TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
🔈#የዜጎችድምጽ ችግሩ ቢነገር ቢነገር መፍትሄ ያልተገኘለት በክልሎች ያለው የቤንዚን ጉዳይ ! በክልል ከተሞች ነዳጅ በተለይም ቤንዚን ማግኘት ፈተና እንደሆነ ቀጥሏል። በርካታ በትራንስፖርት ስራ ላይ የተሰማሩ ወጣቶች ባለው ችግር ምክንያት ሰርቶ መግባት ቤተሰብ ማስተዳደር ከባድ ሆኖባቸዋል። ከክልል ከተሞች አንዷ የሲዳማ መዲናዋ ሀዋሳ ናት። በዚህች ከተማ ነዳጅ እንደልብ ማግኘት ከቆመ ዓመታት አልፈዋል።…
#ቤንዚን🚨

🔴 " በክልሉ የቤንዚን ችግር የፀጥታ ጉዳይ ወደ መሆን ደርሷል " -  የሲዳማ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ

🔵 " በማደያዎች አከባቢ የሚነሱ ሕገ ወጥ ተግባራት ሕብረተሰቡ በመንግስት ላይ እንዲነሳሳ እያደረገ ነዉ " - የሲዳማ ክልል ንግድ ቢሮ


በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በተለይም በመዲናዋ ሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ የመጣዉን ቤንዚን ማግኘት ፈተናን ተከትሎ የተስተዋሉ ችግሮችን በተደጋጋሚ መዘጋባችን ይታወሳል።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር በትላንትናዉ ዕለት በሰጡት መመሪያ፥ በክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ የሚመራ ግብረ-ኃይል ተቋቁሞ ወደ ሥራ ገብቷል።

ግብረ-ኃይሉ በዛሬው ዕለት ሁሉም ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ሰፊ ዉይይት በማድረግ የዉሳኔ ሃሳቦችን ማስተላለፉን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ማወቅ ችሏል።

በዚህም መሰረት በተለያዩ ክልሎች የነዳጅ ምርት እጥረት ቢኖርም በሲዳማ ክልል በተለይም በሀዋሳ ከተማ ያለዉ የህገ-ወጥ ንግድ ህብረተሰቡን ለዘርፈ ብዙ ችግሮች ሲዳርግ መቆየቱ ተጠቅሷል።

በማደያዎች፤ በንግድና ገበያ ልማት ባለሙያዎች ፤ ከፀጥታ አካላት በኩል ያሉ ክፍተቶች በመድረኩ ተነስቷል።

ማደያዎች በሌሊት ለቸርቻሪዎች ከመሸጥ እስከ ነዳጅ ቦቴዎችን መሰወር ድረስ ፤ የንግድና ገበያ ልማት ባለሙያዎች ደግሞ ከሕገ-ወጥ ነጋዴዎች ጋር አብሮ መስራትን ጨምሮ ከማደያ ቀጂዎች ጋር በመመሳጠር ቤንዚን ማሸሽ ድረስ ተሳታፊ ነበሩ ተብሏል።

እንዲሁም የፀጥታ አካላት የሌሎችን ተሽከርካሪዎች የራሳቸዉ በማስመሰል ለህገወጥ ግብይቱ ምክንያት መሆን ጨምሮ ተገቢውን እርምጃ አልወሰዱም የሚል ግምገማም በመድረኩ ቀርቧል።

ግብረ-ኃይሉ ለእነዚህ እና ሌሎችም መሰል ችግሮች የመፍትሔ ኃሳቦች ናቸዉ ያላቸዉን አስቀምጧል።

አቶ አለማየሁ ጢሞቴዎስ የክልሉ ሠላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊና የግብረ-ኃይሉ ሰብሳቢ ምን አሉ ?

በክልሉ የቤንዚን ችግር የፀጥታ ጉዳይ ወደ መሆን ደርሷል ያሉ ሲሆን፥ በዘርፉ አመራሮችና ባለሙያዎች ላይ የተጀመረዉ እርምጃ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ ገልጸዋል።

" መንግስት በከፍተኛ ድጎማ የሚያስገባውን ቤንዚን ማንም ከዚህ በኋላ ለግል መበልፀጊያ  ማድረግ አይችልም ፤ ከዛሬ ጀምሮ የቤንዚ አቅርቦትና ስርጭት ሂደቱን ግብረሃይሉ ይመራዋል " ሲሉ ተናግረዋል።

አክለውም ከዚህ ቀደም ተሽከሪካሪ ተለይቶ ይደለደል የነበረዉ አሰራር ከነገ ጀምሮ አይኖርም ነው ያሉት።

ማደያ ለሌለባቸዉ አከባቢዎች ሲደረግ የነበረዉ አሰራር በሕግና ደንቡ መሠረት ብቻ ይከናወናልም ሲሉ አንስተዋል።

ማንኛዉም የፀጥታ መዋቅር አባላት ያሏቸዉ የቤንዚን ተሽከሪካሪዎች በየተቋሞቻቸዉ ተለይተዉ በሕጋዊ መንገድ በኩፖን ብቻ እንደሚስተናገዱ አቶ አለማየሁ ጢሞቴዎስ ተናግረዋል።

አክለውም " ከነገ ቀን ጀምሮ በቤንዚን ሽያጭ ላይ በክልሉ ሁሉም አከባቢዎች በተለይ ደግሞ ሀዋሳ ከተማ ላይ ይታይ የነበረዉን ሕገ-ወጥ ስርዓት አደብ እናስገዛለን " ብለዋል።

በተጨማሪም ፦

➡️ የፀጥታ መዋቅር አባላት ከየማደያዉ ጣልቃ ገቢነት እንደሚወጡ፤

➡️ ከነገ ጀምሮ ካሜራ ያልገጠሙ ማደያዎች አገልግሎት መስጠት እንደማይችሉ ገልጸዋል።

የክልሉ ንግድ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሰላማዊት መኩሪያ ምን አሉ ?

" በማደያዎች አከባቢ የሚነሱ ህገወጥ ተግባራት ሕብረተሰቡ በመንግስት ላይ እንዲነሳሳ እያደረገ ነዉ " ሲሉ ተናግረዋል።

ኃላፊዋ፥ " እንደ ሀገር የአቅርቦት እጥረት ቢኖርም በሀዋሳ ከተማ በብዛት የሚስተዋለው ግን ሰዉ ሰራሽ ችግር ነዉ ፤ ይህም ችግር ዘርፈ ብዙ መሆኑን በጥናት አረጋግጠናል " ብለዋል።

" መንግስትንና ሕዝብን ለማጣላት የሚሰሩ ማደያዎችን ከድርጊታቸው ካልተቆጠቡ እርምጃው ይቀጥላል፤ ከኤልክትሮንክስ ግብይት ዉጪ ሽያጮችን የሚያካሂዱ ማደያዎችም በሕግ አግባብ ከመጠየቅ ባለፈ የነዳጅ ምርቶችን መግኘት አይችሉም " ሲሉም አስጠንቅቀዋል።

አሁን ላይ ጣት ከመጠቋቆምና አንዱ በሌላዉ ከማማካኘት ይልቅ ሕዝብ በተማረረበት በዚህ የቤንዚን ጉዳይ አስቸኳይ እርምጃ መዉሰድ እንደሚያስፈልግም ወ/ሮ ሠላማዊት መንገሻ በመድረኩ አንስተዋል።

⚠️ከፍተኛ የቤንዚን ችግር ሲዳማ ክልል ውስጥ ብቻ ያለ ሳይሆን ከአዲስ አበባ ውጭ ባሉት ሁሉም ክልሎች ላይ ተመሳሳይ ነው። ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ዜጎች ስራ ሰርተው መግባት መኖር ፤ ቤተሰብ ማስተዳደር ፍጹም አልቻሉም። ህዝቡ እጅግ ተማሯል። ማደያዎች ላይ " የለም " ይባላል ግን በጥቁር ገበያ እስከ 200 ብር ድረስ በግልጽ በአደባባይ ይቸበቸባል። አንዳንድ ከዋና ዋና ከተማ በወጡ ማደያዎች በትውውቅ በሊትር እስከ 200 ብርና ከዛ በላይ ይቸበቸባል። ቤንዚን ለሊት ላይ በድብቅ ከየማደያው እየተጫነ ከከተማ በህገወጥ መንገድ ይወጣል። ይህ ህገወጥ ተግባር መንግሥት እርከን ውስጥ ካሉ አካላት አንስቶ የማደያ ሰዎች፣ የጸጥታ ሰዎች ከላይ እስከ ታች ድረስ ረጅም ሰንሰለት ነው ያለው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የክልሎች የቤንዚን ስርጭትን ጉዳይ አሁንም መከታተሉን ይቀጥላል።

#TIKVAHETHIOPIA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#InfinixEthiopia

የዛንዚባር የቢዝነስ ክላስ ደርሶ መልስ የአውሮፕላን ቲኬት፣ የኢንፊኒክስ ስማርት ቲቪ፣ የኢንፊኒክስ ላፕቶፕ እንዲሁም ሌሎች አጓጊ ሽልማቶችን ኢንፊኒክስ ስማርት ስልኮች የሆኑትን ሆት 40 ፣ ኖት 40 ፣ ዜሮ 40 እና የኢንፊኒክስ ስማርት TVን ሲገበያዩ ኩፖን በመውሰድ አብሮት ካለ ወዳጅ ዘመድ ወይም ጓደኛ ጋር በመረጡት ስፍራ ፎቶ በመነሳት #InfinixEthiopia የሚለውን ሃሽ ታግ በመጠቀም እና ማህበራዊ ሚዲያ ላይ በመለጠፍ ማሸነፍ ይችላሉ ይፍጠኑ የዚህ ልዩ የሽልማት ፕሮግራም አካል ይሁኑ፡፡

1. የኢንፊኒክስ ኢትዮጵያን ፌስ ቡክ ፣ ኢንስታግራም እና ቲክቶክ ገጾችን ፎሎው ያድርጉ፡፡
2. የተነሱትን ፎቶ በመረጡት ማህበራዊ ሚዲያ ሲለጥፉ የኢንፊኒክስ ኢትዮጵያን ገፅ ከፖስቶት ጋር ታግ ያድርጉ፡፡
3. #InfinixEthiopia የሚለውን ሃሽታግ መጠቀሞን አይርሱ፡፡

Tag ሲያደርጉ ለ Facebook @InfinixMobileEthiopia ፣ ለ Instagram @infinixethiopia ለ TikTok @Infinixet እና ለ Telegram @Infinixeth ሜንሽን ማድረግ እንዳይረሱ።
#AddisAbaba

“ አያት 49 ግሎባል ባንክ አካባቢ የጥበቃ ሠራተኛው ሲገደል ጓደኛው ደግሞ ቆስሏል ” - የቲክቫህ ኢትዮጵያ አባል

“ የድርጊቱ ምርመራው ገና አላለቀም ” - የፓሊስ መረጃ ክፍል

በለሚኩራ ክ/ከተማ አያት 49 ተብሎ በሚጠራው አካባቢ አንድ የግሎባል ባንክ የጥበቃ ሠራተኛ በጥይት ተመትቶ መገደሉን በስፍራው ያሉ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ምንጮች ገልጸዋል።

በጥይት የተመታው ጥበቃ ሠራተኛ ጓደኛ እንደቆሰለ አስረድተው፣ ገዳዩና አቁሳዩ በሌላ ብራንች የሚሰራ የጥበቃ ሠራተኛ ሳይሆን እንዳልቀረ ጠቁመዋል።

“ 40/60 ሳይት 3 አያት 49 ግሎባል ባንክ ዘበኛው አሁን በጥይት ተመትቶ ሞተ። ግድያው የተፈጸመው ጠዋት አንድ ሰዓት አካባቢ ነው ” ሲሉ አንዱ የስፍራው ነዋሪ ገልጸዋል።

ሌላኛው ነዋሪ ደግሞ ድርጊቱ የተፈጸመው ዛሬ ጠዋት 1 ሰዓት ገደማ እንደሆነ፣ የግድያውን ምክንያት ግን በግልጽ እንዳላወቁ፣ የተመታው የባንክ የጥበቃ ሠራተኛ መሆኑን ነግረውናል።

የወንጀል ድርጊቱን ሰምተው እንደሁ የጠየቅናቸው የአዲስ አበባ ፓሊስ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ፣ ጉዳዩን እንዳልሰሙ፣ ተፈጽሞ ከሆነ ደግሞ መሰማቱ እንደማይቀር ገልጸዋል።

ኮማንደሩ፣ ጉዳዩን ለማጣራት የፓሊስ መረጃ ክፍል እንዲጠየቅ ያመላከቱ ሲሆን፣ ስለጉዳዩ የጠየቅነው የፓሊስ መረጃ ክፍል ደግሞ ጉዳዩን ካጣሩ በኋላ፣ “ ምርመራው አላለቀም ትንሽ ይጠብቁ አልጨረሱም ገና ” የሚል አጭር ምላሽ ሰጥተዋል።
 
ድርጊቱን ፈጻሚው አካል አልተያዘም እንዴ ? ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ ላቀረበው ጥያቄ፣ “ የድርጊቱ ምርመራው ገና አላለቀም ” ብለው ቀጥተኛ ምላሽ ከመስጠት ተቆጥበዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ጥቆማ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ጥሪ ማስታወቂያ አውጥቷል። ኢትዮጵያ በቀጣይ የካቲት ወር በአፍሪካ ህብረት ጉባኤ የሚሳተፉ እንግዶችን ለመቀበል ዝግጅት እያደረገች ነው። የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከአቀባበል እስከ አሸኛኘት ባለው የመስተንግዶ መርሃግብር በጎ ፍቃደኛ ፕሮቶኮል ካዴቶችን በመቀበል አሰልጥኖ በተለያዩ የፕሮቶኮል ሥራዎች ላይ ማሰማራት እንደሚፈልግ ገልጿል።…
#ማስታወሻ

ምዝገባው ዛሬ ተጀምሯል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ለመስጠት ፍላጎት ያላቸውን ዜጎች ዛሬ መመዝገብ ጀምሯል።

ኢትዮጵያ በቀጣይ የካቲት ወር በአፍሪካ ህብረት ጉባኤ የሚሳተፉ እንግዶችን ለመቀበል ዝግጅት እያደረገች ነው።

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከአቀባበል እስከ አሸኛኘት ባለው የመስተንግዶ መርሃግብር በጎ ፍቃደኛ ፕሮቶኮል ካዴቶችን በመቀበል አሰልጥኖ በተለያዩ የፕሮቶኮል ሥራዎች ላይ ማሰማራት እንደሚፈልግ ገልጿል።

በመሆኑም ፦
- የእንግሊዘኛ፣
- የፈረንሳይኛ
- የዓረብኛ ቋንቋዎችን መናገርና መጻፍ የሚችሉ እና ዕድሚያቸው ከ18-30 የሆነ ኢትዮጵያዊና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ከዛሬ ጀምሮ ለ5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ መመዝገብ ይችላሉ።

ምዝገባው በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዋናው መ/ቤት በአካል በመገኘት ነው የሚከናወነው።

ተመዝጋቢዎች ለምዝገባ ሲመጡ የትምህርት ማስረጃቸውንና ማንነታቸውን የሚገልፅ መታወቂያ ይዘው መቅረብ አለባቸው።

ተጨማሪ መረጃዎችን ደግሞ በስልክ ቁጥር +251911210234 / +251912663737 ላይ ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

@tikvahethiopia
#ጥቆማ

አንድ የስራ ማስታወቂያ እንጠቁማችሁ። ዕድላችሁንም ሞክሩ።

ማስታወቂያውን ያወጣው የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ነው።

የስራ መደቦቹ ምን ምን ናቸው ?

1. ከፍተኛ የኢንቨስትመንት ፕሮሞሽን ባለሙያ

° ደረጃ ፡- 14
° ደመወዝ ፡- 38,557
° ብዛት ፡- 1
° ተፈላጊ የትምህርት አይነት፡- በማርኬቲንግ ማኔጅመንት፣ቢዝነስ አስተዳደር፣ኢኮኖሚክስ እና በተያያዥ የትምህርት መስኮች
° የትምህርት ደረጃ፡- የመጀመሪያ ዲግሪ / ሁለተኛ ዲግሪ
° የስራ ልምድ ፡-3/2 ዓመት
° ተጨማሪ መስፈርት ፡-አይጠይቅም
የቅጥር ሁኔታ ፡- በቋሚነት
የስራ ቦታ፡-ዋናው መ/ቤት


2. ከፍተኛ የማርኬቲንግ ባለሙያ

° ደረጃ ፡- 14
° ደመወዝ ፡- 38,557
° ብዛት ፡- 1
° ተፈላጊ የትምህርት አይነት ፡- በማርኬቲንግ ማኔጅመንት፣ ቢዝነስ አስተዳደር፣ ኢኮኖሚክስ እና ተያያዥ የትምህርት መስኮች
° የትምህርት ደረጃ፡- የመጀመሪያ ዲግሪ/ ሁለተኛ ዲግሪ
° የስራ ልምድ ፡- 3/2 ዓመት
° ተጨማሪ መስፈርት ፡-አይጠይቅም
° የቅጥር ሁኔታ ፡- በቋሚነት
° የስራ ቦታ፡-ዋናው መ/ቤት

3. ከፍተኛ የብራንዲንግ ባለሙያ

° ደረጃ፡- 14
° ደመወዝ፡- 38,557
° ብዛት ፡- 1
° ተፈላጊ የትምህርት አይነት፡- በማርኬቲንግ ፣ ቢዝነስ አስተዳደር እና ተያያዥ የትምህርት መስኮች
° የትምህርት ደረጃ፡- የመጀመሪያ ዲግሪ/ ሁለተኛ ዲግሪ
° የስራ ልምድ ፡-3/2 ዓመት
° ተጨማሪ መስፈርት ፡-በግራፊክስ ፣ በዲዛይን እና ተዛማች ሰርተፊኬሽን ያለው/ያላት
° የቅጥር ሁኔታ ፡- በቋሚነት
° የስራ ቦታ፡-ዋናው መ/ቤት

4. ሁለገብ የጥገና ሠራተኛ

° ደረጃ፡-9
° ደመወዝ፡- 24,435
° ብዛት ፡- 1
° ተፈላጊ የትምህርት አይነት፡- በእንጨት ወይም በብረት ሥራ
° የትምህርት ደረጃ፡- 10+2
° የስራ ልምድ ፡- 3 ዓመት
° ተጨማሪ መስፈርት ፡-አይጠይቅም
° የቅጥር ሁኔታ ፡- በቋሚነት
° የስራ ቦታ፡-ዋናው መ/ቤት

5. የመረጃ ዴስክ ባለሙያ

° ደረጃ፡-11
° ደመወዝ፡- 29,029
° ብዛት ፡- 1
° ተፈላጊ የትምህርት አይነት፡- በጆርናሊዝም፣ ቋንቋና ስነ ፅሁፍ፣ ፖለቲካል ሣይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት እና ተያያዥ የትምህርት መስኮች
° የትምህርት ደረጃ፡- የመጀመሪያ ዲግሪ/ ሁለተኛ ዲግሪ
° የስራ ልምድ ፡-1/0 ዓመት
° ተጨማሪ መስፈርት ፡-አይጠይቅም
° የቅጥር ሁኔታ ፡- በቋሚነት
° የስራ ቦታ፡-ዋናው መ/ቤት

ምዝገባ በኦን ላይን https://tinyurl.com/ipdchoexternalvacancy ላይ ነው የሚከናወነው።

ለሥራ መደቡ የሚያስፈልጉ የትምህርት ፤ሥራ ልምድ እና ሌሎች ማስረጃዎች ወደ ፒዲኤፍ/pdf/ በመቀየር በአንድ ፋይል መያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

ማስታወቂያ ትላንት ነው የወጣው ለ5 ተከታታይ የስራ ቀናት ብቻ ነው የሚቆየው።

አመልካቾች ከስራ መደቡ ጋር #ቀጥተኛ_የሆነ የስራ ልምድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል የተባለ ሲሆን ከግል ድርጅቶች የሚቀርብ ስራ ልምድ ግብር መከፈሉ ማረጋገጫ መቅረብ አለበት።

ተጨማሪ መረጃ ደግሞ በስልክ ቁጥር 0118 72 24 20 ላይ ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

መልካም ዕድል !

@tikvahethiopia
#አሁን : የቀድሞ የትግራይ ተዋጊዎችን ትጥቅ ማስወረድና ወደ ተሃድሶ ማዕከላት የማስገባት ስራ ዛሬ ተጀመረ።

የመጀመሪያው ዙር የትግራይ የቀድሞ ተዋጊዎችን ዲሞብላይዝድ በማድረግ ወደ ስልጠና ማእከላት የማስገባት ስራ በመቐለ ከተማ በይፋ ተጀምሯል።

በመጀመሪያ ዙር በክልሉ 75 ሺህ የቀድሞ ተዋጊዎች ስልጠናና የማቋቋምያ ገንዘብ በመስጠት ወደ ህብረተሰቡ የማቀላቀል ስራ ይሰራል።

በአሁን ሰዓት ታጣቂዎች የኢፌዴሪ ሀገር መከላከያ ሰራዊት ፣ የትግራይ ክልል የፀጥታ ሃይሎች ከፍተኛ አመራሮች ፣ የአፍሪካ ህብረት አደራዳሪዎች እና ሚድያዎች ፊት የታጠቁትን ቀላል መሳሪያ እያስረከቡ ነው።

የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል በስፍራው ተገኝቶ ሁነቱን እየተከታተለ ነው።

ዝርዝር እናቀርባለን !

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
#Update

ዛሬ 320 የትግራይ ተዋጊዎች ትጥቅ አውርደው አስረክበዋል።

የቀድሞ ትግራይ ተዋጊዎች ትጥቅ የማስፈታትና ወደ ተሃድሶ ማዕከላት የማስገባት ስራ በዛሬው ዕለት በይፋ ተጀምሯል።

የኢፌዴሪ ሀገር መከላከያ ሰራዊትም ታጣቂዎች ያወረዷቸውን ትጥቆች ርክክብ አድርጓል።

በዛሬው ዕለት 320 የትግራይ ተዋጊዎች ቀላል መሳሪያዎችን አውርደው በማስረከብ ወደ ተሃድሶ ያስልጠና ማዕከል አቅንተዋል።

እንደ ተነገረው ከሆነ በመጀመሪያው ዙር 75 ሺህ የቀድሞ ተዋጊዎችን ስልጠናና የማቋቋሚያ ድጋፍ በማድረግ ወደ ህብረተሰቡ የመቀላቀል ስራ ይሰራል።

@tikvahethiopia