TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#OFC

“ አሁንም ቢሆን ሀገራዊ ምክክሩ በሚሄድበት አቅጣጫ እርካታ የለንም ” - ኦፌኮ

ከዚህ ቀደም በምክክሩ እንደማይሳተው ገልጾ የነበረው የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረንስ (ኦፌኮ) አሁንም እየተሳተፈ እንዳልሆነ፣ ኮሚሽኑ በሚሄድበት አቅጣጫ እርካታ እንደሌለው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጿል።

ፓርቲው ከዚህ ቀደም በሀገራዊ ምክክሩ እንዲሳተፍ ቢጋበዝም በምክክሩ እንዳልተገኘ አስታውሷል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በበኩሉ፣ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ሥራውን መቀጠሉን እየገለጸ ነው፤ አሁንስ ፓርቲው ከኮሚሽኑ ጋር ተቀራርቦ ለመስራት አላሰበም ? ከምክክሩ የወጣበት ምክንያትስ ምንድን ነው ? ምላሽስ አላገኘም ? ሲል ጥያቄ አቅቧል።

ፓርቲው ምን ምላሽ ሰጠ ?

“ በእርግጥ ከዚህ ቀደምም ጥሪ ተደርጎልን ነበር። ችግሩ ከዝግጅት ጀምሮ ያለው እንቅስቀሴ አሳታፊ አልነበረም።

ሲጀመር የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ተጠሪነቱ 'ለጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤት ይሆናል’ ተባለ፣ ከዚያ ተመልሶ ‘ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይሆናል’ ተባለ። 

ይሄ ልዩነቱም አልታየንም። ምክንያቱም የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትም በገዢው ፓርቲ የተሞላ ስለሆነ ገልተኛነቱ ያን ያክል አስተማማኝ እንዳልሆነ ነው የምንረዳው። 

ምክንያቱም የሌሎች ተሳትፎ ወይ የለም ወይ በጣም አናሳ ነው፤ ኢንሲግኒፊካንት የሚባል ደረጃ ማለት ነው።

የኛ ሀሳብ ፓለቲካዊ ውይይቶች በፓለቲካ ኃይሎች መካከል መካሄድ ይኖርባቸዋል፣ ሁሉንም ኃይሎች አካታች መሆን አለበት የሚል ነው።

እኛ ሕዝብ ማወያየትን አንጠላም ወይም አናናንቅም ነገር ግን ከሕዝብ ጋር ከመድረሱ በፊት ወይም እየደረሰም እያለ ሌሎች የፓለቲካ ኃይሎች ሊነጋገሩበትና ሊፈቷቸው  የሚገቡ ነገሮች አሉ። 

ለምሳሌ በተለያዩ አካባቢዎች የኛ ፅሕፈት ቤቶች ተዘግተው ባሉበት፣ አባሎቻችንን ሰብስበን ማነጋገር ባልቻልንበት ሁኔታ፣ ለሀገራዊ ምክክሩ አጀንዳ መፍጠር የሚባለው ነገር ውስጥ መሳተፍ አስፈላጊ አይደለም።

እንደገናም ጦርነት እየተካሄደ ሀገራዊ ምክክር ብሎ ነገር ምንድን ነው? ይሄ እርስ በእርሱ የሚጋጭ ነገር ነው።

ይሄን እርስ በእርስ የሚጋጨውን ነገር የሆነ ጋፕ ስጡት፣ ለመነጋገር፣ ለመወያየት እድል ይሰጠው አገር እየተጠበቀ አገር ቢነጋገርበት ጥሩ ይሆናል በሚል ጥያቄ አቅርበን ነበር።

ይሄን የኛን ሀሳብና ጥያቄ ምንም ከዚህ ግባ አላሉትም። ምናልበት የተሻለ ነገር ቢያመጡ እኛም አጨብጭበን እንቀበላቸዋለንና እንዲሄዱ ነው የተውናቸው።

ኦፌኮ ብቻ ሳይሆን ሌሎች ፓርቲዎች አሉ እንደዚህ ያደረጉ። ጊዜና መነጋገር የሚፈልጉ፣ አንድ ወገንን ብቻ ተጠያቂ ከማድረግ እንድንቆጠብ የሚያደርጉ ነገሮች አሉ።

ስለዚህ ነገሮቹ መፍትሄ ካላገኙና የተወሰነ አቅጣጫ ካልተቀመጠላቸው እንዲያው ለመሳተፍ ተብሎ የምንሳተፍበት ምክንያት አይኖርም። 

አሁንም ቢሆን ሀገራዊ ምክክሩ በሚሄድበት አቅጣጫ እርካታ የለንም። እርካታ ቢኖረንና ብንሳተፍበት ጥሩ ነበር ”
ብሏል።

ለቀረበበት ትችት ምላሽ እንዲሰጥ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ጥያቄ ያቀረበ ሲሆን፣ ኮሚሽኑ ለጊዜው በተደጋጋሚ ስብሰባ ላይ መሆኑን በመግለጹ ምላሹን እንደሰጠ የሚቀርብ ይሆናል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
ፎቶ፦ ዛሬ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ አንድ መርካቶ ጃቡላኒ ህንፃ በተለምዶ " ድንች በረንዳ " እየተባለ በሚጠራው ቦታ ላይ የእሳት ቃጠሎ አደጋ ተነስቶ ነበር።

እሳቱ ከቀኑ 6:30 ሰዓት ላይ የተነሳ ሲሆን ሳይዛመትና የከፋ ጉዳት ሳያደርስ መቆጣጠር እንደተቻለ የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ገልጿል።

ስለ አደጋው ምክንያት የተባለ ነገር የለም።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ እሳቱ በተነሳበት ወቅት የእሳትና ከደጋ ሥራ አመራር ኮሚሽንን ለማነጋገር ሞክሮ ነበር። አንድ የኮሚሽኑ አካል በቦታው ሱቆች እየተቃጠሉ እንደነበር ገልጸዋል።

እኚሁ አካል በሥራ እየተጣደፉ ስለነበር ወደ በኃላ ዝርዝር ሁነቱን እንደሚያሳውቁ ገልጸዋል። በቃላቸው ከተገኙ ቀጣይ ተጨማሪ ማብራሪያ የምናቀርብ ይሆናል።

በቅርቡ መርካቶ " ሸማ ተራ " ከፍተኛ የእሳት አደጋ ደርሶ በርካታ ዜጎች ንብረታቸውን ማጣታቸው የሚዘነጋ አይደለም። የዚሁ የአደጋው ምክንያት እና አጠቃላይ የደረሰው ውድመት " ተመርምሮና ተጣርቶና ለህዝብ ይፋ ይደረጋል " ከተባለ ሳምንታት ቢቆይም እስካሁን በይፋ የተባለ ነገር የለም።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

የፎቶ ባለቤት ፦ የአዲስ አበባ እሳት አደጋና ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን

@tikvahethiopia
#አቪዬሽን #ኢትዮጵያ

🔴 “ ድርጅታችንን እስከመዝጋት የሚያደርስ ኢፍትሃዊ ችግሮችን ተጋፍጠን ያለንበት ሁኔታ አለ ” - ካፒቴን ሰለሞን ግዛው

🔵 “ ዘርፉን የተሻለ ለማድረግ የተሻለ ፓሊሲ እየቀረጸ ይገኛል ” - አለሙ ስሜ (ዶ/ር)


አቢሲኒያን የበረራ አገልግሎት አቬዬሽን አካዳሚ የፓይለት ማሰልጠኛ የግል ድርጅት ዛሬ የ25ኛ ዓመት የብር እዩበልዩ በዓሉን በስካይ ላይት ሆቴል አክብሯል።

በዓሉን ባከበረበት ወቅትም በዘርፉ ያሰለጠናቸውን ፓይለቶችን አስመርቋል።

የበረራ ትምህርት ቤቱ ሥራ አስኪያጅ ካፒቴን ሰለሞን ግዛው፣ የአቬሽኑ ዘርፉ መንግስት ልዩ ድጋፍ ሊያደርግ እንደሚገባ በአጽንኦት አሳስበዋል።

እንደ አቢሲኒያን ድርጅት በአቬሽን ዘርፍ ፈር ቀዳጅ ሥራ መስራት እንዲቻል በፓሊሲ የተደገፈና የማያሻማ ሁለንተናዊ ድጋፍ በመንግስት በኩል ሊደረግላቸው እንደሚገባ ነው የገለጹት።

ድርጅቱ ድጋፍ በማጣቱ እየሰራ ያለው 20 በመቶ ብቻ እንደሆነም በግልጽ ተናግረዋል።

“ በተለይም በከፍተኛ ካፒታል፣ ወጪ፣ ኢንሹራንስ የአቬሽን ዘርፍ ትልቅ ጫና እየተደረገበት ስለሆነ መንግስት የአቬሽን ዘርፉን ልዩ ባህሪ ግምት ውስጥ ያስገባ ድጋፍ ሊያደርግልን ይገባል ” ነው ያሉት።

“ ድርጅታችንን እስከመዝጋት የሚያደርስ ኢፍትሃዊ ችግሮችን ተጋፍጠን ያለንበት ሁኔታ አለ ” ያሉት ሥራ አስኪያጁ፣ “ የአቬሽን እንቅስቃሴ ድርግም ከማለቱ በፊት መንግስት በባለጉዳይነት እንዲታደገን እጠይቃለሁ ” ብለዋል።

በፕሮግራሙ የተገኙት የትራንስፖርትና ሎጂስቲክ ሚኒስቴር ሚኒስትር አለሙ ስሜ (ዶ/ር) ንግግር ባደረጉበት ወቅት፣ ለዘርፉ “ የግሉ ተሳትፎ እጅግ ወሳኝ ነው። መንግስትም ይህንን ስለተመለከተ ነው ለባለሃብቶች ዘርፉን ክፍት ያደረገው ” ሲሉ ተደምጠዋል።

“ የግሉ ሴክተር በአየር ትራንስፓርት መሳተፍ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ካመደገፍ አንጻር የማይተካ ሚና አለው ” ብለዋል።

“ ካፒቴኑ የገለጿቸውን ችግሮች ለመቅረፍ ተግዳሮቶቹ ተጠንተው ውይይት እየተደረገባቸው ነው። መንግስት የሚጠበቅበትን ሚና የሚጫወት መሆኑን እገልጻለሁ ” ሲሉ ካፒቴን ሰለሞን ለጠቀሷቸው የዘርፉ ችግሮች የመፍትሄ ሀሳብ ሰጥተዋል።

ሚኒስትሩ፣ “ ጥቂት የግል ሴክተሮች በዘርፉ ቢሳተፉም በተለይ አቢሲኒያን ፍላይት የአየር አምቡላንስ አገልግሎት ከመስጠቱ አንጻር እጅግ ሊመሰገን ይገባል ” ብለዋል።

“ ግን ከኢትዮጵያ ስፋት፣ ሕዝብ ብዛት፣ ኢኮኖሚ አንጻር አሁን ያለን የበረራ አገልግሎት ኦፕሬተሮች ብዛት በቂ አይደለም። ያሉትም ራሳቸውን ማሳደግ፣ ማስፋፋት አለባቸው። አዳዲስ ኦፕሬተሮችም ወደ ዘርፉ መግባት አለባቸው ” ነው ያሉት።

መንግስት ዘርፉ ለግል ባለሃብቶች ምቹ እንዲሆን እንቅፋቶች እንዲቀረፉ እየሰራ መሆኑን የገለጹት ሚኒስትሩ፣ “ ዘርፉን የተሻለ ለማድረግ የተሻለ ፓሊሲ እየቀረጸ ይገኛል ” ብለዋል።

ተግዳሮቶቹንም ጥናት አጥንቶ ጨርሶ ውይይት እየተደረገበት ስለመሆኑ አስረድተው፣ ዘርፉ ገና ያልተየካ የኢንቨስትመንት ዘርፉ በመሆኑ አቅሙና እውቀቱ ያላቸው የግል ባለሃብቶች ኢንቨስት ኢንዲያደርጉ ማኒስትሩ ጥሪ አስተላልፈዋል።

#TikvahEthiopiaFamyAA

@tikvahethiopia
#Urgent🚨

እየደበደቡት ጥርሱን አውልቀውታል። ሙሉውን ቪዲዮ ለመመልከት ሰቀጠጠኝ። አጋቾቹ 800 ሺሕ ብር ጠይቀዋል” - እርዱኝ ያሉ የታጋች ወንድም

በባህር ዳር ዩቨርቨሲቲ የ4 ዓመት የመካኒካል ኢንጅነሪንግ ተማሪ የነበረው ወጣት ሙላት ተቀባ አስረሴ በሊቢያ በአጋቾች ተይዞ በድብደባ አካላዊ ጉዳት እየደረሰበት መሆኑን ቤተሰቦቹና የቅርብ ሰዎቹ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጹ።

የታጋች ወንድም አቶ ደጉ ተቀባ አስረሴ፣ “ ጎንደር ጦርነት ስላለ ገንዘቡን ለመላክ ተንቀሳቅሶ መስራት አልተቻለም። ቦታ ነበረችኝ ለመሸጥ እንኳ በዚሁ በጸጥታው ችግር ገዢ የለም። እባካችሁ ወንድሜን አድኑልኝ ” ሲሉ ተማጽዋል።

ታጋቹ ያለበትን ሁኔታ ሲገልጹም፣ “ እየደበደቡት ጥርሱን አውልቀውታል። ሙሉውን ቪዲዮ ለመመልከት ሰቀጠጠኝ። አጋቾቹ 800 ሺሕ ብር ጠይቀዋል። ገንዘቡን መላክ አልቻልኩም። ወላጆቻችን አዛውንቶች ናቸው ” ነው ያሉት።

በሰሜን ጎንደር ዞን ጠለምት ወረዳ አቃቢ ሕግ በመሆን ተቀጥረው እንደሚሰሩ ገልጸው፣ አሁን ባላቸው አነስተኛ ደመወዝ የተጠየቀውን ገንዘብ ማሟላት እንደማይችሉ አስረድተዋል።

“ አጋቾቹ ‘ቶሎ ካላክ እንገለዋለን እያሉኝ’ ነው ” ያሉቴ አቶ ደጉ፣ ወጣቱ ዘንድሮ ተመራቂ እንደነበር፣ ወደ አውሮፓ ድንበር ሊያቋርጥ ሲል ከታገተ ወራቶች እንዳስቆጠረ ገልጸዋል።

በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ የሚገኙ ሁለት የታጋቹ የቅርብ ጓደኞች በበኩላቸው፣ ተማሪ ሙላት ታግቶ እየተደበደበ እንደሆነ፣ ከዩኒቨርሲቲው ደብዳቤ አጽፈው ገንዘብ እያሰባሰቡ መሆኑን ነግረውናል።

ከጓደኞቹ አንዱ በሰጠው ቃል፣ “ ተማሪ ሙላት ወደ አውሮፓ ሊወጣ ሲል ታግቶ ይገኛል። እንደኛ ተመራቂ ነው የነበረው በዚህ ዓመት። የሰሜን ጎንደር ዞን ጠለምት ወረዳ ነዋሪ ነው ” ብሏል።

የታጋቹ ወንድምና ጓደኞቹ፣ ታጋቹ በአጋቾች እየደረሰበት ያለውን ስቃይ የሚያሳይ ቪዲዮ የላኩ ሲሆን፣ ከላይ ተያይዟል።

መርዳት ለምትሹ 1000281326795 የአቶ ደጉ ተቀባ አስረሴ የንግድ ባንክ ሒሳብ ቁጥር ነው። አቶ ደጉን በዚህ ስልክ 0931494332 ማግኘት ይቻላል።

የፖሊ ግቢ ተማሪዎችም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000660181036 እና በአቢሲንያ ባንክ 209476797 አካውንት በመክፈት ድጋፍ እያሰባሰበ ነው።

#TikvahErhiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
#ብርሃን_ባንክ
#በቀላሉ_ይቀበሉ!

ከውጪ ሃገራት የሚላክልዎትን ገንዘብ በባንኩ የስዊፍት ኮድ (BERHETAA) እና ከብርሃን ጋር በሚሰሩ አለምአቀፍ የገንዘብ አስተላላፊዎች #ሪያ #ዳሃብሽል #ዌስተርን_ዩኒየን #መኒግራም #ትራንስ_ፋስትና #ወርልድ_ረሚት በኩል በቀላሉ ይቀበሉ!
#moneytransfer #Stressfreebanking #berhanbank #bank #finance #bankinethiopia

ከታች የሚገኙትን ሊንኮች በመጫን የማህበራዊ ድህረ-ገጾቻችንን ይቀላቀሉ!
➡️ Facebook
➡️ Telegram
➡️ Instagram
➡️ Twitter
➡️ LinkedIn
➡️ YouTube
#InfinixEthiopia

የኢንፊኒክስን Note, Hot, Zero ስማርት ስልኮችን እና የኢንፊኒክስ TVን ሲገበያዩ አብሮት ካለ ወዳጅ ዘመድ ወይም ጓደኛ ጋር በመረጡት ስፍራ ፎቶ በመነሳት #InfinixEthiopia የሚለውን ሃሽ ታግ በመጠቀም የማህበራዊ ገጾት ላይ በመለጠፍ የዛንዚባር የቢዝነስ ክላስ ደርሶ መልስ የአውሮፕላን ቲኬት ፣ የኢንፊኒክስ ስማርት ቲቪ ፣ የኢንፊኒክስ ላፕቶፕ እንዲሁም ሌሎች አጓጊ ሽልማቶችን ያሸንፉ፡፡

መመሪያ

1. የኢንፊኒክስ ኢትዮጵያን ፌስ ቡክ ፣ ኢንስታግራም እና ቲክቶክ ገጾችን ፎሎው ያድርጉ፡፡
2. የተነሱትን ፎቶ በመረጡት ማህበራዊ ሚዲያ ሲለጥፉ የኢንፊኒክስ ኢትዮጵያን ገፅ ከፖስቶት ጋር ታግ ያድርጉ፡፡
3. #InfinixEthiopia የሚለውን ሃሽታግ መጠቀሞን አይርሱ፡፡

Tag ሲያደርጉ ለ Facebook @InfinixMobileEthiopia ፣ ለ Instagram @infinixethiopia ለ TikTok @Infinixet እና ለ Telegram @Infinixeth ሜንሽን ማድረግ እንዳይረሱ።
#MPESASafaricom

ለማይቋረጥ የኢንተርኔት ጌም ወሳኙ የማይቋረጥ ኢንተርኔት ነው ፤ አሁኑኑ የሳፋሪኮምን የ4G ዋይ ፋይ ጥቅል ከM-PESA ሳፋሪኮም mini app በመግዛት በጌማችን እንፍታታ!


#SafaricomEthiopia
#FurtherAheadTogether
“ የትምህርት ጥራት ከዓመት ወደ ዓመት እየወረደ መጥቷል ” - ሰሎሞን አብርሃ (ዶ/ር)

የአሜሪካ ኤምባሲ በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ በኩል በኢትዮጵያ ለራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲዎች ማጠናከሪያ የሚሆን 522 ሺሕ ዶላር የድጋፍ ስምምነት አድርጓል።

የድጋፍ ስምምነቱ በኢትዮጵያ ዘጠኝ ዩኒቨርሲቲዎች በቀጣይ ራስ ገዝ እንዲሆኑ የሚያርችላቸውን ሁኔታዎች ለማመቻቸት የሚረዳ መሆኑ ተገልጿል።

ስለስምምነቱ ምንነት የጠየቅናቸው የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ፕሬዜዳንት በላይ ካሳ (ፕ/ር)፣ “ ዛሬ ከአሜሪካ ኤምባሲ ጋር የተፈራረምነው ስምምነት በኢትዮጵያ ዘጠኝ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎችን ወደ ራስ ገዝነት እንዲሸጋገሩ ቅድመ ዝግጅት የማድረጊያ የሚሰጥ ድጋፍ የሚይዝ ነው ” ብለዋል።

የከፍተኛ ትምህርት ተቋምን ወክለው በመርሃ ግብሩ የተገኙት ሶሎሞን አብርሃ (ዶ/ር) በበኩላቸው፣ የድጋፍ ስምምነቱ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመቀጠል ዘጠኝ ዩኒቨርሲቲዎች አቅማቸውን አጠናክረው በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ራዝ ገዝነት ለማሸጋገር እንደሚረዳ አስረድተዋል።

ዘጠኙ ዩኒቨርሲቲዎች መቼ ራስ ገዝ እንደሚሆኑ ማብራሪያ እንዲሰጡ ሲጠየቁም፣ ዩኒቨርሲቲዎቹ እንደዬ አፈጻጸማቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ ራስ ገዝ እንደሚሆኑ፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሽግግር ጊዜ በዚህ አመት እንደሚጠናቀቅ፣ በ2018 ዓ/ም ከዘጠኙ ዩኒቨርቲዎች ውስጥ የተወሰኑት ወደዚሁ ጉዞ እንደሚገቡ አመላክተዋል።

ጥናት እንደሚያመለክተው፣ “ የትምህርት ጥራት ከዓመት ወደ ዓመት እየወረደ መጥቷል ” ብለው፣ “ የተሰሩት ሥራዎች አመርቂና አበረታች ቢሆንም የዩኒቨርሲቲዎች መስፋፋት እንዳለ ሆኖ ትምህርት ጥራት ላይ ግን ያለው ውጤት በጣም ስብራት ያለበት ነውና መታረም ይገባዋል ” ሲሉ ገልጸዋል።

“ በአጠቃላይ በብዙ ፋክተሮች አስተዋፅኦ ያደረጉበት ጉዳይ ነው የትምህርት ጥራት መጓደል። አንዱና ዋነኛ ተብሎ የተወሰደው ደግም የገነባናቸው ዩኒቨርሲቲዎች ብቃታቸው፣ ውጤታማነታቸው፣ ቀልጣፋነታቸው በጣም ችግር ላይ ነው ” ሲሉ ተናግረዋል።

“ ብቁና ተወዳዳሪ ትምህርት ተቋም አልፈጠርንም። ብቁ ተወዳዳሪ ተቋማትን ለመፍጠር ደግሞ ከሚደረጉ ዘርፈ ብዙ ሥራዎች ውስጥ አንዱና ዋነኛው ተቋማትን ራስ ገዝ ማድረግ ነው ” በማለት አክለዋል።

ዩኒቨርቲዎች ራስ ገዝ ሲሆኑ የትምህርት ጥራት፣ ጥሩ ምርምር እንደሚኖር ያስረዱት ሰለሞን (ዶ/ር)፣ አዲስ አበባ የመጀመሪያው ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ መሆኑን በማስታወስ ዩኒቨርሲቲዎችን በአንድ ጀንበር ራስ ገዝ ማድረግ ስለማይቻል የሁሉም ርብርብ እንደሚያሻ አስገንዝበዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#AddisAbaba

" በቦታው ተመሳሳይ ችግር እንዳያጋጥም ምክረ ሃሳብ ቀርቧል። ያቀረብነው ምክረ ሃሳብ ቦታው እንደ አዲስ በመልሶ ማልማት እንዲለማ ነው " - የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን

ከአንድ ወር ባነሰ ጊዜ ውስጥ በትላንትናው ዕለት ለሁለተኛ ጊዜ የእሳት አደጋ ያጋጠመው በአዲስ አበባ ከተማ መርካቶ ገበያ የሚገኝ አካባቢ፤ " በመልሶ ማልማት እንዲለማ " ምክረ ሃሳብ ቀረበ።

ምክረ ሃሳቡን ያቀረበው የአዲስ አበባ ከተማ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ነው።

ትላንት እሁድ ህዳር 8/2017 እኩለ ቀን ገደማ የእሳት አደጋ የደረሰበት የመርካቶ ገበያ ስፍራ፤ በተለምዶ " ድንች ተራ " የሚል ስያሜ ያለው ነው።

ስፍራው ከሁለት ሳምንት በፊት በተመሳሳይ አደጋ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበት ከነበረው " ነባር የገበያ ማዕከል " በቅርብ ርቀት ላይ የሚገኝ ነው።

የእሁዱ ቃጠሎ የደረሰበት ስፍራ፤ " በነባር የገበያ ማዕከል " ላይ የሚነግዱ ነጋዴዎች ንብረቶቻቸውን የሚያስቀምጡበት መጋዘን እንደነበር የአካባቢው ነዋሪዎች " ለኢትዮጵያ ኢንሳይደር " ድረገጽ ተናግረዋል። 

የእሳት አደጋው " ጌሾ ግቢ " ተብሎ በሚጠራው ስፍራ ከሚገኘው መጋዘን በተጨማሪ በአቅራቢያው የሚገኙ መደብሮች እና መኖሪያ ቤቶች ላይ ውድመት አድርሷል። 

ትላንት በአደጋው ወቅት በርካታ የአካባቢው ነዋሪዎች እና ነጋዴዎች የእሳት ቃጠሎው ወደ ሌሎች የገበያ ማዕከሎች እና መደብሮች እንዳይዛመት በስጋት ሲያስተውሉ ነበር።

የተወሰኑ የአካባቢው ወጣቶች እና ከእሳት አደጋ ተከላካይ ሰራተኞች ጋር በመሆን ቃጠሎውን በቁጥጥር ስር ለማድረግ ርብርብ ሲያደርጉ ነበር።

በአንድ ሰዓት ተኩል ውስጥ በቁጥጥር ስር የዋለውን የእሳት አደጋ ለመከላከል፤ ሰባት የውሃ ቦቴዎች እና 18 የአደጋ መቆጣጠር ተሽከርካሪዎች ተሰማርተው እንደነበር የአዲስ አበባ ከተማ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ንጋቱ ማሞ ለ " ኢትዮጵያ ኢንሳይደር " ድረገጽ ገልጸዋል።

ከእነዚህ ተሽከርካሪዎች በተጨማሪ የኮሚሽኑ እና የቀይ መስቀል ማህበር አምቡላንሶች፤ በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸውን ግለሰቦች ወደ ህክምና ተቋማት በመውሰድ ተሳትፈዋል። 

በትላንቱ የእሳት አደጋ ሶስት የአካባቢው ነዋሪዎች እና ሁለት የኮሚሽኑ ሰራተኞች ላይ ቀላል ጉዳት ደርሷል።

ከሁለት ሳምንት በፊት በዚሁ አካባቢ በደረሰው ተመሳሳይ አደጋ፤ ዘጠኝ ሰዎች መጎዳታቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ማስታወቁ አይዘነጋም።

የትላንቱ አደጋ ከደረሰበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ዛሬ ረፋድ ድረስ፤ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ባልደረቦች አካባቢውን በገመድ በማጠር ጥበቃ ሲያደርጉ ነበር።

ክልከላውን አልፈው ለመግባት ሲሞክሩ የነበሩ ነዋሪዎች እና ነጋዴዎችን፤ የፖሊስ አባላቱ ወደ ቦታው እንዳይጠጉ በኃይል ሲከላከሉም ነበር።

ፖሊሶች እና የእሳት አደጋ ተከላካይ ሰራተኞች ከመድረሳቸው በፊት ግን የተወሰኑ ነጋዴዎች ንብረቶቻቸውን ከቃጠሎ ማትረፍ ችለዋል።

በዚህም ምክንያት በአደጋው " የከፋ ጉዳት " አለመድረሱን አቶ ንጋቱ አስረድተዋል።

ቃጠሎው በቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላም፤ ነጋዴዎች ንብረታቸውንን ከአካባቢው ለማራቅ ሲጥሩ ታይተዋል። 

ነጋዴዎች፤ አካባቢው በተደጋጋሚ የእሳት አደጋ እያጋጠመው በመሆኑ ምክንያት " መንግስት ከስፍራው ያነሳናል " የሚል ከፍተኛ ስጋት አላቸው።

የአዲስ አበባ ከተማ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አካባቢውን " ለአደጋ ተጋላጭ " በሚል አስቀድሞ መለየቱን የገለጹት አቶ ንጋቱ፤ በቦታው ተመሳሳይ ችግር እንዳያጋጥም ምክረ ሃሳብ ማቅረቡን አስረድተዋል። 

" ያቀረብነው ምክረ ሃሳብ ቦታው እንደ አዲስ በመልሶ ማልማት ወይም የአደጋ ደህንነት መስፈርትን ቧሟላ፣ ደረጃውን በጠበቀ መንገድ መገንባት ይኖርበታል ነው። ምክረ ሃሳቡን ተቀብሎ በመልሶ ማልማት ለመስራት የተጀመሩ ስራዎች እንዳሉ መረጃው አለን። በሂደት ላይ ነው ያለው። ታምኖበታል። ምን አልባትም በዚህ አመት ሊጀመር ይችላል ብዬ አስባለሁ " ሲሉ ተናግረዋል።

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የኢትዮጵያ ኢንሳይደር ድረገጽ ነው።

#AddisAbaba #Merkato #EthiopiaInsider

@tikvahethiopia