TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ዛሬ ያለመከከስ መብታቸው የተነሳው የልደታ ክ/ከተማ ዋና ሥራ አስፈጻሚ የነበሩት የአ/አ ም/ቤት አባል ሰዒድ አሊ በምንድነው የተጠረጠሩት ?

ዛሬ የአዲስ አበባ ም/ቤት የልደታ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ የነበሩት አቶ ሰዒድ አሊን ያለመከከስ መብት አንስቷል።

ያለመከሰስ መብታቸው የተነሳው በሙስና ተጠርጥረው እንደሆነ በም/ቤቱ የሰላም ፣ ፍትህ እና መልካም አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ገልጿል።

ኮሚቴው ምን አለ ?

" ከሜክሲኮ እስከ ቄራ ባለው የኮሪደር ስራ ያልተካተቱ እና በመንግሥት ይፈርሳሉ ተብለው ያልተያዙ የመንግሥት ቤቶችን ከባለሃብት እና ከሰራተኞች ጋር በመመሳጠር ግምታቸው ከ3 ሚሊዮን ብር በላይ የሆነ ኮንዶሚኒየም ቤት እንዲሰጥ አድርገዋል።

የፈረሱት የመንግሥት ቤቶች ግለሰቦች ተከራይተውት የነበረ ነው።

እነዚህን ቤቶች እንዲፈርሱ አስደርገው ይዞታውን ከቤቶቹ አጠገብ ለተሰራው " ዋይልድ አፓርትመንት " ለተባለ ህንጻ ባለቤት  ምቹ በማድረግ ግንባታ እንዲገነባና የግሉ እንዲያደርገው ለማድረግ ተንቀሳቅሰዋል።

አጠቃላይ 6 መኖሪያ ቤቶች እና 1 ንግድ ቤት ፦
- ግለሰቦች እየኖሩበትና ንግድ እየተከናወነ ባለበት፤
- ካቢኔው ይፍረሱ ብሎ ባልወሠነበት
- ፕላን፣ ፎርማት እና የካቢኔ ውሳኔ ባልተያዘበት በ503 ካ/ሜ ላይ ያረፉትን ቤቶች እንዲፈርሱ ሰራተኞችን ሰብስበው በማስወሰንና ትዕዛዝ በመስጠት ፤ ቤቶቹ ያሉበት ቦታ በአካል ጭምር በመሄድ እንዲፈርስ መመሪያና ትዕዛዝ ሰጥተዋል።

የመንግሥት መኖሪያ ቤቶች ውስጥ በኪራይ ይኖሩ ለነበሩት ግለሰቦች አጠቃላይ 3,383,202 ብር ከ77 ሳንቲም የሆኑ 6 የጋራ መኖሪያ ኮንዶሚኒየም ቤቶች እንዲሰጣቸው አድርገዋል።

ይዞታውን ሀጂ በገን ኸይሩ ነጋሽ ለተባሉ  በአካባቢው አፓርትመንት ላላቸው ግለሰብ እንዲሰጥና ግንባታ እንዲገነባበት አድርገዋል።

ተጠርጣሪው ለዚህ ስራ ጉቦ መቀበሉ ማስረጃ አለን ብሏል።

በባለቤታቸው ስም ከባለሃብቱና ከድርጅቱ 6 ሚሊዮን ብር ጉቦ ተቀብለዋል። ይህን ብር ከሌላ ግለሰብ ካተላለፈው 8 ሚሊዮን ብር ጋር በመቀላቀል በባንክ ብድር ለገዙት 30,000,000 ብር ለሚያወጣ ቤት 14,000,000 ብር ለቤቱ ግዥ ብድር ክፍያ ከፍለዋል ፤ በዚህም የሙስናና ህገወጥ ገንዘቡን ህጋዊ አስመስሎ በማቅረብ ወንጀል መፈጸም ምርመራ እየታጣራ ይገኛል " ብሏል።

#AddisAbaba

@tikvahethiopia
#MoE

ትምህርት ሚኒስቴር የዩኒቨርሲቲ መምህራንን ፈተና ለመፈተን እየተዘጋጀ መሆኑ ተሰማ።

ትምህርት ሚኒስቴር፤ በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚያስተምሩ መምህራንን ብቃት ለመመዘን ፈተና ለመፈተን ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ገልጿል።

በሚኒስቴሩ የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አገልግሎት ዳይሬክተር የሆኑት እዮብ አየነው(ዶ/ር ) ለሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ በሰጡት ቃል ፥ " የመምህራን ፈተና ከዚህ በፊት በአንደኛ ደረጃ በሚያስተምሩት ላይ ተሞክሮ ነበረ በመሆኑም አልተጀመረም ማለት አይቻልም " ብለዋል።

አሁን ግን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራንን ለመፈተን ዝግጅት እየተደረገ እንደሆነ አስረድተዋል።

ዝግጅቱ እንዳለቀ በዚህ ዓመት ወይም በቀጣዩ 2018 ዓመት ለከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መመህራን ፈተና መሰጠት ይጀምራል ሲሉ ለሬድዮ ጣቢያው ገልጸዋል።

@tikvahethiopia
#InfinixEthiopia

የኢንፊኒክስ ስማርት ስልኮች የሆኑትን ሆት 40 ፣ ኖት 40 ፣ ዜሮ 40 እና የኢንፊኒክስ ስማርት TVን ሲገበያዩ የሽልማት ኩፖን ይውሰዱ፡፡ አብሮት ካለ ወዳጅ ዘመድ ወይም ጓደኛ ጋር በመረጡት ስፍራ ፎቶ በመነሳት #InfinixEthiopia የሚለውን ሃሽታግ በመጠቀም የማህበራዊ ገጾት ላይ ይለጥፉ የዛንዚባር የቢዝነስ ክላስ ደርሶ መልስ የአውሮፕላን ቲኬት ፣ የኢንፊኒክስ ስማርት ቲቪ ፣ የኢንፊኒክስ ላፕቶፕ እንዲሁም ሌሎች አጓጊ ሽልማቶችን ያሸንፉ፡፡

መመሪያ

1. የኢንፊኒክስ ኢትዮጵያን ፌስ ቡክ ፣ ኢንስታግራም እና ቲክቶክ ገጾችን ፎሎው ያድርጉ፡፡
2. የተነሱትን ፎቶ በመረጡት ማህበራዊ ሚዲያ ሲለጥፉ የኢንፊኒክስ ኢትዮጵያን ገፅ ከፖስቶት ጋር ታግ ያድርጉ፡፡
3. #InfinixEthiopia የሚለውን ሃሽታግ መጠቀሞን አይርሱ፡፡

Tag ሲያደርጉ ለ Facebook @InfinixMobileEthiopia ፣ ለ Instagram @infinixethiopia ለ TikTok @Infinixet እና ለ Telegram @Infinixeth ሜንሽን ማድረግ እንዳይረሱ።
#እንድታውቁት

የሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ አገልግሎት በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙት 16 ቅርንጫፎች አገልግሎት ለማግኘት " ፋይዳ " ዲጂታል መታወቂያ ወይም የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ ግዴታ ተደርጎ እየተሰራበት ነው።

@tikvahethiopia
አምባሳደር ሽፈራው ሽጉጤ የኢትዮጵያ ህብረት ስራ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው ከትላንት ጀምሮ መሾማቸው ተሰምቷል።

አምባሳደር ሽፈራው ወደ ህብረት ስራ ኮሚሽነርነት እስከ ተሾሙበት ጊዜ ድረስ የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣንን በዋና ዳይሬክተርነት ሲመሩ ቆይተዋል።

የኢትዮጵያ ኅበረት ሥራ ኮሚሽን ኮሚሽነር የነበሩት ጌታቸው መለሰ (ዶ/ር) ከወር በፊት ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ይታወሳል።

አምባሳደር ሽፈራው ሽጉጤ ፤ ኢህአዴግ ከመፍረሱ በፊት በተለያዩ የክልልና የፌዴራል የስልጣን እርከኖች ላይ ኢህአዴግ ፈርሶ ብልፅግና ከመጣም በኃላ በተለያዩ የስልጣን እርከኖች ላይ ተሹመው እየሰሩ ናቸው።

በሌላ በኩል ፤ በአምባሳደር ሽፈራው ሽጉጤ ምትክ አህመድ አብተው (ዶ/ር) የኢፌዴሪ ትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሆነው ከትላንት ጀምሮ እንደ ተሾሙ ሸገር ኤፍ ኤም ሬድዮ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
#ጥንቃቄ🚨

" ተግባራችሁ በህግ የሚያስጠይቅ ነው። ይህን ተገንዝባችሁ ከእኩይ ተግባራችሁ ታቀቡ " - ጤና ሚኒስቴር

ከሰሞኑን በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች የስኳር ህመምን ጨምሮ ሃሰተኛ የጤና መረጃዎች ሃላፊነት በጎደላቸው አካላት እየተለቀቁ እንደሚገኙ የጤና ሚኒስቴር አሳውቋል።

" ቴክኖሎጂን በመጠቀም በሰዓታት ውስጥ የስኳር በሽታን ማጥፋት ተችሏል " በሚል ሰሞኑን እየተሰራጨ የሚገኘው መረጃ ከእዉነት የራቀና አሳሳች መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡

አሁን አሁን የህክምና ሞያ ሳይኖራቸውና ለሚሠጡት አገልግሎትም ህጋዊ የሆነ የብቃት ማረጋገጫ ሳይኖራቸው በየማህበራዊ ሚዲያው ላይ እየወጡ ማህበረሰቡን የሚጎዱ፣ ከእውነት የራቁ ሀሰተኛ መረጃዎችን የሚለቁ አካላት ተበራክተዋል ብሏል።

ይህ ተግባር ደግሞ ማህበረሰቡን በእጅጉ እየጎዳና ለአላስፈላጊ ወጪና እንግልት ከመዳረግ አልፎ ፈውስ ፈላጊ ዜጎችን ላይ ከፍተኛና የተወሳሰበ የጤና ችግር እየፈጠረ እንደሚገኝ አስገብዟል።

በዚህ መሰል ተግባር ላይ ተሰማርተው የሚገኙ አካላት ይህ ተግባር በህግ የሚያስጠይቅ መሆኑን ተገንዝበው ከእኩይ ተግባራቸው እንዲታቀቡ ሚኒስቴሩ አሳስቧል፡፡

ማህበረሰቡ ምንጫቸው ካልተረጋገጠ አካላት የሚላኩ መልእክቶችን እንዲመረምር ፤ አገልግሎቶችንም ከመጠቀሙ በፊት ጥንቃቄ እንዲያደርግ ተብሏል።

አስፋላጊ ሆኖ ሲገኝም በ "[email protected]" ላይ ጥቆማ እንዲሰጥ ተጠይቋል፡፡

ሀሰተኛ የጤና መረጃ ከፍተኛ ቀውስ የሚፈጥር በመሆኑ ዜጎች ሀሰተኛ የጤና መረጃ የሚያሰራጩትን በመጠቆም ስለ ጤናው የጤና ባለሙያን ብቻ በማማከር ጤንነቱን እንዲጠብቅ መልዕክት ተላልፏል።

#Ethiopia #MinistryofHealth

@tikvahethiopia
#Ethiopia

ከፍተኛ ክርክር የተደረገበት የፌዴራል መንግሥት ሠራተኞች ረቂቅ አዋጅ ከነማሻሻያ አዋጁ ትላንትና ፀድቋል።

የምክር ቤቱ አባላት ረቂቅ አዋጁንና ማሻሻያ ሪፖርቱን አስመልከተው የተለያዩ የድጋፍና የተቃውሞ ሐሳብና አስተያየቶችን ሰጥተዋል፡፡ 
የምክር ቤት አባልት ምን አሉ ?

- ማሻሻያው ከአሁን ቀደም ከሥራ ባህሪያቸው አንፃር ለየት ባለ የአደረጃጀትና የአሠራር መዋቅር ተደራጅተው የነበሩ የፍርድ ቤቶችን መሰል አዋጆችን መሻሩን የወቀሱ ነበሩ፡፡

- ማሻሻያ አዋጁ ልክ ለገቢዎችና ለጉምሩክ ኮሚሽን ሠራተኞች እንደሰጠው ሁሉ፣ ለፌዴራል ፍርድ ቤቶች የአስተዳደር ሠራተኞች ተገቢውን ትኩረት ሊሰጥ ይገባ እንደነበርም ተገልጿል።

- ሥራ ፈላጊ ኢትዮጵያውያን በየትኞቹ የአገሪቱ አካባቢዎች በሚወጡ የሥራ ማስታወቂያዎች በእኩልነትና በፍትሐዊነት ሊወዳደሩ የሚችሉበት አስገዳጅ ሁኔታ በግልጽ በረቂቅ አዋጁ ማሻሻያ አለመቅረቡ ተነስቷል።

- የውስጥ ዝውውርን በተመለከተ አንድ የተቋም ኃላፊ ለውጤታማነት በሚል ሠራተኞችን ወደ የሚፈልግበት ቦታ አዛውሮ ማሠራት፣ ይህንን የማይቀበሉ ሠራተኞች ደግሞ መልቀቅ ይችላሉ መባሉም ጥያቄዎችን አስነስቷል፡፡ የአሠራር ክፍተቶችን የሚፈጥር እንደሆነም ተመላክቷል።

የአብን የምክር ቤት አባል ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) ፦

" እንዲህ ዓይነት አዋጆች ሲዘጋጁ ሰፊ ዝግጅትና ውይይት ይፈልጋሉ። እንዲሁም የሠራተኞችን ሥጋት ማካተት ይገባል።

የረቂቅ አዋጁ መንደርደሪያ በመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ኢትዮጵያን የሚመስል የሠራተኞች ስብጥር እንዲኖር ነው በሚል መገለጹ ችግር አለበት።

' ሲቪል ሰርቪሱ በአንድ ብሔር የበላይነት ተይዟል ' በሚል የቀረበ ነው። ያን ለማለት ደግሞ በሚያስችል መንገድ ተዘጋጅቶ ቀርቧል።

ሲቪል ሰርቪሱ ብቃትንና አቅምን መሠረት አድርጎ ሊገነባ ይገባል። ኮታን ወደ ማከፋፈል አይወስደንም ወይ ? ሥራን በኮታ ማደላደሉ ማቆሚያው የት ነው ?

አንድ ሠራተኛ አፈጻጸሙ ምንም ይሁን ምን ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን እስከፈለገ ድረስ አንስቶ ሌላ ተቋም ላይ በተመሳሳይ ደረጃና ደመወዝ መመደብ ይችላል። ያን የማይፈልግ ከሆነ ሠራተኛው መልቀቅ ይችላል መባሉ የሠራተኞችን መብት የሚጋፋና ዕጣ ፋንታቸውን በአለቆቻቸው እንዲወሰን የሚያደርግ ነው።

እንዲሁም ከሥራ እንዲለቁ የሚገፋፋ ነው።

የሠራተኞች የትርፍ ሰዓት ጉዳይ ከ39 ወደ 48 ሰዓታት እንዲያድግ መደረጉም አግባብነት የሌለው ነው " ብለዋል።


የኢዜማ አባል አወቀ አምዛዬ (ዶ/ር) ምን አሉ ?

" በረቂቅ አዋጁ ' ዘመናዊና ኢትዮጵያን የሚመስል ' መባሉ በዘወርዋራው የኮታ ሥርዓትን የሚመለከት ነው።

' ዘመናዊ አገርና ዘመናዊ ቢሮክራሲ እንፈጥራለን ' እያልን የመንግሥት ሠራተኞችን ከችሎታና አቅም ይልቅ በብሔር ኮታ እንቅጠር ማለት እርስ በርሱ የሚቃረን ሐሳብ ነው።

ማይክሮሶፍትን መሰል ዓለም አቀፍ ተቋማት በአሜሪካውያን ሳይሆን በህንዳውያንና በቻይናውያን የሚመሩና የሚተዳደሩ ናቸው።

የመንግሥት ተቋማት የሃይማኖት የስብከት ቦታዎች እየሆኑ ነው። ይህ በጥብቅ ሕግ ጭምር ሊከለከል ይገባል።

አንድን ሠራተኛ መሥሪያ ቤቱ ወይም የበላይ ኃላፊው በፈለገው ቦታ መድቦ ማሠራት ይችላል የሚለው ሰው በሙያ (ፕሮፌሽን) እንዳያድግና የካበተ ልምድ እንዳይኖረው እንደሚያደርግ፣ ይህ ደግሞ በተቃራኒው ቢሮክራሲውን የበለጠ የሚጎዳ ነው።

የበላይ አመራሩ የመጨረሻ ወሳኝ መሆኑ ከሕግና ከሥርዓት የሚፃረርና ሰብዓዊ መብትንም የሚጋፋ ነው።

ይህ ከሆነ ባርነትን እንደገና በሕግ እያፀደቅን ነው ማለት ነው ? ውሳኔውን ፍርድ ቤት መስጠት አለበት " ብለዋል።


የምክር ቤት አባል አቶ ለማ ተሰማ ምን አሉ ?

" ረቂቅ አዋጁ ሠራተኞች በትምህርት መስክና ደረጃቸው እንዲሁም በልምዳቸው እንጂ፣ ከዚያ ውጪ የሚመደቡበትን አሠራር አይፈጥርም።

የሚነሱ ሥጋቶች ቀጥለው ሊወጡ በሚችሉ ደንቦች ሊመለሱ ይችላሉ።

በረቂቅ አዋጁ የተካተቱ አንዳንድ ጽንሰ ሐሳቦች በጥርጣሬ ሊታዩ አይገባም። ሲቪል ሰርቪሱ መለወጥ አለበት። ትናንት የነበረው አግላይ ነበር። ዕድልንም አይሰጥም ነበር።

ረቂቅ አዋጁ ሁሉንም ጠርጎ የሚያስወጣ ሳይሆን፣ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ በብቃቱ ተወዳድሮ ሠራተኛ መሆን የሚችልበትን ዕድል የሚፈጥር ነው። "


ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡት የሰው ሀብት ልማት ሥራ ሥምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ነገሪ ሌንጮ (ዶ/ር) ምን አሉ ?

🔴 ብዙዎቹ ጥያቄዎች በውይይት ወቅት ተነስተው ምላሽ ተሰጥቶባቸው ነበር።

🔴 ፍርድ ቤቶች በልዩ ሁኔታ መታየት ነበረባቸው መባሉ በረቂቅ አዋጁ በሚቋቋመው በጠቅላይ ሚኒስትሩ በሚመራው የሜሪትና የደመወዝ ቦርድ በኩል ራሱን ችሎ ምላሽ ሊያገኝ ይችላል።

🔴 በረቂቅ አዋጁ ውስጥ ኮታ የሚል ነገር የለም። ኮታ ተቀባይነት እንደሌለው በረቂቅ አዋጁ ውስጥ ተቀምጧል።

🔴 ረቂቅ አዋጁ የሥራ አመራር ኢንስቲቲዩትን እንደ አዲስ የብቃትና ሥራ አመራር ኢንስቲቲዩት በሚል ስያሜ አቋቁሞ ሠራተኞችን በብቃታቸውን ለመመዘን ያስችላል።

🔴 ሠራተኞችን የማዘዋወሩ ኃላፊነት በማኔጅመንት እንጂ በበላይ ኃላፊዎች ብቻ አይወሰንም። የሠራተኛው ምክንያት የሚደመጥበትና መብቱ የሚጠበቅበት አሠራር በረቂቅ አዋጁ ተካቷል።

ከፍተኛ ክርክር የተደረገበት ይህ ረቂቅ አዋጅ የፌዴራል መንግሥት ሠራተኞች አዋጅ ቁጥር 1353/2017 ሆኖ በ3 ተቃውሞ በአራት ድምፀ ተዓቅቦ በአብላጫ ድምፅ ፀድቋል፡፡#ሪፖርተር

@tikvahethiopia
#አፈሳ

🔵 “ ወጣቶች እየታፈሱ ነው። የሚታፈሱትም ያለ ፍላጎታቸው ወደ ግዳጅ ሊላኩ ነው ” - የኦሮሚያ ክልል ነዋሪዎች

🔴 “ ያገኘናቸው በጣም በርካታ ግኝቶች አሉ ” - ኢሰመኮ


በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ወጣቶች “ በመንግስት ፀጥታ አካላት ” እየታፈሱ መሆኑን፣ በዚህም እንዲህ አይነት ድርጊት በሚፈጸምባቸው ቦታዎች ወጣቶች በነጻነት የመንቀሳቀስ መብታቸው እንደተገደበ ነዋሪዎች በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል አቤት ብለዋል።

ነዋሪዎቹ እየተፈጸመ ነው በሚል የተማረሩበት የአፈሳ ድርጊት በይበልጥ እየተካሄደ ያለው በባሌ ሮቤ፣ በሻሽመኔ፣ በአርሲ ነገሌ፣ ባቱ፣ ወንጂ፣ ጅማ፣ በአዳማ ከተሞችና በዙሪያ ገባው መሆኑም ተመላክቷል።

ነዋሪዎቹ፣ “ ወጣቶች እየታፈሱ ነው። የሚታፈሱትም ያለ ፍላጎታቸው ወደ ግዳጅ ሊላኩ ነው ” ሲሉ ተናግረዋል።

“ ወጣቶቹ ለመዝናናትም ሆነ ለሥራ ሰብሰብ ብለው መንገድ ላይ ሲገኙ ያለምንም ጥያቄ ታፍሰው በመኪና እየተጫኑ ወደ ሌሎች አካባቢዎች እየተወሰዱ ነው ” በማለት ሁነቱን አስረድተዋል።

“ ከዚች ቀደምም አፈሳ ወጣቶች በሚሰበሰቡበት ቦታ ለምሳሌ ዴኤስቲቪ ፣ ፑል ቤት ነበር አሁኑ ግን መንገድ ላይ የሚገኙት ጭምር በገፍ እየተወሰዱ ነው ” ብለዋል።

አንዳንድ ከ15 እስከ 18 ዓመት እድሜ ያላቸው ታዳጊዎችም የተወሰዱበት ሁኔታ አለ ሲሉ ገልጸዋል።

አንድ ቃላቸውን የሰጡ የክልሉ ነዋሪ “ ከሻሸመኔ አንድ የምናውቀው የቤተሰብ ልጅ ተወስዷል። ከሻሸመኔ ተጭነው ወደ ወላይታ ሶዶ አካባቢ መሄዳቸውን ለቤተሰቦቹ ተናግሯል ” ብለዋል።

አንድ የአዳማ ከተማ ነዋሪ ደግሞ ፥ “ ሰው በተለይ ወጣቱ ፈርቷል። ያለውን ወቅታዊ ነገር በመፍራት ስራውን ትቶ በጊዜ ቤት የሚመለስ አለ። ከወጣው እታፈሳለሁ በሚል ስጋት ከቤት የማወጡም አሉ። የጊዜ ገደብ የተቀመጠ ይመስል ውጭ ያለው ሰው 12:00 ስሆን ወደ ቤቱ ለመግባት ይጣደፋል ” ሲል ገልጿል።

“ ሰዎችን ያለምክንያት ይዘው ያስራሉ ሰው ካለው እና 20,000-30,000 መክፈል ከቻለ ይለቃሉ። ያልቻለ ደግሞ ተወስዶ ይሄዳል ” ሲልም አክሏል።

ሰሞኑን አንድ ጓደኛቸው ተይዞ የባንክ ሰራተኛ ነኝ ብሎ ማስረጃ አሳይቶ መለቀቁን ጠቁሟል።

ድርጊቱ በሚፈጸምባቸው አካባቢዎችም ሰዎች ከቤት ለመውጣት፣ ሥራ ለመስራት ከፍተኛ ስጋት እንዳደረባቸው አስረድተው፣ “ የሰው ልጅ መብት ግን ለይስሙላ ነው እንዴ የተጻፈው ? መቼ ነው ይህ መብታችን እንኳ የሚከበረው ? ከዚህ ቀደምም አፈሳ ነበር። ያሁኑ ግን ብሷል ” ሲሉ ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

በርካታ እናቶች ልጆቻቸው ከሚኖሩበት ሰፈር ሳይቀር ተወስደውባቸው በስንት ልመና ከተያዙበት ቦታ ያስወጧቸው አሉ።

በተለይ ወጣቶች ከተያዙ በኃላ የሚወሰዱት ወደ ማቆያ ቦታዎች ነው።

ከነዋሪዎች ዘንድ ለቀረበው ሰፊ ቅሬታ ምላሽ ለማግኘት ቲክቫህ ኢትዮጵያ ወደ ኦሮሚያ ክልል ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ሙከራ ቢያደርግም፣ ስልክ ሆነ የፅሑፍ መልዕክት ለመመለስ ፈቃደኛ አልሆነም።

ከቀናት በፊት የክልሉ መንግሥት “ በክልሉ የጅምላ አፈሳ አለ በሚል የሚሰራጨው መረጃ ሀሰት ነው ” ሲል በፋና ብሮድካስት ኮርፖሬት በኩል ገልጾ ነበር።

እየተፈጸመ ነው የተባለውን የአፈሳ ድርጊት ሰምቶ እንደሆን በሚል የጠየቅነው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ግን አፈሳ እየተፈጸመ ነው የሚለው ቅሬታው ትክክል መሆኑን ነግሮናል።

ወጣቶችን ወደ ‘ግዳጅ ትሄዳላችሁ’ በሚል በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች እየተፈጸመ ነው የተባለውን አፈሰ ኮሚሽኑ ሰምቶ ነበር ? ስንል የጠየቅነው ኢሰመኮ በምላሹ፣ “ አፈሳውን በተመለከተ የሰራነው ብዙ ሥራ አለ።  ፐብሊክ ስቴትመንት ይሰጣል ” ብሏል።

“ ምንድን ነው የሚለውን በሂደት የምናያቸው ይሆናል። ግን ጉዳዩ ኦረዲ ብዙ ሥራ ተሰርቶበታል። መግለጫው ሲወጣ ይደርሳችኋል ” ነው ያለው።

አፈሳው ትክክል ነው ? እንዲህ አይነት ድርጊት እየተፈጸመ ነው? ለሚለው የቲክቫህ ጥያቄ ኮሚሽኑ፣ “ በጣም ብዙ የኦሮሚያ አካባቢዎች ላይ ገብተን የሰዎች ማቆያዎችን አይተናል ” የሚል ምላሽ ሰጥቷል።

“ ስለዚህ የማኀበራዊ ሚዲያው አሊጌሽን ምንድን ነው? የሚለው እንዳለ ሆኖ በእኛ በኩል ግን ያገኘናቸው በጣም በርካታ ግኝቶች አሉ ” ሲል አረጋግጧል።

“ ከክልሉ ጋር የተየጋገርንባቸው፣ እያደረግን ያለናቸው ጉዳዮችም አሉ ” ሲል ኮሚሽኑ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

" የቤት ሰራተኛ በአጋዥነት ስትቀጥሩ በህጋዊ መንገድ በቂ ተያዥ በማስቀረብ የተያዣቸውን አድራሻና ማንነት በአግባቡ በማጤን ይሁን " - ፖሊስ

በቤት ሰራተኝነት ተቀጥራ ከምትሰራበት ቤት ከ2 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ንብረት እና ገንዘብ ሰርቃ የተሰወረች ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር መዋሏን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል።

ተጠርጣሪዋ የወንጀል ድርጊቱ የፈጸመችው በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 አያት ዞን1 ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ጥቅምት 22 ቀን 2017 ዓ/ም ነው፡፡

ግለሰቧ በደላላ አማካኝነት በቤት ሰራተኝነት ከተቀጠረችበት መኖሪያ ቤት በ3ኛው ቀን ቆይታዋ ነው ዝርፊያውን የፈጸመችው።

የግል ተበዳይ ስራ በሄዱበት ወቅት አጋጣሚውን በመጠቀም በቤቱ ውስጥ የተቀመጠውን የተለያዩ ሀገራት ገንዘቦች እንዲሁም የተለያዩ የወርቅ ጌጣጌጦችን ሰርቃ በመሰወሯ የግል ተበዳይ የተፈፀመባቸውን የወንጀል ድርጊት ለመሪ ሉቄ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ አመልክተዋል፡፡

ተጠርጣሪዋ የወንጀል ድርጊቱን ከፈፀመች በኋላ የግል ተበዳይ ጋር ከመቀጠሯ በፊት በክፍለ ከተማው ወረዳ 14 አባዶ አካባቢ ኮንዶሚኒየም ቤት ለ3 ወራት ተከራይታ በነበረበት ቤት ተደብቃ በክትትል የፖሊስ አባላት ከሰረቀቻቸው የተለያዩ አልባሳት፣ የተለያዩ የሴትና የወንድ ጫማዎች፣ 18 ሺህ የአሜሪካ ዶላርና የህንድ ሩፒ፣ የተለያዩ የወርቅና ልዩ ልዩ ጌጣጌጦች ጋር በቁጥጥር ስር መዋሏን ፖሊስ ገልጿል።

በ2 የተለያዩ ስሞች የነዋሪነት መታወቂያዎች እንደተገኘባትም ፖሊስ አመልክቷል።

የግል ተበዳይ ተጠርጣሪዋን ለስራ ሲቀጥሯት ያቀረበችው የተያዥ ፎርም የራሷን ፎቶ በትክክል እንዳይለይ አድርጋ የለጠፈች ሲሆን የግል ተበዳይ ይህን ሳያረጋግጡ በእምነት የቀጠሯት መሆኑን ገልፀዋል።

ፖሊስ ፥ ህብረተሰቡ የቤት ሰራተኛ በአጋዥነት መቅጠሩ ተገቢ ቢሆንም በህጋዊ መንገድ በቂ ተያዥ በማስቀረብ የተያዣቸውን አድራሻና ማንነት በአግባቡ በማጤን መቅጠር እንደሚገባ አሳስቧል።

ውድ የሆኑ ንብረቶችን እንዲሁም ገንዘቦችን ደህንነቱ በተጠበቀ ቦታ በማስቀመጥ በተገቢው ሊቆጣጠሩና ንብረታቸውን ከስርቆት ወንጀል ሊታደጉ እንደሚገባም አሳስቧል።

NB. በዚህ የፖሊስ መረጃ ላይ እንዴት አንድ ሰው ቤት ውስጥ ይሄ ሁሉ የአሜሪካ ዶላር በጥሬው ሊቀመጥ እንደቻለ፣ የተገኘው የተጠርጣሪዋ መታወቂያ ከየት እና እንዴት እንደወጣ የተብራራ ነገር የለም።

መረጃውን የተመለከቱ በርካቶች የገለሰቧ መያዝ ትክክል ሆኖ ሳለ እንዴት ይሄ ሁሉ ዶላር ግለሰብ ቤት ተቀምጦ ተገኘ፣ መታወቂያውን የሰጣት አካላስ ማነው ? የሚል ጥያቄ አንስተዋል። ፖሊስ በቀጣይ ስለ ጉዳዩ የሚሰጠው ማብራሪያ ካለ እናቀርባለን።

#AddisAbaba

@tikvahethiopia
#SafaricomEthiopia

⚡️በዕለታዊ የዳታ ጥቅሎች ቀኑን ሙሉ የፈለኘውን ሶሻል ሚዲያ እየተጠቀምን ፈታ እንበል! 🥳 M-PESA ላይ ስንገዛ ሁሉም ቅናሽ አላቸው! 

በልዩ ልዩ አማራጮች የቀረበልንን የሳፋሪኮም የኢንተርኔት ጥቅል የM-PESA Appን በመጠቀም አሁኑኑ እንግዛ! በአስተማማኙ ኔትወርክ ዳታ እንንበሽበሽ!

🔗የM-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያ በዚህ ሊንክ እናዉርድ: https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle

የቴሌግራም ቦታችንን https://t.iss.one/official_safaricomet_bot በመጠቀም የአየር ሰዓት ወይንም ልዩ ልዩ ጥቅሎችን እንግዛ!
ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ  በቴሌግራም ቻናላችን https://t.iss.one/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!

#MPESASafaricom #1wedefit #Furtheraheadtogether
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ዴሞክራሲ 👏 #ሶማሌላንድ

" የምርጫ ውጤቱን እንቀበላለን " - ፕሬዝዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ

ባለፈው ሳምንት በራስ ገዟ ሶማሌላንድ ፕሬዜዳንታዊ ምርጫ መደረጉ ይታወሳል።

በከፍተኛ ብልጫም የተቃዋሚው ዋደኒ ፓርቲ መሪ አብዲራህማን ሞሐመድ አብዱላሂ " ኢሮ " ምርጫውን አሸንፈዋል።

በምርጫው የተሸነፉት ተሰናባቹ ፕሬዜዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ " የምርጫውን ውጤት እንቀበላለን " ብለዋል።

ተመራጩ ፕሬዜዳንትንም " እንኳን ደስ አልዎት ! " ብለዋቸዋል።

" ባስመዘገቡት ድል እንኳን ደስ አልዎት " ያሉት ፕሬዜዳንት ቢሂ " ሰላማዊና የተረጋጋ የስልጣን ሽግግር እንዲደረግ ለማድረግ የተሟላ ድጋፌን አደጋለሁ  " ሲሉ ቃል ገብተዋል።

" የአገልግሎት ዘመንዎ ሰላምን ፣ እድገትን እና ዘላቂ ስኬትን ለሀገራችን እንዲያመጣ እመኛለሁ " ብለዋል።

ተሰናባቹ ፕሬዝዳንት ቢሂ ለህዝቡ ባስተላለፉት መልዕክት " ፕሬዝዳንታችሁ ሆኜ እንዳገለግላችሁ ዕድሉን ስለሰጣችሁኝ አመሰግናለሁ " ሲሉ ገልጸዋል።

" የስልጣን ዘመኔ ማብቂያ ላይ ሆኜ የምለው ነገር ለሀገራችን እድገት ያለኝ ቁርጠኝነት ጸኑ መሆኑን ነው " ሲሉ አክለዋል።

" በአንድነት እና በጋራ ተነስተን ለሶማሌላንድ ብልፅግና እንስራ " ብለዋል።

6ኛው የሶማሌላንድ ፕሬዚዳንት ሆነው የተመረጡት አብዲራህማን ኢሮ " ማንም ተሸናፊ ማንም አሸናፊ የለም ያሸነፈው የሶማሌላንድ ህዝብ ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

ሶማሌላንድ እራሷን እንደ ሉዓላዊ ሀገር ምትቆጥር ናት። ከሶማሊያ መንግሥት ጋርም ግንኙነት የላትም። ላለፉት በርካታ ዓመታት ራሷን በራሷ እያስተዳደረች ነው።

እጅግ ሰለማዊ ፣ የተረጋጋ ፣ ዴሞክራሲያዊ ምርጫ በማድረግ እና ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር በማድረግ ትወደሳለች።

#TikvahEthiopia #ቲክቫህኢትዮጵያ
#Somaliland

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray 🔴 " ተኩስ ተከፍቶብኝ መኪናዬ ላይ ጉዳት ደርሷል " - አቶ ሰለሙን መዓሾ 🟠 " መረጃው ከእውነት የራቀ ነው። የተኮሰበት ሰው የለም " - አቶ ገብረ ተክለሃይማኖት 🔵 " ፓለቲከኞች የልዩነታችሁ ጣጣችሁን እዛው ጨርሱት ወደ ሰራዊቱ አታጋቡት " - ጀነራል ህንፃ ወ/ጊዮርጊስ የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር ከፍተኛ አመራር ከተቃጣባቸው የግድያ ሙከራ ማምለጣቸውን ተሰምቷል። የጊዚያዊ…
#Update

የትግራይ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን በማዕከላዊ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ላይ የተደረገውን የግድያ ሙከራ ወንጀል ማጣራት መጀመሩን አስታውቋል።

ኮሚሽኑ በይፋዊ የማህበራዊ ሚድያ ገፁ በሰጠው ማብራርያ ፤ " ህዳር 8/2017 ዓ.ም ከቀኑ 8 :00 ሰዓት አካባቢ ከአክሱም ወደ መቐለ ከተማ በመኪና በመጓዝ ላይ የነበሩት የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ሰለሙን መዓሾ ላይ የተቃጣው የግድያ ሙከራ የሚያጣራ ቡድን ተቋቁመዋል " ብሏል።

አጣሪ ቡድኑ ከፓሊስ እና ከፍትህ አካላት የተወጣጣ እንደሆነ ገልጿል።

የግድያ ሙከራ ወንጀሉ ተፈፅሟል ተብሎ በማህበራዊ ሚድያ የትስስር ገፆች ከተሰራጨበት ደቂቃ ጀምሮ ጥብቅ የማጣራት ስራ መጀመሩ አብራርቷል።

ኮሚሽኑ የማጣራት ሂደቱ እንዲሳካ የህብረተሰቡን ትብብር ጠይቋል። የማጣራት ሂደቱ የሚጎዱ በማህበራዊ ሚድያ የሚነዙ ሁለት ፅንፍ የያዙ አሉባልታዎች እንዲቆሙ አሳስቧል።

የሚደርስበትን የምርመራ ውጤት ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርግ ቃል ገብቷል።

የግድያ ሙከራ ተደርጎበታል የተባለው ቦታ የማይቅነጣል ወረዳ ሲሆን የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ገብረ ተክለሃይማኖት ለቪኦኤ በሰጡት ቃል ፣ ጉዳዩን ከወረዳው የጸጥታና ፖሊስ አባላት ማጣራታቸውን ገልፀው፣ " መረጃው ከእውነት የራቀ ነው። የተኮሰበት ሰው የለም " ማለታቸው ይታወሳል።

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia