TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ኢምፓወር አዲስ ቲኬት ሽያጭ ተጀምሯል

ህዳር 7 እና 8 ቀን 2017 በሚሊኒየም አዳራሽ የሚካሄደው የሔለን ሾው ኢምፓወር አዲስ ዝግጅት ትኬት ሽያጭ  በቴሌብር ተጀምሯል::

ነፃ የጤና ምርመራን ባካተተው በዚህ ዝግጅት በተለያዩ ርዕሶች ውይይቶች፤ የመገበያያ መድረክ፤ የሙዚቃና የመዝናኛ ዝግጅቶች፤ ከሼፎች ጋር የሚደረግ የምግብ ዝግጅት፤ ደራሲያንን የማግኘትና የማስፈረም፤ ሠዓሊያንን ሌሎች ባለሙያዎችን የማግኘትና ጥያቄ የመጠየቅ እድል ያካትታል፡፡

ይህ ዝግጅት የተዘጋጀው ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ሲሆን ትኬት ሽያጭ በቴሌብር ተጀምሯል::

በቅድሚያ ሲገዙ 300 ብር : በዕለቱ 500 ብር::

ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም ቻነላችንን ይከታተሉ!
https://t.iss.one/EmpowerAddis2024

እንዲሁም ለማብራሪያ https://youtu.be/Havbi-osmtc?si=xGRP-f8Z86tjerVN
Elegant and functional office furniture,  tailored to your needs.
We offer free design and layout consultations to create a workspace that works for you !

Order yours today
For any inquiry :
Call us  📲   0905848586
Text us 💬   @Rosew0od

Join our telegram channel   👇
https://t.iss.one/R0seWood
https://t.iss.one/R0seWood
https://t.iss.one/R0seWood
⚽️አዲስ ነገር ለኳስ አፍቃሪያን...

ፍላጎታችሁን ሰምተናል!
አዲሱን ሜዳ ስፖርት ፓኬጅ በአሪፍ ዋጋ እንኩ ብለናል!

👉ከሕዳር 16 ጀምሮ ፈጥነው ወደ ሜዳ ስፖርት ፓኬጅ ከፍ ይበሉ! ሁሉንም የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታዎችን፣ የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ፣ ሎችም ዋና ዋና እግር ኳስ እና ምርጥ ምርጥ መዝናኛዎችን ያካተቱ ከ129 በላይ ቻናሎችን በወር በ1699 ብር ብቻ!

ℹ️ ለአዲሱ ፓኬጅ የስትሪም አገልግሎት የሚጀምረው የካቲት 2017 በኋላ ይሆናል

ደንብና ሁኔታዎች ተፈፀሚነት አላቸው! ለበለጠ መረጃ
👇
www.dstv.com/en-et

ደንበኝነትዎን ያራዝሙ!
👇
https://bit.ly/48oVhj8

#DStvEthiopia #ሁሉምያለውእኛጋርነው #MedaSport
🔈#የአርሶአደሮችድምጽ

" እኛ ተጠቃሚ ነን አንልም ሚጠቀመው ሌላ አካል ነው " - ቡና አምራች አርሶአደሮች

በሲዳማ ክልል 170 ሺህ ሄክታር በቡና የተሸፈነ ሲሆን ከዚህም ውስጥ 143 ሺህ ሄክታሩ ምርት የሚሰጥ ነው ከዛ 159 ሺህ ቶን ይጠበቃል። አጠቃላይ 401 ሺህ ቡና አምራች የሆነ አርሶ አደርም በክልሉ በዚሁ ዘርፍ ተሰማርቶ ይገኛል።

ሆኖም ቡና አምራች አርሶአደሮች ከተጠቃሚነት አንጻር ቅሬታ ሲያቀርቡ ይደመጣል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በክልሉ በተለያዩ አካባቢዎች ቡናን የሚያመርቱ አርሷደሮችን ጠይቋል።

ቡና አምራች አርሷደሮች ምን አሉ ?

የቡና ተክል ተክለን ፍሬ ለማግኘት ከ3 እስከ 5 ዓመት እንደሚፈጅባቸው የነገሩን አንድ አርሶአደር፥ ቡና በማምረት ውስጥ ያለው ድካም ቀላል እንዳልሆነና ነገር ግን ፍሬው ሲታይ ድካሙ ሁሉ እንደሚጠፋ ይገልጻሉ።

" ሆኖም ለገቢያ ሲወጣ የሚቀርብበት የሽያጭ ዋጋ ልብ ሰባሪ ነው" ሲሉ ነው የተናገሩት።

" ልክ ካመረትን በኋላ ለነጋዴዎች ነው ምናስረክበው ለማህበራት ሚያስረክቡም አሉ። አምና መጨረሻው 30 ብር ነበር ዘንድሮ 35 ብር ነበር የጀመረው አሁን 45 ብር ደርሷል በኪሎ ይህ ደሞ ከልፋታችን አንጻር በጣም የወረደ ሂሳብ ነው " ሲሉ ያስረዳሉ።

" እኛ ተጠቃሚ ነን አንልም ሚጠቀመው ሌላ አካል ነው (በስም ያልገለጿቸው) እንደውም አንዳንዴ መሬቱን ሽጠን ወደሌላ ዘርፍ እንግባ ብለንም እናስባለን፣ በዚህ ሰዓት ቡና ብቻ አምርቼ ኖራለው ብሎ ማሰብ ከባድ ነው " ሲሉም ጉዳቱን ያነሳሉ።

" በአሁን ገበያ አንድ ሰራተኛ ቡና ሊለቅም እንኳን ሚገባ በ120 ብር ነው ሚሰራው አሁን ላይ የሚሸጠው በ45 ብር ነው ምናልባት 10 ሰው ሊለቅም ከገባ ገንዘቡ ለዛ ብቻ ነው ሚውለው ማለት ነው። እንደውም አምና ለሰራተኛ ብቻ ሰጥተን ነው የገባነው ዘንድሮም ያው ነው " በማለት ቅሬታቸውን ያቀርባሉ።

ለመሆኑ ዋጋውን የሚወስነው ማነው ?

" ዋጋውን እራሳቸው ይወስናሉ እኛ ማን እንደሚወስን የምናውቀው ነገር የለም በዚህ ያህል ተከፈተ ሲባል ነው የምናውቀው ህብረቱም በዚህ ዋጋ ከፈተ ሲባል ነው ምንሰማው፣ ምናልባት ባለሀብቱ አንድ ብር እንኳን አሳልፎ ከገዛ እንኳን ያንን ባለሀብት ተረባርበው እንዴት እንዲህ አደረክ ብለው ወዲያው ይጣሉታል የትኛው አካል እንደዚህ እንደሚያደርግ ግን አናውቅም " ሲሉ አርሶ አደሮቹ ይናገራሉ።

አክለውም፥ " እነሱ እኮ (ቡናውን የሚረከቡት ለማለት ነው) ስራውን በጀመሩ ሦስት እና አራት ዓመት ነው በብልጽግና ማማ ላይ የሚወጡት በጣም አልፈው ነው ሚሄዱት፤ አርሷደሩ እንደለፋ አላገኘም ባለስልጣናቱም ጭምር በእኛ ዘንድ ይታማሉም " ብለውናል።

" የሚመለከተው አካል ቢደርስልን እየተንገዳገድን ነው ወደ መውደቅ እየደረስን ነው ታች ተወርዶ ምን እየተካሄደ ነው ሚለውን አይቶ የቡናን ነገር ቢያይልን የዋጋውን ነገር ቢመለከትልን " ሲሉም ጠይቀዋል።

" ቡናችን ለአርሷደሩ ብቻ ሳይሆን ለሀገር የሚጠቅም ነገር ነው ህብረተሰቡ በዋጋ ማነስ ምክንያት ወደሌላ ምርት ፊቱን ካዞረ ጉዳቱ እንደ ሀገር ስለሆነ የገቢ ምንጭም ስለሚቀንስ መንግስት አርሷደሩን ወርዶ ቢመለከት ቢያወያዩ አርሷደሩ እንዳይጎዳ ቢያደርግ መልካም ነው " ሲሉ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

በጉዳዩ ላይ የክልሉ ቡና ፍራፍሬና ቅመማ ቅመም ባለስልጣንን ጠይቀናል ምላሹን የምናቀርብ ይሆናል።

#TikvahEthiopia

Via @tikvahethmagazine
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
"አርሷደሩ ተጠቃሚ ነው ማለት ይቻላል" የሲዳማ ክልል ቡና ፍራፍሬና ቅመማ ቅመም ባለስልጣን

በሲዳማ ክልል ባለፈው ዓመት 25 ሺህ 572 ቶን ነው ወደ ማከላዊ ገበያ መቅረቡን እና በዘንድሮም ዓመትም በ15 ሺ በማሳደግ ወደ አርባ ሺ ቶን ለማዕከላዊ ገቢያ ለማቅረብ እቅድ መያዙን የክልሉ ቡና ፍራፍሬና ቅመማ ቅመም ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር መስፍን ቃሬ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

ቡና በክልሉ በምን መንገድ ነው ለማዕከላዊ ገቢያ የሚቀርበው?

ዋና ዳይሬክተሩ ቡና አሁን ላይ በሦስት ዋና ዋና መንገዶች እየተሰበሰበ ይገኛል ብለዋል። በዚህም የመጀመሪያው በማኅበራት በኩል የሚሰበሰብ እንደሆነ ገልጸዋል።

በክልሉ ከ77 በላይ የቡና ምርት የሚሰበስቡ መሰረታዊ የህብረት ስራ ማኅበራት እንደሚገኙ አስቀምጠዋል። "እነዚህ [ማኅበራቱ] ከአርሷደሩ ምርቱን ተቀብለው ለዩኒየኑ [የሲዳማ ቡና አብቃይ ዩኒየን] አቅርበው ዩኒየኑ ደግሞ እስከውጪ ኤክስፖርት ያደርጋል" ሲሉ ያስረዳሉ።

ሁለተኛው መንገድ ደግሞ አቅራቢ ነጋዴዎች አማካኝነት የሚሰበሰብ እንደሆነ ነው የገለጹት። " ከ205 በላይ በግል ኢንዱስትሪ ያላቸው አቅራቢ ነጋዴዎች እና 129 በአክሲዮን የሚሰሩ አሉ በእነዚህ እየተሰበሰበ ለላኪዎች ቀርቦ ላኪዎች ደግሞ ቡናውን ኤክስፖርት የሚያደርጉበት አሰራር አለ።" ብለዋል። 

አቶ መስፍን ሦስተኛውን መንገድ ሲገልጹ፥ "ሶስተኛው ደግሞ ሁለት ሄክታር እና ከዛ በላይ ቡና ማሳ ያላቸው አርሷደሮች አሉ 262 ናቸው እነዚህ የራሳቸውን ቡና ብቻ ሰብስበው አድርቀው ለውጭ ገበያ ያቀርባሉ።" ሲሉ ተናግረዋል።

በዚህም፥ "ላኪ የሆኑ አርሷደሮች ቡናቸውን ተደራድረው፤ ጥራት ያለው ቡና አዘጋጅተው እስከ ውጪ ድረስ የሚልኩበት አሰራር አለ" ብለዋል።

አክለውም፥ "ለማኅበራት የሚያስረክቡ ደግሞ ሲያስረክቡ ቅድመ ክፍያ ያገኛሉ፤ ማኅበራቱ ካተረፉ ደግሞ ሁለተኛ ክፍያ ያገኛሉ፤ ዩኒየን ካተረፈው ደግሞ ሶስተኛ ክፍያ የሚያገኙበት አሰራር አለ" ሲሉ ያስረዳሉ።

የመሸጫ ዋጋው ጉዳይስ ?

አቶ መስፍን ዋጋውን ሲያስረዱ፥ አሁን ላይ በክልሉ ሁለት አይነት ቡና እንደሚዘጋጅ ይጠቅሳሉ። "በምዕራብ ዞኖች እና ወረዳዎች አካባቢ ማለትም ከሀዋሳ ጀምሮ እስከ ዲላ በንቴ ያሉ ወረዳዎች ከ47-49 ብር ነው በኪሎ እየሸጡ ያሉት፤ በምስራቅ በኩል ያሉ ወረዳዎች ደግሞ ከ50-70 ብር እየሸጡ ነው ያሉት፤ በየወረዳው ዋጋው የሚለዋወጥበት ሁኔታ ነው ያለው ይህ ማለት የቡናው ጥራትም በዛው ልክ ይለያያል ዋጋው ሚለያየውም ለዛ ነው።" የሚል ምላሻቸውን ሰጥተዋል።

አክለውም፥ "አሁን ያነሳነው ዋጋ [ከ47 - 70 ብር በኪሎ ብለው ከላይ የጠቀሱት] የእሸት ቡና ዋጋ ነው። ከ100 ኪሎ እሸት ቡና ከ 19-20 ኪሎ ደረቅ ቡና ይወጣል። [ይኽም] 5.5 ኪሎ እሸት ቡና አንድ ኪሎ ንጹህ ቡና ይወጣዋል የሚለውን ካሰላን በዛ ማግኘት ይቻላል።" ሲሉ ያስረዳሉ።

አርሶአደሩ ተጠቃሚ ነው ማለት ይቻላል?

ይህንን ጥያቄ ያቀረብንላቸው ዋና ዳይሬክተሩ፥ "አዎ አርሷደሩ ተጠቃሚ ነው ማለት ይቻላል" የሚል ምላሽ ሰጥተውናል። አክለውም "ዝቅተኛ መሬት ያለው አርሷደር ብዙም ተጠቃሚ ላይሆን ይችላል፤ ግን አማካይ እና ደህና መሬት ያለው ተጠቃሚ የሚሆንበት አግባብ አለ" ነው ያሉት።

ይኽን ሲያስረዱም፥ "ምርትና ምርታማነቱን የሚያሳድግ አርሷደር ተጠቃሚ ነው የሚሆነው ዝቅተኛ፣ መካከለኛ እና ከፍተኛ ምርት ሚያገኝ አለ ያ ከፍተኛ ምርት የሚያገኘው የባለሙያ ምክር እና ሳይንሳዊ ፓኬጁን በአግባቡ ተግባራዊ ያደረገ አርሷደር ነው። የተሰጠውን ምክር ቶሎ ተቀብሎ ተግባራዊ የሚያደርግ አርሷደር የተሻለ ተጠቃሚ ነው የሚሆነው።" ሲሉ ይገልጻሉ።

"ቡናን ተክለው ቡናን አምርተው እስከ ኢንዱስትሪ የደረሱ አርሷደሮች አሉ፤ ሁለት እና ከዛ በላይ ሄክታር ያላቸው አርሷደሮች ምርታቸውን እስከ ውጭ ሀገር ድረስ ልከው ሀብታም የሆኑ አሉ፤ በ2016 ዓ.ም እራሱ "Cup of Excellency" ላይ ተወዳድሮ ያሸነፈ አለ፤ ይሄ አርሶአደር ምርቱን አዘጋጅቶ ከ10 ሚልዮን ብር በላይ ነው የሸጠው ይህ ቀላል ነገር አይደለም። ስለዚህ ተጠቃሚነታቸው በሰሩት እና በለፉት ልክ ነው ሚሆነው ማለት ነው።" ሲሉ ያነሳሉ።

አክለውም "የተሻለ መሬት ያለው አርሷደር በቡና ምርት ላይ የሚሳተፍ ከሆነ የተሰጠውን የባለሙያ ምክር በአግባቡ የሚጠቀም ከሆነ እና ፓኬጁን ተግባራዊ የሚያደርግ ከሆነ ቡና ላይ ተጠቃሚ የሚሆንበት አግባብ ነው ያለው።" ሲሉ ተናግረዋል።

#TikvahEthiopia

Via @tikvahethmagazine
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

ሲጠበቁ የነበሩ ሁለት መመሪያዎች ፍትህ ሚኒስቴር ማጽደቁ ተሰምቷል።

መመሪያዎቹ " የሰነደ ሙዓለ ነዋይን ለህዝብ የማቅረብ ግብይት መመሪያ " እና "ራሳቸውን በራሳቸው የሚያስተዳድሩ ድርጅቶች ቁጥጥር መመሪያ  "  ናቸው።

ሁለቱን መመሪያዎች ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ  በትላንትናው ዕለት መዝግቦ አጽድቋቸዋል።

የሰነደ ሙዓለ ነዋይን ለህዝብ የማቅረብ ግብይት መመሪያን በሚመለከት የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ሃና ተልህኩ ዝርዝር ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ሰነደ ሙዓለ ነዋይን በሚመለከት ከዚህ ቀደም የተማከለ እና ሂደቱን የሚቆጣጠር ህግ እና ተቆጣጣሪ አካል ያልነበረ በመሆኑ የሰነደ ሙዓለ ነዋዮችን ማውጣት እና ግብይት በርካታ ችግሮች እንደነበሩበት ገልጸዋል።

በዚህ መሃል ለህዝብ የሚቀርቡ መረጃዎች ምንነት ፣ ለሚቀርቡ መረጃዎች ሃላፊነት የሚወስዱ ሰዎች ማንነት፣ ሃላፊነት እና ግዴታቸው ምን ድረስ ነው፣ ሰነደ ሙዓለ ነዋይ ከወጣ በኋላ በዛ መንገድ የሚገኘው ገንዘብ ለምን ዓላማ እንደሚውል፣ አውጪዎች የሚኖርባቸው ተግባር እና ሃላፊነት ምንድነው የሚለውን ማወቅ ላይ ከዚህ ቀደም በነበሩ ህጎች ያለተዳሰሱ ስለነበር ገበያው በርካታ ችግሮች እንደነበሩበት ዳይሬክተሯ ተናግረዋል።

ይህንን ችግር ለመቅረፍም የካፒታል ገበያ አዋጅን መሰረት በማድረግ አዲሱ መመሪያ መዘጋጀቱን ጠቁመዋል።

መመሪያው በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ውስጥ የሰነደ ሙዓለ ነዋይ ለሽያጭ የሚቀርብበትን እና የሰነደ ሙዓለ ነዋይ ግብይት የሚገዛበት ዝርዝር የያዘ የህግ ማዕቀፍ ነው።

በአዲሱ መመሪያ መሰረት ከአሁን በኋላ ሁሉም ሰነደ ሙዓለ ነዋዮች በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ቀርበው መጽደቅ አለባቸው።

በዚህ ሂደት ላይ የሚሳተፉ አካላት የምዝገባ ሰነዳቸውን ለባለሥልጣኑ አቅርበው ማጸደቅ የሚጠበቅባቸው ሲሆን የምዝገባ ሂደቱም ዝርዝር ሂደቶችን የያዘ ነው።

በአዲሱ መመሪያ መሰረት ከሰነደ ሙዓለ ነዋይ ጋር የተያያዙ ማስታወቂያዎች የሚተላለፉት ይዘታቸው እና ለህዝብ ይፋ የሚደረጉበት መንገድ ባለሥልጣኑ ተመልክቶ ሲያጸድቀው ብቻ ይሆናል።

መመሪያው ካካተታቸው እና ከዘረዘራቸው ጉዳዮች መካከል ዋና ዋናዎቹ :-

1. የሰነደ ሙዓለ ነዋይ ምዝገባ

2. ለኢንቨስተሮች መቅረብ ስላለበት የደንበኛ ሳቢ መግለጫ ይዘት እና የአቀራረብ መንገድ ሂደት እንዲሁም ተያይዞ ስለሚመጣ ሃላፊነት።

3. ስለ ሰነደ ሙዓለ ነዋይ ማስታወቂያ ይዘት እና አቀራረብ እንዲሁም ስለሚያስፈልገው ፍቃድ።

4. የሰነድ ሙዓለ ነዋይ ሽያጭ እና ድልድል
አጠቃቀሙ እና ስራ ላይ ስለሚውልበት አካሄድ እና ሁኔታ።

5. አንድ የሰነደ ሙዓለ ነዋይ አውጪ ሰነደ ሙዓለ ነዋይ ለህዝብ ሽጦ እንደ ህዝብ ኩባንያ በሚንቀሳቀስበት ጊዜ በቀጣይነት ስለሚኖርበት ሃላፊነት እና የዚህ የህግ ጥሰቶች በቀጣይነት ስለሚያስከትሉት አስተዳደራዊ እርምጃዎች ይገኙበታል።

በዚህ መሰረት ከዚህ በኋላ የሰነደ ሙዓለ ነዋዮች በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ካልተመዘገቡ ወይም በአዋጁ እና በመመሪያው ከዚህ ምዝገባ ነጻ ካልተደረጉ በቀር በኢትዮጵያ ውስጥ ለሽያጭ መቅረብ አይችሉም።

በተጨማሪም ማንኛውም ሰነደ ሙዓለ ነዋዮችን ለህዝብ ለማቅረብ የሚፈልግ ኩባንያ ሰነዶችን ለህዝብ ከማቅረቡ በፊት ዝርዝር መረጃዎችን ያካተተ የደንበኛ ሳቢ መግለጫ ለባለሥልጣኑ ማቅረብ እና ማጸደቅ የሚጠበቅበት ሲሆን ይህንን ከማድረጉ በፊት ማስታወቂያ ማሰራትም ሆነ ከኢንቨስተሮች ጋር ግንኙነት ማድረግ አይችልም።

መመሪያው በባለሥልጣኑ ገጽ ላይ ከተጫነበት ጊዜ ጀምሮ ተግባራዊ መሆን ይጀምራል።

በመመሪያው የመሸጋገሪያ ድንጋጌ መሰረትም አሁን ላይ ሰነደ ሙዓለ ነዋዮችን እያቀረቡ ያሉ ኩባንያዎች እና አስቀድመው ተሽጠው በአክስዮን ባለድርሻዎች እጅ ላይ የሚገኙ ሰነደ ሙዓለ ነዋዮችን በሚመለከት በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ መመዝገብ እንዳለባቸው አስቀምጧል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
#ወጣቶቻችን😥

" ከአንድ ወረዳ ብቻ ከ2 ሺህ በላይ ወጣቶች በህገ-ወጥ መንገድ ተሰደው 200 ያህሉ ለህልፈት ተዳርገዋል " - የእገላ ወረዳ አስተዳደር

እገላ ከትግራይ ማእከላዊ ዞን ወረዳዎች አንድዋ ስትሆን የኤርትራዋ ፆሮና ጎረቤት ናት።

ከትግራዩ ጦርነቱ በፊት የወረዳዋ ዋና ከተማ በሆነችው ገርሁስርናይ በቀን በርካታ የኤርትራ ስደተኞች በህገወጥ መንገድ ወደ ኢትዮጵያ ትግራይ ክልል የሚተላለፉባት ነበረች።

ከጦርነቱ በኋላ በእገላ ወረዳ በተለይ በገርሁስርናይ ከተማ ብዙ ነገሮች ተቀያይረዋል።

ወረዳዋ በተለይ ከተማዋ በከፍተኛ ሁኔታ ወድመዋል።

አሁንም ድረስ ወረዳዋ በኤትርራ ድንበር የምትገኝ በመሆንዋ የተሟላ ፀጥታ አላት ለማለት ያስቸግራል ይላሉ የአከባቢው ነዋሪዎች።

በወረዳዋ የሚታየው ህገ-ወጥ ስደት እጅግ አስደንጋጭና አስፈሪ መሆኑ የአደጋው ሰለባዎች እና የመንግስት አካላት ጭምር ይናገራሉ።

አቶ ዘርኢሰናይ መንግስቱ የተባሉ የገርሁስርናይ ከተማ ነዋሪ ለትግራይ የመገናኛ ብዙሃን ኤጀንሲ ሬድዮ ባጋሩት መረጃ የህዝብ ማመላለሻ መኪና ሹፌር በመሆን ሲተዳደር የነበረው የ22 ወጣት ልጃቸው ህገ-ወጥ ስደት ተነጥቀዋል።

ከእገላ ወረዳ አስተዳደር የተገኘው መረጃ እንደሚያሳየው ባለፈው 2016 ዓ/ም የመጨረሻ ወራት ብቻ 192 ሴቶች የሚገኙባቸው ከ 2 ሺህ በላይ  ወጣቶች በህገ-ወጥ መንገድ ተሰደው ከ1300 በላይ በስደት በተጓዙበት አገር ፓሊስ በአጭር ጊዜ ተይዘው ሲመለሱ 200 የሚያህሉ ግን ለህልፈት ተዳርገዋል።

የወረዳው ከፍተኛ አመራር ፅጌ ተ/ማርያም እንዳሉት፤ በአከባቢው የሚታየው ህገ-ወጥ የስደት ፍልሰት እጅግ አስፈሪና አስደንጋጭ ነው።

ወረዳው ከጦርነቱ ጋር በተያያዘ ይህ ነው የሚባል በጀት ያለው ባይሆንም የወጣቶች ስደት ለማስቀረት ያለመ የመስሪያ ቦታ በመስጠት ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

በተያዘው የበጀት ዓመት የህገ-ወጥ ስደት ፍልሰት በከፍተኛ ቁጥር ለመቀነስ ወረዳው አቅዶ እየሰራ ነው።

ይሁን እንጂ ጦርነት ወለዱ የበጀት እጥረት ለተያዘው እቅድ መሳካት ሳንካ ሊሆን ስለሚችል በወጣቶች አቅም ግንባታ እና ህገ-ወጥ ስደት መከላከል ዙሪያ የሚሰሩ ምግባረ ሰናይ ድርጅቶች እንዲያግዙዋቸው ሃላፊው ጥሪ አቅርባዋል።

#Ethiopia #TigrayRegion

@tikvahethiopia
ዶዳይ ማኑፋክቸሪንግ
የዴሊቨሪ ቢዝነስ በዶዳይ ኤ-ሞተሮች ይቀላቀሉ

በአንድ ጊዜ ቻርጅ እስከ 150ኪሜ መጓዝ የሚችሉ
•⁠ ⁠ለሙሉ ቻርጅ 10ብር ብቻ ሚጠይቁ
•⁠ ⁠⁠150ኪሎ ተሸክመው በሰአት እስከ 60ኪሜ የሚሄዱ
•⁠ ⁠ለእለት ተለት ጉዞ ቢሉ ፣ አልያም ለዲሊቨሪ ስራ የሚሆኑ

ይሂዱ > ይጎብኙ > ይግዙ!

ለበለጠ መረጃ
📍ሾው ሩም: ጎፋ ገብርኤል
📲 ስልክ: 0938022222
🌐 ethiopia.dodai.co

•⁠ ⁠TikTok Page: https://www.tiktok.com/@dodai_et?is_from_webapp=1&sender_device=pc
•⁠ ⁠Telegram Page: https://t.iss.one/+z09SxQgb6vsyNzU8
🎉 በሚወዱት ዜማ ዘና እያሉ ሽልማቶችን ይውሰዱ!!

ለጥሪ ማሳመሪያ ተመዝግበው ሙዚቃዎችን ወይም መንፈሳዊ ዜማዎችን እንደገዙ ከ645 ለሚደርስዎት ጥያቄዎች ትክክለኛ ምላሽ በመስጠት ዕድልዎን ይሞክሩ!

📺 ስማርት ቴሌቪዥኖች
💻 ላፕቶፖች
📱 5ጂ ስማርት ስልኮችና ሳምሰንግ ታብሌቶች
🎁 እንዲሁም በርካታ የሞባይል ጥቅሎችን በሽልማት ያግኙ!

ለመመዝገብ 822 ወይም *822# ይደውሉ አልያም https://www.crbt.et ይጎብኙ!

🗓 እስከ ታኅሣሥ 28/2017 ዓ.ም ብቻ!

#CRBT
#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
🔈 #የመምህራንድምጽ

🔵 "የሁለት ወራት ደመወዝ አልተከፈለንም። ቤተሰብ እንዴት እናስተዳድር?" - የደቡብ ወሎ ዞን መምህራን

🟢 " የሚመለከተው ኮማንድ ፓስቱን ስለሆነ በወረዳ በኩል እንዲፈቱ አነጋግረናል " - የዞኑ መምህራን ማኀበር

በአማራ ክልል፣ ደቡብ ወሎ ዞን ወግዲ ወረዳ የሚገኙ መምህራን የሁለት ወራት የደመወዝ ክፍያ ስላልተፈጸመላቸው የከፋ ችግር ላይ በመሆናቸው አማረዋል።

ክፍያው ያልተፈጸመላቸው በክልሉ ባለው የሰላም መደፍረስ ሳቢያ ተማሪዎች በትምህርት ገበታ ላይ ባለመገኘታቸው ' ሳታስተምሩ ደመወዝ አይከፈላችሁም ' በሚል መሆኑን አስረድተዋል።

" የሁለት ወራት ደመወዝ አልተከፈለንም። ቤተሰብ እንዴት እናስተዳድር ? " ሲሉ ጠይቀው፣ ከዚሁ ትንሽ ደመወዝ ብሶ ባለመከፈሉ ችግር ላይ በመውደቃቸው የሚመለከታቸው አካላት አፋጣኝ መፍትሄ እንዲሰጧቸው በአጽንኦት ጠይቀዋል።

የቀረበው ቅሬታ እንዲቀረፍ ምን እየተሰራ እንደሆነ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ የቀረበለት የዞኑ መምህራን ማኀበር፣ " የሚመለከተው ኮማንድ ፓስቱን ስለሆነ በወረዳ በኩል እንዲፈቱ አነጋግረናል " የሚል ምላሽ ሰጥቷል።

" መምሪያ ኃላፊው ጋ ተነጋግረናል። በዚያ በኩል እየገመገሙ መስራት የሚችሉና መምህራን ያልገቡባቸው ትምህርት ቤቶቸ ከሆነ የግድ የማይከፈል መሆኑን፤ ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ከሆነ ግን እንዲከፈል እየተደረገ እንደሆነ ነው " ብሏል።

በትምህርት ቤት ቢገኙም ተማሪ ባለመገኘቱ ብቻ ስላላስተማሩ ደመወዝ እየተከፈላቸው  ቅሬታ ለሚያቀርቡት መምህራን ምላሽ እንዲሰጥ ላቀረብንለት ጥያቄ በሰጠን ምላሽ ደግሞ፣ " ትምህርት መምሪያን አነጋግሩ " ብሏል።

የቀረበውን ቅሬታ በመግለጽ ምላሽ እንዲሰጡ ለሳምንት የጠበቅናቸው የዞኑ ትምህርት መምሪያና የክልሉ ትምህርት ቢሮ ጉዳዩን በጽሞና ከሰሙ በኋላ ምላሽ ከመስጠት ተቆጥበዋል።

በተጨማሪ፣ መምህራን እያቀረቡት ያለውን የደመወዝ አለመከፈል ቅሬታ ሰምቷል? ስንል ጥያቄ ያቀረብንለት የኢትዮጵያ መምህራን ማኀበር (ኢመማ) ማብራሪያ ሰጥቷል።

ማኅበሩ ፦

" በአካባቢው ካለው ችግር አንጻር ፎርማል ሆኖ የመጣልን ነገር የለም። ግን በወግዲ ወረዳ ብቻ ሳይሆን በሌሎች አካባቢዎችም እስከ ለሁለት ወራት እየተከፈለ አይደለም ከባንክም ከሌላም  ኬዝ ጋር በተያያዘ።

እንደተባለው መምህራን እየተጎዱ ነው። በይበልጥ ጉዳዩ የክልሉን መምህራን ማኅበር ይመለከታል። ፎርማል ሆኖ ወደኛ ቢመጣ ወደ ፌደራል መንግስትም ልንወስደው እንችላለን፡፡

ፎርዛትማተር መንግስት 'የክልሎቹ ማንዴት ነው' ነው የሚለን፡፡ ከዚህ ቀደም የትግራይ ክልል መምህራን መጥተው ያን ያህል ሲንገላቱ የኢትዮጵያ መምህራን ማኀበር ነበር ለሻይ ሲላቸው የነበረው።

አማራ ክልል አይነት የጦርነት ሁነት ላይ ስለሆነ ፎርማሊ በሕግ አግባብ የሚጠየቅ ድርጅት የለም፡፡ በዚህ ነው የተቸገርነው "
ነው ያለው።

በጸጥታው ችግር ትምህርት ቤቶች ስለተዘጉ ሳያስተምሩ ደመወዝ እንደማይፈጸምላቸው እንደተነገራቸው ነው መምህራኑ የሚገልጹት፤ ይህ አግባብ ነው ? በሚል ቲክቫህ ኢትዮጵያ ላቀረበው ጥያቄ የማኀበሩ ፣ " ልክ አይደለም " የሚል መልስ ሰጥቷል።

" ተማሪ እስከመጣላቸው ድረስ አላስተምርም ያሉ መምህራን ካሉ ነው እንጂ መምህራኑ ትምህርት ቤት ቁጭ ብለው ተማሪ እየጠበቁ ነገር ግን በጸጥታ ችግር ተማሪ ካልመጣላቸው ማንን ነው የሚያስተምሩት ? " በማለት ጉዳዩ ልክ ያልሆነበትን ምክንያት በመጠይቅ አስረድቷል፡፡

" ጸጥታውን ማስከበር ያለበት እኮ የመንግስት አካል ነው " ያለው ማኀበሩ፣ " የራሱን ሥራ እንዴት መምህራን ላይ ይጥላል? ትክክል የማይሆነው ይሄ ነው፡፡ መምህራን ትምህርት ቤት ላይ ከሌሉ ትክክል ነው ደመወዛቸው መክፈል አይገባም የት እንዳሉ አይታወቅምና " ብሏል።

" ነገር ግን ማኀበረሰቡ ልጆችን ትምህርት ቤት ልጆቹን አልክም ብሎ ከሆነ መምህራን ደግሞ ትምህርት ቤታቸው ላይ ሆነው እንዴት ነው የማይከፈሉት። ይሄ አህያውን ፈርቶ ዳውላውን መቱት አይነት ነገር ነውና ትክክል አይደለም " ሲል አክሏል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
#ትግራይ " ቡድኑ ለስልጣን ሲል ማንኛውም ዓይነት ጥፋት ከመፈፀም ወደ ኋላ እንደማይል በተደጋጋሚ እየታየ ነው " - የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የትግራይ ጊዚያዊ አስተደደር ዛሬ ህዳር 1/2017 ዓ.ም የፅሁፍ መግለጫ አውጥቷል። በዚህም " በአንደኛው ገፅ ልዩነቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተካረሩ ሄደዋል በሌላኛው ገፅ ደግሞ የጊዚያዊ አስተዳደሩ እቅዶች የማደናቀፍ እና የማዳከም የተቀናጀ ዘመቻ ሲደረግ ቆይቷል…
#ትግራይ

" ህጋዊ ያልሆነ ጉባኤ ያካሄደው ህጋዊ ያልሆነው ቡድን የሚመድባቸው አስተዳዳሪዎች እና የስራ ሃላፊዎች የሚያስተዳድሩት ሃብት የለም " ሲል የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር አስታወቀ።

ጊዚያዊ አስተዳደሩ ይህን ያለው በፕሬዜዳንት ፅ/ቤት በኩል ባወጣው መግለጫ ነው።

" ህጋዊ ያልሆነው ቡድን "  ሲል የገለፀው በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት ግልፅ የመንግስት ግልበጣ አካሂደዋል ሲል በድጋሜ ከሷል።

" ህጋዊ ያልሆነው ቡድን " በተለያዩ የክልሉ አከባቢዎች " ህጋዊ ያልሆነ " የስራ ምድባ በማካሄደ የመንግስት ግለበጣ በማካሄድ የቀን ተቀን ስራ የማደናቀፍ ኢ-ህጋዊ ተግባሩ ቀጥሎበታል ሲል ጠቅሰዋል።

" ህጋዊ ያልሆነ ቡድን " ህጋዊ ያልሆኑ የስራ ምደባዎች በማካሄድ የጊዚያዊ አስተዳደሩ ስራዎች ከማደናቀፍ አልፎ ስራውን በሚመሩት ላይ አላስፈላጊ ጫና በመፍጠር የመንግስት ስራ እንዲቆም እያደረገ ነው ሲልም ገልጿል።

በየደረጃው የሚገኙ የጊዚያዊ አስተዳደሩ መዋቅሮች ፣ በትግራይ በህጋዊ መንገድ የሚንቀሳቀሱ አካላት እና ተቋማት ፣ የፌደራል መንግስት እንዲሁም የዓለም ማህበረሰብ " ህጋዊ ባልሆነው መንገድ " የሚመድቡ እና የሚመደቡ በማንኛውም መንግስታዊ ሃላፊነት ስም እንዲንቀሳቀሱ ምንም እውቅና የሌላቸው እንደሆኑ እንዲገነዘቡ የጊዚያዊ አስተዳደሩ አመልክቷል።

" ህጋዊ ባልሆነው ቡድን " የሚመደቡት አካላት የሚያስተዳድሩት ማንኛውም ሃብት የለም ያለ ሲሆን የፀጥታ አካላት ፣ የፍትህ መዋቅር እና ባንኮች ይህንኑ በመገንዘብ ህግ እንዲያስፈፅሙ ሲል አስገንዝበዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ከታማኝ ምንጮች ባገኘው መረጃ ጊዚያዊ አስተዳደሩ " ህጋዊ ያልሆነ ቡድን " ሲል በፈረጀው በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት የተመደቡ የአስተዳደር አካላት ስም ጠቅሶ ማንኛውም የመንግስት ገንዘብ እንዳያንቀሳቅሱ የሚያግድ ደብዳቤ ወደ ባንኮች ፅፏል።

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ሳህለወርቅ_ዘውዴ

“ አቅጣጫዬን አሳይቻለሁ፤ በዛ መሠረት ለመስራት ሞክሬአለሁ ” - የቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዜዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ

በበጎ ፈቃድ የተሰባሰቡ ሴቶችና የሴት መሪ ድርጅቶች በጋራ በመሆን በቅርቡ የሥራ ዘመናቸውን ላጠናቀቁት ለቀድሞዋ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በሸራተን አዲስ ሆቴል ዛሬ የምስጋና ፕሮግራም አዘጋጅተው ነበር።

በዚሁ መርሀ ግብር አቶ አባዱላ ገመዳ፣ አምባሳደር ተሾመ ቶጋ፣ ተፅዕኖ ፈጣሪ ሰዎች ፣ የሴቶች ማኀበራት መሪዎችና በሌሎች የሥራ ዘርፎች ላይ የተሰማሩ ጥሪ የተደረገላቸው በርካታ ሴቶች ተገኝተዋል።

ፕሮግራሙ ከተዘጋጀበት ዓላማ አኳያም ለቀድሞ ፕሬዜዳንቷ “ በጣም ውድ ” እና “ ከኢትዮጵያ እንዳይወጣ ” የተባለለት የሀገር ቅርስ ጭምር የተቀረጸበት የስዕል ስጦታ የተበረከተላቸው ሲሆን፣ “ ከሚገባው ቦታ አስቀምጠዋለሁ ” በማለት ስጦታውን ላበረከቱላቸው ምስጋና አቅርበዋል።

በመርሀ ግብሩ ባደረጉት ንግግር ደግሞ፣ “ የዛሬ 6 ዓመት ገደማ ያደረኩት ንግግር የ18 ደቂቃ ነበር። ጥቂት ጊዜ ነው የነበረኝ ለመዘጋጀት። የደረሰብኝም አልገባኝም ነበር ” ሲሉ አስተውሰዋል የቀድሞ ፕሬዜዳንቷ።

“ ሴቶች የሚለውን ቃል 29 ጊዜ፣ ሰላም የሚውን ቃል 30 ጊዜ ተናግሬ ነበር ” ያሉት ሳህለወርቅ፣ “ ለራሴ አልዋሽም፣ ለሌላም አልዋሽም። አቅጣጫዬን አሳይቻለሁ፣ በዛ መሠረት ለመስራት ሞክሬአለሁ ” ሲሉም አክለዋል።

“ ተያይዘን መስራት አለብን። ጡረታ የሚባለውን ነገር አሁን ነው የጀመርኩት ግን እረፍት የለም። ጡረታም ተወጥቶ እንደማይታረፍ የቀደሙኝ እያሳዩኝ ነው። ላደረጋችሁልኝ በጣም ነው የማመሰግነው ” ነው ያሉት።

የቀድሞዋ ፕሬዜዳንት ከዚህ ቀደም፣ “ ‘የሰው ልጅ ሆዱ ሲከፋው ጊዜም እንደ ሰው ሲገፋው፣ መሄጃ መውጫ ሲጠፋው ዝምታ ብቻ ነው ተስፋው’ ይላል ማህሙድ ‘ዝምታ ነው መልሴ’ን ሲያዜም ” ብለው፣ “ አንድ ዓመት ሞከርኩ ” የሚል ፅሑፍ በX (ቲዊተር) ገጻቸው አጋርተው ነበር።

በወቅቱም ከፍተኛ መነጋገሪያ ሆኖ ነበር። ይህንን ምስጢር አዘል የሆነ ፅሑፋቸውን በተመለከተ ግን ዛሬም የሰጡት ማብራሪያ የለም።

የቀድሞዋ ፕሬዜዳንት ሳልለወርቅ ዘውዴ የመጀመሪያዋ ሴት የኢትዮጵያ ፕሬዜዳንት ሆነው ለ6 ዓመታት 4ኛ የኢትዮጵያ ፕሬዜዳንት ሆነው ሲያገለግሉ ቆይተው፣ የሥልጣን ዘመናቸው በመጠናቀቁ ኃላፊነታቸውን ለፕሬዚዳንት አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ማስረከባቸው የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia