተገደን እንጂ ወደን የገባነው ጦርነት የለም ፤ ስለሆነም የነበረው ችግር በጠረጴዛ ውይይት መፍታት ከተቻለ ትጥቅ አንግበን የምንኖርበት ፍላጎት ስለሌለን  በDDR አሰራር ወደ ህዝባችን ለመቀላቀል ፍቃደኞች ነን " ብለዋል።

ታጣቂዎች " የመጀመሪያ እና የመጨረሻ ምርጫችን ሰላም ነው የተሟላ ሰላም እንዲሰፍን አሁንም ከፌደራል የሀገር መከላከያ ሰራዊት ውጪ በትግራይ መሬት ያሉ ታጣቂዎች ለቀው እንዲወጡ ለፌደራል መንግስት እና ለአደራዳሪዎች እንጠይቃለን " ሲሉ ተናግረዋል። 

" ለቀድሞ ታጣቂዎች ለማቋቋምያ የተመደበው በቂ ስላልሆነ ቀጣይ የሆነ ድጋፍ እንሻለን " በማለትም ተናግረዋል።

በመርሃ ግብሩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ (ዶ/ር) ፣ የብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን፣ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳን ጨምሮ ሌሎች የፌዴራልና የክልል አመራሮች ተገኝተው ነበር።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

Photo Credit - DW

@tikvahethiopia 
#SafaricomEthiopia

ለማይቋረጥ የኢንተርኔት ጌም ወሳኙ የማይቋረጥ ኢንተርኔት ነው ፤ አሁኑኑ የሳፋሪኮምን የ4G ዋይ ፋይ ጥቅል ከM-PESA ሳፋሪኮም mini app በመግዛት በጌማችን እንፍታታ!

#MPESASafaricom #FurtherAheadTogether
#DStvEthiopia

⚽️አዲስ ነገር ለኳስ አፍቃሪያን...
👉ከሕዳር 16 ጀምሮ ፈጥነው ወደ ሜዳ ስፖርት ፓኬጅ ከፍ ይበሉ! ሁሉንም የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታዎችን፣ የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ፣ ሎችም ዋና ዋና እግር ኳስ እና ምርጥ ምርጥ መዝናኛዎችን ያካተቱ ከ129 በላይ ቻናሎችን በወር በ1699 ብር ብቻ!

ደንብና ሁኔታዎች ተፈፀሚነት አላቸው! ለበለጠ መረጃ
👇
www.dstv.com/en-et

ደንበኝነትዎን ያራዝሙ!
👇
https://bit.ly/48oVhj8
#ሁሉምያለውእኛጋርነው #MedaSport
TIKVAH-ETHIOPIA
#ጥንቃቄ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ፥ " ዜጎች በሕገ ወጥ ደላሎች ማታለያ ወደ ማይናማር እና ታይላንድ ከመጓዝ ሊታቀቡ ይገባል " ሲል አሳስቧል። ሕገ ወጥ አዘዋዋሪዎች በይነ መረብን በመጠቀም በርካታ ዜጎች ችግር ላይ እንዲወድቁ ማድረጋቸውን  የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው ተናግረዋል። " ዜጎች ባልተረጋገጡ አማላይ ማስታወቂያዎች ጉዳት እየደረሰባቸው ነው " ብለዋል። "…
#ማይናማር🚨

🔴 “ አምልጠን እንኳ ብንወጣ ያመለጠውን ኢትዮጵያዊ ለሚይዙ 500 ዶላር ይከፈላቸዋል። ” -ኢትዮጵያዊያን በማይናማር

🔵 “ ደብድበውት ራሱን አያውቅም ወጣቶች ተሸክመው ሆስፒታል ሲወስዱት የውጪ ዜጋ አናክምም ብለው መለሱት ” - በእንባ የታጀቡ እናት

ሰርተን እንለወጣለን፣ ቤተሰብም እንለውጣለን ብለው ከአገር የወጡ በርካታ ኢትዮጵያዊያን በማይናማር በስቃይ ውስጥ መሆናቸው ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ መገለጻችን አይዘነጋም።

ኢትዮጵያዊያኑ ከሀገር ሲወጡ የተነገራቸውና አሁን ያሉበት ሁኔታ የማይገናኝ ነው።

ጉልበታቸው እየተበዘበዘ ከሆኑም ባሻገር የሚፈጸምባቸው ድብደባና የአካል ጉዳት አሰቃቂ መሆኑን የገፈቱ ቀማሾች ከዚህ ቀደም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸው ነበር።

የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር በበኩሉ፣ ኢትዮጵያዊያኑን ወደ አገራቸው ለመመለስ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየተየጋገረ መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መግለጹ ይታወሳል።

የኢትዮጵያዊያኖቹ ጉዳይ አሁንስ ከምን ደረሰ ?

በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ፣ ያገቷቸው አካላት ካሉበት አገር መንግስት ጋር ያላቸውን ግንኙት…በተመለከተ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ማብራሪያ የጠየቃቸው በማይናማር የሚገኙት ኢትዮጵያዊያን፣ በጣም በከፋ ሁኔታ ውስጥ መሆናቸውን በሀዘን ስሜት ገልጸው፣ የመንግስትን እርዳታ ጠይቀዋል።

በዝርዝር ምን አሉ ?

“ የኢትዮጵያ መንግስት ሙሉ ኃላፊነት ወስዶ ከረዳን ብቻ ነው መውጣት የሚቻለው። የሌሎች አገራት እንዳደረጉት።  ነገር ግን የተባልነው ነገር የለም እስካሁን በስቃይ ላይ ነን።

ያለንበት አገር ብዙም የተጠናከረ መንግስት የለውም። እንደሚታወቀው ወታደራዊ መንግስት ነውና። መንግስት ከመንግስት ጋር ተነጋግሮ ሊያስወጣን ከቻለ ብቻ ነው እንጂ።

እንወጣለን በሚል ተስፋ እያደረግን፣ እያለምን ነው እንጂ እስካሁን ምንም የተባልነው ነገር የለም። የኢትዮጵያ መንግስት ጫና ካላደረገ በስተቀር የያዙን ሽፍታዎችና የአገሪቱ መንግስት በጥቅም የተሳሰሩ ናቸውና መውጣት ይከብዳል።

አምልጠን እንኳ ብንወጣ ያመለጠውን ኢትዮጵያዊ ለሚይዙ 500 ዶላር ይከፈላቸዋል። ስለዚህ ተሳክቶልን ብናመልጥ እንኳ የአካባቢው ማህበረሰብ ይዞ አሳልፎ ይሰጠናል።

ሽፍቶቹ በቁጥር ብዙ ባይሆኑም መመሪያ የተሰጣቸው ናቸው። በዬቦታው ተሰራጭተው ነው የሚጠብቁት። ከእገታ ቦታው ወጣ ብለው በእስናይፐር የሚጠብቀ አሉ። በቁጥር ትንሽ ቢሆኑም የተጠናከረ ጥበቃ ላይ ያሉ ሽፍቶች ናቸው የያዙን።

የሚያሰሩን ቻይያዎች ናቸው። ያለነው ማይናማር ነው። ዜጎቹ ግን የቻይና ናቸው። ከአገሪቱ መንግስት ጋር በጥቅም የተሳሰሩ ናቸው። ለዚሁ መንግስት ግብር ይከፍላሁና ነገሩን ከባድ ያደረገው ከመንግስት ጋር የተያያዙ መሆናቸው ነው።

ወታደራዊ መንግስት ነው ያለው። ስለዚህ ከእኛ ከሚሰበሰው ገቢ ውስጥ ለመንግስት ይከፈላል። ለዛም ነው ሽፍቶቹ ደኀንነታቸው ተጠብቆ ሙሉ ድፍረት አግኝተው የሚሰሩት። የሕግ ከለላም አላቸው ነገሩ የተሳሰረ ነው። አጠቃላይ የአገራቱ መንግስት ሁኔታውን ሁሉ ያውቃል።

በስልክ እየደወልን ቤተሰብን ከመጠየቅ በስተቀር የኢትዮጵያ መንግስት ስለመውጣታችን እንዲህ ነው ያለን የሰማነው ነገር የለም። እባካችሁ በሕይወት ድረሱልን ”
ሲሉ ተማጽነዋል።
 
ልጆቻቸው፣ የትዳር አጋሮቻቸው፣ እህትና ወንድሞቻቸው በማይናማር በከፋ ሁኔታ የሚገኙ ቤተሰቦች በበኩላቸው፣ ለወራት በከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ እንደሆኑ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ልጃቸው የታገተባቸው አንዲት እናት እያለቀሱ በሰጡን ቃል፣ “ እኛም በጭንቀት ተሰቃዬን እንዴት አድርጌ እንደምገልጽ አላውቅም ” ሲሉ ጭንቀታቸውን አጋርተዋል። 

እኝሁ እናት አክለው ፦

“ ደብድበውት ራሱን አያውቅም ወጣቶች ተሸክመው ሆስፒታል ቢወስዱት 'የውጪ አገር ዜጋ አናክምም ' ብለው መለሱት።

እንደ ዜጋ መንግስት በዚህ ጉዳይ ላይ ጣልቃ መግባት ሲገባው ‘የራሳቸው ጉዳይ’ የተባለ ነው የሚመስለው። በጣም ያሳዝናል ለመናገር በጣም ነው የሚቸግረኝ።

እንደ ወላድ ይጨንቃል። ተቸግረን አሳድገን እንዲህ ሲሆኑ። እንደ ሀገር እኛ ከኡጋንዳ ሀገር በታች ነው እንዴ የኛ ሀገር መንግስት ! እንዲያው ጆሮ ዳባ ብለውን ነው እንጂ።

ስቲል ይሄዳሉ ልጆች ወደ ውጪ አገር። አምባሳደሩን ገብተን የውጪ ጉዳይ ቆንጽላ ጽህፈት ቤት ተሰባስበን አነጋግረን ነበር ከ15 ቀናት በፊት። 

ልጆቻችን አካለ ጎደሎ እየሆኑ፣ በሥነ ልቦና እየተሰቃዩ፣ እየተጎዱ ነው ዳግም ሌላ ወጣት እንዳይሄድ ስንል ‘የመንቀሳቀስ መብትን መንፈግ ነው የሚሆነው እኛ እንዴት ብለን እናሳግዳለን ?’ ነው ያሉን ”
ሲሉ ገልጸዋል።

ገና የ8 ወር ልጅ ይዘው የቀሩ የትዳር አጋራቸው በማይናማር እንደታገተባቸው የገለጹ ሌላኛዋ እናት በበኩላቸው፣ ባለቤታቸው በከፋ ሁኔታ እንደሚገኝ፣ ልጅ አዝለው ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ድረስ ቢሄዱም አጥጋቢ ምላሽ እንዳላገኙ ተናግረዋል።

በዝርዝር ምን አሉ ?

“ ባለቤቴ ማይናማር በስቃይ ውሰጥ ነው። ከሄደ 5 ወራት አስቆጥሯል። ‘የሥራ እድል አለ’ ተብሎ በደላሎች አማካኝነት ነበር ወደ ታይላንድ የሄደው። በሙያው ሐኪም ነው። ከሄደ በኋላ ግን ታይላንድ አይደለም የቀረው ወደ ማይናማር ነው የወሰዱት።

ያለበት ሁኔታ በጣም ከባድ ነው። የጨለማ ክፍል የሚባል አለ፤ ድብደባ አለ። በነገረኝ መሠረት አሰቃቂ ሁኔታ ነው። እኔም መፍትሄ ፍለጋ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ልጅ አዝዬ ጭምር ብዙ ጊዜ ተመላልሻለሁ። 

የሚሰጠኝ ምላሽ በራሳቸው ፍላጎት እንደሄዱ፣ በሕገወጥ መንገድ እንደሄዱ ነው። ከሦስት ቀናት በፊትም ሂጀ ነበርና ከታች ያሉት የቀረበውን ቅሬታ ካሳወቁ ከ10 ወራት በላይ እንዳስቆጠረ፣ ግን መፍትሄ እንዳልተገኘለት ነው የነገሩኝ።

‘ ከላይ ያሉት አካላት ናቸው መስራት ያለባቸው ’ ነው ያሉኝ። ጥሩ መልስ የሰጠን የኤምባሲ አካል ግን አላገኘንም። ቤተሰቡ በጭንቀት ውስጥ ነው ያለው። ባለቤቴ ከሄደ በኋላ ኑሮው ከብዶኛል።

ስለእርሱ መጨነቁ፣ የኑሮ ውድነቱ ተደራረቡብኝ። የባለቤቴ ደመወዝ ተቋርጧል። አዲስ አበባ ከተማ ላይ ብቻዬን ልጅ እያሳደኩ ስቃይ ላይ ነኝ።

የኢትዮጵያ መንግስት በደንብ ትኩረት ሰጥቶ ቢሰራበት የማይናማር መንግስት ሊለቃቸው እንደሚችል ባለቤቴ ነገሮኛል። ባለቤቴ ጋር የነበሩ የህንድ አገር ዜጎች ወጥተዋል። መንግስት መፍትሄ ይስጠን ”
ሲሉ ተማጽነዋል።

ማይናማር ውስጥ የሚገኙ የታጋች ኢትዮጵያዊያኑ ወላጅች ያቋቋሙት ኮሚቴ በበኩሉ፣ መፍትሄ እየጠየቀ መሆኑን የገለጸ ሲሆን፣ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ምን እየሰራ እንሆነ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ከሰጠው ምላሽ ጋር በቀጣይ ይቀርባል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ማይናማር🚨 🔴 “ አምልጠን እንኳ ብንወጣ ያመለጠውን ኢትዮጵያዊ ለሚይዙ 500 ዶላር ይከፈላቸዋል። ” -ኢትዮጵያዊያን በማይናማር 🔵 “ ደብድበውት ራሱን አያውቅም ወጣቶች ተሸክመው ሆስፒታል ሲወስዱት የውጪ ዜጋ አናክምም ብለው መለሱት ” - በእንባ የታጀቡ እናት ሰርተን እንለወጣለን፣ ቤተሰብም እንለውጣለን ብለው ከአገር የወጡ በርካታ ኢትዮጵያዊያን በማይናማር በስቃይ ውስጥ መሆናቸው ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ…
#ማይናማር🚨

🔴 “ ልጆቻችን በስቃይ ውስጥ ነው ያሉት። መንግስት አንድ መፍትሄ ይፍጠርልን ” - የወላጆች ኮሚቴ

🔵 “ ከአገራቱ ጋር የስራ ሥምሪት ስምምነት ባለመኖሩ፣ ሰዎቹም ያቀኑት በህገ ወጥ መንገድ በመሆኑ ያሉበት ቦታና ቁጥራቸውን በትክክል ለማወቅ አስቸጋሪ ሆኗል ” - ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር

ማይናማር የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ወላጆች ኮሚቴ አዋቅረው የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ልጆቻቸው ካሉበት አስከፊ ሁኔታ እንዲያወጣላቸው እየጠየቁ ቢሆንም እስካሁን ልጆቻቸው ወደ አገር ባለመመለሳቸው ጥልቅ ጭንቀት ላይ መሆናቸውን በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል ተናግረዋል።

መንግስት ለጉዳዩ ይበልጥ ትኩረት እንዲሰጥም በአጽንኦት ጠይቀዋል።

የኮሚቴው በዝርዝር ምን አለ ?

“ ልጆቻችን አሁንም እየተገረፉ፤ እየተደበደቡ ነው። 18 ሰዓት እያሰሯቸው ነው። ጭራሽ ገንዘብ ካልገባና አጨበርብረው ብር ካላመጡ 24 ሰዓት ሙሉ ኮምፑዩተር ላይ ቁጭ ስለሚያደርጓቸው ፌንት እየነቀሉ የሚወድቁበት ሁኔታ አለ።

ልጆቻችን በስቃይ ውስጥ ነው ያሉት። መንግስት አንድ መፍትሄ ይፍጠርልን። በአካባቢው ያሉ ዲፕሎማቶች እንዲሰሩ የሚያሳስብ ነው የኛ ማመልከቻ።

ታግተው ካሉት ውስጥ 2 ሴት ወጣቶች መለቀቃቸውን ብቻ ነው የማውቀው። እኛ ወደ 153 ወጣቶችን ዝርዝር ነው ይዘን ወደ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር እየሄድን ያለው። 

ከእነዛ ውስጥ ወደ 2 ሴቶች ብቻ ናቸው የወጡት። በመንግስት በኩል ወደ 31 ወጣቶች ወጥተዋል የሚል ዜና ነው ያየነው። በተጨባጭ የወጡትን ልጆች አላየናቸውም።

ይሄው 11ኛ ወራችን ነው በማመልከቻ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር መመላለስ ከጀመርን እካሁን ጠብ ያለ መፍትሄ የለም። ከ3,000 በላይ ኢትዮጵያን ናቸው እዛ እየተሰቃዩ ያሉት።

በስቃይ ላይ የሚገኙት ቢያንስ ከመጀመሪያ ድግሪ በላይ የትምህርት ደረጃ ያላቸው ልጆች ናቸው። ይሄ ለቤተሰብ ብቻ ሳይሆን ለአገርም ኪሳራ ነው። ለኛም ትልቅ ጭንቀት ነው ሆኖብን ያለው ” ብሏል።

የኢትዮጵያ ውጪ ጉዳይ ሚኒስትርን እየተመላለሳችሁ እየጠየቃችሁ ከሆነ ምን ምላሽ ሰጣችሁ? የሚል ጥያቄ ያቀሰብንለት ኮሚቴው፣ “ ‘ለተወካዮች እናሳውቃለን በዛ በኩል ነው መታዬት ያለበት፤ ቶኪዮ ያለው ነው ማይናማርን የሚመለከተው’ የሚል መልስ የሚሰጡን ” ብሏል።

በማይናማር ስለሚገኙ ኢትዮጵያዊያንና ቤተሰቦቻቸው ዜጎቹ በስቃይ ውስጥ እንደሆኑ፣ ለዚህም መንግስት መፍትሄ እንዲሰጣቸው እየተማጸኑ እንደሆነ በመግለጽ፣ ምን እየሰራ ነው ? ጉዳዩ ተስፋ አለው ? ስንል የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴርን ጠይቀናል።

የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው በበኩላቸው ተከታዩን አጭር ምላሽ ሰጥተዋል።

አምባደር ነብያት ጌታቸው ፦

“ ባለፈው ሳምንት መግለጫ ሰጥተን ነበር። በዛ ላይ እስከ ባለፈው ሳምነት መጨረሻ ያሉ ደቨሎፕመንቶችን ነው ያቀረብነው። 

ከዚያ ወዲህ የክትትል ሥራ ነው የተሰራው ቶኪዮ ያለው ኤምባሲያችን ከማይናማር መንግስት አካላት ጋር በዚህ ሳምነት ውስጥ ክትትል እንደተደረገ ተገልጾልናል። እስካሁን ያለው ሂደት እዚህ ላይ ነው ያለው።


እስካሁን በተደረገ ጥረት 31 ዜጎቻችን ከነበሩበት አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ወጥተው ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ማድረግ ተችሏል።

ከአገራቱ ጋር የስራ ሥምሪት ስምምነት ባለመኖሩ እና ሰዎቹም ያቀኑት በህገ ወጥ መንገድ በመሆኑ ያሉበት ቦታ እና ቁጥራቸውን በትክክል ለማወቅ አስቸጋሪ ሆኗል።

መንግሥት ለዜጋ ተኮር ቅድሚያ ትኩረት ስለሚሰጥ ጥረቱን አጠናክሮ ይቀጥላል።

አሁንም ህብረተሰባችን ከህገ ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎችና ህገ ወጥ ጉዞ ራሱንና ልጆቹን መጠበቅ አለበት።

መገናኛ ብዙኃንም ይህን ጉዳይ ልዩ ትኩረት ሰጥተው መስራት ይገባል። ዜጎቻችን የህገ ወጥ ሰዎች አዘዋዋሪዎች ሰለባ መሆን የለባቸውም ”
ብለዋል።

ቤተሰቦቻቸው በጣም ተጨንቀው እያለቀሱ ነው። ታጋቾቹም አብረዋቸው የነበሩ የሌሎች አገራት እየተለቀቁ ስለሆነ የኢትዮጵያ መንግስትም ጫና ቢያደርግ የመውጣት እድል እንዳላቸው እየገለጹ ነው፤ እንዲያው ሚኒስቴር መስሪያ ቤትዎ ምን ያህል ጥረት አድርጓል ? ስንል ለአምባሳደሩ ጥያቄ አቅርበናል።

አምባሳደር ነብያት ፤ “ ከአገራቱ ጋር የሥራ ስምሪት ስምምነት ያለበት ቦታ አይደለም። ሰዎቹም የሄዱት ሕገ ወጥ በሆነ መንገድ ነው። ያሉበትን ቦታና ቁጥራቸውን ራሱ በትክክል ለማወቅ እጅግ አዳጋች ነው ” ብለዋል።

“ የማይናማር መንግስት ከሚቆጣጠረው አካባቢም ያሉ አይደሉም ለዛነው ችግሩ እጅግ አስቸጋሪ የሆነው ” ሲሉ አክለዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ትግራይ

" ' ተቀምተናል ' የሚሉትን ስልጣን ለማስመለስ ስም ከማጥፋት ባለፈ እስከ ፕሬዜዳንት መቀየር ያለመ አደገኛ እንቅስቃሴ እየተካሄደ ነው "  - ፕረዚደንት አቶ ጌታቸው ረዳ 

ዛሬ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ በወቅታዊ የፀጥታ እና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ መግለጫ ሰጥተው ነበር።

በዚህም ወቅት አቶ ጌታቸው ፥ " የህዝብ ጥቅም ማእከል አድርጎ በሚንቀሳቀስ የፓለቲካ ፓርቲ ውስጥ ለግሉ ጥቅም ብቻ የሚያስብ አመራር ከተፈጠረ ረጅም ጊዜ ሆኗል " ብለዋል።

" ' ስልጣን ለኛ ነው የሚገባው ' የሚሉ የህዝብ አጀንዳ በማፈን ፍላጎታቸው ለማሳካት የግጭትና የግርግር መልእክቶች በማስተላለፍ ላይ ይገኛሉ " ሲሉም ገልጸዋል።

እነዚህን አካላት በስም አልጠቀሷቸውም።

ፕሬዜዳንቱ በስም ያልገለፁዋቸው አካላት " ተቀምተናል " የሚሉት ስልጣን ለማስመለስ ስም ከማጥፋት ባለፈ እስከ ፕሬዜዳንት መቀየር ያለመ አደገኛ እንቅስቃሴ እያካሄዱ እንደሆነ አመላክተዋል። 

" ትኩረታችን የትግራይ ህዝብ መሆን ይገባ ነበር " ያሉት ፕሬዜዳንቱ " ለወንበር ሲባል የጊዚያዊ አስተዳደሩ ስራዎች የማደናቅፍ ስራዎች ተባብሰው ቀጥለዋል " ሲሉ ገልፀዋል። 

" ' ሰራዊት ከኛ ጎን ነው ' በማለት የግለሰቦችን ስልጣን ለማርካት ታስቦ የፀጥታ ሃይል ለመከፋፈል አልሞ እየተሰራ ነው " ሲሉም አክለዋል። 

አቶ ጌታቸው ፥ " በትግራይ ሁሉንም ነገር በብቸኝነት ተቆጣጥሮ የቆየ ሃይል አሁንም የፀጥታ ሃይል ፤ ሚድያ ተቆጣጥሮ በለመደው መንገድ በመሄድ የግል ጥቅሙን ለማረጋገጥ ጠላት ከሚለው እየተደራደረ ይገኛል " ብለዋብ።

" ጠላት " ያሉትን ሃይል በስም አልገለፁም። 

የም/ ቤት አባላት በማንሳት የአስተዳዳሪዎች ስልጣን እንዲለወጥ መስራት መፈንቅለ መንግስት ነው ያሉት አቶ ጌታቸው " መንግስትን ለማፍረስ የሚደረጉ መድረኮች በመንግስት በጀት ነው የሚካሄዱት " ሲሉ ተግባሩን ኮንነዋል።

" ' የፀጥታ ሃይል ከኛ ነው ' የሚለው አነጋገር የፀጥታ ሃይሉን በመጠቀም ' ከስልጣን እናስወግዳችኋለን ' የሚል መልእክት ለማስተላለፍ ተፈልጎ የሚሰራ ነው " ሲሉም ተናግረዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

ፎቶ፦ DW

@tikvahethiopia 
#SafaricomEthiopia

💫ከዳር እስከ ዳር አስተማማኙን ኔትወርካችንን እያሰፋን ወደ እናንተ እየቀረብን ነው!🙌👏ከአስተማማኙ ኔትወርካችን ጋር አሁንም በአብሮነት ወደፊት!

አስተማማኙን ኔትወርክ ዛሬውኑ እንቀላቀል!

የቴሌግራም ቦታችንን https://t.iss.one/official_safaricomet_bot በመጠቀም የአየር ሰዓት ወይንም ልዩ ልዩ ጥቅሎችን እንግዛ!

#MPESASafaricom #1Wedefit
#Furtheraheadtogether
#ሴጅ_ማሰልጠኛ

የግራፊክ ዲዛይን፣ ቪዲዮ ኢዲቲንግ፣ ሞሽን ግራፊክ እና ዲጂታል ማርኬቲንግ ስልጠና በፒያሣ እና መገናኛ ካምፓስ ሰኞ ህዳር 23/2017 ዓ.ም ይጀምራል። 
👉 100% በተግባር የተደገፈ ስልጠና
👉 Advanced Graphics + Video Editing + Motion Graphics + Digital Marketing በአንድ ላይ
👉 ከ50 በላይ ፕሮጀክቶች ያሉት
👉 የሥራ ላይ ስልጠና (Internship) የተመቻቸለት
ስልክ ፦ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ፦ ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ እና ቁ.2 መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ

Telegram: https://t.iss.one/sagetraininginstitute
Tiktok: https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
Linkedin: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute